• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከእሁድ እስከ እሁድ

November 26, 2012 10:18 am by Editor 1 Comment

የእስክንድር ነጋ ጉዳይ ለመንግሥታቱ ድርጅት ቀረበ

የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጉዳይ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያላግባብ የታሠሩ ሰዎችን ጉዳይ ለሚያጠናው ግብረኃይል መቅረቡን ለህሊና እስረኞች የሚሟገተው ፍሪደም ናው “Freedom Now” ስራ አስፈጻሚ ዋና ዳይሬክተር ማርዳ ተርነር ለአሜሪካ ሬዲዮ አስታውቀዋል።

ዳይሬክተሯ እንዳሉት ድርጅታቸው የእስክንድር ነጋን ጉዳይ በጥልቀት ከመረመረ በኋላ የጋዜጠኛነት ስራውን ብቻ ሲያከናውን እንደነበር ሙሉ አረጋግጠዋል። የታሰረውም ያለ አግባብ እንደሆነ ታምኖበታል። በእስር ቤት ከአያያዝ ጀምሮ በርካታ ጥሰቶች እንደተፈጸሙበት አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ለዓለም አቀፍ ህግጋት የገባውን ኪዳንና ግዴታ በመጣሱ የእስክንድር ጉዳይ  በተባበሩት መንግስታት ያለ አግባብ የታሰሩ ሰዎችን ጉዳይ ለሚመረምረው አካል ባለፈው ሚያዚያ ቀርቧል። የእስክንድር ጉዳይን የያዘው አካል ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀበለቻቸውን የሰብአዊና ፖለቲካ ጉዳዮች ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ህጎች ስለመጣሷ መርምሮ ውሳኔውን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። ለእስክንድር ነጋ ጉዳይ አዲስ አበባ መሄዳቸውን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሯ በውሳኔው መጨረሻ እስክንድር ነጻ ሊወጣ እንደሚችል ቀደም ሲል በፓኪስታንና በበርማ ከተሰሩት ስራዎች ጋር በማነጻጸር አስረድተዋል “እንደ መንግስታቱ ድርጅት ያሉ አካሎች የሚወሰኑት ውሳኔ ቀላል አይደለም” በማለት ተናግረዋል፡፡

እስክንድር ነጋ በአሸባሪነትና በአገር መክዳት ወንጀሎች ተከሶ 18 ዓመት እንደተፈረደበት ይታወሳል።

የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ገቢ አሽቆለቆለ

የግል ባንኮች የውጪ ምንዛሪ ገቢ በአማካይ 34 በመቶ ማሽቆልቆሉን በሂሳብ ሪፖርታቸው ታወቀ። የባንኮቹ ከውጭ ምንዛሪ ግብይት የሚያገኙት ገቢ የቀነሰው  ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ቀውስ ጋር በተያያዘ ዜጎች ወደ አገር ቤት የሚልኩት ሐዋላ በመቀነሱ ሲሆን፣ በሌላ በኩል የአገሪቱ የውጪ ንግድ ገቢ ዝቅተኛ እየሆነ መምጣቱና አገሪቱ ባጋጠማት የወጪ ምንዛሪ እጥረት ሳቢያ የውጪ ምንዛሬ ግብይት መቀነሱ ዋናው ተጠቃሽ የችግሩ መንስዔ መሆኑን ሪፖርተር ጋዜጣ አስታውቋል።

የግል ባንኮቹ ያጋጠማቸው ችግር ካለፈው ሁለት ዓመት ጀምሮ እየተባባሰ እንደሚሄድ ባለሙያዎችን አነጋግሮ የዘገበው ሪፖርተር እንዳለው በሚቀጥለው አሁን ባለው የውጪ ምንዛሪ እጥረት አንጻር የተያዘው የበጀት ዓመት የግል ባንኮች ገቢ በጣም ዝቅ እንደሚል ተገምቷል።ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ የውጪ ምንዛሪ እጥረት እንደሌለ በቅርቡ ለፓርላማቸው ተናግረው ነበር።

የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ሊፈርስ ነው

ሰሞኑን ከአዲስ አበባ የሚወጣው አስደንጋጭ ዜና የሰማዐቱ አቡነ ጴጥሮስ ሃውልት እንደሚፈርስ፣ የአጤ ሚኒልክም ሃውልት በተመሳሳይ አደጋ ውስጥ እንደሆነ የሚያመለክት ነው። አዲስ አበባን ይዞራታል ተብሎ የተነገረለት የባቡር መስመር ግንባታ ለጊዜው ሁለቱን ሃውልት ሊያፈርስ እንደሚችል በርካታ የዜና አውታሮች አስተጋብተዋል።

ኢሣትን ጨምሮ የተለያዩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የባቡሩ መስመር የአቡነ ጴጥሮስን ሃውልት እንደሚያፈርሰው የሚያመላክት ቁፋሮ እየተካሄደ ነው። መንግስት ከመስመሩ ግንባታ በኋላ ሃውልቱ ተመልሶ በነበረበት ይተከላል ቢልም ሃውልቱ ለእይታ ከተሸፈነ ምን ዋጋ አለው የሚል ጥያቄ እየተነሳ ነው። የሰማዕታት፣ የታጋዮች፣ የኦህዴድ ጀግኖች፣ የብአዴን ታጋዮች፣ የህወሃት የተሰዉ … እያለ በከፍተኛ ወጪ ሃውልት የሚገነባውና ለማያውቃቸው አምባገነን የአፍሪካ መሪዎች ጎዳና በስማቸው የሚሰይመው ኢህአዴግ ፕሮጀክቱ ሲጠና ጀምሮ ሃውልቶቹን በማይነካ መልኩ ማድረግ ይገባው እንደነበር አስተያየት እየተሰጠ ነው። አስተያየት ሰጪዎቹ “ህወሃት ቀደም ሲል ጀምሮ ኢትዮጵያዊነትንና የኢትዮጵያን ማንነት የሚያጎሉ ታሪካዊ ቅርሶችን በማጥፋት ለሚወቀስበት እኩይ ተግባሩ መገለጫ ነው” በማለት ድርጊቱን ኮንነዋል።በግልጽ ባይወጣም አራዳ ጊዮርጊስ የቆመው የአጤ ሚኒሊክ ሃውልትም አደጋው እያንዣበበው ነው።

ይህ ዜና በተላለፈ ጥቂት ቀናት ውስጥ ከምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አቶ አበበ ምህረቱ የአቡነ ጴጥሮስ ሃውልት እንደሚነሳ ገልጸው ይህም የሚሆነው ከስዊድን በሚመጣ ከፍተኛ አማካሪ ተቆጣጣሪነት እንደሚሆንና የባቡር ዋሻው ሥራው “እንደተጠናቀቀ አንዲትም ሣ/ሜትር ሳይዛነፍ እንደነበረ በቦታው ላይ በክብር” እንደሚቀመጥ አስታውቀዋል፡፡ የአጤ ምኒልክ ሃውልት ግን አሁን ባለበት ሁኔታ እንደሚቀጥል አስታቀዋል፡፡

በዚህ በሃውልቶቹ መነሳት ጉዳይ እስካሁን ድምጹን ያሰማ የተቃዋሚ ድርጅት ካገር ቤት አልተሰማም።

ኢህአዴግ ሰሞኑን እነዚህ ታሪካዊ ሃውልቶችን አስመልክቶ ይህንን የመሰለ ውሳኔ ሲያስተላልፍ የአዲስ አበባን 125ዓመት እንዲከበር ማድረጉ ሰንደቅዓላማን እየናቀ “የባንዲራን ቀን” ከማክበሩ ስላቅ ጋር በርካታዎች አያይዘውታል።

አቶ ሳምሶን በመመሪያ መፈታታቸውን አመኑ

የኢትዮ ቻናል ጋዜጣ ባለቤት አቶ ሳምሶን ማሞ ወዳጆቹ ከእስር እንዳስፈቱት አስታወቀ። ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር ቃለምልልስ ያደረጉት አቶ ሳምሶን “ወዳጆቻችን አስፈቱን አላልኩም፤ ወዳጆቻችን ለሚመለከተው የመንግስት ባለስልጣን አሳውቀው አስፈቱን ነው ያልኩት” በማለት ተናግረዋል። “ለሁሉም አለቃ አለው፤ ህገወጥ ውሳኔ ነበር። ያንን እንዲያስተካክሉ እዛ የነበሩ ጓደኞቻችን ለሚመለከታቸው ሃላፊዎች አሳውቀው ነው የተፈታነው” ያሉት አቶ ሳምሶን ኢህአዴግን እንደሚወዱ በይፋ አስታውቀዋል። ኢትዮ ቻናል ጋዜጣ በራሱ በጀት የሚተዳደር እንጂ በኢህአዴግም ሆነ በሼኽ መሃመድ አላሙዲ እንደማይደጎም ሸምጥጠው ክደዋል።

አቶ  ሳምሶን ከህግ ውጪ መታሰራቸውን ደጋግመው በገለጹበት ቃለ ምልልስ እንደ እሳቸው የሰብአዊ መብት ጥሰት ለሚካሄድባቸው ጠበቃ በመሆን እስከ ህይወታቸው ህልፈት ድረስ እንደሚሟገቱ ተናግረዋል። እግረ መንገዳቸውንም የማስታወቂያ ድርጅታቸው 1.7 ሚሊዮን ብር የግብር ዕዳና የገንዘብ መቀበያ (ካሽ ረጂስተር) ሳይኖራቸው እንደሚሰሩ አምነዋል። አቶ ሳምሶን ለኢትዮ ቻናል ጋዜጣ በጀትና ስራ ማስኬጃ በአቶ አብነት ገ/መስቀል አማካይነት እንደሚረዱ፣ ስራቸውም ኢህአዴግን የሚደግፉ መረጃዎችን በመጻፍ የሼክ መሐመድን ሁሴን አለሙዲን ስምና ድርጅቶች መጠበቅ ቢሆንም በእውቀት ማነስ ኢህዴግን በማስወቀስና ሼኩን ትዝብት ውስጥ የሚጥል ሪፖርት በማስተላለፋቸው ፊት እንደተነሱ የጎልጉል ምንጮች ገልጸዋል። አቶ ሳምሶን ኢህአዴግንና ሼኩን ያስደሰቱ እየመሰላቸው የሚጽፉት ጽሁፍ በአስነዋሪነቱ ምሳሌ እየሆነ ለተሳዳቢ ስላጋለጣቸው ወዳጆቹ “የደንቆሮ ብዕር” እያሉ እንደሚሳለቁበትም ታውቋል። አቶ ሳምሶን በህወሃት ነባር ታጋዮች ዘንድ በጣም የሚጠሉና ከአቶ አማረ የግድያ ሙከራ ጋር በተያያዘ ስማቸው በተደጋጋሚ የሚነሳ መሆኑ የሚታወስ ነው።

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. demelash says

    November 27, 2012 03:08 pm at 3:08 pm

    thank you bertu informatlin is very important

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
Copyright © 2026 · Goolgule