በዛሬው እለት በ14/11/2012 በእስራኤል አገር በእየሩሳሌም ከተማ ቁጥራቸው ከ10000 እስከ 15000 የሚገመቱ ኢትዮጵያውያን ቤተ እስራኤላውያን በተገኙበት የስግድ በአል በከፍተኛ ድምቀት ተከብሯል። የበአሉ አብይ ትርጉም ኢትዮጵያዊ አይሁዳውያን በኢትዮጵያ በነበሩበት ጊዜ አምላካቸው ቅድስት አገር እየሩሳሌም ያደርሳቸው ዘንድ ተሰባስበው የምኞት ፀሎታቸውን ሲያደርሱ የነበረው በፀሎት ያሰሙት ልመና ፈጣሪ ሰምቷቸው በቅድስት አገር እስራኤል መሰባሰባቸውን ምክንያት በማድረግ በየአመቱ የምስጋና ፀሎት ከተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች በመምጣት ሲያከብሩት አመታት ተቆጥሯል። ሆኖም በተጠቀሰው የበአል አከባበር እለት የኢትዮጵያን መንግስት የሚያወግዝ ባለ 14 ነጥብ የተቃውሞ ሀሳብ የያዘ “ለትግል እንነሳ” በሚል ርእስ በርካታ ወረቀቶች ተበትነው በበአሉ ታዳሚዎች እጅ የደረሱ ሲሆን በፅሁፉ ላይ … [Read more...] about “ለትግል እንነሳ”
suffering
የእህቶቻችን ሰቆቃ በአረብ ምድር
ይህ የምትመለከቱትን ፎት ያነሳሁት በጅዳው አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ በሚገኝ የጸጥታ አስከባሪ ፖሊሶች አንድ ጽህፈት ቤት ውስጥ ነው፡፡ ይህች የምታይዋት እህትም ምን እዚያ አመጣት እንዳትሉ ! ከአንድ ወር ከሳምንት በፊት በኮንትራት ስራ ከሀገር ቤት የመጣች መሆኗን ሳውዲው የእድሜ ባለጸጋ አሰሪዋ ተነገረውኛል፡፡ እኔም ሆንኩ ይህንን ጉድ አብረውኝ የሚመከቱ እህቶቸ ሁላችንም ወደ ሃገር ቤት የሚሸኙ ዘመዶቻችንና ወዳጆቻችን አጅበን ነና የመጣነው የዚህች እህት ወደ አየር መንገዱ ለምን እንዳመጣች መጠየቅ አላስፈለገኝም ፡፡ በሰውነቷ ላይ ባረፈውን እስራትና ድብደባ ከመገለ እጇና ገላዋ ላይ ሰንበር የመሰለ የጉዳት ምልክት ይታያል፡፡ (ሙሉው ታሪክ እዚህ ላይ ይገኛል) … [Read more...] about የእህቶቻችን ሰቆቃ በአረብ ምድር