• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የከረረው የአሜሪካና የህወሓት “ወዳጅነት ተበጥሷል”

February 18, 2018 11:51 pm by Editor 4 Comments

  • አጋራችን ብትሆኑ ኤምባሲችን ወደየሩሳሌም እንዲዛወር ድምፅ ትሰጡ ነበር – አሜሪካ ለህወሓት

ህወሓት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዳያውጅ በጌቶቹ ከተነገረው በኋላ በራሱ መንገድ መሄዱ የግንኙነት “ገመዱን እንደበጠሰው” ተነገረ። አሜሪካ ኤምባሲዋ ወደየሩሳሌም እንዳይሄድ የተቃወሙ አገራትን ዋጋ ትከፍላላችሁ ያለችውን በህወሓት ላይ ተግብራዋለች። አውሮጳውያን የጠነከረ ተቃውሟቸውን በህወሓት ላይ በዚህ ሳምንት ውስጥ እንደሚያሰሙ ይጠበቃል።

በባራክ ኦባማ አስተዳደር የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብቶች ረዳት ሚኒስትር የነበሩት ቶም ማሊኖውስኪ ባለፈው ዓመት ታህሳስ ወር ኢትዮጵያን ከጎበኙ በኋላ የአገሪቱን ሁኔታ የገለጹበትን አስመልክቶ ጎልጉል ይህንን መዘገቡ ይታወሳል። “ለለውጥ የተገባውን ቃል ተግባራዊ ማድረግ የኢትዮጵያ መንግሥት ብቸኛ ሃላፊነት ነው፤ … በኢትዮጵያ እንዲመጣ የሚፈለገው ለውጥ ሥርዓቱን ለዝነተ ዓለም ለማፅናት በሚደረግ ትግል ወይንም ሥርዓቱን በኃይል ለማፍረስ በሚወሰድ እርምጃም ሊሆን አይገባም፤ ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ ሥልጣን ማስረከብ ደረጃ ሊደረስ ይችላል” ካሉ በኋላ ሲቀጥሉም “እንደ ወዳጅ መክረናል … ምክንያቱም … ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ነገር ቢፈጠር ሙሉ ምስራቅ አፍሪቃ ምን ሊከተል እንደሚችል ስለምናውቅ … ነው” ብለው ነበር። “አገሪቱ አሁን ያለችበት ሂደት በእሳት ላይ ተጥዶ እንደሚንተከተክ ማሰሮ ይመስላል። እናም እንዲህ የሚንተከተክ ማሰሮ ለማስተንፈስ ያለው ምርጫ ክዳኑን ማንሳት ብቻ ነው፤ ያ ካልተደረገ መንተከተኩ አያቆምም። በዚያ ከቀጠለ ደግሞ መገንፈሉ አይቀርም። ከዚያ በኋላ የሚሆነው ሁላችንም እናውቀዋለን” ብለው ነበር።

ህወሓት/ኢህአዴግ “በአሻባሪነት” ስም በሶማሊያ የሚያደርገው ማስፈራሪያ ጊዜው ያለፈበት ይመስላል። የህወሃትና የአልሸባብ ግንኙነት እንዳለ ሆኖ አሸባሪነትን ለመዋጋት በሚል አርባ ምንጭ የሰው-አልባ አሮፕላን ማረፊያ (ድሮን ቤዝ) ማቋቋም ደርሳ የነበረችው አሜሪካ ከህወሓት ጋር ያላትን ፕሮጀክት ያጠናቀቀች ይመስላል። “ሶማሊያ ውስጥ … በኮንዶም አንዋጋም!” እያለ የሚያምታታ መለስ የሌለው ህወሃት/ኢህአዴግ ቁንጮውን ብቻ ሳይሆን ከበረሃ ጀምሮ ሲያግዙት የነበሩትን “ነጭ ወያኔዎችም” እያጣ ነው። ይህም ከሌሎች የአሜሪካ ማስጠንቀቂያዎችና ምክሮች ጋር ተዳምሮ የግንኙነት ገመዱ እንዲበጠስ ያደረጉ ምክንያቶች ናቸው።

ከዚህ በፊት በነበሩት ዓመታት ሁሉ ግምገማ በማካሄድ ራሱን ሲያብጠለጥል የኖረው ህወሓት/ኢህአዴግ እንደከዚህ በፊቱ በቃል ደረጃ ሟቹ መለስ እንዳለው “እስከ እንጥላችን ገምተናል” ባይልም ከዚያ ባልተለየ አገላለጽ አመራሩ እንደከሸፈ በገሃድ መስክሯል። ይህንን ካለ በኋላ ግን መላው አመራር ከያዘው ሥልጣን መነሳት ሲገባው ይኸው በመለስ አጠራር “እስከ እንጥሉ የገማው” አመራር በሥልጣኑ ላይ አንዳች ለውጥ ሳያደርግ ቀጥሏል።

በተደጋጋሚ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማውጣት በአገሪቱ ውስጥ የተነሳውን የተቃውሞ ማዕበል ለማብረድ ህወሓት ሙከራ ቢያደርግም አልተሳካለትም። ከጥቂት ወራት በፊት የተነሳውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ በአገሪቱ ውስጥ የለውጥ እንቅስቃሴ አገርሽቷል። በየአቅጣጫው ዜጎች ያነሱትን ጥያቄ በግድያና በእስር ለመመለስ የሞከረው ህወሓት ሕዝባዊ ጽናትና የHR 128 ጡንቻ ተባብረውበት “አሸባሪ” እያለ ያሰራቸውን የፖለቲካ እስረኞች ለመፍታት ተገድዷል።

በዚህ ሁሉ ውስጥ የተለያዩ ማባበያዎችንና ማስፈራሪዎችን ለመጠቀም የሞከረው ህወሓት “እኛ ከተነሳን አልሸባብ ሶማሊያን ይቆጣጠራል፤ ቀጣናው ሰላም አልባ ይሆናል፤ …” የሚሉትን ራሱን የአሜሪካ እውነተኛ አጋር አድርጎ ለማቅረብ የሄደበትም መንገድ አልሠራለትም። እንዲያውም ሌላ አቧራ አስነስቶበታል።

(በትልቁ ለመመልከት ምስሉ ላይ ይጫኑ)

የትራምፕ አስተዳደር በእስራኤል የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ከቴል አቪቭ ወደየሩሳሌም እንዲዛወር ውሳኔ ካደረገ በኋላ የተባበሩት መንግሥታት በጉዳዩ ላይ ድምፅ ሰጥቶበት ነበር። ኢየሩሳሌም ዓለምአቀፋዊ ከተማ ከመሆኗ አንጻር ኤምባሲው ወደዚያ እንዳይዛወር የመንግሥታቱ ድርጅት ያቀረበውን ሃሳብ ኢትዮጵያን ጨምሮ 128 አገራት ሲደግፉ አሜሪካንን ጨምሮ 9 አገራት ብቻ ተቃውመውታል። ከአፍሪካ ደቡብ ሱዳን፣ ዑጋንዳ፣ ሩዋንዳ እና ሌሎች አገራት ድምጸ ተዓቅቦ ማድረጋቸው ይታወሳል። ከአሜሪካ ዕርዳታና ድጎማ እያገኙ አሜሪካንን መደገፍ ሲገባቸው የመንግሥታቱን ድርጅት በመደገፍ አሜሪካንን የተቃወሙትን 128 አገራት አስመልክቶ “ዋጋ እንደሚከፍሉ” በወቅቱ ከትራምፕ አስተዳደር ተነግሮ ነበር።

በምዕራባውያን የበጀት ድጎማና ዕርዳታ ኅልውናው የታሠረው ህወሓት ጌቶቹ የሚያዙትን በተግባር መፈጸም ግዴታው ከሆነ ሰነባብቷል። በአሜሪካ በኩል ያለውን የጠነከረ አቋም ለማለሳለስ፤ “እኛ ብቸኛ የአሜሪካ ጥቅም አስከባሪና አጋር ነን” በማለት በሹሞቹ በኩል ለማሳመን ሙከራ ቢያደርግም አልተሳካለትም። “አጋራችን ብትሆኑ ኖሮ ኤምባሲያችን ወደየሩሳሌም እንዲዛወር ያቀረብነውን ሃሳብ በተበባበሩት መንግሥታት ፊት ትደግፉ ነበር” በማለት “ተገቢ” ምላሽ እንደተሰጣቸው ጎልጉል ያገኘው መረጃ ይጠቁማል።

በመሆኑንም ሌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ ተቀባይነት እንደማይኖረው የተነገረው ህወሓት ከምዕራባውያን የተሰጠውን ትዕዛዝ ሳይቀበል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል። ይህ እንደተሰማ በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ከዚህ በፊት ከሚያወጣው መግለጫ ለየት ባለ መልኩ የህወሓትን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ “አጥብቆ” ተቃውሞታል። ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ይልቅ ሊሰጥ የሚገባው “ምላሽ ነጻነትን በማሳነስ ሳይሆን በማብዛት” መሆን እንዳለበት ኤምባሲው እንደሚያምን በመግለጫው ጠቁሟል። ይህ የኤምባሲው አቋም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ (ስቴት ዲፓርትመንት) ውሳኔ ተደርጎ የሚታይ ሲሆን እስካሁን ከወጡት መግለጫዎች በዓይነቱም በይዘቱና በቃላት አጠቃቀሙ ጠንከር ያለ ሆኗል።

ይህንን የአሜሪካ አቋም ተከትሎ በዚህ በያዝነው ሳምንት ውስጥ የአውሮጳ ኅብረት፣ እንደ ጀርመን ያሉ አገራት በተናጠል እንዲሁም ካናዳ ተመሳሳይ ተቃውሞ እንደሚያሰሙ ጎልጉል ያገኘው መረጃ ይጠቁማል።

የጌቶቹ የተጠናከረ ተቃውሞ ያሳሰበው ህወሓት ያስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በተመለከተ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል። ተቃውሞውን ሰምቶ ያወጣውን አዋጅ ከሰረዘ ተሸናፊነቱን የሚያሳይ ይሆናል። አሻፈረን ብሎ ከገፋበትም ከድርጎ ሰፋሪዎቹ ጋር ሊቆራረጥ ነው። ስለዚህ “መንግሥት ይህንን (የአስቸኳይ ጊዜ) ውሳኔ በሚቀጥሉት 15ቀናት ለብሔራዊ ፓርላማ በማቅረብ ያስጽድቃል” በማለት በዕንጥልጥል ሊተወው ይችላል የሚል ግምት ይሰጣል።

መለስ በG-20 ስብሰባ

ከመለስ ሞት በኋላ በህወሓትና በአሜሪካ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚከታተሉ እንደሚሉት፤ አሜሪካ በተደጋጋሚ በገሃድም ይሁን በምስጢር ህወሓትን ስትመክር ቆይታለች። ከዚህ በኋላም እንዲሁ በምክርና በመግለጫ ብቻ መቀጠሏ የማይታይ ከመሆኑ የተነሳ ነው “የህወሓት እና የአሜሪካ የግንኙነት ገመድ ተበጥሷል” በማለት የመረጃው ባለቤቶች ለጎልጉል ለመናገር የደፈሩት። ይህ ይበል የሚያሰኝ በመሆኑ በአገር ውስጥ ያለው የለውጥ ኃይል በአስቸኳይ ከውጪው ጋር በቅንጅት በመሥራት የጌቶቹ ድጋፍ እየተነፈገ ያለውን ህወሓት/ኢህአዴግን እንዳይመለስ አድርጎ መሸኘት ያስፈልጋል በማለት ተናግረዋል።  (ፎቶ: በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ)


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Ezira says

    February 20, 2018 12:12 am at 12:12 am

    it is very Good News!
    God Bless Ethiopia

    Reply
  2. Benkamin says

    February 20, 2018 12:17 am at 12:17 am

    TPLF is the dictator regime! We Ethiopian against this terrible regime and fight until we get our freedom! One Ethiopia forever!??❤

    Reply
  3. Benjamin says

    February 20, 2018 12:20 am at 12:20 am

    Am against the tplf regime!

    Reply
  4. Mulugeta Andargie says

    February 20, 2018 01:28 am at 1:28 am

    ሰዎች!! የጎልጉል ዜና ኣቅራቢዎችም ሆኑ፣ ጎልጉልና የዝግጅቱ ክፍል፤ ወሬው የወተላገደ ከመሆኑም በላይ፤ የተዘበራረቀ ሆኖ ኣግኝቸዋለሁ። እስቲ ረጋ ብላችሁ ከላይ ጀምራችሁ እየጨመቃችሁ ዝለቁት፣ ትንቢት ለመናገርም ይቃጣውና፣መልሶ ከጀልባ ላይ የወደቀ ዋነተኛ ሆኖ ሲንቦጫረቅ ያስቀናል። በሃገሪቱ የሌለ ወይም ያልተደረገ ዝብርቅርቅ ቅጥ ኣንባሩ ጥፍት ያለ ወሬ ሆኖ ታገኙታላችሁ። ወሬ የት ትሄዳለህ ብሎ እንዱ ጠየቀው ኣሉ ወሬን፣ ወሬም፣ ጎልጉል ቤት፣ እስቲ ኣረፍ በልና እህልም ቀማሰህ ይሉታል፣ወሬም፣ጎልጉል ቤት ሳልደርስ፣ኣፈር ድሜ ልቅመስ ብሎ ነጎደ ይባላል።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule