• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

News
ዜና

ህወሓት ደብረጽዮንን ቀጣይ ጠ/ሚ/ር ያደርጋል!

December 3, 2012 02:48 am by Editor 7 Comments

ህወሓት ደብረጽዮንን ቀጣይ ጠ/ሚ/ር ያደርጋል!

ከአቶ መለስ መለየት በኋላ ወደ አደባባይ የወጡት ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሆኑ እንደሚችሉ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ግምታቸውን ሰጡ። አገር ቤት ተቀምጠው በኢህአዴግ ላይ የሰላ ትችት በማሰማት ቀዳሚውን ስፍራ የያዙት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፍልስፍና መምህርና እንደ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም የአደባባይ ምሁር በመባል የሚታወቁት ዶ/ር ዳኛቸው ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ይፋ እንዳደረጉት ለግምታቸው ምክንያት ሰጥተዋል። አቶ መለስ በህይወት እያሉ የስልጣን ክፍፍሉን በሶስት ለመመደብ መታሰቡን ሰምተው እንደነበር ያስታወሱት ዶ/ር ዳኛቸው፣ ሃሳቡ ከስምምነት ላይ ሊደረስ ባለመቻሉ ተግባራዊ ሊሆን እንዳልቻለ አመልክተዋል። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ማንም ይሁን ማን ከዚህ ቀደም እንደነበረው ስልጣኑ በአንድ ሰው ላይ ተጭኖ ሊቀጥል እንደማይችል … [Read more...] about ህወሓት ደብረጽዮንን ቀጣይ ጠ/ሚ/ር ያደርጋል!

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

ከእሁድ እስከ እሁድ

December 2, 2012 04:37 pm by Editor Leave a Comment

ከእሁድ እስከ እሁድ

በዱባይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነጋዴ ወይስ ለወገን ደራሽ? በዱባይ ኢትዮጵያ ኤምባሲ ፓስፖርታቸው በአሰሪዎቻቸው አማካይነት ለተመለሰላቸው ወገኖች የፓስፖርት እድሳት በሚል አንድ ሺህ አንድ መቶ ድራም እንደሚያስከፍል ተሰማ። ለጎልጉል በስልክ መረጃ የሰጠች አንድ የዱባይ ነዋሪ ኤምባሲው አገልግሎቱን መጀመሩ እንደሚያስመሰግነው ጠቁማ፣ ክፍያው ግን የተጋነነ ንግድ እንደሚመስል አስታውቃለች። ዘጠና ከመቶ የዱባይ ነዋሪዎች ፓስፖርታቸው ጊዜው ያለፈበትና በአሰሪዎቻቸው በመያዣነት የተያዘ እንደሆነ የጠቀሰችው ይህች ወጣት “በችግር ላይ ካሉ ዜጎች ላይ ከስድሰት ሺህ በላይ የኢትዮጵያ ብር መቀበል አግባብ አይደለም። ኤምባሲው ፓስፖርታቸው ለተወሰደባቸውም መላ ይፈልግ” ስትል ጠይቃለች። አሰሪዎቻቸው በሚያደርሱባቸው በደል ተማረው የሚጠፋ ወገኖች ፓስፖርታቸው በመያዣነት አሰሪዎቻቸው ዘንድ ስለሚቀር የጉዞ … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

የጁነዲን መጨረሻ አልታወቀም

December 1, 2012 12:58 am by Editor 1 Comment

የጁነዲን መጨረሻ አልታወቀም

ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም የኢትዮጵያን ታላቅ የሥልጣን መቀመጫ ሲረከቡ “ለተደረገልን ምደባ አመሰግናለሁ” ማለታቸውን ተከትሎ የከፍተኛ ባለሥልጣናት ሹመት “ምደባ” የሚል ስያሜ አግኝቷል። ትላንት ለተወካዮች ምክር ቤት በቀረበ የሽግሽግ ምደባ አቶ ጁነዲን ሳዶ ከምደባ ተዘለው ከሃላፊነታቸው መነሳታቸው ይፋ ሆኗል። የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ጁነዲን ሳዶ ወንበራቸውን ለአቶ ሙክታር ከድር እንዲያስረክቡ ተደርጓል። ኦህዴዱ አቶ ሙክታር የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግ ታክሎላቸው አቶ ጁነዲን ሲመሩት የነበረውን የሲቪል ሰርቪስ ተቋም እንዲመሩ ሲደረግ አቶ ሃይለማርያም ስለአዲሱ ተሿሚ አቶ ሙክታር ቁርጠኛነትና ብቃት ሲያብራሩ ስለ አቶ ጁነዲን ከሃላፊነት መነሳት ግን ያሉት ነገር የለም። ለዚህም ይመስላል የመድረክ አባል ብቸኛው ተቃዋሚ አቶ ግርማ ሰይፉ “ህዝብ … [Read more...] about የጁነዲን መጨረሻ አልታወቀም

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

ህወሃት አረጋግቶ አገገመ

December 1, 2012 12:55 am by Editor Leave a Comment

ህወሃት አረጋግቶ አገገመ

ኢህአዴግ “አረጋግቶ አገገመ” ከተባለው አዲሱ “ምደባ” መካከል የንግድ ሚኒስትር  ተብለው በተሰየሙት ላይ ብቸኛው የፓርላማ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉ ጠንካራ መከራከሪያ በማቅረብ ተቃወሙ። አቶ ግርማ የሚሾሙ ብቻ ሳይሆን የሚነሱ ባለስልጣናት ከሃላፊነታቸው የተነሱበት ምክንያትም ለህዝብ መቅረብ እንዳለበት አሳሰቡ። አቶ ሃይለማርያም ተቃውሞውን “መክረንና ገምግመን ያደረግነው ነው” ሲሉ ተከላከሉ። አቶ ግርማ ብሩ (አሁን አምባሳደር) ሲመሩት የነበረውን ሚኒስቴር መ/ቤት “ስያሜና ምልክት መለየት የማይችል” በማለት አንቋሸሹት። ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ አገሪቱን በመሩበት ሶስት ወራት ካቢኒያቸውን በደንብ መገምገማቸውን በግምት በመግለጽ ተቃውሞ ያቀረቡት አቶ ግርማ ሰይፉ በምደባው በተወሰነ ደረጃ እንደሚስማሙ ተናግረዋል። የንግድ ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔን ምደባ የተቃወሙት በማስረጃ … [Read more...] about ህወሃት አረጋግቶ አገገመ

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

የጎልጉል ቅምሻ

November 27, 2012 08:09 am by Editor 1 Comment

የጎልጉል ቅምሻ

ለቢንላደን ቀብር ምስካሪ የባህር ኃይል የለም በሚያዚያ ወር 2003ዓም ድንገተኛ ወረራ ተካሂዶበት ቀብሩም ወዲው ተጠናቅቆዋል የተባለው ኦሳማ ቢንላደን ባህር ውስጥ ሲቀበር የተመለከተ አንድም የአሜሪካ የባህር ኃይል አባል እንደሌለ ተገለጸ፡፡ አሶሺየትድ ፕሬስ “የመረጃ ነጻነት ሕግን” ጠቅሶ በጠየቀውና ባገኘው መረጃ መሠረት “ባልታወቀ ባህር” ተቀበረ የተባለው ቢንላደን ሲቀበር ምስካሪ እንደሌለ የዘገበ ሲሆን ከፓኪስታን ወደ ካርል ቪንስ የአሜሪካ የጦር መርከብ በተጫነበት ወቅት የተነሳ ፎቶግራፍም ሆነ ቪዲዮ የመከላከያ ሚኒስቴር (ፔንታጎን) ማግኘት እንዳልቻለ ጨምሮ አስታውቋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የድህረሞት ምርመራ፣ የሞት ሠርቲፊኬት፣ የዲኤንኤ ምርመራ፣ … እንዳልተካሄደና ይህንኑ የሚያሳይ መረጃ የመከላከያ ሚ/ር ማቅረብ እንዳልተቻለ ተገልጾዋል፡፡ የቢንላደን ሬሣ ከታጠበና በነጭ ጨርቅ … [Read more...] about የጎልጉል ቅምሻ

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

ከእሁድ እስከ እሁድ

November 26, 2012 10:18 am by Editor 1 Comment

ከእሁድ እስከ እሁድ

የእስክንድር ነጋ ጉዳይ ለመንግሥታቱ ድርጅት ቀረበ የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጉዳይ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያላግባብ የታሠሩ ሰዎችን ጉዳይ ለሚያጠናው ግብረኃይል መቅረቡን ለህሊና እስረኞች የሚሟገተው ፍሪደም ናው “Freedom Now” ስራ አስፈጻሚ ዋና ዳይሬክተር ማርዳ ተርነር ለአሜሪካ ሬዲዮ አስታውቀዋል። ዳይሬክተሯ እንዳሉት ድርጅታቸው የእስክንድር ነጋን ጉዳይ በጥልቀት ከመረመረ በኋላ የጋዜጠኛነት ስራውን ብቻ ሲያከናውን እንደነበር ሙሉ አረጋግጠዋል። የታሰረውም ያለ አግባብ እንደሆነ ታምኖበታል። በእስር ቤት ከአያያዝ ጀምሮ በርካታ ጥሰቶች እንደተፈጸሙበት አመልክተዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ለዓለም አቀፍ ህግጋት የገባውን ኪዳንና ግዴታ በመጣሱ የእስክንድር ጉዳይ  በተባበሩት መንግስታት ያለ አግባብ የታሰሩ ሰዎችን ጉዳይ ለሚመረምረው አካል ባለፈው ሚያዚያ ቀርቧል። … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

“የኢሳያስ ልጅ አይከዳም! አናምንም”

November 24, 2012 04:48 am by Editor 1 Comment

“የኢሳያስ ልጅ አይከዳም! አናምንም”

ከኤርትራ ሰሞኑን የሚወጡ መረጃዎች ከጉዳዩ ባለቤቶች ማረጋገጫ ወይም ማስተባበያ ባይቀርብበትም ከኤርትራ ጋር በተያያዘ የተለያዩ አቋምና ተስፋ ባላቸው ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት የሳበ ጉዳይ ሆኗል። አንዳንድ በብሎግ ሂሳብ የሚጫወቱ የኤርትራ መንግሥት አገልጋዮች ለጉዳዩ ጆሮ ዳባ ቢሉም በዋና በተቃዋሚነት የሚታወቁት የኢሳያስ ባላንጣዎች ለወሬዎቹ ሽፋን በመስጠት ግንባር ቀደም ሆነዋል። የ1997 ምርጫን ተከትሎ በተፈጠረው አለመረጋጋት “ህወሃት ሰራዊቴን በመያዝ ጓዜን ጠቅልዬ ወደ ትግራይ ምድር እገባለሁ” ማለቱን አስነብቦ የነበረው ኢንዲያን ኦሽን ኒውስ ሌተር ሰሞኑን የህወሃት ሊቀመንበርን ጠቅሶ ኤርትራ ላይ ጦርነት የማወጅ ፍላጎት እንዳለ ይፋ አድርጓል። ኢንዲያን ኦሽን ከውስጥ አዋቂዎች አገኘሁ በማለት ሌላ ያሰነበበው ዜና የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ አሊ አብዶ ካናዳ ጥገኝነት … [Read more...] about “የኢሳያስ ልጅ አይከዳም! አናምንም”

Filed Under: News Tagged With: ali abdu, Eritrea, Full Width Top, isayas afereki, Middle Column

ኢህአዴግ ኢህአዴግን ማፈን ጀመረ!

November 22, 2012 12:01 pm by Editor 1 Comment

ኢህአዴግ ኢህአዴግን ማፈን ጀመረ!

የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ስም ሲነሳ አቶ በረከት ስምዖን በግንባር ቀደም ይጠቀሳሉ። የአቶ በረከት ንብረት ሆኖ የመለስን አመራር በታማኝነት ሲያገለግል የኖረው ይህ ተቋም ቆርጦ በመቀጠል፣ የዜጎችን ሃሳብ በማዛባት፣ ወሬን ባለማመጣጠንና የሃሰት ፕሮፓጋንዳ በማስተላለፍ የሚታወቅ ነው። ስለሚጠየፉት የማይመለከቱት እንዳሉ አፍ አውጥተው የሚናገሩም አሉ። ለሙያው ቅርብ የሆኑ አስተያየት ሰጪዎች “ወገንተኛ እንኳን ቢኾን መሰረታዊ የሙያው ግዴታ ሳይጣስ ሊሆን ይገባል። አንድ መገናኛ ማመጣጠን ካልቻለ በራሱ ሙት ነው። እያደር ብቻውን ይቀራል” ሲሉ ኢቲቪን ይገልጹታል። እንደነሱ አባባል ኢቲቪ ከህዝብ ሳይሆን ከራሱ ጌቶችም ጋር ተነጥሎ የአንድ ወገን (ግለሰብ) ሎሌ የሆነ በድርጅት ቅርጽ የሚከላወስ ሱቅ በደረቴ አይነት ነው። ኢቲቪ ሃሳባቸውን፣ ንግግራቸውን፣ አቋማቸውን፣ ጥቆማቸውንና … [Read more...] about ኢህአዴግ ኢህአዴግን ማፈን ጀመረ!

Filed Under: News Tagged With: abay, bereket simon, etv, Full Width Top, meles, Middle Column

ከዚህም ከዚያም

November 20, 2012 12:41 pm by Editor Leave a Comment

ከዚህም ከዚያም

በአለባበሳችሁ አትፈታተኑ በሜኔሶታ ጠቅላይ ግዛት የሜኔቶንካ ሁለተኛ ደረጃ ሴት ተማሪዎች የመቀመጫና የኋላ ክፍላቸውን የሚያሳይ አለባበስ እንዲያቆሙ ትዕዛዝ ተላልፎላቸዋል፡፡ የት/ቤቱ ርዕሰ መምህር የሆኑት ዴቪድ አድኔይ ለወላጆች በላኩት የኢሜይል (የጾዳቤ) መልዕክት ወላጆች ሴት ልጆቻቸውን እንዲመክሩና የመቀመጫ ክፍላቸውን አወጣጥሮ እንዲሁም እግራቸውን በብዛት የሚያሳይ አለባበስ ሌሎችን የሚረብሽ በመሆኑ እንዳይለብሱ እንዲያደርጉ በማሳሰቢያው ጠቁመዋል፡፡ ርዕሰመምህሩ ለወሰዱት እርምጃ ከወረዳው ትምህርትቤት አስተዳደር፣ ከበርካታ ወላጆችና ከሌሎች ት/ቤቶች ድጋፍን አግኝተዋል፡፡ ውሳኔውን የተቃወሙ ተማሪዎች ሲኖሩ አንዳንድ ወላጆች ደግሞ “በየማስታወቂያው፣ በየቲቪው፣ በየመጽሔቱ፣ በሙዚቃው፣ … የሚሰራጨው የአለባበስ ዓይነት በየሱቁ ሲኬድ ከሚገኘው ጋር አንድ በመሆኑ ሰውነትን የማያሳይና … [Read more...] about ከዚህም ከዚያም

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

ከእሁድ እስከ እሁድ

November 19, 2012 10:39 am by Editor 2 Comments

ከእሁድ እስከ እሁድ

የዋቄፈታ እምነት ተከታዮች በማህበር ተደራጅተው እውቅና ጠየቁ! ባለአወልያዎችም ተደራጅተዋል በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የዋቄፈታ እምነት ተከታዮች በማህበር ተደራጅተው ህጋዊ ፈቃድና የህጋዊነት ማረጋገጫ የምሰክር ወረቀት የጠየቁት “ይበራል ይከንፋል፣ አይሞትም ያርጋል” እየተባለ ሲመለክ የነበረው ታምራት ገለታ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተከትሎ ነበር። የእምነቱ መሪዎች በ2002 ዓ ም ወልመራ ከተማ ቆቦ በምትባል ቀበሌ መስራች ስብሰባ አካሂደው እንደነበረ ያስታውሳሉ። ከሁለት ዓመት በፊት የወልመራ ወረዳ ከተማ በሆነችው ሆለታ የተደራጁት የዋቄፈታ ስርዓተ አምልኮ ተከታዮች የህጋዊነት ጥያቄ ያቀረቡት ለኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ መሆኑን የሚጠቅሱት እነዚህ የእምነቱ ተከታዮች ለጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ እንደገለጹለት ከሆነ ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቷል። መንግሥት በተደጋጋሚ … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

  • « Previous Page
  • Page 1
  • …
  • Page 132
  • Page 133
  • Page 134
  • Page 135
  • Page 136
  • …
  • Page 138
  • Next Page »

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule