በዛሬው እለት በ14/11/2012 በእስራኤል አገር በእየሩሳሌም ከተማ ቁጥራቸው ከ10000 እስከ 15000 የሚገመቱ ኢትዮጵያውያን ቤተ እስራኤላውያን በተገኙበት የስግድ በአል በከፍተኛ ድምቀት ተከብሯል።
የበአሉ አብይ ትርጉም ኢትዮጵያዊ አይሁዳውያን በኢትዮጵያ በነበሩበት ጊዜ አምላካቸው ቅድስት አገር እየሩሳሌም ያደርሳቸው ዘንድ ተሰባስበው የምኞት ፀሎታቸውን ሲያደርሱ የነበረው በፀሎት ያሰሙት ልመና ፈጣሪ ሰምቷቸው በቅድስት አገር እስራኤል መሰባሰባቸውን ምክንያት በማድረግ በየአመቱ የምስጋና ፀሎት ከተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች በመምጣት ሲያከብሩት አመታት ተቆጥሯል።
ሆኖም በተጠቀሰው የበአል አከባበር እለት የኢትዮጵያን መንግስት የሚያወግዝ ባለ 14 ነጥብ የተቃውሞ ሀሳብ የያዘ “ለትግል እንነሳ” በሚል ርእስ በርካታ ወረቀቶች ተበትነው በበአሉ ታዳሚዎች እጅ የደረሱ ሲሆን በፅሁፉ ላይ የተጠቀሱት ሀሳቦች የወያኔ አምባገነንነት በውል ያመላከቱ ሲሆን የወያኔ መንግስት ቀደም ሲል በመካከለኛው ምስራቅ ውስጥ በዘፈቀደ የሚያካሄደውን ፕሮፖጋንዳ ያመከነ እንቅስቃሴ ሲሆን ከዚህ እንቅስቃሴ ከአንድ ሳምንት ቀደም ብሎ በቴላቪቭ ከተማ አፍቃሪ ወያኔዎች ለአቶ መለስ ዜናዊ መታሰቢያ ባዘጋጁት ፕሮግራም ዋዜማ ላይ የተቃውሞ ፅሁፍ በቴላቪቭ ከተማ ተበትኖ ነበረ፡፡
በአጠቃላይ ኢህአዲግ በመካከለኛው ምስራቅ ውስጥ የነበረውን የበላይነት እየተነጠቀና ደጋፊዎቹም እየተመናመኑ እንደሚገኙ የሚያሳይ ክፍተት መፈጠሩን በመግለጽ ህዝቡ ለተጨማሪ ትግልና ድል በጋራ ለመስራት በየአቅጣጫው ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን በማስታወቅ በእለቱ በበአሉ ላይ የተበተነውን የተቃውሞ ፅሁፍና የበአሉን ስነስርአት የሚያመለክት የቪዲዮ መረጃ ከዚሁ ጋር አብሮ ቀርቧል፡፡
Leave a Reply