ሚስጢሩ ወደኛ እየቀረበ ይሆን? የሚስጢሩን መጽሃፍ እያሳጠርኩ በመጻፍ ላይ እያለሁ ሚስጢሩን የሚአጠናክር ነገር ገጠመኝ። ከጓደኛዬ ጋር አልፈን አልፈን ውሃ የምንጎነጭባት ቤት አለች። እንደወትሮው በዛው ቤት ተገኝተናል። አንዲት ወጣት ስዊድናዊት ልታስተናግደን መጣች። ለጓደኛዬ የሞቀ ሰላምታ ሰጠችው። ስትስቅ ጉንጭና ጉንጮቿ ላይ የሚወጡት ጎድጓዳ ምልክቶች አይን ይስባሉ። ‹‹ባለፈው ጊዜ ስራ ለመቀጠር አስበሽ ያነጋገርኩሽ አይደለሽ?» አላት «አዎን! ተቀጠርኩ በጣም አመሰግናለሁ» «እኔ ምንም ያደረኩልሽ ነገር እኮ የለም» «አንተ ሄደሽ ባለቤቱን ተይቂው ባትለኝ አልጠይቀውም ነበር። ስለጠየኩት ተቀጠርኩ። በድጋሚ አመሰግናለሁ»። ፈገግታዋን ከጎድጓዳ ጉንጮቿ የሚረጭ ይመስላል። ተለየችን «ምንድነው ነገሩ? ስራ አስቀጣሪ ሆንክ እንዴ?» ጠየኩ ባለፈው ሰሞን እዚህ መጥቼ… ይቺ … [Read more...] about The Secret (ሚስጢሩ…)
Archives for November 2013
“ከወገኖቻችን ጐን በመቆም ብሄራዊ ክብራችንን እናስመልሳለን”
ሰሞኑን የሳውዲ አረቢያ መንግሥት በኢትዮጵያዊያን ላይ እየፈፀመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመቃወም ሰማያዊ ፓርቲ ታላቅ የተቃውሞ ጥሪ አስተላልፏል፡፡ በመሆኑም በዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን ኢሰብዓዊ ድርጊት ለማስቆምና የዜጐችን ህይወት ለመታደግ እንዲሁም ዜጐቻችን በአፋጣኝ ወደ ሀገራቸው የሚመለሱበትን ሁኔታ መንግሥት እንዲያመቻች እና በተጨማሪም በዜጐቻችን ላይ ለደረሰው የአካል መጉደል፣ እንግልት፣ ድብደባ፣ አስገድዶ መድፈርና የህይወት መጥፋት ኃላፊነቱን የሚወስዱ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ፤ ለተጐዱ ወገኖቻችንና ቤተሰቦቻቸውም አስፈላጊው ካሳ እንዲደረግላቸው ፓርቲያችን አበክሮ እያሳሰበ፤ የብሄራዊ ክብርና የወገኖች ስቃይ የሚያሳስባቸው አካላት በሙሉ በዚህ ታላቅ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ የተቃውሞ እንቅስቃሴ አፈፃፀም፡- 1. በዜጐቻችን … [Read more...] about “ከወገኖቻችን ጐን በመቆም ብሄራዊ ክብራችንን እናስመልሳለን”
በሳዑዲ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን ጥቃት ለማውገዝ ሰላማዊ ሰልፍ ተጠራ
ከጥቅምት 26 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ በሳዑዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን የኃይል ጥቃት ለማውገዝ በአዲስ አበባ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ ተጠራ። የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) አባል ፓርቲዎች ትናንት በመድረክ ጽ/ቤት በስራ አስፈፃሚ ደረጃ ባካሄዱት አስቸኳይ ስብሰባ በሳዑዲ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የሳዑዲ ፖሊስ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት መፈፀሙን፣ አልፎ ተርፎም እስካሁን ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ኢትዮጵያውያን መገደላቸውን በመግለፅ ሁኔታውን አውግዟል። የችግሩ ክብደትና አሳዛኝነት በመቀጠሉ ድርጊቱን በመግለጫ ከማውገዝ ባለፈ ሁኔታውን በሰላማዊ ሰልፍ ለመቃወም ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። የወቅቱ የመድረክ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ከመድረክ የስራ አስፈፃሚ ስብሰባ በኋላ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንዳረጋገጡት መድረክ የጉዳዩን … [Read more...] about በሳዑዲ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን ጥቃት ለማውገዝ ሰላማዊ ሰልፍ ተጠራ
“ለኢትዮጵያውያን በችግሩ ዙሪያ ማብራሪያ እንዲሰጥ እንጠይቃል”
ሰሞኑን በሳውዲ አረቢያ በተለይ በኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ እየተፈፀመ ያለው እንግልት፣ ድብደባ፣ ግድያና ለህይወት አስጊ በሆነ ሥፍራ ማጎር ከኢሰብአዊነትም በላይበኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ የተሰነዘረ ጥቃት ነው፡፡ ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድት) የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ! በአባቶቻችን ደም ታፍራና ተከብራ የኖረችው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በገዢው ፓርቲ ቸልታ፣ የፖሊሲ ችግርና የሀገር ፍቅር ማጣት የተነሳ ዜጎቿ በውርደት እንዲኖሩ ተፈርዶባቸዋል፡፡ ዛሬም መገለጫችን ስደት፣ ጦርነት፣ በዜግነታችን ክብር ማጣትና ሞት ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ ሀገራዊ ውርደትና ሞት ከተበላሸ ሥርዓት የሚወለድ፣ ካልተስተካከለ የኢኮኖሚ ፖሊሲ የሚፈጠር ነው፡፡ ፓርቲያችን የተሻለ ኢኮኖሚ ፍለጋ፣ የተሻለ ማህበራዊ ፍትህ ለማግኘትና አሰቃቂ የሆነውን ፖለቲካ ሽሽት ኢትዮጵያውያን ዜጎች ሀገራቸውን … [Read more...] about “ለኢትዮጵያውያን በችግሩ ዙሪያ ማብራሪያ እንዲሰጥ እንጠይቃል”
ወገኔ በከንቱ
እዩት በየቦታው የሚታደገው አጥቶ እንዲያው ሲንከራተት ከሀገሩ ወጥቶ ወይ አላለፈለት ወይ እፎይ አላለ ሁሌ በባርነት እንዲሁ እንደቆዘመ ዘመናዊ ለማኝ አስጠጉኝ ባይ ሆነ መገፋቱ ሳያንስ መገደሉ ባሰ ። ባርነት ባአረብ አገር እስር በዐገር ቤት ስደት ካገር ውጭ ችግር በራስ አገር እርዛት አና እስር ሆኖል የብሶት መንደር ። ወገን አልባው ወገን ጠባቂ አልባው ግልገል መንጋው ተበተነ ዋይታው ለኛ ሆነ ገዳዩም ጠያቂ አጣ ስቃዩም ቀጠለ ። አቤት ፍርጃ ለዛውም ጠያቂ ያጣ ምን ይሆን ሚስጥሩ እንዲህ የመሆኑ? ማብቂያውስ መቸ ነው እንግልት ስደቱ አገር ሰላም ሆኖ ሰርቶ እሚኖርበት ሁሉም አንደቤቱ። መንግስት ምን አገባኝ ጆሮ ዳባ ልበስ ካለ ለህዝብ ለወገኑ ላገሩ ካልቆመ የወገን ደም እንደቀለም መንገድ ላይ ሲዘራ በባእዳን እጂ ወገን ሲሆን መቀለጃ ቆሞ … [Read more...] about ወገኔ በከንቱ
“ሁለቱም ባዶዎች ነበሩ!”
እ’ስራና ቅል ... አፈጣጠራቸው፣ ቢሆንም ለየቅል፤ እንደ አቅማቸው፣ ሠርተው በሀሳብ - ተግባር፣ ተግባብተው፤ ሰላም አግኝተው፣ አንድነት ይኖሩ ነበር፣ በአንድ ቤት። በፍቅራቸው፣ የሚቀናው ዱባ ግን፣ ጉረቤታቸው፤ ያሴር ነበር ሴራ፣ የሚያሥር ይሸርብ ነበር ነገር፣ የሚያደናግር፤ ያጠምድ ነበር፣ ወጥመድ ባረፉበት ቤት፣ ሳይቀር በመንገድ። እ’ሰራን ሲያገኘው፣ ብሎ ጎንበስ - ቀና የሰላምታ አይነት፣ ያዥጎደጉድና፤ በማር የተቀባ፣ የመርዝ ቃላት ይነግረው ነበረ፣ መስሎ ተቆርቅሪ፣ ለሱ ያዘነለት። ቅልንም ሲያገኘው ወይም ቤቱ ሄዶ ከአስረደው በኋላ፣ እንደሚፈልግው በፍቅሩ ተገዶ፤ ምክር ነው እያለ፣ ነገር ይነግረዋል በማያውቀው ጉዳይ፣ ደሙን ያፈለዋል። ከለ'ታት አንድ ቀን፣ ሥራ በፈቱበት በነገር ተይዘው፣ ''በተሰለቡበት''፤ እ’ስራ ተክዞ፣ … [Read more...] about “ሁለቱም ባዶዎች ነበሩ!”
SMNE: Confronting Official Corruption in Ethiopia
SMNE Calls for Strong Measures from the International Community, Donors and International Investors in Confronting Official Corruption in Ethiopia The Government of Ethiopia is broadly soliciting for development aid, foreign-based business partnerships and financial investors; yet, the unpopular ruling party has been accused of abuse of state power, misuse of donor funds, widespread party-run business monopolies, illicit financial practices and endemic corruption. It is time to demand … [Read more...] about SMNE: Confronting Official Corruption in Ethiopia
Help Get Eskinder Home
Eskinder is serving an 18 year prison sentence in Ethiopia for ‘incitement to commit terrorist acts’ and ‘treason’ - but he is neither a terrorist nor a traitor. He’s a firm believer in free speech. Sign our petition and help get Eskinder home to his family - and return to work as a journalist, championing free speech. Please click here to sign the petition. … [Read more...] about Help Get Eskinder Home
“ፍቅርን እንደወረደ እሰብካለሁ” አርቲስት ሃኒሻ ሰለሞን
ለማዘንም ለመደሰትም የቀረበች ናት። ስለዘርና ስለቋንቋ ያላት እምነት የሚለካው በፍቅርና በፍቅር ብቻ እንደሆነ ደጋግማ ትናገራለች። ቋንቋም ሆነ ዘር የማንነት መለኪያ እንዳልሆነ አጥብቃ ትከራከራለች። ፍቅርን እንደወረደ ከመስበክና ወገኖቿን የመርዳት ዓላማዋን ከማሳካት የሚበልጥባት ጉዳይ እንደሌለ አበክራ ትናገራለች። ገና ጀማሪ ብትሆንም ሙዚቃዎቿ ተወደውላታል የሚሉ እየበረከቱ ነው። እኔ ዘር የለኝም በሚል የሰፋ ሃሳብ ያለው ሙዚቃ ተቀኝታለች። ኢትዮጵያ የፍቅር ምድር እንድትሆን አብዝታ እንደምትሰራ ቃል በመግባት ከጎልጉል ጋር ቃለ ምልልስ አደረገችው አርቲስት ሃኒሻ ሰለሞን የምትኖረው ሎንዶን ነው። እንደሚከተለው ቀርቧል። በቃለ ምልልሱ ሃኒሻ ላይ በደል ፈጽሟል የተባለው የባላገሩ አይዶል ባለቤት አብርሃም ወልዴ ለቀረበበት ውንጀላ ምላሽ መስጠት ከፈለገ ዝግጅት ክፍላችን በደስታ … [Read more...] about “ፍቅርን እንደወረደ እሰብካለሁ” አርቲስት ሃኒሻ ሰለሞን
የተከለከለውን እንደተፈቀደ…
... ይህን ሁሉ ሰብአዊ ክብራችንን ያሳጣን ዘረኛ አስተዳደር፤ ይህ አልበቃ ብሎት በታሪካችን፣ በሐይማኖታችን፣ በወንጀለኛ መቅጫ ሕጋችን ሳይቀር የተከለከለን ድርጊት የመንግስት የፀጥታና የደህንነት አስከባሪ ነን በሚሉ አስተሳሰበ ድውያን ሰሞኑን በአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል በአቶ አበበ አካሉ ላይ አስገድደው የአልኮል መጠጥ በመጋት የተፈፀመባቸውን የወሲብ ጥቃት ወንጀል ማህበራችን በፅኑ ያወግዛል። በረጅም ዘመን የነጻነት ታሪካችን በግብረ ሰዶማዊነት ራሳቸው ፈቅደው ከተሰማሩ ሰዎች ውጭ ሕግ እናስከብራለን በሚሉ ኃይሎች እንዲህ አይነቱ ነውር በእኛ ትውልድ ሲፈፀም በማየታችን በህሊናችን ውስጥ ጊዜ የማይሽረው ጠባሳ አሳርፈውብናል። የመጨረሻውንም የውርደት ሸማ ሊያከናንቡን በቅተዋል።... (የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about የተከለከለውን እንደተፈቀደ…