
ለማዘንም ለመደሰትም የቀረበች ናት። ስለዘርና ስለቋንቋ ያላት እምነት የሚለካው በፍቅርና በፍቅር ብቻ እንደሆነ ደጋግማ ትናገራለች። ቋንቋም ሆነ ዘር የማንነት መለኪያ እንዳልሆነ አጥብቃ ትከራከራለች። ፍቅርን እንደወረደ ከመስበክና ወገኖቿን የመርዳት ዓላማዋን ከማሳካት የሚበልጥባት ጉዳይ እንደሌለ አበክራ ትናገራለች። ገና ጀማሪ ብትሆንም ሙዚቃዎቿ ተወደውላታል የሚሉ እየበረከቱ ነው። እኔ ዘር የለኝም በሚል የሰፋ ሃሳብ ያለው ሙዚቃ ተቀኝታለች። ኢትዮጵያ የፍቅር ምድር እንድትሆን አብዝታ እንደምትሰራ ቃል በመግባት ከጎልጉል ጋር ቃለ ምልልስ አደረገችው አርቲስት ሃኒሻ ሰለሞን የምትኖረው ሎንዶን ነው። እንደሚከተለው ቀርቧል።
በቃለ ምልልሱ ሃኒሻ ላይ በደል ፈጽሟል የተባለው የባላገሩ አይዶል ባለቤት አብርሃም ወልዴ ለቀረበበት ውንጀላ ምላሽ መስጠት ከፈለገ ዝግጅት ክፍላችን በደስታ እንደሚያስተናግደው ከወዲሁ ለመግለጽ ይወዳል። በተመሳሳይ በደል የደረሰባቸው አርቲስቶች እንዳሉ መረጃዎች ስላሉ ተበዳዮችም ሃሳባቸውን ቢሰጡ እናበረታታለን።
ጎልጉል፦ ከቋንቋ እንጀምር?
ሃኒሻ፦ ከስርአቱ እንጂ ከቋንቋ ጋር የሚደረግ ጸብ ለእኔ ግልጽ አይደለም። አይገባኝም። ቋንቋ መግባቢያ እንጂ የዘር መለኪያ ሚዛን አይደለም። አንድ ቋንቋ ግን አለኝ። እሱም ፍቅር ነው። ቋንቋዬ ፍቅር ነው ብዬ የዘፈንኩትም ለዚህ ነው። በጥንቃቄ ከታሰበ ከፍቅር በላይ ምንም ቋንቋ የለም። ፍቅርን፣ እንደወረደ እሰብካለሁ።
ጎልጉል፦ ስለ ብሔር ምን ትያለሽ?
ሃኒሻ፦ ሁሉም ብሄር ብሄረሰብ በእኩልነት አንዱ አዛዥ ሌላው ታዛዥ ሳይሆን ተከባብሮ በፍቅር አብሮ መኖር ተገቢ ነው ብዬ አምናለሁ።
ጎልጉል፦ ሃኒሻ ሁለት ጉዳዮች ተደባልቀውባታል የሚሉ አሉ፤
ሃኒሻ፦ ግልጽ ብታደርገ ው?
ጎልጉል፦ “መንፈሳዊ ሰው ነበረች” ይላሉ፤
ሃኒሻ፦ ሳቀች! (ቃለምልልሱ በስልክ ስለነበር ፊቷን አላየሁትም።ማዘኗን ግን ተረድቻለሁ። ተነፈሰችና ቀጠለች።) እኔ ከመንፈሳዊ እምነቴ አልራቅሁም። የሚገርመው ሰዎች ስንባል ራሳችን የማናደርገውን ነገር በሌሎች ላይ እንደስህተት አድርገን እንገልጻለን። መጠቋቆም እንወዳለን። በዚህች ዓለም ላይ ሙሉ ነገር የለም። ለስጋህ ስትሮጥ መንፈሳዊ ነገር ይጎድልብሃል። ሁሌም በጉድለት ነው የምኖረው። በሌላ በኩል ደግሞ የተፈለገውን ያህል መልካም ነገር ቢደረግ ከወቀሳ መዳን አይቻልም።
ጎልጉል፦ መንፈሳዊ ህይወትሽ የበዛ ነበር?
ሃኒሻ፦ አዎ ምንም ጥርጣሬ የለኝም። ያደኩትም ቤተክርስቲያን ዙሪያ ነው። የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ዘማሪ ነበርኩ።
ጎልጉል፦ “ፍቅር ነው ቋንቋዬ” የሚለው ዜማ ዋናው መልዕክቱ ምንድ ነው?
ሃኒሻ፦ “እኔ አገር የለኝም፣ ዓለም ነው አገሬ፤ እኔ ዘር የለኝም የሰው ልጅ ነው ዘሬ” የሚል ሃረግ አለበት። ግጥሙ የተገጠመው ለኔ ነው። “ከቅን ጋር ዋል ቅን ሆነህ ትገኛለህ” እንደሚባለው ቀና የሆኑት የልቤን ገጠሙልኝ። አዜምኩትና ራሴንና እኔን መሰሎችን ገለጽኳቸው። ፍቅር ቋንቋ ይሆን ዘንድ፣ ፍቅር አገር ይሆን ዘንድ፣ ፍቅር ድንበራችን ይሆን ዘንድ ፍቅር መግባቢያባችን ይሆን ዘንድ የበኩሌን አደርጋለሁ። እኛን የራበን ፍቅር ነው። አይደለም?
ጎልጉል፦ ኦሮሞ ሆነሽ “ለምን በአማርኛ ዘፈንሽ” በሚል ተቃውሞ አጋጥሞሻል? ካጋጠመሽ በዝርዝር ልታስረጂኝ ትችያለሽ?
ሃኒሻ፦ እንደዚህ የሚል ነገር አላጋጠመኝም። አልደረሰብኝም። ከአዘፋፈን ስልት አንፃር ግን በየትኛው ቋንቋ በይበልጥ ብጫወት ጥሩ እንደሚሆን ምክር አዘል አስተያየት የሰጡ አሉ።
ጎልጉል፦ ያጋጠመሽን ችግር አንባቢያን ቢያውቁትና ቢወያዩበት በሚል ነው? “ኦሮሞ ሆነሽ ለምን በአማርኛ ትዘፍኚያለሽ” በሚል የተቃወሙ የሉም ነው የምትይው?
ሃኒሻ፦ ያጋጠመኝ ችግር የለም። ግን ማወቅ ያለብን ነገር ቢኖር አንድ ነገር ስትሰራ በማንኛውም መንገድ የሚቃወሙና የሚደግፉ መኖራቸውን ነው። ትልቁ ነገር የሚደግፉትን እያመሰገንህ የሚቃወሙህን ደግሞ ቀና በሆነ መንገድ ተወያይቶ እንዲወዱኝ ማድረግ ነው። ፍቅር ነው ቋንቋዬ ብዬሃለሁ እኮ …። አንድ ሰው ደግሞ ብዙ ቋንቋ ከቻለ መልእክቱን በሚችላቸው ቋንቋዎች ሁሉ ማስተላለፉ ታላቅ ችሎታ ነው። ይህን ችሎታዬን እንድቀጥልበት እንዲያውም በርቺ ነው የሚሉኝ።
ጎልጉል፦ ስለ ዘር ፖለቲካ ምን ሃሳብ አለሽ?
ሃኒሻ፦ ፖለቲካውን ለፖለቲከኞች እተወዋለሁ። ዓለም ዛሬ ድንበር አፍርሶ አንድ እንሁን ባለበት ዘመን ዘርና ጎሳ መቁጠር በግል ያሳዝነኛል። ጎሳና ዘር ቆጥረን ለምን እንለያያለን? ተለያይትንስ መጨረሻው ወዴት? መድረሻውና ማቆሚያውስ? ግን ይህንን ስል አንዱ ከሌላው በላይ ሆኖ የሌሎችን መብት እኩልነት ነፍጎ ሳይሆን ማንኛውም የሰው ልጅ እኩል መሆኑ ታምኖ በእኩልነት ተከባብሮና ተፋቅሮ መኖር ያስፈልጋል ብዬ አምናለሁ።
ጎልጉል፦ በዘርና በጎሳ ሃሳብ ላይ የመስራት እቅድ አለሽ?
ሃኒሻ፦ አዲስና ታዳጊ አርቲስት ነኝ። በማህበራዊ ጉዳየች ላይ ብዙ እቅዶች አሉኝ። ዝም ብሎ ለመዝፈን ሳይሆን ትርጉም ያላቸው ስራዎች ለመስራት እፈልጋለሁ። ማናጀሬ ካሰብኩት ግብ እደርስ ዘንድ እንደሚረዳኝ የጸና እምነት አለኝ።
ጎልጉል፦ ለመሪዎቻችንስ ትዘፍኝላቸዋለሽ?
ሃኒሻ፦ እነሱም እኮ ሰው ናቸው። ለህዝብ ሲዘፈን እነሱንም ያካትታል። ለሚሰማ ሁሉ እዘፍናለሁ። የኔም ሆነ የሌሎች አቀንቃኞች ድርሻ የራሳችንን መወጣት ነው።
ጎልጉል፦ በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ አቋምሽ እንዴት ይገለጻል?
ሃኒሻ፦ አብሮ መኖር፣ መስራት፣ መከባበር፣ መፈቃቀር፣ የወደቀውን መደገፍ….
ጎልጉል፦ በተለይ የሚያስደስትሽ?
ሃኒሻ፦ የተቸገሩ ሰዎችን መርዳት በጣም ያስደስተኛል። ወደፊትም በዚህ ዙሪያ ሰፊ እቅድ አለኝ። የታመሙ ሰዎችን መጎብኘት ልዩ ርካታ ይሰጠኛል።
ጎልጉል፦ ሃብታም ነሽ?
ሃኒሻ፦ (ሳቅ…) ምነው አበድሪኝ እንዳትል ብቻ? የእኔ ገንዘብ ባካባቢዬ ያሉ ናቸው። የኔ ሃብት ህዝብ ነው። የኔ ሃብት የሰው ዘሮች ናቸው።
ጎልጉል፦ ጥሬ ገንዘብ አትወጂም ማለት ነው?
ሃኒሻ፦ ሆ ሆ ምነው? ማን ብር ይጠላል? ገንዘብ እኮ የፈለከውን ታደርግበታለህ። የሚያስደስትህን ነገር ለማድረግ ያለ ገንዘብ አይሆንም። ገንዘብ ጥሩ ነው። ግን ልዩና ከሁሉም በላይ ተደርጎ የሚቀመጥ አይመስለኝም።
ጎልጉል፦ እና ላንቺ ሃብት ምንድ ነው?
ሃኒሻ፦ ሃብት የሰው መውደድ ነው የእግዚአብሄር ፀጋ ነው። በእምነት፣ በፍቅር ተከባብሮ መኖርና ሃሳብን በነጻነት ማንሸራሸርም ትልቅ ሃብት ነው።
ጎልጉል፦ ድህነትን ጠንቅቀሽ ታውቂዋለሽ?
ሃኒሻ፦ በሚገባ!! ጥሩ የደሃ ልጅ ነኝ። የድህነት መገለጫዎች በህይወቴ አልፈዋል። ባደኩበት ገጠር አንድ የገጠር ደሃ ቤተሰብ ያሳለፈውን ህይወት አልፌያለሁ። አብዛኛው ህዝብ በድህነት ከሚኖርበት ማህበረሰብ የወጣን ሁላችንም ድሆች ነን። ለኔ ግን ትልቁ ድህነት ሌላ ነው።
ጎልጉል፦ ምንድነው?
ሃኒሻ፦ ሃሳብን እንደልብ መግለጽ አለመቻል ለኔ ትልቁ ድህነት ነው።
ጎልጉል፦ እስኪ ስለ “አፍሪካ ተባበሪ” ንገሪኝ?
ሃኒሻ፦ መነሻው የኔ ባይሆንም “አፍሪካ ተባበሪ” የሚል ዜማ አለኝ። ቀደምት የአፍሪካ መሪዎች ፓንአፍሪአካኒዝም ብለው ሲጀምሩ፣ አፍሪካ በአንድ መሪ እንድትመራ ሳይሆን አፍሪካውያን ሰላም ፈጥረው ድንበር የለሽ ኑሮ እንዲኖሩ ነበር። አሁን በተጨባጭ የምናየው የአፍሪካውያን ዕጣ ስደት፣ ረሃብና እርዛት ነው። እንደምታየው አውሮፓውያን ሁለት ጊዜ የአለም ጦርነት አድርገዋል። አሁን ግን አዲሱ ትውልድ በሰላም በመከባበር በእኩልነት ይኖራሉ። ሀያ ስምንት አገሮች ለዜጎቻቸው ድንበር የለሽ ለመሆን ተስማምተው እየኖሩ ነው። እኛ አፍሪቃውያንም እንደነሱ የማንሆንበት ምክንያት የለም። አዲሱ ትውልድ መንቃት አለበት።
ጎልጉል፦ “አዮ – እናት” የሚለው ዘፈን ለእናት ይከራከራል፤ ለምን?
ሃኒሻ፦ እናት ዘጠኝ ወር ተሸክማ፣ አምጣ ወልዳ፣ አጥብታ አሳድጋ፣ ልጇ የሚጠራው ወይም የምትጠራው በአባት ስም ነው። ለምን እናት አትካተትም? “ለኔ ስም ሲያወጡልኝ፣ ያንቺ ስም ወዴት ተፋቀ?” በማለት መብትን የሚጠይቅ ዘፈን ነው። በነገራችን ላይ በሴቶች ዙሪያ ከሰብአዊ መብት አንጻር ወደፊት ትኩረት ሰጥቼ የምሰራው ሌላው ስራዬ ነው።
ጎልጉል፦ ሙዚቃ አድጓል የሚሉትን ትደግፊያለሽ?
ሃኒሻ፦ ሙዚቃ እድገት የሚኖረው የሙዚቃ ድርጅት ሲኖር ነው። አለበለዚያ አርቲስቱ ለግጥም፣ ለዜማ፣ ለማቀነባበሪያ ለማሳተሚያ ወዘተ እያወጣ ሙዚቃው አድጓል ለማለት ያስቸግራል። እንዲያድግ ከተፈለገ የሙዚቃ ድርጅቶች ታላቅ ሚና መጫወት ይኖርባቸዋል። ታላላቅ ችሎታ ያላቸው ከያንያን አሉ ግን በግላቸው ያለ ድርጅት እርዳታ እነሱም ለማደግ ይቸገራሉ የሙዚቃዉም እድገት በዓለም ደረጃ ውስን ይሆናል።
ጎልጉል፦ ሁሌም የሚያባንንሽ ድንጋጤ አለ ይባላል፣ እውነት ነው?
ሃኒሻ፦ አዎ! የመኪና አደጋ ደርሶብኝ ነበር።
ጎልጉል፦ በወቅቱ ሞተሽ የተነሳሽ ያህል ተሰምቶሽ ነበር?
ሃኒሻ፦ አዎ! እንቅልፍ እንኳ የሞት ታናሽ ይባል የለ። ከመኪና አደጋ በአሰቃቂ ሁኔታ መትረፍ፣ እውነት ለመናገር አሳዛኝ ጊዜ ነበር። አምላክ ምስጋና ይግባውና አለሁ።
ጎልጉል፦ የተለየ ክስተት ነበር?
ሃኒሻ፦ ቤቴ አካባቢ ከሚኒባስ ወርጄ መንገድ ሳቋርጥ መኪና መታኝ። እንደገጨኝ ተነስቼ በሩጫ ቤት ገባሁ።
ጎልጉል፦ መኪናውስ?
ሃኒሻ፦ እኔ እንጃ፤ የማውቀው ነገር የለም።
ጎልጉል፦ ሲገጭሽ ለምን ሮጥሽ?
ሃኒሻ፦ ደነገጥሁ በተጨማሪ ከገጨኝ መኪና ጋር መከራከር የማልችልበት ወቅት ላይ ነበርኩ። ስደት!! እቤቴ ስገባ እጄ፣ ጉልበቴ፣ ትከሻዬ ጀርባዬ ደምቷል። ተጎድቻለሁ። ከዓመት በላይ ህክምና ሳላገኝ ቆየሁ። ላገሩ አዲስ ስለነበርኩና የመኖሪያ ፈቃድ ስላልነበረኝ ህክምና ለማግኘት ተቸግሬ ነበር። አሁን ድረስ የሚሰማኝ ስሜት አለ። ችግሩ ብዙ ነበር እንለፈው።
ጎልጉል፦ ለንዶን የተሳካልሽ ይመስላል?
ሃኒሻ፦ ፈጣሪ ምስጋና ይግባው ሰላም ነው።
ጎልጉል፦ ለእድገትሽ በስራሽ ላይ መሰናክል የሆኑ ነገሮችስ አጋጥሞሻል?
ሃኒሻ፦ አዎ! ግጥም እንሰራለን ዜማ እንደርሳለን እያሉ ገንዘብ ከተቀበሉ በኋላ በቃላቸው በማይገኙ ስዎች የተነሳ ጊዜየ ባክኗል፡፡
ጎልጉል፦ “አብርሃም ወልዴ የባላገሩ አይዶል ባለቤት አጭበርብሮሻል” ይባላል ምንድነው ያጭበረበረሽ? እውነት ነው?
ሃኒሻ፦ በዚህ ጉዳይ ላይ ውሉን የተዋዋለው ማኔጀሬ ስለሆነ መናገር የሚችለው ማኔጀሬ ነው እና እሱን ብትጠይቀው ይሻላል፡፡ አለችኝ።
ጎልጉል፦ እኔም መልካም በማለት የሃኒሻን የሙዚቃ ሃላፊ ጋዜጠኛ ድልነሳውን ስለ አብርሃም ወልዴ ማጭበርበር እንዲያብራራልኝ ጠየቅሁት::

ጋዜጠኛ ድልነሳው፦ እኔ የምኖረው ሎንዶን ነው። እና አብርሀም ወልዴን እዚህ በመጣበት ወቅት አፈላልገን አግኝተነው ስንስማማ ፍትህ ወዳድ፣ ጥሩ ሰው፣ ሀቀኛና እውነተኛ ሙያውን የሚያከብር እንደሆነ አጫወተኝ። እኔም አመንሁት ለሃኒሻ ሙዚቃ ስራ መሳካት እኔ ገንዘብ ስለከፈልኩት ብቻ ሳይሆን እሱም በተጨማሪ እንደሚረዳት አብረን በሙዚቃ ሙያዋ እንደምናሳድጋት ቃል ገባ። እኔም አመንሁት 8 ዘፈኖችን ለማዘጋጀት 5ሺህ ፓውንድ ወሰደ። በተጨማሪ ደግሞ ሁለት ዘፈኖችን በሌላ ሰው ሊያስራላት 12ሺህ የኢትዮጵያ ብር መስማማቱን ገለጸልኝ። ገንዘቡ ተከፈለው። በጣም ተከራክሮ ዋጋ እንዳስቀነሰም ነገረኝና አመንኩት። እሱ የሚሰራቸውን ስምንት ዘፈኖችና በሌላ ሰው የሚያሰራቸውን ሁለት ዘፈኖች በጥቅሉ 10 ዘፈኖችን በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ግጥምና ዜማውን እሰጣለሁ ብሎ ቃል ገብቶ ተስማማን። እንኳን በሶስት ወር ቀርቶ አምስት አመት ጠብቀን አላገኘነውም። አብርሃም የውሃ ሽታ ሆነ። እምነቱን አጎደለ። የተረዳሁት ነገር ቢኖር ከአብርሃም ወልዴ ጋር ስትወያይ በብርጭቆ ድንጋይ እሰብራለሁ ብሎ የሚያሳምን ምላስ ያለው ሰው መሆኑን ነው። የሚገርመው በተገናኘንበት ወቅት አብርሀም እንዲያዉም “ፕሮጀክቴን ቀድተው ኢህዴጎች ለራሳቸው ሰዎች ሰጡብኝ” በማለት በሙያዬ ሁሉ እንድረዳው ጠይቆኛል። ከዛሬ አስር ዓመት በፊት እንግዲህ ተጭበረበርሁ ያለ ሰው እራሱ አጭበርባሪ ሲሆን በጣም ያሳዝናል። 5ሺህ ፓውንድ ቀላል ገንዘብ አይደለም። ከሁሉም በላይ ደግሞ የምታድገዋን ልጅ እድል መግደል ወንጀል ነው። በስልክ የተነጋገርናቸው ጉዳች በሙሉ ተመዝግበው ተይዘዋል። በተጨማሪ ሌሎችም ያጭበረበሩና ዘፈን የሰረቁን ሁሉ አሉ። ያም ሆነ ይህ ወደፊት ትልቅ አርቲስት እንደምትሆን ስለተረዳሁ የሁለት ልጆች አባት እንደመሆኔ ሶስተኛ ልጄ ትሆኛለሽ በማለት ልረዳት ቃል በገባሁላት መሰረት ሃኒሻን ትልቅ ቦታ ለማድረስ ጥረቴ ይቀጥላል።
ጎልጉል፦ ሃኒሻ የምትጨምሪው አለ?
ሃኒሻ፦ ወደ ሙዚቃው ዓለም ስገባ አንድ የኦሮምኛና አንድ የአማርኛ ሲዲ ለማሳተም ነበር የመጀመሪያ አላማዬ። ግን ያው ማኔጀሬ እንዳለው በደረሰብን ችግር የተነሳ ስድስት የአማርኛና ስድስት የኦሮምኛ ዘፈኖችን ለማሳተም ሲወሰን እንዴት አማርኛውና ኦሮምኛው ተቀላቅሎ ይቀርባል? ግማሽ ኦሮምኛ ግማሽ አማርኛ ያልተለመደ ስራ ይዘጋጃል በሚልና አንድ አማርኛ አስራ አንድ ኦሮምኛ ወይም አንድ ኦሮምኛ አስራ አንድ አማርኛ ዘፈን መሆን አለበት የሚለው ጉዳይ በሙዚቃ አሳታሚዎች ዘንድ አነታራኪ ሆነ። ለምን አንድ ኦሮሞኛ ወይም አንድ አማረኛ ይሆናል በማለት ማኔጀሬ ድልነሳው ሲጠይቃቸው የሰጡት መልስ ያልተለመደ ስራ ነው የሚል ነው። በመጨረሻ ማናጀሬ ጋዜጠኛ ድልነሳው “እኔ እራሴ አሳትመዋለሁ” በማለት ጠንካራ አቋም በመውሰድ አልበሙ ታተመ።
ጎልጉል፦ ማናጀርሽን ድልነሳውን እንዴት አገኘሽው?
ሃኒሻ፦ እዚህ እግሊዝ አገር ፊልም ለመስራት ምልመላ በነበረበት ወቅት እሱም አንዱ መላማይ ሆኖ ተገኝቶ ነበር። እዛ ኩኩ የምትባል ጓደኛዬ አብራኝ ነበረች፤ ጎበዝ ናት እና እሷ ስትዘፍን በዕረፍት ጊዜአችን እሷን እየተቀበልሁ ስጫወት ሰማኝና ዘፋኝ መሆን የሚያስችል ድምጽ እንዳለኝና ዘፋኝ መሆን እንደምችል ሲነግረኝ “የሚረዳኝ ካለ” አልኩት። “ሁለት ሴት ልጆች አሉኝ ሶስተኛ ልጄ ትሆኛለሽ” አለኝ። በዚሁ አባቴም፣ ማናጀሬም፣ የህይወቴ አዲሱ መንገድ መሪ ሆነ።
ጎልጉል፦ የአዘንሽበት ቀን አለ?
ሃኒሻ፦ ማናጀሬ ድልነሳው ታሞ የቀዶ ጥገና ለማድረግ ሆስፒታል ገብቶ ነበር። በቅርቡ እንደገና መልሼ የማላገኘው መስሎኝ ነበር። በህይወቴ ያዘንኩበትና በጣም የተጨነኩበት ጊዜ ነው። አምላክ ቸር ነውና በሚገባ ድኖ … (አለችና … አለቀሰች። ከቆይታ በኋላ እንደመሳቅ ብላ) … ሰሞኑን በባህር የሰመጡ ምስኪን ወንድሞችና እህቶች ዜና ክፉኛ ልቤን ነክቶታል አለችኝ። ዳግም አለቀሰች …
ጎልጉል፦ ዘፋኝ እሆናለሁ ብለሽ ግን አስበሽ አታውቂም ነበር?
ሃኒሻ፦ በፍጹም። ሰዎች በተደጋጋሚ ድምጽሽ ጥሩ ነው ይሉኝ ነበር። እናቴ ሃኒሻ ብላ የቤት ስም ሰጠችኝ። ማናጀሬ የቤት ስሜን አደባባይ አወጣውና ታዋቂ አደረገኝ። በዚህ አጋጣሚ ስለ መልካምነቱና ስላደረገልኝ ሁሉ ምስጋናዬ ትልቅ ነው።
ጎልጉል፦ ለመጀመሪያ ጊዜ መድረክ ላይ የታየሽው የት ነው?
ሃኒሻ፦ በተለያዩ የርዳታ ማሰባሰቢያ ድራማዎች ላይ ተሳትፌያለሁ። በ2001 ለንደን በተካሔደ የኢትዮጵያዊያኖች የቁንጅና ውድድር ተሳትፌ 3ኛደረጃ አግኝቻለሁ። ግን በመዝፈን ደረጃ ከሆነ በ23ኛውና በ24ኛው በሎንደን የገለስፒ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ነው። በ2012 ደግሞ በቦትስዋና የነፃነት ክብረ በኣል ላይ ተጋብዠ ተጫውቻለሁ። እና አሁን በቅርቡ ደግሞ በ11ኛው የአፍሪቃ አገሮች የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ተጫውቻለሁ።
ጎልጉል፦ ተስፋ ስለመቁረጥ አስበሽ ታውቂያለሽ?
ሃኒሻ፦ ብዙ ተፈትኛለሁ። ብዙ የህይወት ውጣ ውረድና ክህደት አዳክሞኝ ነበር። ግን ሁሌም አንድ ትልቅ እምነት አለኝና እዚህ ደረስኩ። እምነቴ በማንኛውን ሁኔታ ውስጥ ማለፍ የምችልበት ሃይል እንዳለኝ ማመኔ ነው። አሁን በጥሩ ጅምር ላይ ነኝ። አሰብኩበት እደርሳለሁ የሚል ሙሉ እምነት አለኝ። ከእግዚአብሔር ሳልርቅ!!
ጎልጉል፦ ከዘፈንሻቸው ዘፈኖች ውስጥ ባልዘፈንኩት የምትይው ዘፈን አለ?
ሃኒሻ፦ ገና መቼ ዘፈንኩና!
ጎልጉል፦ ሞዴል አድርገሽ የወሰድሽው ዘፋኝ አለ?
ሃኒሻ፦ የለም።
ጎልጉል፦ እንዴት ነበር የምትለማመጂው?
ሃኒሻ፦ ድምጽሽ ረበሸኝ የምትል ምቀኛ ጎረቤት ብትኖረኝም ጭር ሲልልኝ ቤቴን ዘግቼ በቴፕሪኮርደር እየቀዳሁ እለማመድ ነበር። እድሜ ለማናጀሬ እያረመኝ እዚህ ደርሻለሁ። ስለቅላጼ እንኳን የማውቀው ነገር አልነበረኝም። ቅላጼ ምን እንደሆነ የተረዳሁት ሲዲው ከታተመ በኋላ ነው። እኔን በማነጽ ማናጀሬ ድልነሳው ታላቅ ስራ ሰርቷልና ሁሌም ለምስጋናው ከፊት ለፊት ረድፍ የሚገኝ ይሆናል።
ጎልጉል፦ ባንድ አለሽ?
ሃኒሻ፦ አዎ፤ አለኝ ሙሉ ባንድ። የባንዱ ማለትም የሙዚቃ ቡድኑ ኃላፊ ጋናዊ ነው። አዲስ ጅምር ነው እናድጋለን።
ጎልጉል፦ በካፒታል ምን ያህል ይገመታል?
ሃኒሻ፦ ስለገንዘብና ሃብት መጠየቅ ታበዛለህ። አዲስ ነን። ግን በቅርቡ እናድጋለን። አብረን ለመስራት ቃል ገብተዋል።
ጎልጉል፦ በአስራ አንደኛው የአፍሪቃ ሙዚቃ ዝግጅት ፌስቲቫል ላይ ተሳትፈሽ ነበር ተሳካልሽ?
ሃኒሻ፦ በጣም ውብ ዝግጅት ነበር። ኢትዮጵያ አገሬን ወክዬ ነበር የተሳተፍኩት። የፌስቲቫሉ መዝጊያው ላይ ሙሉ ስራዬን አቅርቤ ተወዶልኛል። መድረክ ላይ ሆኜ የተሰጠኝ ምላሽ ግሩም ነበር። ከመድረክ ስወርድም ዘወትር እንደማደርገው የማናጀሬን ፊት ሳየው ጥሩ እንደሰራሁ አመንኩ። እኔ ሲቀናኝ መደሰቱን ፊቱ ላይ አነበዋለሁ። ሳቅ …
ጎልጉል፦ ወደ እንግሊዝኛው ዘፈን ለማምራት ታስቢያለሽ?
ሃኒሻ፦ ለጊዜው ሀሳብ የለኝም። የአገሬን ባህልና ወግ መልቀቅ አልፈልግም። ብዙ ውብ መልክና ገጽታ አለን። አገሬን በሙያዬ አጎላለሁ ብዬ አስባለሁ እንጂ ሎንዶን ስለምኖር እንግሊዘኛ ልዝፈን ብዬ ከኔ ከሚበልጡት ተወላጆች ጋር ግፊያ ውስጥ አልገባም። የማሊ፣ የካሜሮንና የሴኔጋል ዘፋኞች በውጪው ዓለም በራሳቸው ቋንቋ በከፍተኛ ደራጃ ተደማጭ ሆነዋል ። እኔም ባገሬ ቋንቋ ዘመንን ተከትዬ መግፋት ነው ፍላጎቴ።
ጎልጉል፦ በጣም የሚያስደስትሽ ምንድ ነው?
ሃኒሻ፦ ማይክ ይዞ መድረክ ላይ መውጣት ያስደስተኛል። የሰዎችን ጭንቀት መጋራት፣ በሰዎች ሃዘን ውስጥ መሳተፍና ራሴን በተጎዱ ሰዎች ቦታ በማስቀመጥ ለተወሰነ ጊዜ ማሰብ እጅግ ያስደስተኛል።
ጎልጉል፦ የምትጠየፊው ነገር አለ?
ሃኒሻ፦ ቃሉ ከበደ። የምትጠይው ነገር ለማለት ከሆነ ግን ሰው ማማት አልወድም። ሰው የማያከብር ሰው አልወድም። በደልን ማድረግ አግባብ አይደለም ብየ አምናለሁ። በደልን በጠየከኝ ቃል መጠን አልወድም።
<
ጎልጉል፦ ምኞትሽ?
ሃኒሻ፦ በሴቶች ጉዳይና በሰብአዊ መብት ዙሪያ የመስራት እቅዴ እውን ሆኖ ማየት እፈልጋለሁ። የርዳታ ስራ ላይ ለመሰማራት የጀመርኩት ስራ አለ። እሱም እንዲጠናቀቅልኝ እመኛለሁ። ከሁሉም በላይ የፍላጎቶቼ ሁሉ መሰረትና የህልሞቼ ቁልፍ በሆነው ሙያዬ ታላቅ ስም መትከል እፈልጋለሁ። የማናጀሬ ድልነሳው ፍላጎትና ህልም በእግዚአብሔር አርዳታ ይሰካ ዘንድ ጸሎቴ ነው። የሚወዱኝም በሃሳብ እንዲተባበሩኝ እፈልጋለሁ።
ጎልጉል፦ በምን እንጨርስ?
ሃኒሻ፦ ስራዬን ለተከታተሉልኝ፣ ሃሰብ ለሰጡኝና መልካም ለተመኙልኝ ሁሉ የልብ ምኞታቸው እንዲደርስላቸው እመኛለሁ። ክህደት መልካም አይደለምና የክህደት ልብ ያላቸውን ተግባራቸውን እንጂ እነሱን እንደማልጠላቸው በዚህ አጋጣሚ ለማሳወቅ እፈልጋለሁ። ወደልባቸው በመመለስ ህሊናቸውን አጽድተው እንዲኖሩም እመክራቸዋለሁ። ለሁሉም የአገሬ ሰዎች ቋንቋቸው ፍቅር፣ አገራቸው ፍቅር፣ ህይወታቸው ፍቅር እንዲሆን እመኛለሁ። አመሰግናለሁ!! (የሃኒሻ ፎቶዎች በሙሉ የተወሰዱት ከHanisha Solomon Facebbok ነው)
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
Thank you Gulgule for the complete and wholehearted interview. Hanish – Do not listen to your dis – tractors. Hope is a vital element for life. As for poem writers – Tell us the subject matter you would like to sing and we can formulate the best of best in a short period of time. Keep rolling!
Hanisha Kiyyaa,
Even if you love and respect them, they will never reciprocate and spit you once they used you. Even if you judge and respect them as a human being, they will discriminate against you just because you are an Oromo(May be they want your land, not you!). So my dear sister you better stand by your people before it is too late!
Alagaan alaguma!
U r not a man with a normal mind ,so not allowed to give a comment that u didn’t deserve. first b a man & think just like a man.
What an intelligent and genuine girl she is!! The way she uses words is amazing. She is our precious resource, needs encouragement and support at all levels. Thank you golgule, for the media coverage.
ye lb derash blsh , maganen ayhunbng ,, eneam flagotea yanchwu flagot hono agngchewalehu,, baqedkut eqdm baysaka, yanchn eqd ena flagot bemesmatea kelb elshalehu rekawu yenea eht, endanchi dmTs norong yelbeaan zefngea lesewu lji fqr balgelTsm, and qen gn sle sewu lji fqr mehonu qonqowu, besrayea beEmnetea endemasakawu feTari yagzengal byea amnalhuw,, anchi eht alem gn yhn bemadregsh kelb amesegnshalehu, yelb derash byeshalehu,, endihum lemanajersh kelb amesegnlshalehu kbr lesu yhun,,, berchi good luck my lovely sis, “Hanisha“
እናመሠግናለን ጎልጉሎች!
ሃኒሻ ሰለሞን በጣም በርች። ሙዚቃሽ ልብ ይሰርቃል። አንች እንዳልሸው አገርሸ ዓለም ነው፤ ቋንቋሽ ፍቅር ነው፤ ሃብትሽ ህዝቡ ነው። የ ቁንጅናሽ ምንጭ ደግሞ ኢትዮጵያዊነትሽ ነው። በሙዚቃዎችሽ ይዘት ሆነ በቃለ መጠይቅሽም ብዙዎችን ሳታስተምሪ እንዳላለፈሽ ስገልፅልሽ በደስታ ነው። በነገው ወይም በመጭው የሥራ/የሙዚቃ እቅድሽ ላይ ከዚሕ የበለጠ ሠርተሽ ትቀርቢ ዘንድ አምላክ ከጎንሽ ይቆም ዘንድ አሜን!
የአብርሃም ወልዴ ተግባር ግን አሳዝኖኛል፤ አብርሃምን በዚህ መልክ አልጠበቅሁትም ነበር። እዉነት ይሄንን አደርጎ ከሆነ ግን በጣም አሳፋሪ ተግባር ነው። ጎልጉሎች እባካችሁ የአብርሃም ወልዴን መልስ እንጠብቃለንና አብርሃም ወልዴ በቀረበበት የክስ ጉዳይ ላይ ቀርቦ ራሱን ለህዝብ ግልፅ ያደርግ ዘንድ ጠይቁልን።
Thanks
This interview shows how Hanisha smarted the interviewer. she is very smart and very articulate. she absolutely read and understood the inner intention of of the interviewer who continuously tried her to say something about her ethnicity. Good job Hanisha.
በቅድምያ የኢዚአብሔርን ሰላምታዬን በማስቀደም ሃንሻ ሰለሞን እንደምነሺ ሰላምነሺ ፍቅር እና ስላም ለኛ ለኢትዮጵያን ወሳኝ ነው ኢትዮጵያ 85
ቓንቓ እዳለን ይታወቃል ያግን ሊከፋፍለን አይችልም ቓንቓዎቹ አብረዉ ለሺ ዘመናት በፍቅር በአንድነት ንሮዋል አሁንም ለዘል ዓለም ይኖራሉ
በቓንቓ በዘር በቢሄር በጎጥ በክልል በዘረኝነት የሚያምኑ ጠባቦች ጥቂቶች ለማንምን መወከል አይችሉም ጠባብንት ይሰበራል በፍቅር በአንድነት
ኢትዮጵያ ትኖራለች ለዘል ዓለም
አርቲስት ሃንሻ ሰለሞን ቀጥይበት እንወድሽ አለን ከቅድስ ሀገር እራኤል
lovely lady ,well done
Wey Good Hnisha konjo kale melelesnew, Zefenocheshe astemarewoch nachewe. Batekaly yemasdeset new yemejemray beeselet yetmolu zefenoch besekat makereb kelale ayedelem. Keep it up.
you are great as artist and as human ….so be proud of you…..
ሃኒሻ በሥራሽ ብቻ ደግማለሁ በሥራሽ ብቻ በርቺ።
I have known Hanisha Solomon over the last 16 years, ever since she was a little choire girl at the London Debretsion St Mary church. She is amazing. You take one look at her lovely face, you think thie girl is ““አንድ ቁጥር አራዳ”. You take a bit closer look! NO! She is down to earth kind and trusting girl. I loved the way she served the church, be it in the Choire Group, drama or even running around for collections, or selling church hymn books and so on. Here is what I would never ever forget about Hanisha! It was Easter Eve. The church was full of people upstairs and down staires, at our rented Green Park church. People were standing because there was no sit left except some pockets, where some decide to put their bags or things to prevent others from sitting. Young Hanish saw a space and very politely asked a lady to move a little but so that an elderly man stand would get a space to sit. The woman literally barked at. We expected Hanisha to shout back. Surprise, Hanisha’s eyes almost were full of tears and she was begging her for forgiveness as she did not mean to. I saw Hanisha dancing to traditional “እስክስታ” at a wedding. She took all of us by surprise. The professional singer, Assefu Debalqie, had to match her. No way! Young Hanisha shined, shaking those tiny shoulders like an እንዝርት and those talking eys cutting her oponent here and there. None of us dared to challenge her. Hanisha grew, while I am watching her, no night-clubs, no dodgy places to hold concert, but only dignified places. Her manager is my best friend. I am watching her rising like a star, still with her dignity intact. The kind hearted, considerate and trusting Hanisha is an angel at heart. She may rise and rise, I full heartdly trust that she would remain the same loving, caring and kind Hanisha! Hanisha, may the Lord bless you!
I love z way u describe her & this is what our lovely tradition & religion thought us.my Religion teaches me to Love even my Enemy.GOD BLESS ETHIOPIA.
Beautiful girl inside out. We need more girls like you Hanisha. Smart, intellegent, beautiful and gifted in many ways. I have always suspected there is more to you than the eye can meet.
Keep it up. I will go a long way.
Respect
Hirut
“ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።”
Perfect,but only z diamonds can do that….!!!!!
Meche new metmleshew wed abateshe bet
medere bente ser ylelachu sera fetoch yet abatachehun new degmo enante ye mecherashawn seat yemtawukut acheberbarewatch
Wow It is so interesting interview and teachable,manner able and so on.
Jesus is the only way to Heaven and Satan and the world will push you to hell. Come back to Jesus. God bless you
10Q golgol its best for our people
THIS IS THE MOST INSPIRED AND REFLECTED, AUTOMATICALLY, I, WOULD SAY A PERSON WHO LOVES HIS COUNTRY, HIS PEOPLE HAS TO EMERGE SAME GOOD, BEAUTIFUL, AND SWEET WORDS TO HIS BELOVED PEOPLE, WELL DONE
Dear Readers,
I like this artist, she is honest and growing young artist. I know Abrham Woldi very well. Abrahm is Guragi by his mother and father. He is very approachable person, I strongly advice her to contact him and get back her money if the case is true. He has brothers in London and it is not difficult to contact him. I am sure this case could be dealt through friends, Abrahm is very generous and he came from very rich family and not greedy at all. But you need to contact him or travel to ethiopia. Otherwise you need to deal with it legally. You didn’t tell us what you have tried through legal means.
Great people speaks great words, I salute you Hanisha for your wonderful words , love respect and belief to wards human being . these everlasting words of you can be a good lesson for those who are dreaming and digging the whole to hide the fact that Ethiopia is the home of all ethinic groups (85) none of them are the same but equal in dignity with beautiful culter which sum up to form the country Ethiopia. Once again I appreciate that you are such a genuine bilingual or multilingual artist. Keep on doing good job gulgul
Hanisha you are very beautiful in and out ,a whole heartd Ethiopian woman let the almighty God be with you my sister .
Thanks Golgul for this interesting interview. Hanysha, u will be done well, God be with u & be strong
Waw migerm ka meteyikina melis new azinagnim astemarim new beteley be gosa ena be kuankuaw lemikora hager lemafres leminkesakesu hulu fikir hulum neger new fikir hulunim yashenifal gin esua lay yederesew neger betam yadazinal abiraham endezih kaderege fetari libona yistew anchim berchi ayizosh fetari miwefewin yifeyonal fetenawin yetekukuamem yetebareke new yilal berchi berchi berchi hagerachinin ena hizibun fetari yitebikilin Ethiopia le zelalem tinur
abo kefe bey …. wedfit tleke chigrachnen kemystmru …..talakoch mehal honsh ayshalhu. ….
Hanisha is a great girl. I wish everybody understand her talent.
ይድረስ ለጎልጉል አዘጋጅ፣
አርቲስት አብርሃም ወልዴ በበጎ ምግባሩና በሥራው ኮርቶ የሚኖር ጨዋ ሰው ነው፡፡ ሚሊዮኖች ይህን ይመሰክሩለታል፡፡ አኒሻም ሆንሽ ድልነሳሁ፣ የመልካም ሰውን ስም ለማጥፋት እንዲህ መጣደፋችሁ ከምን የሚነጨ እንደሁ፣ ይህን እርባና ቢስ ቃለ መጠይቃችሁን ያነበበ ሁሉ በግልጽ ይረዳል፡፡ ”በውሉ መሰረት ጉዳያችንን አልፈጸመልንምና ገንዘባችንን ይመልስልን” ከሆነ ጥያቄያችሁ፣ አብርሃምን ባጭበርባሪነት ወይም በቀማኛነት የሚያስፈርጀው አንዳችም ጭብጥ የለም፡፡ እሱም በነጻ አካል ተጠይቆ የመለሰው መልስ ነው የምትሉት እንዳችም ማስረጃ አላቀረባችሁም፡፡ እንዲሁ በእመሃበ አልቦ ካንድ ጥግ ቁሞ እሌላው ላይ ጣትን መቀሰር የሰለቸን የቸከን የዲያስፖራ የስም ማጥፋት እስታይል ነው፡፡ እናም ይህን ቃለመጠይቅ ያዘጋጀ የጎልጉል ሰው አብርሃም ወልዴን አፈላልጎ /ዪሱንም ምላሽ ጭምር እስካላስተናገደ ድረስ፣ ሚዛናዊ ግዘጣ እንዳልታሄደ ሊስተዋል ይገባል፡፡ አብርሃም ወልዴ ድብቅ ወይ ስውር ሰው አይደለም፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣት የጥበብ ሰዎችን ገጠር ለገጠር እየዞረ የሚያሰባስብና ወደ መድረክ የሚያወጣ ሰው መሆኑን፣ ዝነኛውን ”የባላገሩ አይዶል” ያየ ሁሉ የሚመሰክረው ሃቅ ነው፡፡
በተጨማሪም አቶ ድልነሳሁም ሆነ ወይዘሮ ሃኒሻ ማስረጃቸውን ይዘው በሕግ ፊት አብርሃምን ማንበርከክ ሲችሉ (እውነት እነሱ እንደሚሉት ገንዘባቸውን ከዘረፋቸው) በእንዲህ አይነት ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያንድን ስመ ጥር ባለሙያ ስም ማጥፋት ከትዝብት በስተቀር የመያተርፈው አንዳችም ፋይዳ የለም፡፡ አስተዋይ ልቡና ይስጥልኝ እላለሁ፡፡
ከሰላምታ ጋር፣
ማስተዋል
ሰላም ማስተዋል
ቃለምልልሱ ሲጀምር ባለው የመጀመሪያ ሁለተኛ አንቀጽ ላይ እንዲህ ብለን ነበር:: ምናልባት ካላስተዋሉት እንድንደግመው ይፍቀዱልን:-
“በቃለ ምልልሱ ሃኒሻ ላይ በደል ፈጽሟል የተባለው የባላገሩ አይዶል ባለቤት አብርሃም ወልዴ ለቀረበበት ውንጀላ ምላሽ መስጠት ከፈለገ ዝግጅት ክፍላችን በደስታ እንደሚያስተናግደው ከወዲሁ ለመግለጽ ይወዳል።”
ስለሆነም ቃለምልልሱ ከታተመበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ከአቶ አብርሃም ወልዴ ምንም ዓይነት ምላሽ አላገኘንም:: ሙልሉበሙሉ እርግጠኛ ባንሆንም ይህ ቃለምልልስ በስፋት የተሰራጨ በመሆኑ ደርሶዋቸዋል ብለን እናምናለን:: ከዚህ ውጪ እርስዎ አንዳንድ ተቀጽላ (adjectives) ቃላትን በመጠቀም ስለጋዜጣችን የተናገሩት አግባብነት የሌለው ፍረጃ ነው:: ሃሳብን መደገፍም ሆነ መቃወም ይቻላል:: ነገርግን አንዱን ለመደገፍ የግድ ሌላውን አለአግባብ መንቀፍና መፈረጅ አግባብነት የለውም:: ጋዜጣችን የሕዝብ ልሳን እንደመሆኑ በአግባቡ የሚቀርቡ ጽሁፎችን እንደምናስተናግድ “ስለ እኛ” በሚለው ዓምድ ሥር በግልጽ ያሰፈርነው እውነታ ነው::
ከሰላምታ ጋር
አርታኢ/Editor
ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ/Golgul: the Internet Newspaper
http://www.goolgule.com
editor@goolgule.com
ማስተዋል ; አብርሀአአም ወልዴ በተለያዩ የብዙሀን መገናኛዎች መልስ እዲሰጥ ተጠይቆ ፈቃደአኛ እንዳልሆነ የዘገቡትን እንላነበብህም የሬዲዎ ጣቢያዎችም ተመሳሳይ ጥሪ እንእዳደረጉለት አላዳመጥህም ።ሌላው ቀርቶ አዲስ አበባ የሚታተሙ መጽሄቶች ለምሳሌ ቃል ኪዳን መጽሄት ጃኖ መጽሄት እንዲሁም ሌሎች መጽሄቶች መልስ እንዲሰጥ ሲደውሉለት መልእስ ለመስጠት ፈቃደኛ እንዳልሆነ ፅፈዋል ፥ መረጃ ላልዀአው እኔም እእደግእፋለሁ ግን መረጃ ማቅረአብ ያለባቸው እሱ ላለ ማጭበርሩ መልስ ከሰጠ በኋላ ነው። አሁን ጎልጉል ላይም መልስ አንዲሰጥ ተአጋኣብዟል ጥሪውን ተቀብሎ መልስ ቢሰጥ ጥሩ ነው።መልስ ካኣልሰጠ ጥፉቱ የአብርሃም መሆኑ አያጠራጥርም።