በመጀመሪያ ደረጃ “የትግራይ ህዝብ” ስል ከኢትዮጵያ ህዝብ በተዘረፈ ሃብት የቅንጦት ህይወት የሚኖሩትን፣ በስርቆት ሃብት አጉል የሚቀብጡትን የካድሬ ልጆችና ወዳጆች አይመለከትም። “የትግራይ ህዝብ” ስል በህወሓት ድጋፍና ድጎማ የሚኖሩ የድርጅቱን አባላትና ፅንፈኛ ደጋፊዎች አይመለከትም። የእነዚህ ሰዎች ስኬት እና ውድቀት፣ ድህነት እና ሃብት፣… በአጠቃላይ ሁሉ ነገራቸው ከህወሓት ጋር የተቆራኘ ስለሆነ የድርጅቱ አመራሮች የደገፉትን ይደግፋሉ፣ የተቃወሙትን ይቃወማሉ። የእነሱ ዕለት-ከእለት ኑሮ ከህወሓት መኖርና አለመኖር ጋር የተቆራኘ ስለሆነ ህወሓት የህልውናቸው መሰረት ነው። በእርግጥ እነዚህ ሰዎች የትግራይ ተወላጆች ናቸው። ነገር ግን እነዚህ ሰዎች “የህወሓት አፈ-ቀላጤዎች” እንጂ “የትግራይ ህዝብ” ሊሆኑ አይችሉም፤ እነሱ የህወሓት ካድሬዎች እንጂ የትግራይ ህዝብ አይደሉም! ከዚያ … [Read more...] about የትግራይ ህዝብ ሆይ፦ “ሀገርና ህዝብ ከህወሓት በፊት ነበሩ፣ ከውድቀቱም በኋላ ይኖራሉ!”
Opinions
የኔ ሃሳብ
በኮሞሮስ ባንዲራ የሚቀዝፉት የሜቴክ መርከቦች እና በካሪቢያን ስም የምትቀዝፈው የኢትዮጵያ መርከብ
የፌደራል ዋና አቃቢ ህግ ሜቴክ ከተቋቋመበት ዓላማ ውጪ በገዛቸው ሁለት መርከቦች አማካኝነት በህግወጥ የንግድ እንቅስቃሴ መሰማራቱን ገልፆ እንደነበር ይታወሳል። ሆኖም ግን በሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ሜ/ጄ ክንፈ ዳኘው ላይ የቀረበው ክስ ድርጅቱ ከተቋቋመበት ዓላማ ውጪ አባይ እና ህዳሴ የተባሉትን ሁለት መርከቦች በመግዛት ከፍተኛ የገንዘብ ብክነት የሀገርና ህዝብን ሃብት ያለ አግባብ አባክኗል የሚል ነው። ሆኖም ግን ለድረገፃች አዘጋጅ በደረሰው መረጃ መሠረት ሜቴክ የገዛቸው ሁለት መርከቦች እ.አ.አ. እስከ 02 – 07/-01-2016 በምስራቅ አፍሪካዊቷ የኮሞሮስ (Comoros) ደሴት ሰንደቅ ዓላማ አያውለበልቡ በህገወጥ ንግድ ተሰማርተው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ በቀረበው የቴሌቪዥን ዶክመንተሪ ሜቴክ እ.አ.አ. በ2014 ዓ.ም አባይ እና ህዳሴ የተባሉን መርከቦች … [Read more...] about በኮሞሮስ ባንዲራ የሚቀዝፉት የሜቴክ መርከቦች እና በካሪቢያን ስም የምትቀዝፈው የኢትዮጵያ መርከብ
THE WAY FORWARD: CAN THE RIGHT CHANGE BE SUSTAINED IN ETHIOPIA?
Mr. Obang Metho, Executive Director, Solidarity Movement for a New Ethiopia (SMNE) will be a Guest Lecturer at The University of Gondar Lecture Title and Description: THE WAY FORWARD: CAN THE RIGHT CHANGE BE SUSTAINED IN ETHIOPIA? Ethiopia is in a state of great change. Many regard it as a miracle, a door that few believed could be opened, a glimmer of light that has resurrected hope for change that seemed impossible less than a year ago. This momentum for change has led to new freedoms and … [Read more...] about THE WAY FORWARD: CAN THE RIGHT CHANGE BE SUSTAINED IN ETHIOPIA?
በድሬዳዋ ከተማ የሰው ህይወት አለፈ
ቅዳሜ ምሽት በድሬዳዋ ከተማ በተለምዶ ገንደ ቦዬ ተብሎ በሚጠራው መንደር በተቀሰቀሰው ግጭት የአንድ ወጣት ህይወት ማለፉ ተሰምቷል። ምሽቱ በጥይት እሩምታና በአስለቃሽ ጭስ ተኩስ ነዋሪዎችን ጭንቀት ውስጥ ከቶ ያለፈ ነበር። በምሽቱ ግጭት ህይወቱን ያጣው ወጣት አብዱረዛቅ ሪቫቶ ከፀጥታ ኃይሎች በተተኮሰበት ጥይት ለአካል መቁሰል ተዳርጎ ወደ ድል ጮራ ሆስፒታል ቢወሰድም ህይወቱን ለማትረፍ አልተቻለም። ፍፁም መከሰት የሌለበትና በቀላሉ ሊፈታ የሚገባው ችግር ማመዛዘን በጎደለውና በቸኮለ እርምጃ የሰው ህይወት በድሬዳዋ ተቀጥፏል ብሏል ዜናውን ያሰራጨው ድሬ ትዩብ። ጨምሮም የህግ አስከባሪዎች ለሚወስዱት ማንኛውም እርምጃ ሞያዊ ክህሎት የተላበሰና ማስተዋል የተጨመረበት መሆን አለበት፤ ኮሽ ባለ ቁጥር አፈ ሙዝ የሚደቅን የፀጥታ ሀይል አላግባብ በሆነ መልኩ ህይወትን ያሳጣል ብሏል። በድሬዳዋ … [Read more...] about በድሬዳዋ ከተማ የሰው ህይወት አለፈ
“እርካብና መንበር” – ሙሴ እና ዐብይ*
ሳይታሰብ ብልጭ ብላ እንደገና ድርግም ያለችው የለውጥ ጭላንጭል፣ በእያንዳንዱ ልብ ውስጥ ተቋጥራ የነበረች የተስፋ ስንቅንም ይዛ ጭልጥ ያለች ይመስላል። አዕምሯችን ይህንን ቅጽበታዊ ለውጥ ለመቀበል ቢቸግረውም፣ በሌላኛው መነጽር ስንመለከተው ግን ይህ ሊሆን ግድ ይላል። በተዓምር የቆመች የዚህች የደም ምድር እጣ ፈንታን መጽሃፉ በአንዲት ምዕራፍ ውስጥ እንደቋጫት እንገነዘባለን። አይናችንን በደንብ ካልገለጥን ግን ነገሩን ላናየው እንችላለን። ስለዚህ መፅሐፉን ማንበብ ብቻ በቂ አይደለም። መረዳትንም ይጠይቃል። በደንብ የተረዳው ሰው፣ በለሆሳስ የተላለፈ መልዕክቱን ያገኘዋል። መልዕክቱም ግልጽ ነው። የነጻነት ተጋድሎ። በዚህ ፍልሚያ ውስጥ ሶስት ተዋንያን ይኖራሉ። ተሻጋሪ ሕዝብ፣ አሻጋሪ ሰው እና አሳዳጅ ሃይል። ከብዙ ትንቅንቅ እና ተጋድሎ በኋላ የአሳዳጁ ገቢር ከትዕይንቱ ይወጣና ሁለቱ … [Read more...] about “እርካብና መንበር” – ሙሴ እና ዐብይ*
የኢህአዴግ የመጨረሻ ጉባኤ…
ኢህአዴግ መሽቶበታል። አቅሙ ክዶታል። ባልሞት ባይ ተጋዳይነት አለሁ ቢልም ዘላለማዊ ዕንቅልፉ ግን የሚቀርለት አይመስልም። የሜክሲኮውን ፒ አር አይ ፓርቲ አርአያው አድርጎ ሰባ አመታትን እጓዛለሁ ብሎ የተነሳው ድርጅት ግማሽ መንገድ እንኳን ሳይጓዝ ሊፈርስ ከጫፍ ደርሷል። ገዥው ፓርቲ ውስጥ ያለው የርዕዮተዓለም ልዩነት በማይታረቅ መንገድ የአደባባይ ሙግት ጀምሯል። ኦዲፒ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ መማል ካቆመ ቆይቷል። ሊቀመንበሩ ዓብይ አህምድም (ዶ/ር) ከትናንት ጋር የተኳረፉት ለዚህ ይመስላል። ብአዴን የምመራበትን ርዕዮተ ዓለም ዳግም አጤነዋለሁ ብሎ ዛሬ መወያየቱን ጀምሯል (ይህ ዘገባ ከተጻፈ በኋላ ብአዴን አዴፓ በሚል ህወሓት የሰጠውን ቀይሮታል)። ከዚህ በአንጻሩ ህወሓት አብዮታዊ ዲሞክራሲን ብረሳ ቀኜ ትርሳኝ ብሎ ሙጥኝ ማለትን ወዷል። ደኢህዴን ሁለት ጎራ ይዞ የለየለት ፍልሚውን … [Read more...] about የኢህአዴግ የመጨረሻ ጉባኤ…
መንገዳችን በፍጥነት ይቃና!
በብዙ ዓይነት ወንጀሎች የሚታሙት የወያኔ አዛዦች ሥልጣናቸውን እንደያዙ ከሥልጣን ወረዱ ቢባል ግራ ይሆናል፤ ነገር ግን ሆነ! በሕጋዊ ምርመራ ሳይጣራና ከሳሾቹን በፍርድ ቤት ሳይሞግት የሰው ልጅ እንደከብት ከመንገድ በጉልበተኞች እየተያዘ መታሰር የቀረ መስሎን ነበር፤ አልቀረም አሉ! ጉልበተኞች በወንጀላቸው ክብደት ከሕግ ይከለላሉ ይባል ነበር፤ አሁንም ያው ይመስላል! ያነበብሁትን በትክክል ካስታወስሁት በጥንታውያን ግሪኮች ሰርቀው መያዝ እንጂ መስረቅ ወንጀል አልነበረም (የምታስታውሱ አርሙት)፤ የምንመሳሰለው በጥንታዊነት ብቻ መስሎኝ ነበር! ከዚህ ቀደም ጸጋዬ ገብረ መድኅን (ይመስለኛል) ተረግመናል ብሎ፤ ነበር፤ እኔንም መሰለኝ! ኢትዮጵያውያን መልካቸውን፣ ነብሮች ቆዳቸውን እንዴት ይለውጣሉ ያለው መልካችንን ነበር፣ ወይስ ጠባያችንን ማለቱ ነበር! ነገሬ ሁሉ የጥንቶቹን አባትና እናት … [Read more...] about መንገዳችን በፍጥነት ይቃና!
ኢትዮጵያዊነትና የብሔር ማንነት ተደጋጋፊ ወይስ ተገዳዳሪ?
“ኢትዮጵያ አገራችን የየራሳችን አኩሪ ባህል ያለን፣ የየራሳችን መልክዓ ምድር፣ አሰፋፈር የነበረንና ያለን፣ ብሔር ብሐረሰቦችና ሕዝቦች በተለያዩ መስኮችና የግንኙነት ደረጃዎች ተሳስረን አብረን የኖርንባትና የምንኖርባት አገር በመሆንዋ ያፈራነው የጋራ ጥቅምና አመለካከት አለን ብለን ስለምናምን፣ መጪው የጋራ ዕድላችን መመሥረት ያለበት ከታሪካችን የወረስነውን የተዛባ ግንኙነት በማረምና የጋራ ጥቅማችንን በማሳደግ ላይ መሆኑን በመቀበል ጥቅማችንን፣ መብታችንንና ነፃነታችንን በጋራና በተደጋጋፊነት ለማሳደግና አንድ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ የመገንባቱን አስፈላጊነት በማመን እኛ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ይኼንን ሕገ መንግሥት በተወካዮቻቸው አማካይነት አፅድቀነዋል።” ከላይ የተገለጸው በ1987 ዓ.ም. ከፀደቀው የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት መግቢያ ላይ የተወሰደና አገሪቱ ካለፉት 23 … [Read more...] about ኢትዮጵያዊነትና የብሔር ማንነት ተደጋጋፊ ወይስ ተገዳዳሪ?
በባንዲራና አርማ ዙርያ ያሉ ውዝግቦች
ባንዲራ የአንድ አገር ሕዝብ ማንነት መገለጫ ነው። የሰው ልጆች በታሪካቸው ውስጥ የየራሳቸውን ቡድን ወይም ወገን ከሌሎች ለመለየት ጨርቅን በተለያዩ ቀለሞች በመቀባት፣ እንጨት ላይ ሰክተው በእጃቸው ይዘው በመዞር፣ አንገታቸው ላይ በማሰር ወይም ጎልቶ እንዲታይ ከማሰብ አንጻር ረዘም ባሉ እንጨቶች ላይ እየሰቀሉ ከማንነት መገለጫም ባሻገር ይዞታን ወይም ባለቤትነትን ለማረጋገጥ ይጠቀሙበት እንደነበር የሕብረተሰብ ታሪኮች መዝግበዋል። ባገራችን ባንዲራ እንደ ኢትዮጵያ መገለጫ ሆኖ መቼ እንደቀረበ በትክክል ባይታወቅም፣ ባንዲራን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ለመጀመርያ ጊዜ ያስተዋወቁት አጼ ምኒልክ መሆናቸው በሰፊው ይነገራል። ያኔ ትክክለኛ ስሙ “ሰንደቅ ዓላማ” በመባል ቢታወቅም፣ ጣሊያኖች ኢትዮጵያን ከወረሩ በኋላ ግን “ባንዲራ” በሚለው የጣሊያንኛ ቃል ተተክቶ ዛሬ በስፋት እየተጠቀምንበት ነው። … [Read more...] about በባንዲራና አርማ ዙርያ ያሉ ውዝግቦች
የጎሳ ፖለቲካ ጣጣ፣ ‘ሀዘናችን ቅጥ አጣ’
ከአንድ ሃዘን ወደ ሌላ፤ ላለፉት ጥቂት ወራት ክልላትን እያዳረሰ ያለውና ጎሳ ላይ ያነጣጠረው ግጭት ከቡራዩ ሃዘን ሳናገግም በዚህ ሳምንት ደግሞ ዳግም ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ዞረ። በክልሉ ይኖሩ የነበሩ የኦሮሞ፣ አማራ እና የሌሎች ብሔር ተወላጆች ላይ ሌላ አስከፊ ጥቃት መፈጸሙን መርዶ ሰማን። ሰዎች ተገድለዋል፤ በአሥር ሺዎች ተፈናቅለዋል። ለዚህም ጥቃት የተለያዩ ኃይሎች እንደ ምክንያት እየተጠቀሱ ነው። ከእንዲህ ያለው አስነዋሪ እና እጅግ ኋላ ቀር ከሆነ የጎጠኝነት ስሜት እንዴት ይሆን የምንላቀቀው? በጎጥ ጥላቻ ላይ ምህለቁን የጣለው ዘር ተኮር ፖለቲካችንስ መቼ ይሆን የሚጸዳው? ከእንዲህ ያለው ቅርቃር ለመውጣት እንደ ሰው ማሰብ ብቻ ይበቃን ነበር። ከዚያም ሲያልፍ የአንድ አገር ልጆች በመሆናችን ብቻ ልንተዛዘን፣ ልንደጋገፍ እና አብረን ልንኖር በቻልን ነበር። ይህ ሁሉ ቢቀር በየጎሳ … [Read more...] about የጎሳ ፖለቲካ ጣጣ፣ ‘ሀዘናችን ቅጥ አጣ’










