• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) በከፍተኛ ሥልጣንና ጉልበት በድጋሚ ሊቋቋም ነው

November 4, 2013 04:58 pm by Editor Leave a Comment

ባለፉት በርካታ ዓመታት በሥራ ላይ የሚገኘውን የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ከፍተኛ ኃላፊነትና ጉልበት የሚሰጥና በድጋሚ እንዲቋቋም የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ፡፡

በፓርላማው ቋሚ ኮሚቴዎች ተጨማሪ ውይይት እየተደረገበት የሚገኘው ይህ ረቂቅ አዋጅ፣ በቀጣዮቹ ጥቂት ሳምንታት ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ረቂቅ አዋጁ ከፀደቀ በኋላ ኤጀንሲው በድጋሚ የሚዋቀር ሲሆን የአገሪቱ የፋይናንስ ተቋማትን፣ ብሔራዊ የኤሌክትሪክ ኃይል መረብን፣ በግንባታ ላይ የሚገኘውን አገራዊ የባቡር ትራንስፖርት መረብን፣ ወታደራዊ የኮምፒዩተር ሥርዓትንና ሌሎች ኮምፒዩተራይዝድ የሆኑ መሠረተ ልማቶችን በኮምፒዩተር አማካይነት ከሚቃጡ ጥቃቶች የመጠበቅ ኃላፊነት ይኖረዋል፡፡

የረቂቅ አዋጁ አባሪ ሰነድ ሆኖ የቀረበው ማብራሪያ እንደሚያስረዳው፣ በአገሪቱ በሚታየው የኢኮኖሚ ዕድገት ሳቢያ በርካታ የአገሪቱ እንቅስቃሴዎችና አገልግሎቶች የኮምፒዩተርና የኮምፒዩተር መረብ ጥገኛ መሆናቸው፣ እንዲሁም የዓለም ነባራዊ ሁኔታ አዋጁ እንዲዘጋጅና ኤጀንሲውን በድጋሚ እንዲቋቋም ለማድረግ ምክንያቶች ናቸው፡፡

የአገሪቱ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ የባቡር፣ የአቪዬሽን፣ የውኃ አቅርቦትና ሌሎች ኮምፒዩተራይዝድ በሆኑ ሥርዓቶች እየተመሩ መሆኑን በአብነት ያነሳል፡፡ በምሳሌነትም የአገሪቱ የኃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫ፣ ማስፋፊያና ማሠራጫ ሥርዓቱ በኮምፒዩተራይዝድ ሥርዓት የሚመራ በመሆኑ፣ በዚህ ሥርዓት ላይ የሚደረግ የኮምፒዩተር ጥቃት የአገሪቱን የኃይል አቅርቦት ከማቋረጡም በተጨማሪ፣ ኃይል አመንጪ ግድቦች ውስጥ የተጠራቀመ ውኃ ፍሰቱ እንዲዛባ በማድረግ መሠረተ ልማቱ ሙሉ በሙሉ እንዲወድም ሊያደርግ እንደሚችል ይገልጻል፡፡

በተመሳሳይ በአገሪቱ እየተገነባ ያለው የባቡር ትራንስፖርት በኮምፒዩተር ሥርዓት ቁጥጥር የሚደረግበት በመሆኑ፣ በዚህ ሥርዓት ላይ ጥቃት በማድረስ ባቡሮች ከመስመራቸው ውጪ እንዲንቀሳቀሱና አደጋ እንዲደርስባቸው ምክንያት ሊሆን ይችላል በማለት ያስረዳል፡፡

በመሆኑም ኤጀንሲውን በድጋሚ በማዋቀር ሰፊ የደኅንነት ኃላፊነቶችን እንዲወጣ ማድረግ ተገቢ መሆኑን ይገልጻል፡፡ ይህንን ኃላፊነት ኤጀንሲው እንዲወጣ በኤጀንሲው ሥር ብሔራዊ የኮምፒዩተር ድንገተኛ አደጋ ምላሽ መስጫ ማዕከል እንዲቋቋም የሚያስችል አንቀጽ በረቂቅ አዋጁ ተካቷል፡፡ ማዕከሉ ሊደርሱ የሚችሉ ጥቃቶችን ለመለየት፣ ጥቃቶችን ቀድሞ በመተንተን ለማወቅ፣ ጥቃት ሲከሰት በብቃት መግታት ወይም መጠነ ሰፊ ጉዳት ሳያስከትል መቆጣጠርና ሌሎችንም ተግባራት የሚያከናውን ይሆናል፡፡

ኤጀንሲው ይህንን ኃላፊነቱን በአግባቡ ለመወጣት እንዲያስችለው የደኅንነት ኦዲት ማድረግ የሚያስችል ሥልጣን በረቂቁ ተካቷል፡፡ የደኅንነት ኦዲት ማለት ኮምፒዩተርን መሠረት ባደረገ ቁልፍ መሠረተ ልማት ላይ ተጋላጭነትን ለማወቅ የዘልቆ ገብ ፍተሻ ተግባራትን ማከናወንና አገራዊ የኢንፎርሜሽን ፖሊሲና ስታንዳርድን መሠረት በማድረግ፣ የተቋማቱን የኢንፎርሜሽን ደኅንነት ሥርዓት በመገምገም የእርምት ዕርምጃ እንዲወስዱ ማድረግ የሚል ትርጓሜ በረቂቁ ተሰጥቶታል፡፡

ኢንፎርሜሽን (መረጃን) መሠረት ባደረጉ ቁልፍ መሠረተ ልማቶች ወይም ሥርዓቶች ላይ እንዲሁም በዜጎች ሥነ ልቦና ላይ የሚሰነዘሩ የሳይበርና የኤሌክትሮማግኔቲክ ጥቃቶችን ለመከላከል አስፈላጊ አፀፋዊ ዕርምጃ የመውሰድ ኃላፊነት ይኖረዋል፡፡ የሳይበርና የኤሌክትሮማግኔቲክ ጥቃቶች የሚባሉት የኢንተርኔት ሬዲዮ ወይም ቴሌቪዥን፣ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ አገልግሎቶች፣ የማኅበራዊ ሚዲያዎች (ማለትም ፌስቡክን የመሳሰሉ)፣ ዌብሳይቶች፣ ብሎጐችንና የመሳሰሉትን በመጠቀም የሚተላለፍ መሆኑን የአዋጁ ማብራሪያ ያትታል፡፡

በእነዚህ የመገናኛ አውታሮች የሚተላለፉ መረጃዎች ለማኅበራዊ፣ ለፖለቲካዊና ለኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ያላቸው ፋይዳ ግዙፍ ቢሆንም በተቃራኒው ለጦርነት ቅስቀሳ፣ የአገርን ገጽታ ለማጉደፍ፣ ፀረ ልማት ፕሮፓጋንዳዎችንና ኢኮኖሚያዊ ትንበያ (ስፔኩሌሽን) ማሠራጨት መጠቀሚያ ሊሆኑ እንደሚችሉ ማብራሪያው ይገልጻል፡፡ በመሆኑም የአዋጁን መፅደቅ ተከትሎ የተጠቀሱትን ጉዳት ያላቸውን መረጃዎች ኤጀንሲው የማክሸፍ ሕጋዊ ሥልጣን አለው፡፡

ኢንፎርሜሽንና ኮምፒዩተርን መሠረት ያደረጉ ቁልፍ መሠረተ ልማቶች ደኅንነትን ለማረጋገጥ ሲባል ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ በማውጣት የጥቃት ሰለባ ወይም መነሻ ናቸው ተብለው በተጠረጠሩ ኮምፒዩተሮች ወይም መሠረተ ልማቶች ላይ አስፈላጊውን ምርመራ ማካሄድ፣ ሌላው በረቂቅ አዋጁ የተካተተ የኤጀንሲው የወደፊት ኃላፊነት ነው፡፡ (ምንጭ፡ ሪፖርተር)

Filed Under: Politics Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
Copyright © 2026 · Goolgule