“My countrymen… do not believe the fascists if they tell you that the patriots are bandits. The patriots are people who yearn for freedom from the terrors of fascism...” (Read more) … [Read more...] about Statue of bishop, Abune Petros, to be removed
Opinions
የኔ ሃሳብ
የእምነትና የሞራል ግዴታ
በአገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ በመንግስትና በቤተ ክርስቲያን አካባቢ ያሉ ሰዎች ስለየሚያደርጓቸው ተደጋጋሚ በደሎች ዘወትር የሚነገሩትና የሚጻፉት ነገሮች እንደሚያሰለቹ የታወቀ ነገር ነው። በሆንም ቀድሞ በባህላችን ሲደረጉ አስገራሚና አስደንጋጭ የነበሩ ስህተቶች ተደጋግመው በመደረጋቸው እየተለመዱ፤ ስለነሱም በተደጋጋሚ የሚነገሩትና የሚጻፉት አሰልችተውናል። ቢሆንም፤ ሰልችተን ርግፍ አርገን ከተውናቸው፤ ስሀተተ ፈጻሚዎች በስህተታቸው ስለሚቀጥሉና ስህተቶችም የባህል ውርስ ሆኖነው እንዳሸገሩ፤ ስህተተኞችም ከስህተታቸው እንዲገቱ ለማሳሰብ፤ የእምነትና የሞራል ግዴታ በሚል ርእስ ይህችን ጦማር አዘጋጀሁ። (ሙሉው ጽሑፍ እዚህ ላይ ይገኛል) … [Read more...] about የእምነትና የሞራል ግዴታ
“ለትግል እንነሳ”
በዛሬው እለት በ14/11/2012 በእስራኤል አገር በእየሩሳሌም ከተማ ቁጥራቸው ከ10000 እስከ 15000 የሚገመቱ ኢትዮጵያውያን ቤተ እስራኤላውያን በተገኙበት የስግድ በአል በከፍተኛ ድምቀት ተከብሯል። የበአሉ አብይ ትርጉም ኢትዮጵያዊ አይሁዳውያን በኢትዮጵያ በነበሩበት ጊዜ አምላካቸው ቅድስት አገር እየሩሳሌም ያደርሳቸው ዘንድ ተሰባስበው የምኞት ፀሎታቸውን ሲያደርሱ የነበረው በፀሎት ያሰሙት ልመና ፈጣሪ ሰምቷቸው በቅድስት አገር እስራኤል መሰባሰባቸውን ምክንያት በማድረግ በየአመቱ የምስጋና ፀሎት ከተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች በመምጣት ሲያከብሩት አመታት ተቆጥሯል። ሆኖም በተጠቀሰው የበአል አከባበር እለት የኢትዮጵያን መንግስት የሚያወግዝ ባለ 14 ነጥብ የተቃውሞ ሀሳብ የያዘ “ለትግል እንነሳ” በሚል ርእስ በርካታ ወረቀቶች ተበትነው በበአሉ ታዳሚዎች እጅ የደረሱ ሲሆን በፅሁፉ ላይ … [Read more...] about “ለትግል እንነሳ”
እስራኤል ልጆቿን አሰረች
“አንተም በግብፅ ምድር ባሪያ እንደነበርክ አስብ ይህንን ስርአት ጠብቀውም አድርገውም” ኦሪት ዘዳግም 16 – 12 የንግስት ሳባና የጠቢቡ የንጉስ ሰለሞንን ግንኙነት ተገን አድርጎ የተፈጠረው ሚኒሊክና ሚኒሊክን አጅቦ ከተስፋይቱ ምድር ወደ ታላቋ አገራችን የገባው የኦሪት እምነት አያሌ ሺህ ዘመናትን ማስቆጠሩን የሁለቱም አገር ሕዝቦችና መንግስታት ሊዘነጉት የማይችሉት የእምነት ትስስር ቁርኝቱ እስከ ዛሬ ድረስ አልተበጠሰም። የክርስትናው እምነት ገኖ በበላይነት እስከተስፋፋበት ጊዜ ድረስ በኢትዮጵያ የኦሪት እምነትን ተከታይ እንደነበረችና በአገራችን ለእምነት ፅኑ መሰረት ወይም ትኩረት የማይሰጡ መንግስታት በተፈራረቁ ቁጥር ሕዝባችን ዛሬም “የእስራኤል አምላክ የተመሰገነ ይሁን” የሚለውን የምስጋና ቃል ከማስተጋባት አልቦዘነም። የዛሬዋ ነፃይቱ እስራኤል ገና የ64 አመት እድሜ ባለፀጋና … [Read more...] about እስራኤል ልጆቿን አሰረች
”እናቴ አልዳነችም!…….’’
እናት ለልጇ ያላትን ፍቅር መለኪያ፣ ወሰን፣ ድንበርና ግዜ ይኖረው ይሆን?……. በእግዚአብሄር ፈጣሪነትና ፈቃድ፤ ዘጠኝ ወር በመሀጸኔ ተሸክሜ፣በጭንቅና በጣር አምጨ ወለድኩት። አርባ ቀን ሲሞለው እምነታችን በሚያዘው መሰረት ክርስትና አስነሳሁት። በክርሰትና ስሙ ኅይለማርያም ብዩ ስም አወጣሁለት። ጡቶቸን እያጠባሁ፣ የምችለውን ሁሉ እያደረኩና የማይጠገበውን የእናትነትን ፍቅር እየመገብኩ አሳደኩት። ወደ ዘመናዊ ትምህርት ቤትም ላኩት። ልጀም ለቁምነገር በቃ። ከስልጣን ወደ ስልጣን ተሸጋገረ። ከትልቅ ደራጃም ደረሰ። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒሰተርም ተባለ። ኅይለማርያም ደሳለኝ፤ የኔ ልጅ። መቼም የእናት ፍቅርና ስቃይ መሳ-ለመሳ ነው። ትልቅ ደረጃ ላይ መድረሱ የሚያስድስተኝን ያህል፤''ምን ይሆን? ወይስ ምን ይደርስበት ይሆን?....''የሚለው የሌት-ተቀን ሀሳብና ጭንቀቴን እናት ብቻ ነው … [Read more...] about ”እናቴ አልዳነችም!…….’’
ኢትዮጵያዊው ዑሴይን ቦልት የራሱን ሪከርድ አሻሻለ!
ለለውጥ ያህል ለምን አንባቢን ፈገግ ልታደርግ በምትችል የአዲስ አበባ ዘመነኛ ቀልድ አልጀምርም? አንድ የወያኔ ከፍተኛ ባለሥልጣን በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ሲዝናና ያመሻል፡፡ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት አካባቢ ሲሆን ወደቤቱ ሊሄድ ቄንጠኛ ፕራዶ መኪናውን ሊያስነሳ ቢሞክር ያልታሰበ ብልሽት ያጋጥመውና ሞተሩ ለመነሣት እምቢዬው ይለዋል፡፡ ቢለው፣ ቢለው አልሆነለትም፡፡ ከዚያም ሌላ ምርጫ ሲያጣ ላዳ ታክሲ ያስጠራና ወደቤቱ እንዲያደርሰው ሹፌሩን ይጠይቀዋል፡፡ በቅድሚያ ግን በስንት እንደሚያደርሰው ሒሳቡን ለማወቅ ይፈልግና “ለቡልጋሪያ ማዞሪያ ነው ቤቴን፣ በስንት ነው እንዴ’ምታደርሰኝ?” ይለዋል፡፡ ይህ ባለታክሲም ብዙም ሳያቅማማ “150 ብር ይከፍላሉ፤ ይግቡ” ይልና ጋቢናውን ይከፍትለታል፡፡ ይሄኔ ባለሥልጣኑ ተገርሞ “ቧይ! ለቡልጋሪያ ማዞሪያ ለዚህን ያህል ቡዙ ገንዘብ ማለተይ ለሞቶ ሃምሳ ብር … [Read more...] about ኢትዮጵያዊው ዑሴይን ቦልት የራሱን ሪከርድ አሻሻለ!
“አትነሳም ወይ?!”
"አትነሳም ወይ" በሚል በሰማያዊ ፓርቲ ድረገጽ አናንያ ሶሪ ባስነበቡት ጽሁፍ ስለ “መነሳት” የተለያዩ ሃሳቦችን በማንሳት እይታቸውን አስፍረዋል። መነሳትን ከህይወት፣ ከህይወት ክንውኖች፣ ከህይወት ስንብትና ከመቃብር እስከመውጣት ባሉ ጉዳዮች በማዋዛት አሳይተዋል።በተለይም "አትነሳም ወይ" በማለት ኢህአዴግንም ፈክረውለታል። ጎልጉል በቀጥታ ከጽሁፉ የወሰደውን በማቃመስ ዋናውን ጽሁፍ በድረገጹ ላይ ታነቡ ዘንድ ይጋብዛል። “ ... አትነሳም ወይ?! ከእንቅልፍ ነው? ከሞት ነው? ከሞት ከበረታ ድንዛዜ ነው? ፎቶ ነው? ራጂ ነው? ክርስትና ነው? … በክፉ ነው የምትነሳው? በደግ ነው የምትነሳው? በትንሳዔ-ሙታን ነው የምትነሳው? በምንድነው የምትነሳው? ለምንድነው የምትነሳው? ወዴት ነው የምትነሳው? መቼ ነው የምትነሳው? እንዴትስ ነው የምትነሳው?... “… መቼም ኢትዮጵያውያን … [Read more...] about “አትነሳም ወይ?!”
አስደሳቹ የብሔራዊ ቡድን ውጤትና ቅሌት
ባሳለፍናቸው ሳምንታት እሁድ ዕለት አንበሳው የብሔራዊ ቡድናችን ያደረገው ለአፍሪካ ዋንጫ የማለፍ ትንቅንቅ በጣም አጓጊና አስደሳች እንደነበር አይተነዋል። ጀግናው ብሔራዊ ቡድናችን የሱዳን አቻውን ሁለት- ለዐልቦ በሆነ ውጤት በዝረራ አሸንፎ እነሆ ከሰላሳ አንድ አመታት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ እንድናልፍና ልክ አረንጓዴ ጎርፍ ተብለው የሚጠሩት አትሌቶቻችን ሰንደቅ ዓላማችንን ከፍ አድርገን እንድናውለበልብ እንዳደረጉን ሁሉ ዛሬም ብሔራዊ ቡድናችን አፍሪካ ላይ ለጊዜውም ቢሆን መሀሉ ላይ የሰይጣን አምልኮት ምልክት ያለበትን ባለኮከቡን አረንጓዴ ፥ ቢጫና ፥ ቀዩን ሠንደቅ ዓላማችንን እንድናውለበልብ አድርገውልናል፡፡ ምስጋና ይግባቸው ለዋልያዎቹ። ይህን ድል አቶ መለስ በህይወት ኖረው ቢያዩት ደስ ይለኝ ነበር። የሚሉትን ለመስማት፡፡ ግን አፈር ይክበዳቸውና የሉም። ሀገራችን ኢትዮጵያን … [Read more...] about አስደሳቹ የብሔራዊ ቡድን ውጤትና ቅሌት
ለመሆኑ ኢሕአዴግ አለ እንዴ?
ጤና ይስጥልኝ ክቡራትና ክቡራን አንባቢያን፤ በዚያኛው ሰሞን ስለብዙዎቹ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ከእግዚአብሔር መንገድ መራቅና ስለሕዝበ ክርስቲያን የመንፈስና የልብ መሸፈት አንዳንድ ነጥቦችን ተናግሬ ነበር፡፡ አንድ ሦስት ያህል የነጻው ሚዲያ ድረገጾች አስተናግደውታል፡፡ እግዚአብሔር ይባርክልኝ፤ መንግሥተ ሰማይንም ያውርስልኝ፡፡ ሙከራየ ጥቂቶችን ከገቡበት አረንቋ እንዲወጡ - እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ - ለማሳሰብ እንጂ ሃይማኖተኝነትን ለመክሰስ ወይ ለመውቀስ አይደለም፡፡ ሃይማኖት የሌለው ሰው ልጓም እንደሌለው የጋማ ከብት ሊሆን የሚችልበት አጋጣሚ እንደመኖሩ በዚያው መጠን ሃይማኖት አለኝ የሚልም ሰው ከለየለት ሃይማኖት የለሹ ሰው ባላነሰ ምናልባትም በከፋ ደረጃ አጥፊ ሊሆን የሚችልበት አጋጣሚ ይስተዋላልና ያን መረዳትና ሲቻልም ማስቀረት እንዲቻለን በዚህ ረገድ የሚታዩብንን … [Read more...] about ለመሆኑ ኢሕአዴግ አለ እንዴ?
ዛሬ ነገ ሳንል መነሳት የዜግነት ግዴታችን ነው!
ለቀድሞው የወያኔ ጠቅላይ ሚኒስትር ለጊዜው ኳሷ በእሳቸው ቁጥጥር ስር እንደሆነች እና የኢትዮጵያ ህዝብን ፍላጎት ማክበር አለበለዚያም የኢትዮጵያ ህዝብ እና ታሪክ ጠላት ሆነው የመቀጠል ሁለት ምርጫ እንዳላቸው በኢትዮጵያ ምሁራን በየአቅጣጫው ቢነገራቸውም ፤ በማን አለብኝነት ኳሷን ባለማከፋፈል ችግር ፣ እኔ ብቻ በኳሷ እንደፈለኩ ከምፈልገው ወገን ጋር ልጫወትባት ፣ ስለ ኳሷ አትጠይቁኝ ፣ ወደ ኳሷም አትጠጉ በማለት ቀይ መስመር በማስመር እና እኔ ብቻ አውቃለሁ በማለት በ 80 ሚሊዮን ህዝብ ራእይ እና ተስፋ ላይ እንደቀለዱ ... (ሙሉውን ጽሑፍ እዚህ ላይ ይገኛል) … [Read more...] about ዛሬ ነገ ሳንል መነሳት የዜግነት ግዴታችን ነው!