ኖቬበር 4 2013 የሳውዲ አረቢያ መንግስት የምህረት አዋጅ የግዜ ገደብ መጠናቀቅ አስመልክቶ ለተለያዩ የልማት ማህበር አባላት ኤምባሲው አርብ ኖቬምበር 1 2013 በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት አዳራሽ ስብሰባ ጠርቶ እንደነበር የሚገልጹ ምንጮች ስብሰባው በኢትዮጵያውያን ቆጨራ እና ሳንጃ መታጠቅ ዙሪያ ኤምባሲው ማህብረሰቡን ለመነጋጋር አጀንዳ ይዞ መቅረቡ ስብሰባው በጣም አሳፋሪ እና ኢትዮጵያውያንን በጅምላ ለመወንጀል ሆን ተብሎ የታቀደ ከስም ማጥፋት ዘመቻ ተለይቶ የማይታይ መሆኑንን ገልጸዋል።
በተለይ አምባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን በወቅቱ ለተሰባስቢው ስለአጀንዳው ሲገልጹ ሪያድ ከተማ በተለምዶ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራው አካባቢ አያሌ በባህር የመጡ ኢትዮጵያውያን በተለምዶ «ባህር ሃይል እየተባሉ የሚታወቁ» መኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን እንዳሉ ጠቀሰው እነዚህ ህገወጦች የሳውዲ አረቢያ መንግስት ያወጣውን ህግ ተከትሎ የሚወሰድባቸውን እርምጃ ለመከላከል ሳንጃ መታጠቃቸውን ኤምባሲው በመረጃ አረጋገጦል ብለው መናገራቸው በአብዛኛው ተሰብሳቢ ዘንድ ተቃውሞን ቀስቅሷባቸዋል። አምባሳደሩ በዚህ ዙሪያ ሰላማዊ ወገኖቻችንን በመወንጀል የሃገራችንን በጎ ገጽታ ለማጠልሸት በኤምባሲ ደረጃ አጀንዳ ተይዞ ስብሰባ መጠራቱ ያበሳጫቸው ተሰብሳቢዎች የአምባሳደሩን ጤናማነት እስከ መጠራጠር መድረሳቸውን ምንጮቻን አክለው ገልጸዋል። ድጋፍ እናገኛለን ብለው የጠሯቸው ታማኝ የልማት ማህበራቱ ስራ አመራር የአምባሳደር መሃመድ ሃሰን ያቀረቡት ክስ ከምን ጭብጥ ተነስተው እንደሆነ ማብራሪያ እንዲሰጦቸው ስብሰባው ላይ ወጥረው ይዘዋቸው እንደነበር የሚገልጹት ምንጮች ስብሰባው ገና ከመነሻው በተሳታፊው ከፍተኛ ተቃውሞ አለመግባባቶች ተፈጥረው እንደነበር ይገልጻሉ፡፡
አንዳንድ የአምባሳደር መሃመድ ሃሰን አባባል ያንገበገባቸው አስተያየት ሰጪ የቀረበው አንጀዳ ስህተት መሆኑንን ገልጸው ሴት እህቶቻችን ጉልበታቸውን ያፈሰሱበትን የወር ደሞዛቸውን ተነጥቀው ተደብድበው እና ተደፍረው በየጎዳናው ወድቀው የፍትህ ያለህ እያልን ጣረሞት እያሰማን ባለንበት የስደት አለም እኛው አጥፊ እኛው ገዳይ አረመኔ እና ጨካኝ ተብለን በተለያዩ ሚዲያዎች ስማችን ሲጠፋ እና የሃገራችን በጎ ገጽታ በማጉደፍ በባእዳን ጥላቻ የተቃጣብንን የስም ማጥፋት ዘመቻ አምባሳደሩ እንደ አንድ ሃገር መሪ ተወካይ መጋፈጥ ሲገባቸው የዝሆን ጆሮ ይስጥኝ ብለው ከርመው ዛሬ በድፍረት እኛ ፊት ቆመው እኛኑ ለመወንጀል መቃጣታቸው በጣም ያሳዝናል ብለዋል።
በሌላ በኩል አንድ አስተያየት ሰጪ በበኩላቸው ሲናገሩ አምባሳደር መሃመድ ሃሰንን ከእንግዲህ እንደማያውቋቸው ገልጸው ስለኢትዮጵያውያን ለመናገር የሞራል ብቃት የሌላቸው ከሳቸው ይልቅ በዲፕሎማት ደረጃ አንቱ የሚባሉ እንደነ አቶ መስፍን እና መሰል ዲሲፒሊን ያላቸው ኢትዮጵያዊያን የመንግስት ተወካዮች ስለኮሚኒቲው ችግር ህዝቡን ማወያየት እንደሚገባቸው በአጽኖት ጥቀስ በኤምባሲው ዝርክርክ አሰራር የእድሉ ተጠቃሚ መሆን የተሳናቸው ወገኖቻችን ላይ ለሚደረሰው ማንኛውም አደጋ አምባሳደሩ ሃላፊነትን መውሰድ እንደሚገባቸው በሰጡት አስተያየት ከተሰብሳቢው በተደረገላቸው የድጋፍ ጭብጨባ በወቅቱ የስብሰባ አዳራሹን ድባባ ለውጦታል።
አምባሳደር መሃመድ ሃሰን በአምባሳደርነት ማዕረግ ተሹመው ወደ ሳውዲ አረቢያ ከተላኩ ጀምረው በተለያዩ የግል ንግድ ላይ በእጅ አዙር ተሰማርተው ያለአግባብ የበለጽጉ ከበርቴ አምባሳደር መሆናቸውን የሪያድ ነዋሪዎች ያናገራሉ። አምባሳደር መሃመድ ሃሰን ኢትዮጵያ ውስጥ በአቶ ሙስጠፋ ሁሴን አሊዬ ስም በከፈቱት 2 የአሰሪ እና ስራተኛ ኤጄንሲ አማኝነት ወደ ሳውዲ አረቢያ መጥተው እስካሁን ድረስ ህልፈተ ህይወታቸውን ቤተሰቦቻቸው ላልተረዱ 3 ሴት እህቶቻችን ሞት ተጠያቂ ከመሆናቸውም በላይ በቅርቡ 2 ሚሊዮን ሪያል «5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር» ወደ ሌላ ሃገር ለማሸሽ ሲሞክሩ በሳውዲ ደህንነት ሃይሎች ቁጥጥር ስር ከዋሉት ከቀድሞው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሊቀመንበር አቶ ሙስጠፋ ሁሴን አልዬ ጋር አምባሳደሩ እጃቸው እንዳለበት ይጠረጠራል።
በአጠቃላይ አምባሳደር መሃመድ ሃሰን መንፍሃ ውስጥ ቆጨራ እና ሳንጃ ታጥቆ መሽጓል ብለው ለመወንጀል የፈለጉት የየተኛውን ብሄር አባል እንደሆነ ስብሰባው ላይ በይፋ ባይናገሩም በዚህ አካባቢ ቀደም ብሎ ጥቂት ስርዓት አልበኛ ኢትዮጵያውያን መሃከል አልፎ አልፎ በሚቀሰቀስ የጉሩፕ ግጭት በሳንጃ እርስ በእርሳቸው ይተራረዱ እንደነበርና በአካባቢው ማህበረሰብ የዕለት ተዕለት እንቅስቅሴ ላይ ቀላል የማይባል ተጸኖ ያሳድሩ የነበሩ ወጣቶችን ለማስታረቅ ኤምባሲው ቢጠይቀም ፈቅደኛ ሳይሆን መቅረቱ ይታወሳል። ይህ በተለምዶ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራው አካባቢ ብዛት ያላቸው በባህር የሚመጡ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የከተሙባት እና አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በንግድ ዘርፍ የተሰማራባት በመሆኑ በመርካቶነት የሚሰይሙት ወገኖች ለአያሌ ኢትዮጵያውያን የእድገት ማዕከል በመሆኗ በማውሳት የአምባሳደሩን ንግግር ቀደም ሲል በተለያዩ ሚዲያዎች በኢትዮጵያውያን ላይ ከተቃጣ ውንጀላ ለይተው እንደማያዩት ይገልጻሉ።
የጎልጉል ደንበኛ በፌስቡክ የላኩት
Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ
Leave a Reply