የሃገራችን ፖለቲካ በፍጥነት በሚለዋወጡና አቅጣጫቸውን ለመተመን በሚከብዱ ሁኔታዎች ውስጥ ይዋኛል። ለእነዚህ በፍጥነት ለሚለዋወጡ ፖለቲካዊ ክስተቶች ገፊው ነገር (driving force የምንለው) ምንድን ነው? ካለን በተለይም ላለፉት ሶስት ዓመታት በተከታታይ በመካሄድ ላይ ያለው ህዝባዊ ኣመጽ ነው። ይህ ኣመጽ በከፍተኛ ሁኔታ በፖለቲካው ላይ ተጽእኖ እየፈጠረ ነው። በብዙ ሃገራት ህዝቦች በአምባገነን ስርዓት ላይ ሲያምጹ 5 ዋና ዋና ክስተቶች ይፈጠራሉ። ህዝብ እምቢኝ ሲል አገዛዙ መረረኝ ብሎ ሲያምጽ አመጹ ተጽእኖ ፈጥሮበት የሚከሰቱት እነዚህ 5 ጉዳዮች፦ በገዢው ፓርቲ ውስጥ መሰንጠቅ፣ መፈረካከስና አለመረጋጋትን ያመጣል። ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ያጠነክራል፣ ያበረታታል፣ ያደራጃል፣ ወኔ ይሰጣል። አዳዲስ መሪዎችን ከአመጹ መሃል ያወጣል:: የለሂቁን ልዩነት ያጠባል። … [Read more...] about በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የግል አስተያየት
Opinions
የኔ ሃሳብ
ብሔራዊ የመረጋጋትና የሰላም ጥሪ፤ ከሕጋዊው ሲኖዶስ
የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ … [Read more...] about ብሔራዊ የመረጋጋትና የሰላም ጥሪ፤ ከሕጋዊው ሲኖዶስ
ኃይለማርያም ደሳለኝ ለምን ለቀቁ?
ኢ.ቢ.ሲ. በሰበር ያስተናግደውን የኃይለማርያም ደሳለኝ መግለጫ፤ ዞምቢዎቹ ተሯሩጠው ለማጽደቅ ግዜ አልወሰደባቸውም። እሳቸውም ልክ ስልጣን እንደነበረው ጠቅላይ ሚኒስትር "ስልጣን አስረክቢያለሁ" ሲሉ እፍረት የሚባል ነገር ፊታቸው ላይ አይታይባቸውም ነበር። ሹመት እንጂ ሕገ-መንግስቱ የሚፈቅደው ስልጣን እጃቸው ላይ እንዳልነበር ሕጻናትም ያውቁታል። የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መልቀቅያቸውን በብርሃን ፍጥነት ሲያጸድቀው፤ ድርጊትዋን ከደቡብ አፍሪካው ጃኮብ ዙማ ክስተት ጋር ለማመሳሰል የተተወነች ድራማም አስመስሏታል። ስልጣን ሳይኖር “ሰላማዊ ሽግግር” የሚሏት ፌዝ … ኃይለማርያም ደሳለኝ ተሸክመውት የነበረው ሹመት ይሁን ስልጣን ሲለቅቁ፤ "ከደሙ ነጻ ነኝ" ብለው ለተሰራው ወንጀል ሁሉ እንደ ጲላጦስ እጃቸውን ሊታጠቡ እንደማይችሉ ግን እርግጥ ነው። ከዚህ ባለፈ ግን የእሳቸው መውረድ … [Read more...] about ኃይለማርያም ደሳለኝ ለምን ለቀቁ?
ዘብረቅራቃው የባህር ዳር “ቅጠል ሰፈር” ጉድ!
ልብ-ወለድ ታሪኮችን አብዝቶ መጻፍ፣ ዕውነታዉን በግማሹም ቢሆን አስቶ፣ በራስህ የህልም ዓለም ዉስጥ እንድትዋኝ ያደርግሃል፡፡ የCreative writing ኪኑ ከአምላክ ቢሰጥህም፣ ጭቆናንና መገፋትን-ድህነትንና መቆራመድን በጠራ-ገለጥለጥ ባለ አማርኛ ከመግለጽ ግን አትታጎልም፡፡ የኔ ሁለት የሃሳብ ጽንፎች እንደዚህ ሲጓተቱ ቆይተው፣ በስተመጨረሻ "ዕውነታን በኪነት" አሉና ተስማሙ፡፡ ሰፈሬ ከከተማዋ (ከባህር ዳር) አንዷ ክፍል ሆና በመጠራት ትታወቃለች፡፡ በአሁኑ የቀበሌ አወቃቀር፣ "ክፍለ-ከተማ" ተባለች፤ "ሽምብጥ ክፍለ-ከተማ"! አብዛኛው ነዋሪዎቿ በዝቅተኛ የአኗኗር መደብ ዉስጥ ይካተታሉ፡፡ ጠላና አረቄ በመሸጥ የሚተዳደሩ ባልቴቶች በእልፍዓእላፋት መዝገብ ውስጥ ሊመዘገቡ አንድ ሃሙስ የቀራቸው ናቸው፡፡ የህወሃት "እያደኸዩ መግዛት" ፖሊሲ በትክክል ውጤት ያመጣው (በባህርዳር ደረጃ) … [Read more...] about ዘብረቅራቃው የባህር ዳር “ቅጠል ሰፈር” ጉድ!
ህወሓትና ኢትዮጵያን የማፈራረስ ዓላማው!
የአዘጋጆቹ ማስታወሻ፤ ባለፉት ዓመታት ከህወሓት እየኮበለሉ የወጡ የቀድሞ አባላት በርካታ ናቸው። እንዳንዳቸው የሚወጡበት ምክንያት ቢኖራቸውም ህወሃትን በማጋለጥና ማንነቱን ለኢትዮጵያ ሕዝብ በማሳወቅ የአቶ ገብረመድኅን አርአያን ያህል ታላቅ ሥራ የሠራና መስዋዕትነት የከፈለ አለ ለማለት ያስቸግራል። አብዛኛዎቹ የቀድሞው አባላቱ የህወሓትን ምሥጢራዊ አሠራር እና እጅግ አረመኔያዊ ግፍ፤ ኤፈርት በኢትዮጵያ ሐብት ላይ የፈጸመውንና እስካሁንም እየፈጸመ ያለውን የኢኮኖሚ ግፍ፣ ዝርፊያ፣ ሌብነት፣ … የመሳሰሉ ጉዳዮች በአደባባይ ከመናገር ሲቆጠቡ ተስተውለዋል። አንዳንዶቹም በህወሓት ከፍተኛ አመራር ላይ የነበሩ የቀድሞ አባላት ቢሆኑም፤ ኤፈርትም ሲያስተዳድሩ የቆዩ ቢሆኑም ስለጉዳዩ ሲጠየቁ የሚሰጡት ምላሽ አባይ ጸሐዬ ወይም ስብሃት ነጋ ከሚሰጡት ምላሽ ያልተለየ ሆኖ ተገኝቷል። አቶ ገብረመድኅን … [Read more...] about ህወሓትና ኢትዮጵያን የማፈራረስ ዓላማው!
መሆን ካልነበረበት ድርጊት ጋር ስንላመድ
(ለውይይት መነሻ) በዚህ ጽሁፌ ላንባቢዎቼ ለማቅረብ የፈለግሁት ሁለት ተያያዥ ጉዳዮችን ነው። የመጀመርያው፣ ወያኔ ላለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት ሲፈጽማቸው የነበረውን “ነውሮች” እንዴት እንደ “ጽድቅ” እንደተጠቀማባቸውና የኢትዮጵያንም ህዝብ “ጽድቅ” ነው ብላችሁ ተቀበሉ ብሎ እንዳስገደንና እኛም በመላመድ ብዛት ተዋህዶን እንደተቀበልነው፣ ሁለተኛው ደግሞ ይህንን “ነውር” እንደ “ጽድቅ” በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ጭኖ ሲበድል የነበረው ወያኔ (ህወሃት)፣ በምንም መልኩ የትግራይን ህዝብ እንደማይወክል ለማስረዳት ነው። ግምቱ የግሌ እንጂ የሌላ የማንንም አካል አስተሳሰብ ስላይደለ፣ በዚህ ጽሁፍ ውስጥ ለተካተቱት ግምቶች፣ መረጃዎችም ሆነ መደምደሚያዎች ተጠያቂው እኔ ብቻ ነኝ። ይህ እንግዲህ “ለውይይት መነሻ” የቀረበ ስለሆነ በይዘቱ ላይ ያላችሁን ሃሳብ እንደኔው በጽሁፍ ብታወጡ፣ ባገራችንን ላይ … [Read more...] about መሆን ካልነበረበት ድርጊት ጋር ስንላመድ
“እናንተ ሰው ናችሁ?” ትራምፕ ለአፍሪካ መሪዎች
ከዚህ በታች የተጻፈውን ፕሬዚደንት ትራምፕ አለ ተብሎ ፌስቡክ ላይ ያገኘሁት ነው፤ “ነፃነታችሁን ካገኛችሁ ከ50 ዓመታችሁ በኋላ ለሕዝቦቻችሁ አስፈላጊውን የመገናኛ ዘዴ ካልሠራችሁላቸው እናንተ ሰው ናችሁ? እናንተ በወርቅ ላይ፣ በዕንቁ ላይ፣ በዘይት ላይ፣ በማንጋኒዝ ላይ፣ በዩራኒየም ላይ ተቀምጣችሁ ሕዝቦቻችሁ የሚበሉት ሳይኖራቸው ሲቀር እናንተ ሰው ናችሁ? እናንተ በሥልጣን ላይ ሆናችሁ የጦር መሣሪያ ከባዕዳን ለመግዛትና ዜጎቻችሁን ለመግደል የማታመነቱ ከሆነ እናንተ ሰው ናችሁ? የናንተ ማኅበረሰባዊ ዓላማ ሕይወታችሁን በሙሉ በሥልጣን መንበር ላይ መቆየት ከሆነ እናንተ ሰው ናችሁ? እንደሚታደን አውሬ ዜጎቻችሁን የምትገድሏቸው ከሆነ ማን ያከብራቸዋል? ” (ባለቤት ያቀለለውን አሞሌ ባለዕዳ አይቀበለውም!) እነዚህ ሁሉ እውነቶች የሚያጠራጥሩ አይመስለኝም። … [Read more...] about “እናንተ ሰው ናችሁ?” ትራምፕ ለአፍሪካ መሪዎች
Ailing Civic Space in an Authoritarian State: The State of Human Rights Defenders and Cost of Dissent in Ethiopia
Journalists, activists, and other civil society actors play a pivotal role in building a transparent system of governance in any society. The UN Declaration on Human Rights Defenders* affirms that everyone, individually and in association with others, has the right to submit to governmental public bodies, criticism and proposals for improving their functioning, and to draw attention to any aspect of their work that may hinder or impede the promotion, protection, and realisation of human rights … [Read more...] about Ailing Civic Space in an Authoritarian State: The State of Human Rights Defenders and Cost of Dissent in Ethiopia
የወሎ ዐማራ የሰሞኑ ጉዳይ ማጠቃለያ ሪፖርት (የእስካሁኑ ሒደት)
የትግሬ ወያኔ አፈ ቀላጤዎች ዘርን መሠረት ያደረገ ጥቃት በወልዲያና በመርሣ ቆቦ አካባቢ እንደደረሰ ኡኡታቸውን ሲያሰሙ ሰንብተዋል። ዕውነታው ግን ሌላ ነው። የወሎ ዐማራ ጠላቱን በደንብ ለይቶ ነው ጥቃት ያደረሰው። ለዚህም ማሳያ የሚሆነው ከትግሬዎች ንብረት በላይ የዐማራ ተወላጅ (ባንዶች) ንብረት ላይ ነው ጉዳት የደረሰው። ሁሉንም በዝርዝር ከዚህ በታች አቅርበነዋል። በባንዳ ዐማሮች ላይ የተወሰደው እርምጃ አስተማሪ ይመስለኛል። ሰውን ያክል ነገር ገድሎ እስከማቃጠል ያደረሰው በደል ምን ቢሆን ነው ብሎ የማይጠይቅ አእምሮ መቼም ቢሆን ሊማር ስለማይችል ቀጣይ ተረኛ መሆኑ አይቀርለትም። ጠቅለል አድርገን ሪፖርቱን ስናየው በመርሳ ወረዳ ለሕዝብ ተብለው የተቋቋሙ ግን ምንም ያልፈየዱ የወያኔ መሥሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል። ለመዘርዘር ያክል፤ 1. የሀብሩ/መርሳ ከተማ ፍ/ቤት 2. … [Read more...] about የወሎ ዐማራ የሰሞኑ ጉዳይ ማጠቃለያ ሪፖርት (የእስካሁኑ ሒደት)
“የሃይማኖት አባቶች” የሰላም ጥሪ
“ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት ስንት ወልድያ ያስፈልገናል?” ዳንኤል ክብረት በትናንት ምሽቱ የ“ሰላም ዋጋ” ዲስኩር አፈሙዝ ሳይሆን “ዘመናዊ መገናኛ ብዙሃን” ተወግዟል። የሃገሪቱ እድገት እና ትራንስፎርሜሽንም ተወድሷል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ዻዻስ፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቴያስ ፓትሪያሪክ፣ ርዕሳነ ሊቃነ ጳጳሳት ዘአክሱም ወጨጌ፣ ዘመንበረ ተክለሐይማኖት…. ወዘተ “… (ሃገሪቱ) ለሁሉም ልጆችዋ የምታበላው ከሌላት ከየት ታምጣ?” ብለውናል። “ሕዝቡ ቢያገኝም አይረካም” የሚሉን አቡነ ማቴያስ እዚያች ቦታ ላይ እንዴት እንደተቀመጡ የታወቀ ነውና ከእርሳቸው ከዚህ የተለየ ነገር ፈጽሞ አንጠብቅም። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሃጂ ከድር ሁሴንም እንደ ገለልተኛ ሰው ተሰይመዋል። የአብያተክርስቲያናት ህብረት … [Read more...] about “የሃይማኖት አባቶች” የሰላም ጥሪ










