• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ዘብረቅራቃው የባህር ዳር “ቅጠል ሰፈር” ጉድ!

February 16, 2018 06:04 am by Editor 4 Comments

ልብ-ወለድ ታሪኮችን አብዝቶ መጻፍ፣ ዕውነታዉን በግማሹም ቢሆን አስቶ፣ በራስህ የህልም ዓለም ዉስጥ እንድትዋኝ ያደርግሃል፡፡ የCreative writing ኪኑ ከአምላክ ቢሰጥህም፣ ጭቆናንና መገፋትን-ድህነትንና መቆራመድን በጠራ-ገለጥለጥ ባለ አማርኛ ከመግለጽ ግን አትታጎልም፡፡ የኔ ሁለት የሃሳብ ጽንፎች እንደዚህ ሲጓተቱ ቆይተው፣ በስተመጨረሻ “ዕውነታን በኪነት” አሉና ተስማሙ፡፡

ሰፈሬ ከከተማዋ (ከባህር ዳር) አንዷ ክፍል ሆና በመጠራት ትታወቃለች፡፡ በአሁኑ የቀበሌ አወቃቀር፣ “ክፍለ-ከተማ” ተባለች፤ “ሽምብጥ ክፍለ-ከተማ”! አብዛኛው ነዋሪዎቿ በዝቅተኛ የአኗኗር መደብ ዉስጥ ይካተታሉ፡፡ ጠላና አረቄ በመሸጥ የሚተዳደሩ ባልቴቶች በእልፍዓእላፋት መዝገብ ውስጥ ሊመዘገቡ አንድ ሃሙስ የቀራቸው ናቸው፡፡ የህወሃት “እያደኸዩ መግዛት” ፖሊሲ በትክክል ውጤት ያመጣው (በባህርዳር ደረጃ) “ሽምብጥ” ቀበሌ ዉስጥ ነዉ፡፡ ለአብነት፣ እኔ የምኖርበት ቦታ ከ”ቅጠል ሰፈር” ፈቀቅ ብሎ የሚገኝ ስፍራ ነው፡፡ “ቅጠል ሰፈር” በድህነት በጨረጨሱ ሰዎች የተሞላ ነው፡፡ ከላይ እንደጠቀስኩት ሴቶቹ ጠላና አረቄ በመሸጥ ይተዳደራሉ፡፡ ወንዶቹ ደሞ፣ በቀን ሰራተኝነት- በአናጢነት፤ ከፍ ካለ በጫት ነጋዴነት ተሰማርተው፣ የቤታቸውን ካስማ ከመዝመምና ከመውደቅ ታድገውታል፡፡ በተለይ የጫት ንግድ ባህርዳር ዉስጥ አዋጪ እየሆነ መጥቷል፡፡ የወጣቱን ወኔ “ሰልቧል” እየተባለ የሚደሰኮርለት ጫት፣ ለ’ነዚህ አባወራዎች ጥሩ የሚታለብ የቢዝነስ ዓውድ በመሆን ያገለግላል፡፡ አውራ-ጎዳናዎች ላይ የሚተምሙት ፈጥኖ-ሂያጅ ሞተር ሳክሎችን እግር ጥልዎት ከተመለከቱ፣ ጫት ነጋዴዎች መሆናቸውን፣ ከልብ ጠጥረው ማመን አለብዎት፡፡ ቤተ-ክርስቲያናትም ጭምር “ስራዬ!” ብለው ጫትን እንደገቢ ምንጭነት ቆጥረው በማልማት ላይ ይገኛሉ፡፡

ስለ”ቤት መዝመም” በጨረፍታ ያነሳሁትን ሃሳብ ላስፋፋው!

የህወሃት ተለጣፊ ካድሬዎች እዚህ ቀበሌ ዉስጥ የፈጸሙትና እየፈጸሙት ያለው ወንጀል ሰፊ ነው፡፡ የቆዬ ጉዳይ ቢሆንም፣ አንዳንድ አንኳር ጉዳዮችን እያነሳሁ ብተርክ ደስ ይለኛል!

የዛሬ 10ና 11 ዓመት “ቅጠል ሰፈር” አካባቢ የተመሩ ቦታዎች፣ ከህግ ውጭ መንገድ እንደተመሩ ይነገራል፡፡ ያኔ “የቀበሌ አስተዳዳሪ” ተብሎ የተሾመው፣ “አቶ መላክ” የተባለው ካድሬ፣ እግሩ ላይ ወድቀው ለለመኑት ሰዎች ሁሉ በገፍ ቦታ ሰጥቷል፡፡ “ጻድቅ እባላለሁ!” በሚል ስሌት፣ ከህግ ውጭ የሆነ ቦታ በመስጠቱ ሳቢያ፣ ነዋሪዎች ቅሬታ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከዛም አልፎ፣ በቅርቡ “የኮብል ስቶን መንገድ ይሰራላችኋል!” የሚል ቃል የተገባለት የቀበሌው ነዋሪ በአባወራ ደረጃ ለመንገዱ ስራ የሚውል መዋጮ አዋጥቶ ነበር፡፡ አንድ ሺህ፣ አንድ ሺህ ብሩን በአስተባባሪዎች የተዘረፈበት ህዝብ፣ ለማን “አቤት!” እንደሚል አቅጣጫው ጠፍቶት፣ በግራ መጋባት ስሜት ተሞልቶ፣ በሩን ዘግቶ ተቀምጧል፡፡ ይህ የ”ኮብል ስቶን” መንገድ “ይሰራ!” ተብሎ ቢወሰን እንኳ፣ እነዛ የ”ቅጠል ሰፈር” ነዋሪዎች ትክ ቦታ ሊሰጣቸው የሚችል አካል የለም፡፡ አካል ኖሮ፣ “ትክ ቦታ ይሰጥ!” ከተባለ ወስደው የሚጥሏቸው በአዲስ አበባ መስመር በኩል ወይም ደሞ በጎንደር መስመር በኩል ስለሚሆን፣ ከመሃል ከተማ ያለው ርቀትም ሰፊ ስለሆነ፣ ነዋሪዎች ወደአዲስ “ትክ” ቦታቸው ለመሄድ ፍላጎታቸው አይደለም፡፡ ከዚህ ቀደም የህወሃት የፕሮፖጋንዳ ማሽን የሆነው “ETV/EBC”፣ “ዓይናችን” በተሰኘ “ፕሮግራሙ” ጉዳዩን በለብ-ለብ ነካክቶት ነበር፤ በጥልቀት አልዘገበውም እንጂ! ካድሬው አቶ መላክ ለተጠየቀው አነስተኛ ጥያቄ መልስ መስጠት አቅቶት ሲንተባተብ በቴሌቪዥን ታይቷል፡፡ ነገሩ አስመራሪ ደረጃ ደርሶ ማህበረሰቡን ወደድንዛዜ ባልከተተበት ወቅት፣ የህዝቡን ጥያቄ አንስቶ መናገር ሲቻል፣ ሁሉም ሰው ዝምታን መርጦ መቀመጡ በጣም አስገርሞኛል፡፡

በቁንጽሉ ለማሳየት የሞከርኩትን ጉዳይ በሌላ ጊዜ በሰፊው የምመለስበት ይመስለኛል፡፡ ግን ህወሃት በራሱ ካድሬዎች ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ የከተማ ቦታዎችን ከቸበቸበ በኋላ፣ ቆይቶ…”ህገ-ወጥ ናችሁ!” ብሎ ህዝቡን ሲያፈናቅል፣ እትብታቸው ከተቀበረበት ቦታ ሲያባርር፣ “ሃይ!” የሚል የህዝብ ወገን ያስፈልጋል፡፡ የአብዛኛው አስተሳሰብ ወደ “ምን አገባኝነት” ተሸጋግሯል፡፡ መጨረሻችን ምን ይሆን?

ማሳሰቢያ፤ ይህንን መረጃ በተለይ ለጎልጉል የላኩት ሚኪያስ ጥላሁን ናቸው። ለዚህ ጽሁፍ ምላሽ አለኝ የሚል አካል ለዝግጅት ክፍላችን editor@goolgule.com መጻፍ ይችላል።


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. Mulugeta Andargie says

    February 17, 2018 02:03 am at 2:03 am

    ኣቶ ሚኪያስ ጥላሁን!! ይህ የጅላጅል ኣባባሎን ለዚይው ለለመዱት ሰፈሮ ያጫውቷቸው!!! ህወሃት፣ይህን ብሩህ ተስፋን የተሸከመ የልማት፣የኣንድነት፣የዲሞክራሲ፣የመብት፣የጤና፣የትምህርት፣የቴክኖሎጂንና የሳይንስ፣የዘመናዊ እርሻን፣የኢንዱስትሪን፣የባህል ዕድገትን፣የስፖርት ዕድገትን፣የከተማ ልማትን፣ ከመሳሪያ ትግል ወልዳ፣ ብዙ የህይወት መስዋዕትነት ክፍላ፣(ያውም ለሻዕብያም ጭምር) ኣቆናጣን፣ በክልልና በብሄር ተሳስረን፣ኣንዱ ያንዱን ሳይነካ ወይም ሳይነጥቅ፣ በክልሉ ተወስኖ በመረዳዳት፣ተደጋግፈን እንድንኖር ኣቅጣጫ የቀየሰች፣ውድ ድርጅት ናት። ኣሁንም እንኳን በትግራይ፣ሻብያን ድንበር ላይ ለሃያ ዓመታት ፎክሮ የመጣን ጠላት ወዝታዋለች። ምኑ ላይ ነው ጥፋቷ!??? ምግብ ቀረበልህ፣እንዲያጎርሱህ ትጠብቃለህ??? ተሳተፍ እንጂ!! ወዳጄ!!! ደርግን ማን ይደግፋል?? ወታደሩ!!! ሃይለስላሴን ማን ይደግፈው ነበር?? የኣማራው ብሄር!! ኣሁንስ??? ራስን በራስ ማስተዳደር ብቅ አለ!! የቱ ላይ ነው የወያኔ ኩነኔ???? ባወጣ ያውጣው ጽሁፍህ በመንሽ ገበሬው ቢያገላብጠው ምንም ኣላገኘበትም።

    Reply
    • ሚኪያስ says

      February 22, 2018 12:42 pm at 12:42 pm

      ሃይለስላሴን የአማራው ብሄር እንዴት ሊደግፈው ቻለ?ራሱ ጭሰኛ ሆኖ፣ በጎጃሙ አመፅ የቀ.ኃ.ስን ጦር ያፍረከረከን ህዝብ፣ በቀ.ኃ.ስ ደጋፊነት እንዴት ይፈርጁታል?

      Reply
  2. ali says

    February 17, 2018 02:54 pm at 2:54 pm

    Dear Mulugeta (I don’t think this is your real name)
    You are crying loud because you are benefiting from this corrupt system. Even though they paid scarifies, they were not the only person and all Ethiopians paid scarifies dearly. Moreover even if they paid that much the reason was to benefit themselves (including you).

    Let me advice you instead of supporting the unjust system of corruption you better fight for a fair system where humanity is superior than ethnicity. If you continue telling lies you will be the most miserable person on the whole world. If you really have truth on your side then reveal yourself and let us debate. I am sure you are not courageous enough to do that.
    May God help you to live your life responsibly.

    Reply
  3. Netsanet says

    February 18, 2018 01:09 am at 1:09 am

    Hey Mulugeta,

    Don’t you have any life other than sitting behind the computer and comment for each and every article. Whether you like it or not, one day TPLF will become history. Those of you bandas will be judged by the people of Ethiopia. You’re mocking now at our suffering and pain. For with whatever judgment you judge, you will be judged; and with whatever measure you measure, it will be measured to you. No more, no less. wait and see.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule