… ይህን ሁሉ ሰብአዊ ክብራችንን ያሳጣን ዘረኛ አስተዳደር፤ ይህ አልበቃ ብሎት በታሪካችን፣ በሐይማኖታችን፣ በወንጀለኛ መቅጫ ሕጋችን ሳይቀር የተከለከለን ድርጊት የመንግስት የፀጥታና የደህንነት አስከባሪ ነን በሚሉ አስተሳሰበ ድውያን ሰሞኑን በአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል በአቶ አበበ አካሉ ላይ አስገድደው የአልኮል መጠጥ በመጋት የተፈፀመባቸውን የወሲብ ጥቃት ወንጀል ማህበራችን በፅኑ ያወግዛል። በረጅም ዘመን የነጻነት ታሪካችን በግብረ ሰዶማዊነት ራሳቸው ፈቅደው ከተሰማሩ ሰዎች ውጭ ሕግ እናስከብራለን በሚሉ ኃይሎች እንዲህ አይነቱ ነውር በእኛ ትውልድ ሲፈፀም በማየታችን በህሊናችን ውስጥ ጊዜ የማይሽረው ጠባሳ አሳርፈውብናል። የመጨረሻውንም የውርደት ሸማ ሊያከናንቡን በቅተዋል።… (የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
andnet berhane says
በአቶ አባብ አካሉ ላይ ተፈጸመ የሚባለው የመጠጥ ይሁን ሌላም ተግባራት በቃልና በምልጃ መልስ ለማግኘት ሳይሆን እያያንዳዱ ዜጋ ወሳኝ የሆና እርምጃ በወያኔ አሸባሪዎች ሎሌዎች ላይ የማያዳግም ክንዱን ማንሳትና ራሱን ለመጠበቅ የሚያቅደው የጎበዝ አለቃ መፍጠርና መንነቱን ማሳወቅ ይኖርባታል፡ ይህም ጉዳይ በጉምጉታ የሚታለፍ ሳይሆን ታሪክና ማንነታችንን ስለሚያበላሽ መቀጨት አለበት፡ የዚህን ድርጊት የፈጸሙ የጸትታ ኃይሎች በግለሰብ ሳይሆን በጅምላ በሁሉም ላይ እርምጃ መወሰድ አለበት፡ ምክንያቱም ሰርዓቱን ተገን በማድረግ ለሚያደርጉት ማንኛውም ጥቃት ሕዝብም በተመሳሳይ አጸፋውን መመለስ አለበት። የዚህ ጉዳይ በቂ አስረጅ በማያዝ ለዓለም ሕብረተሰብ መጋለጥና ይህ ሰርዓት ሃገር የማስተዳደር ሳይሆን በሕብረተሰቡና በቀጠናው የሚያካሄደው ሕገወጥ ተግባራት፡ ምእራባውያን በተሞክራቸው ሊማሩት ያልቻሉት ተደጋሚ ታሪካዊ ክሰት ውስጥ እንደሚጥላቸው ባለማሰብ የራሳቸውን ፍርሃት በፈጠሩት አሸባሪ የሚል ተግባር ሰላምና መረጋጋት እንዳይሰፍን፡ በዓለም አካባቢ ያሉትደካማ የስልጣን ጥማተኞች ሕዝቦችን በማግለል እየፈጠሩት አንጻር ኢዲሞክራሲ ስራአት ኢሰባዊነት የህግ በላይነት አለመከበር ቁጥጥርና ተጠያቂነት የጎደለው ተግባር እያዩ በዝምታ የሚያልፉት እኛ ጠንክረን ያለውን ስራአት ለመጋፈጥ በአንድነት ባለመቆማችን በመሆኑ፡ ከነሱ የነጻነት ጥበቃ ሳይሆን እኛው ነጻነትና እኩልነት መብታችንን ለማስከበር የምናደርገው ጠንካራ እርምጃ ወደድንም ጠላን ምእራባውያንን ማሳመን የምንችለው የኃይል እርምጃ በነሱ ጋሻ ጃግሬዎች ላይ ስንወስድ ብቻ ነው። ያለፉት ትግሎች የተካሄዱት እንዳሁኑ በቀለለና በለሰለሰ መንገድ ሳይሆን በጣም ጠንካራና አስቸጋሪ እንደነበር በትግል የነበሩት አስረጂዎች ናቸው፡ በአሁኑ ሰዓት ኤሌክትሮኒክ ዘመን ሁሉንም እመገናኛና የሚፈለገውን ለማግኘት የጠላትን እንቅስቅሴና እቅዳዊ ተግባራት ለማግኘት አስቸጋሪ ባልሆነበት ወቅት ወያኔን ለመፈለም አስቸጋር እንዳልሆነ የምናየው በመሆኑ በፍርሃት ከመገዛት በጥንካትሬ ለመታገል የሚያስችል እንቅስቃሴ ማድረግ ከወርደት ያድናል
ድል ለመላው ተቃዋሚ ኃይሎች ውድቀት ለሕግ አልበኞች
ኢትዮጵያ በነጻነቷዋ ተከብራ ለዘላለም ትኑር
ምንግዜም ሕዝብ አሸናፊ ነው