ኖቬበር 4 2013 የሳውዲ አረቢያ መንግስት የምህረት አዋጅ የግዜ ገደብ መጠናቀቅ አስመልክቶ ለተለያዩ የልማት ማህበር አባላት ኤምባሲው አርብ ኖቬምበር 1 2013 በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት አዳራሽ ስብሰባ ጠርቶ እንደነበር የሚገልጹ ምንጮች ስብሰባው በኢትዮጵያውያን ቆጨራ እና ሳንጃ መታጠቅ ዙሪያ ኤምባሲው ማህብረሰቡን ለመነጋጋር አጀንዳ ይዞ መቅረቡ ስብሰባው በጣም አሳፋሪ እና ኢትዮጵያውያንን በጅምላ ለመወንጀል ሆን ተብሎ የታቀደ ከስም ማጥፋት ዘመቻ ተለይቶ የማይታይ መሆኑንን ገልጸዋል። በተለይ አምባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን በወቅቱ ለተሰባስቢው ስለአጀንዳው ሲገልጹ ሪያድ ከተማ በተለምዶ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራው አካባቢ አያሌ በባህር የመጡ ኢትዮጵያውያን በተለምዶ «ባህር ሃይል እየተባሉ የሚታወቁ» መኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን እንዳሉ ጠቀሰው እነዚህ ህገወጦች የሳውዲ … [Read more...] about “በሳዑዲ ኢትዮጵያዊ ህገ ወጥ ስደተኞች ሳንጃና ቆንጨራ መታጠቃቸውን አረጋግጠናል” አምባሳደሩ
Archives for November 2013
ዕርቅን የሚፈልግና የሚቀበል በራሱ የሚተማመንና ደፋር ነው
ከዝግጅት ክፍሉ፡ "በህወሃት ውስጥ የዕርቅ ሃሳብ መነሳቱ ተሰማ" በሚል ርዕስ ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ላቀረበው የዜና ዘገባ አቶ አንዱ ዓለም ተፈራ የሚከተለውን የአጸፋ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በቅድሚያ ጊዜያቸውን ወስደው ይህንን ምላሽ ስለጻፉ እያመሰገንን ይህንን ዓይነቱን ባህል ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሚያደፋፍር መሆኑን እንወዳለን፡፡ በኢትዮጵያዊያን ዘንዳ፤ ይቅር ለፈጣሪ ብሎ ከተጣሉት ጋር እንዲታረቁ፤ ከልበ ሙሉዎች፣ ከባህል አካሪዎችና ለነገ ግምት ካላቸው ሰዎች ይጠበቃል። እናም አመዛዛኝ የሆኑ፤ አክብሮት፣ ርጋታና ፍቅር ያላቸው፤ ለእርቅ ምን ጊዜም በራቸው ክፍት ነው። አጉል የሆኑት ደግሞ፤ እኔ ስህተት አልሠራም፣ እኔ ምን ጊዜም ትክክለኛ ነኝ፤ ስለሚሉና ሌላው ሁሉ ለነሱ ሰግዶ እንዲልመጠመጥ ስለሚፈልጉ፤ ለእርቅ በራቸው ዝግ ነው። አጉል የሆኑ ማለት፤ እብሪተኞች፣ … [Read more...] about ዕርቅን የሚፈልግና የሚቀበል በራሱ የሚተማመንና ደፋር ነው
አይ አበሻ! አበሻና ሆድ፤ አንድ
ወያኔና የነፖሊቲካ አጋሮቹ የሚያደርጉትን ለእነሱ የሚመች አከፋፈል ትተን አበሻን ለሁለት እንክፈለው፤ ሆድ ያለውና ሆድ የሌለው፤ ወይም የሚበላና የማይበላ፤ ዛሬ የምናገረው ሆድ ስላለው ወይም ስለሚበላው አበሻ ነው፤ አታውቁት እንደሆነ ተዋወቁት፤ በአጠቃላይ ስንመለከተው ግን የአበሻ ፍቅርም ሆነ ጠብ ለሆድ ነው፤ አበሻን የሚያጣላው፣ የሚያነታርከው፣ የሚያቧጭቀው የሆድ ነገር ነው፤ ለመብላት ነው፤ አንዳንዴም ሎሌውን ለማብላት ነው፤ ግብር ለማግባት ነው። አዳም አበሻ ሳይሆን አይቀርም፤ ሁሉንም ነገር ብላ ከተከለከለው በቀር ብሎ ያስቀመጠው ይመስላል፤በላባችሁ ወዝ ብሉ ተብለው አዳምና ሔዋን መረገማቸውን አበሻ ገና አልሰማም፤ አበሻ የተፈጠረው ገነት ውስጥ ቁጭ ብለህ ያለውን ሁሉ ብላ በተባለበት ጊዜ ነው፤ እግዚአብሔር አበሻን ሁሉንም ብላ ሲለው ምናልባትም በጆሮው ጭራሽ አታስብ ብሎት ይሆናል፤ … [Read more...] about አይ አበሻ! አበሻና ሆድ፤ አንድ
በህወሃት ውስጥ የዕርቅ ሃሳብ መነሳቱ ተሰማ
ኢትዮጵያ ግራ በሚያጋባና ሊተነበይ በማይችል የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ መገኘቷን ያመኑ የህወሃት ሰዎች መካካል የእርቅ ሃሳብ ላይ ለማተኮር እቅድ እንዲያዝ ሃሳብ ማንሳታቸው ተሰማ። ኢህአዴግ የቀድሞው የአፈና ገመዱ መንተቡን የሚያሳዩ ምልክቶች መታየታቸውና አለመተማመን መንገሱ ተጠቆመ። ለጎልጉል መረጃ በመስጠት የሚታወቁ የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራርና ዲፕሎማት እንዳሉት ህወሃት ውስጥ "እርቅ አስፈላጊ ነው" በሚል እቅድ እንዲያዝና እንዲሰራበት ሃሳብ ቀርቧል። በድርጅቱ ውስጥ በተፈጠረ አለመተማመን ሳቢያ ስጋት የገባቸው የህወሃት ሰዎች የእርቅ ሃሳብ እንዲሰራበት ያቀረቡት ሃሳብ ግን በመደበኛ ስብሰባ አይደለም። በህወሃትና ህወሃት በሚያዛቸው አቻ ፓርቲዎች መካከል ያለው የመከባበርና የመገዛት ስሜት ከመለስ ሞት በኋላ መበላሸቱ፣ በኢህአዴግም ሆነ በህወሃት ደረጃ የተፈጠረው ልዩነትና በሙስና ስም … [Read more...] about በህወሃት ውስጥ የዕርቅ ሃሳብ መነሳቱ ተሰማ
“ኧረ እኔስ ጨነቀኝ”
ሰውየው ያገባት ሚስቱ ቤተሰቦቿ ሃብታሞች ነበሩ። እሱ ደግሞ መናጢ የሚባል ደሃ ነበር። አንድ ቀን የማይቀረው ሞት የሚስቱን አባት ነጠቀና ቀብር ወጡ። አስከሬን እየተከተሉ ሲያለቅሱ ባል ሚስቱ ጎን ሆኖ ልክ እንደሷ "አባቴ አባቴ" በማለት ያለቅስ ጀመር። ሚስትም " የት የወለደህን ነው አባቴ የምትለው" በማለት አፍታ ወስዳ ባሏን ገሰጸችው። ባል ለቅሶውን ቀየረና "አባቷ፣ አባቷ …” በማለት ያስነካው ጀመር። ይህን ጊዜ ሚስት አሁንም ለቅሶዋን ቆም አድርጋ "የበላኸው ጨማ፣ የጠጣኸው ጠጅ አያንቅህም? አባቷ አባቷ የምትለው" አለችው። ባልም ደንግጦ ላፍታ ዝም በማለት ካሰበ በኋላ "አረ እኔስ ጨነቀኝ፣ አረ እኔስ ጨነቀኝ … ” በማለት እያለቀሰ የባለቤቱን አባት ሸኘ። ይህ አጠር ተደርጎ የቀረበ የቀድሞ ምሳሌ ነው። ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ይወዳሉ። አገራቸውን በልጅ፣ በሚስት፣ በእናት፣ … [Read more...] about “ኧረ እኔስ ጨነቀኝ”
የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) በከፍተኛ ሥልጣንና ጉልበት በድጋሚ ሊቋቋም ነው
ባለፉት በርካታ ዓመታት በሥራ ላይ የሚገኘውን የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ከፍተኛ ኃላፊነትና ጉልበት የሚሰጥና በድጋሚ እንዲቋቋም የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ፡፡ በፓርላማው ቋሚ ኮሚቴዎች ተጨማሪ ውይይት እየተደረገበት የሚገኘው ይህ ረቂቅ አዋጅ፣ በቀጣዮቹ ጥቂት ሳምንታት ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ረቂቅ አዋጁ ከፀደቀ በኋላ ኤጀንሲው በድጋሚ የሚዋቀር ሲሆን የአገሪቱ የፋይናንስ ተቋማትን፣ ብሔራዊ የኤሌክትሪክ ኃይል መረብን፣ በግንባታ ላይ የሚገኘውን አገራዊ የባቡር ትራንስፖርት መረብን፣ ወታደራዊ የኮምፒዩተር ሥርዓትንና ሌሎች ኮምፒዩተራይዝድ የሆኑ መሠረተ ልማቶችን በኮምፒዩተር አማካይነት ከሚቃጡ ጥቃቶች የመጠበቅ ኃላፊነት ይኖረዋል፡፡ የረቂቅ አዋጁ አባሪ ሰነድ ሆኖ የቀረበው ማብራሪያ እንደሚያስረዳው፣ በአገሪቱ በሚታየው የኢኮኖሚ ዕድገት ሳቢያ በርካታ የአገሪቱ … [Read more...] about የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) በከፍተኛ ሥልጣንና ጉልበት በድጋሚ ሊቋቋም ነው
በሚዩኒክ ጀርመን የወያኔ የአባይ ግድብ ቦንድ ሽያጭ ተስተጓጎለ
እ.ኤ.አ. ቅዳሜ ኖቬምበር 02, 2013 ዓ.ም. በጀርመን ሚዩኒክ ከተማ ወያኔ ሊያደርግ ያሰበው የአባይ ግድብ ቦንድ ሽያጭ ከተለያዩ የጀርመን ከተሞች በተሰበሰቡ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ሊከሽፍ ችሏል። ከዚህ በፊት በጀርመን ፍራንክፈርት ጨምሮ በተለያዩ የአውሮፓና ሰሜን አሜሪካ ከተሞች እክል የገጠመው የወያኔ የቦንድ ሽያጭ ኮሚቴ አካሄዱን በመቀየር የቦንድ ሽያጩ ይጀመራል ተብሎ ከታሰበበት ጊዜ ሶስት ሰዓት ያህል በማዘግየት ለተቃውሞ የመጡትን ሰዎች ተስፋ ለማስቆረጥ ያደረገው ሙከራ ሳይሳካ ከመቅረቱም በላይ በወቅቱ በነበረው ቅዝቃዜና ብርድ ሳይበገሩ የፕሮግራሙን መጀመር በትዕግስት በቅርብ ርቀት የተከታተሉት እነዚህ ተቃዋሚዎች የመግቢያ ትኬት ሽያጭ ሲጀመር በአንድ ጊዜ ቁጥራቸው ከሶስት መቶ በላይ የሚሆኑ የኦነግ አባላት፣የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር አባላት፣የኢህአፓ … [Read more...] about በሚዩኒክ ጀርመን የወያኔ የአባይ ግድብ ቦንድ ሽያጭ ተስተጓጎለ
ስቀው ያሳሳቁን፣ በርተው የጠፉ የጥበብ ሰዎች እና ልናሽረው የማንችለው ቁስል!
ቀልድ ሲነሳ አስቂኝ ሶስቱ ድንቅ ተዋናዮች አለባቸው ተካ፣ ልመንህ ታደሰና አብርሃም አስመላሽ በልዩ ችሎታቸው ለእኔ እና ለብዙዎች ከፍ ያለ ቦታ አላቸው። ነፍሱን ይማረው አለባቸው ተካ ድሃ እንደደገፈ በአሳዛኝ የመኪና አደጋ አለፈ! ህይወቱን ለጥበብና በፋና ወጊ መልካም ተግባር ተሰልፎ ሲያሳልፍ ተስገብግቦ ሃብት አላካበተምና ለእሱና ለቤተሰቦቹ የረባ ጥሪት ሳይጥል አለፈ ... መልከ መልካሙ ልመንህ ከምድረ አሜሪካ አዕምሮውን ስቶ ከሞቱት በላይ ካሉት በታች ሆኖ በአዲስ አበባ አውራ ጎዳናዎች ይንከራተታል ... የሙያ አጋሮቹ ከምድረ አሜሪካ ያደረጉት ሁሉ ትብብር ቢሳካ ኖሮ ልመንህ ዛሬ ድኖ እናየው ነበር፣ ግን አልሆነምና በናኘበት ከተማ ራሱን ጥሎ ነሁልሎ ማየቱ ልብ ይሰብራል፣ ያሳዝናል! አንዳንድ ወዳጆቸ ልመንህን ለመደገፍ በግል ከሚደረገው ጥረት ባለፈ በተቀናጀ መልኩ እርዳታ … [Read more...] about ስቀው ያሳሳቁን፣ በርተው የጠፉ የጥበብ ሰዎች እና ልናሽረው የማንችለው ቁስል!
እኔና አንቺ…፪
መቼም እኔና አንቺን ሲፈጥረን ጉዳችሁ አይለቅ ያለን ነን የኛ ብለን ክብር ሰጥተን ያመነው ሰው ደ’ሞ ከዳን። ይሄን ሰማሁ ይሄውልሽ አንቺም ሰሚው አይቅርብሽ እንደው ቢገርመኝ እንጂ ነገሩ፥ይሄማ ምኑ ይወራል የኛ ያሉት ሲከዳ፥ቃሉ ለአፍ ይመራል ብቻ ምን ይደረግ? ”ውሻ በቀደደው…” ይባል የል የሱስ መክደት ምን ይደንቃል? እንደው ግን ለነገሩ፤ እየገደሉ እያያቸው በደም ተጨማልቆ እጃቸው ከነሱ ጋር አብሮ እየደለቀ ከበሮ የተለጠፈው ውስጣቸው ምን አግኝቶ ምን አጥቶ ነው? በምኑስ ላይ ምን ሊጨምር? መች አነሰው? ንዋይ ክብር በይ ተይው ግድ የለም፤ መቼም-እኔና አንቺን ሲፈጥረን ጉዳችሁ አይለቅ ያለን ነን። እንግዲህ ካልሰማሽም ስሚ፤ ከሰማሽም-ቻልአድርጊው እኛን ያልከዳን ማን አለ? የበደለን … [Read more...] about እኔና አንቺ…፪