• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አይ አበሻ! አበሻና ሆድ፤ አንድ

November 6, 2013 09:35 am by Editor Leave a Comment

ወያኔና የነፖሊቲካ አጋሮቹ የሚያደርጉትን ለእነሱ የሚመች አከፋፈል ትተን አበሻን ለሁለት እንክፈለው፤ ሆድ ያለውና ሆድ የሌለው፤ ወይም የሚበላና የማይበላ፤ ዛሬ የምናገረው ሆድ ስላለው ወይም ስለሚበላው አበሻ ነው፤ አታውቁት እንደሆነ ተዋወቁት፤ በአጠቃላይ ስንመለከተው ግን የአበሻ ፍቅርም ሆነ ጠብ ለሆድ ነው፤ አበሻን የሚያጣላው፣ የሚያነታርከው፣ የሚያቧጭቀው የሆድ ነገር ነው፤ ለመብላት ነው፤ አንዳንዴም ሎሌውን ለማብላት ነው፤ ግብር ለማግባት ነው።

አዳም አበሻ ሳይሆን አይቀርም፤ ሁሉንም ነገር ብላ ከተከለከለው በቀር ብሎ ያስቀመጠው ይመስላል፤በላባችሁ ወዝ ብሉ ተብለው አዳምና ሔዋን መረገማቸውን አበሻ ገና አልሰማም፤ አበሻ የተፈጠረው ገነት ውስጥ ቁጭ ብለህ ያለውን ሁሉ ብላ በተባለበት ጊዜ ነው፤ እግዚአብሔር አበሻን ሁሉንም ብላ ሲለው ምናልባትም በጆሮው ጭራሽ አታስብ ብሎት ይሆናል፤ እስቲ በመጀመሪያ ስለምግብ እንነጋገር።

በሌላው ነገር ሁሉ ኋላ-ቀር ቢሆንም በምግብ ጉዳይ አበሻን የመበልጠው ያለ አይመስለኝም፤ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ የምግብ ውድድር ቢያደርጉ በምግብ ዓይነት፣ በጣዕም፣ በአሠራሩ ጥበብ አበሻ በቀላሉ እንደሚያሸንፍ በፍጹም አልጠራጠርም፤ የቱ አገር ነው ወዝ ያለውና ለስላሳ እንጀራ ያለው? በነጭ ጤፍ በሠርገኛው፣ በጥቁር ጤፍ፣ በስንዴውና በገብሱ፣ በማሽላውና በዘንጋዳው፣ በበቆሎው በእጅ ለመጠቅለል፣ በጉሮሮ ለማውረድ እንደአበሻ አመቻችቶ የሚሠራ የቱ ሕዝብ ነው? እንጀራው ሲፈለግ ቃተኛ፣ ሲፈለግ አነባበሮ እየሆነ በቅቤና በአዋዜ ርሶ ሆድ የሚያርስ ምግብ ማን ይሠራል፣ ከአበሻ በቀር?

የዳቦው ዓይነትስ ቢሆን ብዛቱና ጣዕሙ! ድፎው፣ የዶሮ ዳቦው፣ አምባሻው፣ ሙልሙሉ፣ ቂጣውስ ቢሆን ስንት ዓይነት ነው?

አበሻ ከጥንትም ጀምሮ የእግዚአብሔር ሰው ነው፤ ስለዚህም ይጾማል፤ ለእግዚአብሔር ሲል፣ መንግሥተ ሰማያት ለመግባት ሲል ከወዳጁ ከምግብ፣ በተለይም ከሥጋና ከቅቤ ይለያል፤ መጾም ዓላማው ለነፍስ ቢሆንም ለሥጋም ትልቅ ጠቀሜታ አለው፤ በአካል ውስጥ የተጠራቀመውን ጮማና ሞራ ለማራገፍ ይረዳል፤ አበሻ ግን ምኑ ሞኝ ነው፤ በሆድ ቀልድ የለም! የጾም ምግብ የሚባል ነገር ፈጥሮ ሆዱን ያስደስተዋል፤ ሥጋና ቅቤ ቀረብኝ ብሎ እንዳይጠወልግ ተቆጥሮ ብዛቱ የማይታወቅ ዓይነት የጾም ወጥ አለው፤ ስንት ዓይነት የአትክልት ምግብ፣ በዚያ ላይ ሹሮው፣ ክኩ፣ ስልጆው፣ ተልባው፣ ሱፉ፣ የሽምብራ ዓሣው፣ አዚፋው፣ ስንቱ ይቆጠራል!

ጾሙ ያልፍና ፍስኩ ሲመጣ አበሻ ፊቱን ከአትክልት ዓለም ወደእንስሳት ዓለም ያዞራል፤ ከዶሮ ጀምሮ እስከበሬው ኡኡ እያለ ለእርድ ይሰለፋል፤ የዶሮው ወጥ፣ የበጉ ወጥና አልጫው፣ ቅቅሉ፣ ምንቸት አብሹ፣ ክትፎው፣ ጥብሱ፣ ዱለቱ፣ ጥሬ ሥጋው፣ ምኑ ቅጡ!

የአበሻ ምግብ በዚህ ብቻ አይቆምም፤ አንዳንድ አበሻን የማያውቁ ሰዎች አበሻ ፍቅር አያውቅም ይላሉ፤ አበሻ ሌላ ቀርቶ በምግብም ፍቅሩን ይገልጻል፤ የመዝናኛና የፍቅር ምግብም አለ፤ እነቅንጬ፣ እነጨጨብሳ፣ እነግፍልፍል እዚህ ውስጥ የሚመደቡ ናቸው።

አበሻ የመንገድ ምግብም አለው፤ አገልግሉ፣ ቋንጣው፣ በሶው፣ ጭኮው፣ ጭኮው፣ የቡና ቁርስ እያለ ቆሎውን፣ ንፍሮውን፣ በቅቤና በአዋዜ የራሰ ቂጣውን፣ አነባበሮውን፣ አሹቁን ይከሰክሳል፤ አበሻ ከተመቸው መቼ ነው ከመብላት የሚያርፈው? የቱ አገር ነው በዚህ ሁሉ ምግብ ተወዳድሮ አበሻን ማሸነፍ የሚችለው?

አበሻ ምግብ ስለሚወድ የሚያስበላው ነገርም ይወዳል፤ ቃሪያን መብላት ልዩ ጥበብ ያደረገው ለዚህ ነው፤ ቂሉ ፈረንጅ አፐረቲቭ እያለ (ከሣቴ ከርስ መሆኑ ነው፤) አንጀቱን የሚጠብሰውን አረቄ ይጠጣል፤ በቅመማቅመምና በድልህ የተቁላላውን ወጥ በእንጀራ እየጠቀለለ ቢጎርስ እያላበው ይበላ ነበር!

የአበሻ ምግብ የሚበላው ወገን በፈረንጅ አገር ሲኖር አገሬ የሚለውና የሚናፍቀው የአበሻ ምግብ ነው! ስለዚህም በሄደበት የአበሻ ምግብ አይለየውም! አበሻ ሆዱን ትቶ አይሰደድም! እንዴት ብሎ!

ምንጭ: Mesfin Woldemariam Blog

Filed Under: Social Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የቴሌኮም ጌትዌይ፣ የዳታ ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ደህንነት – የዌብስፕሪክስ ጉዳይ ከባለቤትነት ክርክር በላይ ነው! November 17, 2026 11:54 pm
  • “የጫካ ቱጃሮች!”— የፋኖ አመራሮች ስለተሰማሩበት የገንዘብ ዝርፊያ አስደንጋጭ መረጃ November 17, 2026 05:43 pm
  • በየወሩ 4 ሚሊዮን ብር እየተከፈለው ሀገር ሲያፈርስ የነበረው ሪፖርተር November 16, 2026 01:17 am
  • ሻርኮቹ ከውጭ እስከ ሀገር ውስጥ ያደሩት ድር፣ ዌብስፕሪክስን (WebSprix) የመጠቅለሉ ድራማና ብሔራዊ ስጋት November 14, 2026 12:42 am
  • የመለስ ዜናዊን ጭንብል የገፈፈው የትህነግ ሚዲያ (EMF) ምስክርነት November 13, 2026 03:32 pm
  • ትህነግ በወታደራዊና በፖለቲካዊ መስክ እንደሞተ ሁሉ በሪፖርተር በኩል የሚዲያ ግብዓተ መሬቱ ተፈጽሟል November 13, 2026 01:13 am
  • በከባድ ታክስ ማጭበርበር የሚፈለጉት አቶ አበባው ደስታ፣ አማራጭ የቴሌኮም ጌትዌይ ፕሮጀክትን ሊጠቀልሉ ነው November 12, 2026 03:50 am
  • “ፋኖ ወደ ኦሮሚያ ገብቶ ሕዝብ እየገደለ ነው” የኦነግ ሸኔ (OLF/OLA) ተወካይ ጃል ጅረኛ November 10, 2026 05:12 pm
  • ከትህነግ የተማረኩና ከውጭ ሀገራት የገቡ ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎች በቃሊቲ ለእይታ ቀረቡ November 6, 2026 03:36 pm
  • የመንግሥት ኃላፊዎች ወደ ሁርሶ የተወሰዱበት ምሥጢር November 5, 2026 12:43 pm
  • መንግሥት ሰማ፤ ሪፖርተር ተዘጋ፤ ግን ለምን? ምሥጢሩ ምንድነው? November 3, 2026 12:09 am
  • ኢትዮጵያ በሰማይ ላይ ነዳጅ የሚሞሉ የኢሉሺን (Il-78) አውሮፕላኖችን ከሩሲያ ልትገዛ ነው October 30, 2026 08:57 am
  • ካይሮ ያጣችውን የሩሲያ ጄቶች አዲስ አበባ የታጠቀችበት ምሥጢር October 29, 2026 10:26 am
  • ኢትዮጵያ ሱ-35 ተዋጊ ጄቶች እና የኤስ-400 ዘመናዊ የአየር መከላከያ ስርአት በመታጠቅ ከሰሃራ በታች ብቸኛዋ ሀገር ሆናለች October 28, 2026 11:00 am
  • ሻዕቢያ ኢትዮጵያን በ“ካሚካዜ” ድሮኖች ለመምታትና በዘር ግጭት ለማፍረስ ሰፊ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተሰማ October 27, 2026 11:14 pm
  • ጆን መዲድ “ቀዝኖ እና ልብሱ ተበላሽቶ” ነው መከላከያ የማረከው October 27, 2026 08:41 pm
  • በጆን መዲድ መማረክ አደረጃጀቱ እየተፈረካከሰ በመሆኑ እነ ወዲ እምበይተይ፣ ምግበይ፣ ቀጣዮች ሊሆኑ ይችላሉ October 27, 2026 09:17 am
  • ከታክስ ስወራ እስከ ሐሰተኛ ጋብቻ፦ በኢትዮጵያ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊ ዳያስፖራዎችን ለማደን የተዘረጋው አዲሱ የአሜሪካ መረብ October 21, 2026 09:26 am
  • ኔታንያሁ የሶማሊላንድን ሉዓላዊነት ያረጋገጠ አዲስ ቀጣናዊ ካርታ ይፋ አደረጉ October 20, 2026 03:20 pm
  • ትውልደ ሶማሊያዊቷ ናፊሳ በተዘቀዘቀ የአሜሪካ ሠንደቅ ፊት በሶማሊኛ ምርጫ ቅስቀሳ ማድረጓ ቁጣ ቀሰቀሰ October 20, 2026 09:21 am
  • በአሜሪካ የሚገኙ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊዎች ላይ የተደቀነው አዲስ ስጋት October 19, 2026 08:58 pm
  • ዜግነት ሊያሰርዝ በሚችለው የኢልሃን ዑመር ምርመራ ላይ አዳዲስ መረጃ ተገኝቷል October 19, 2026 04:45 pm
  • በትግራይ የሚገኙ የሚዲያ ተቋማት ስም በአስቸኳይ ሊቀየር ይገባል! October 19, 2026 02:55 am
  • በትግራይ ሕዝብ ደም የሚደረገው የሥልጣን ቁማር ያብቃ! October 14, 2026 11:04 pm
Copyright © 2026 · Goolgule