• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

እስራኤል ልጆቿን አሰረች

November 14, 2012 08:11 pm by Editor 6 Comments

“አንተም በግብፅ ምድር ባሪያ እንደነበርክ አስብ ይህንን ስርአት ጠብቀውም አድርገውም”

ኦሪት ዘዳግም 16 – 12

 የንግስት ሳባና የጠቢቡ የንጉስ ሰለሞንን ግንኙነት ተገን አድርጎ የተፈጠረው ሚኒሊክና ሚኒሊክን አጅቦ ከተስፋይቱ ምድር ወደ ታላቋ አገራችን የገባው የኦሪት እምነት አያሌ ሺህ ዘመናትን ማስቆጠሩን የሁለቱም አገር ሕዝቦችና መንግስታት ሊዘነጉት የማይችሉት የእምነት ትስስር ቁርኝቱ እስከ ዛሬ ድረስ አልተበጠሰም።

የክርስትናው እምነት ገኖ በበላይነት እስከተስፋፋበት ጊዜ ድረስ በኢትዮጵያ የኦሪት እምነትን ተከታይ እንደነበረችና በአገራችን ለእምነት ፅኑ መሰረት ወይም ትኩረት የማይሰጡ መንግስታት በተፈራረቁ ቁጥር ሕዝባችን ዛሬም “የእስራኤል አምላክ የተመሰገነ ይሁን” የሚለውን የምስጋና ቃል ከማስተጋባት አልቦዘነም።

የዛሬዋ ነፃይቱ እስራኤል ገና የ64 አመት እድሜ ባለፀጋና በወሽመጥ መሰል ካርታዋ ተከልላ ከአረብ አገራት ጋር ተፋጣ ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊና ማህበራዊ መሰረቷን አጎልብታ በአለም አሉ ከሚባሉና በሁሉም ረገድ ተፅእኖ ለማሳረፍ በሚችሉ ጠንካራ ህዝቦቿ ህብረት ከብረት በጠነከረ ፅናቷ ጠላቶቿን ድል አድርጋ ዛሬ በወታደራዊ ሆነ በኢኮናሚያዊ ዘርፎች ክንዷን አፈርጥማ በመካከለኛው ምስራቅ ብቸኛዋ የዲሞክራሲ ስርአት ጮራ ፈንጣቂ ለመሆን የበቃች የቆዳ ስፋቷ ትንሽ ጥበቧ ትልቅ የሆነች አገር ናት።

የእስራኤል የነፃነት ኩራት በዋዛ የተገኘ ሳይሆን አገሪቱ እንደ አገር ያቆማት በዜጎቿ ደምና አጥንት የተማገረች እንደሆነች ብዙ ዋቢ መጥቀስ ይቻላል ሆኖም የዚህ ፅሁፍ አላማ ናዚ ያደሰውን ጨካኝ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ማስተጋባት ሳይሆን የተስፋይቱ ምድር ከነፃነቷ በኋላም እስከ ዛሬ ልጆቿን ከአለም ዳርቻ ሳትሰበስብ በስደተኛ ወገኖቼ ላይ እየወሰደች ያለችውን መራር እርምጃ መንግስቷና ሕዝቧ የስደተኛውን ችግር በመገንዘብና በኦሪት ዘፍጥረት 15 – 15 ላይ “አንተም በግብፅ ምድር ባሪያ ነበርህ አምላክህ እግዚአብሔር እንዳዳነህ አስብ” የሚለው አምላካዊ ቃል  ትእዛዝ መሆኑ ቀርቶ በባለጊዜዎች እንደ ተረት መታየቱ በኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ላይ እየደረሰባቸው ያለውን ሰቆቃ ለማሰማትና ኢትዮጵያውያኑ እንደ አገራቸው ለመኖር ተስፋ ያደረጉባት ምድር ሲኦል ልትሆንባቸው እንደማይገባ የበኩሌን ለማለት ስለፈቀድኩ በታሳሪዎች ስም አለማቀፍ ማህበረሰብ ይታደገን ዘንድ ማለት የሚገባኝን ለማለት ወደድኩ።

ዛሬ እኛ የነበረችንን ታላቅ አገር ጥቂት ጎጠኞች በሚያራምዱት የበቀል ፖለቲካ አገራችንን በታትነው እኛንም የመኖር ዋስትና አሳጥተው ለስደት ለእስራት ለሞት የዳረጉን የአገራችንን ታሪክና እምነት እያጎደፉ ካሉ ሞገደኞች ሕይወታቸውን ለማትረፍ ከሞት ጋር ትንቅንቅ ገጥመው የሲናን በረሃ ዘግናኝ ጉዞ ኩላሊታቸውንና ሌላ የሰውነት አካላቸውን የተነጠቁ /የተዘረፉ/ እና በአምላክ ቸርነት ይህ የበረሃ ላይ የውስጥ አካልን ከመዘረፍ ያመለጡ ሕፃናት፣ ወጣቶችና ጎልማሳዎች ነፍሳችን ተረፈች በማለት በተስፋይቱ ምድር በአዲስ ተስፋ ተሞልተው በተገቢው የስደተኛ መብት በመጠቀም የራሳቸውን የአገራቸውንና የሕዝባቸውን የሰቆቃ ኑሮና እንግልት ለአለም ህዝቦች ለማሰማት እየፈለጉ በተቃራኒው ከነ መከራቸው ተስፋና መሸሸጊያ ትሆነናለች ባሉት ቅድስት አገር ኢትዮጵያውያኑ ከድንኳን በተዘጋጁ የጠረፍ እስር ቤቶች ያለ ጠያቂ ያለፉትን ሶስትና አራት አመታት እሮጠው ያልጠገቡ ሕፃናት ሳይቀሩ በበጋ ሐሩር በክረምት ቅዝቃዜ ሲጠበሱ ማየት ኢትዮጵያውያንን ብቻ የሚያሳስብ ሳይሆን ማንም የሰከነ ህሊና ላለው ፍጡር ሁሉ የኢትዮጵያውያኑ መከራ ሊያሳስበው ሊያስጨንቀው መላ ሊያፈላልግለት የሚገባው ጉዳይ ሊሆን እንደሚችል አያከራክርም።

ማንም ሰው አስገዳጅ ሁኔታ ካልተከሰተበት በነፃነት የሚኖርባትን የራሱን የክብር ስፍራ ጥሎ በዘመናዊ ባርነት ለመገዛት የሚቋምጥ ይኖራል ብዬ አላምንም። ማንም ክብሩን ትቢያ ላይ መጣል አይሻም። የማንንም አገር ዘላለማዊ እርስቱ አድርጎ ለመኖር የሚሻ ቀን የጎደለበት ስደተኛ ይኖራል ብዬ አላስብም። መንግስታት ዜጎቻቸውን እንዳይሰደዱ ሀላፊነት የሚሰማው ተግባር ለመከወን ዝግጁ ቢሆኑ ዛሬ የሰው ልጅ ባህር እያሰመጠው እንደ ሸቀጥ በኮንቴይነር እየታሸገ በሚፈጠር የአየር እጥረት እየሞተ ከዚያም ተረፍኩ ሲል የባእዳን ዜጎች ክብረ ነክ የሆነ የወሲብ ፈረሳቸውን ጭነው የሚጋልቡበት መሆንን ማንም እንዲህ አይነቱን ፅልመት ወይም የሞት ታናሽ ወንድም ወደ ሆነ መንከራተት ሊያመራ እንደማይሻ እያንዳንዱ አገር እመራለሁ የሚል የመንግስት አካል ሊያውቅ ይገባዋል።

ዛሬ እስራኤላውያን በአለም ዙሪያ ከሚኖሩበት የማይኖሩበትን አገር መቁጠር ይቀላል፣ እነሱ በመላው አለም የመኖር ዋስትናቸውን አረጋግጠው ሐብት አፍርተው በእውቀት ደርጅተው እየኖሩ የገዛ አገሩ ሳትሆን አገር እንመራለን በሚሉ ለኢትዮጵያና ሕዝቧ መቅሰፍት የሆኑ የራሳቸውን ሕዝብ እያሸበሩ ሽብርተኛነትን እንዋጋለን በሚሉ አስተሳሰብ ድውያን የተፈጠረን ችግር የሌላ አገር መንግስታት እስራኤልን ጨምሮ ለኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጆሮ ዳባ ልበስ ማለታቸውን በእጅጉ ያሳዝናል።

የዛሬዋ እስራኤል በ1948 በውድ ልጇ በዳቪድ ቬንጎሪዮን የነፃነት ሸማዋን መልበሷ ከመታወጁ በፊት የእኛ ኢትዮጵያውያን የቀደሙ ወገኖቻችን በእስራኤል ምድር መኖራቸው የዛሬዎቹ የእስራኤል ሹማምንት ለምን ትዝ አልላቸው አለ? ለምንስ እንደ እንግዳ ሊመለከቱን አሰቡ? “ከኋላ የበቀለ ቀንድ ጆሮን ቀደመው”  እንደተባለው ለአገሪቱ ቀዳሚ  የነበርን የዛሬ ታሳሪ የሆንን ወገኖች በአሳሪዎቻችን ምን ይወሰንብን ይሆን? “ጊዜ ለኩሉ” የተባለው ለእንዲህ አይነት ገጠመኝ ይመስለኛል። “የጊዜ እንጂ የሰው ጀግና የለውም” እንዲሉ ጊዜ ተለውጦ በክብር መኖር የሚገባን የእስራኤል ወዳጆች በምናከብራቸውና በእምነት በምንመስላቸው ወገኖቻችን መታሰራችን አስገራሚም አሳዛኝም ክስተት ነው ብዬ አምናለሁ።

የኢትዮጵያውያንን ዛሬ በእስራኤል ምድር መታሰር በተመለከተ ነፍስ ዘርቶ መቃብር ፈንቅሎ ጠቢቡ ሰለሞን ቢሰማ የዛሬዎቹ እስራኤላውያን ያንን ዘመን ያስቆጠረን የፍቅርና የእምነት ትስስር አፈር እያለበሱት እንዳሉ ይረዱ ይሆን? ሰው በቤቱ እንዴት ይታሰራል? ዛሬ ኢትዮጵያውያን በቅድስት አገር ነፍሳቸውን ለመታደግ የሚያደርጉትን እሩጫ ለነፍሳቸው መድህን መሆን የሚጋባው አካል በአገራቸው ከፈሩትና ከሸሹት ባልተናነሰ መጠን በእስር ለአመታት ሲያሰቃያቸው ማየት ለኔ ኦሪትን መፃረርና የእስራኤል አምላክ ሲል የኖረን የኢትዮጵያን ሕዝብ የፍቅር ልብ ማጉደፍ ይመስለኛል።

የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ይላል ኦሪት ዘዳግም 5 – 6 “ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ” ይላል።

እናም የሚያመልኩት አምላክ የባርነት ሰንሰላታቸውን የፈታላቸው እስራኤላውያን አምላክ ያላቸውን እረስተው ዛሬ ማጣፊያ አጥሮት የመኖር ህልውናው አደጋ ላይ የወደቀን ስደተኛን አስሮ  ማስጨነቅ የትላንት የግብፅ ምድርን ባርነት መዘንጋትና መንፈሳዊ ተቃርኖን መፍጠር እንደሆነ አያጠያይቅም።

ኦሪትን እከታተላለሁ ቃሉንም አከብራለሁ እንደ እምነቴ በቃሉ እመራለሁ የሚል መንግስትና ሕዝብ መጠጊያ ያጣን ወገን በበረሃ አስሮ ማሰቃየትና ማስጨነቅ የበደል ሁሉ በደል የጭካኔ ሁሉ ጭካኔ ከመሆን አልፎ በኦሪት ዘፍጥረት 24 – 14 ላይ የተጠቀሰውን “ደሃና ችግረኛውን አታስጨንቀው” የሚለውን አምላካዊ ትእዛዝ መሸርሸር እንደሆነ የድርጊቱ ፈፃሚዎች ሊረዱት ይገባል።

በአጠቃላይ ዛሬ ፍትህ፣ ዲምክራሲና ሰላም ከራቋት አገራችን በሚደርስብን የገዥው መደብ በደል ተገፍትረን ሳንወድ በግድ በተለያየ ቦታ የመከራ ቁና እየሰፈርን የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ለመታደግ እጅግ የተቀነባበረና አንድ ወጥ ዘመቻ በስደተኞች ዙሪያ የማድረጉ ተልእኮ በታዋቂ ኢትዮጵያውያን ጥረትና መሉ ፈቃደኛነት እራሱን የቻለ ግብረ ኃይል በመላው አለም ወገንን የመታደግ ዘመቻ ነገ ዛሬ ሳይባል በተለይ ጉዳዩ የሚመለከተው UNHCR የተባለን ተቋምና ሌሎች የግብረ ሰናይ ድርጅቶችን በማስተባበር በተለያየ የአለም ክፍል በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ ከአገር ቤት ባልተናነሰ መጠን የሚዘንብብንን የመከራ ዝናብ እንዲያባራልን ሁሉም አገርና ወገን ወዳድ የሆነ ግለሰብም ሆነ አንጋፋ የፖለቲካ ድርጅቶች ፖለቲካው ላይ ብቻ የሚያሰሙንት እሰጥ አገባ እንደተጠበቀ  ሆኖ የወገኖቻቸውን ሰቆቃ ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ የማሰማት ግዴታ ይጠበቅባቸዋል። በዚፍ ዘርፍ አዲስ መርሐ ግብር መንደፍ ካልቻሉ እንመራዋለን የሚሉት ፖለቲካ ያለ ህዝብ ድጋፍ ውሀ ስለማይቋጥር አዲስ የአሰራር ስልት በአፋጣኛ ሊፈጥሩ ሁኔታዎች ያስገድዳሉ። ይህንንም የወገን የድረሱልኝ ጥሪ ምላሽ ለማስገኘት ሊተባበሩ ይገባል የሚል እምነት አለኝ።

የዚህ ፅሑፍ ማሳረጊያ ለማድረግ የምሻው በመላው አለም የምንገኝ ኢትዮጵያውያን የተነጠቅነውን በአገራችን የመኖር ዋስትና ዳግመኛ እንጎናፀፈው ዘንድ ከምንጊዜውም ይበልጥ ለነፃነታችን መመለስ ባለን አጋጣሚ ሁሉ በመታገዝ ፀረ ወያኔ ትግላችንን ማጎልበትና ከመበታተን ወደ አንድነት የምናመራበትን አማራጭ በማጎልበት ለአገራችን ምድር እንበቃ ዘንድ በአንድነት በያለንበት ለወሳኝ ትግልና ድል እንነሳ።

ቸር ይግጠመን

ሳሙኤል /ከእስራኤል/

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Alida says

    November 15, 2012 08:09 pm at 8:09 pm

    Dnt blame israel for ethiopian problem . U must understand that israel is very small country dnt have enough place even for its own citizen and ethiopians are all overe the place and i dnt think king solomon wary about ethiopia .the lady saba went there by her own and slept with him she is not maried with him

    Reply
  2. jj says

    November 16, 2012 12:00 pm at 12:00 pm

    what a crap article.everyone think israel is best friend of ethiopia that is bullshit.right now ethiopia have more trade with arab countries than israel.when we ethiopians learn and stand up for our nation advantage.we should be like other nation ,keep our interest first.israel glory is for the jews not ethiopians.our refuges must be treat humanly according to united nation cord.israel is well known not respecting UN cord.you dont detain refugees indefinate,i dont ask to give them resident permit but atleast let them apply refugee status with UN.there is much better countries which can give them settlment.when they migrate to ethiopia long time ago we dont detain them prehapes freedom which never enjoy in their life.they should known better what goes around, come around.

    Reply
  3. Basha Ashebir says

    November 17, 2012 02:24 pm at 2:24 pm

    Hi Mr. Samuel ! I totally understand your point. You need some help for the imprisoned migrants, yeah! But don’t mix up things to justify your case. All your arguments are irrelevant to support your message. BTW, ኦሪት ዘፍጥረት 15 – 15 tells nothing like what you said it refers to. Second, you said “…እምነት በምንመስላቸው ወገኖቻችን መታሰራችን አስገራሚም አሳዛኝም ክስተት ነው ብዬ አምናለሁ።” That is ridiculous man! Since when did the Israelites become Christians? I don’t know what kind of Bible you are reading from! But if we both are reading the same Bible, go and read Mt. 27- 25. It says “All the people answered, ‘His blood be on us and on our children! Then he released for them Barab’bas, and having scourged Jesus, delivered him to be crucified.” You see… these people were murderers and still are !! They don’t have a heart for outsiders. See what they are doing to their Palestinian brothers. We are not any closer to them than the Palestinians. The fact that Ethiopian Christians refer to Israel is for the place not for the people.

    Reply
  4. Yasebnew Ayekrem says

    November 18, 2012 01:28 am at 1:28 am

    Criticizing Israelis is correct as they should not forget very quickly their suffering and humiliation in Egypt and under Nazi Germany. In my opinion, they must be defenders of human rights and protectors of all persecuted refugees who seek shelter in Israel. unfortunately, the fact is the opposite and many Ethiopians are suffering in their prisons. The person before me has said that Ethiopia has more trade with the Arabs than Israel and Ethiopia has to strength her relation with Arabs. But doing more trade is not a sign of friendship and good relation. It should not be forgotten that it is Middle East Arabs who are beating, torturing, raping, humiliating and killing Ethiopian maids as if Ethiopians are born for suffering and brutal killing. Last but not least, I would like to appreciate the writer of the article.

    Reply
  5. GETACHEW REDA says

    November 19, 2012 12:16 am at 12:16 am

    አይሁድ ማለት፤የጀርመን ናዚ ማለት ነው። አይሁድ ማለት የክርስትያኖችን እየሱስ ክርስቶስ ጠላት ማለት ነው። ከእስራኤሎች የምትጠብቁ የተረት ተረት አሞጋሾች ዝዮኒዝምን (ናዚኢዝምን) ማሞገስ ማለት ስለሆነ ካሁኑኑ ቅዠታችሁን አቁሙ። በቤተ እስራል ስም “ጥቁር አይሁድ” እያሉ ከእስራሎች ጋር የሚያገናኘን ምንም ደም ሳይኖረን ወያኔ፤ሻዕቢያ፤ደረግ፤ሶአይ ኤ፤ ሞሳድ እና አንዳንድ ባነዳ ህለሰቦች ዘመዶቻችን በዘመናዊ ባርያነት በገንዘብ ሸጠዋቸው ወደ ባርያ ፈንጋይዋ አይሁዳዊቷ እስራል ተሽጠዋል። እዛ ሲደርሱም የባሰ ዘረኝነት ገጥሟቸው ይኸው በዜና እያነበብን ነው። ለዚህ ሁሉ ውረርደት ተጠያቂው ማን ይሆን።

    ስለዚህ “አስሬ” እሳራኤል ቅብጥርጥርዮሽ የምትሉት ተረት ተረት ውዳሴአችሁን ካሁኑኑ አቁሙ። እስራል ማለት ማዚ ማለት ነው። ዘመዶቼ በባርነት ተይዘው በገንዘብ ተሽጠዋል። ለዚህ ደግሞ ጥቂት ሰዎች ካልሆኑ ያወገዙት “ባርነቱን” ሕጋዊ ነው ብለውታል። የእስራል ናዚዎች ሌላ ቀርቶ ወያኔን ተገን አድርገው በሰንደቃላማችን ላይ ኰኮባቸውን ለጥፈውበታል። ስንት ጊዜ ልት ኙ ነው እናንተ ኢትዮጵያያን? እስራኤል ሳትኦን ኢትዮጵያ ናት የአምላክ መናኸርያ እና ክርስቶስ የተወለደባት ምድር። የተቀረው ተረት ነው። ናዚዎች/ዘጽዮናዊያን የገለበጡት ውሸት ታሪካችንን አስመልሱ። እስራልን ማሞገስ ይብቃ; እኛ የኢትዮጵያ ልጆች አንጂ የነዚዎቹ ባርያ ፈንጋዮች የእስረኤል ልጆች አይደለንም። አመሰግናለሁ።ይልቁንስ የተሸጡት ዘመዶቻችን የሚያስመልስ ግብረሃይል ባስቸኳይ አቋቁሙልን፤፡ ከመነሻው “አረብ እና አይሁዶች” የኢትዮጵያ መርዞች ሆነው ነው የተፈጠሩት ናቸው። ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ)

    Reply
  6. Tesfai says

    November 25, 2012 04:13 pm at 4:13 pm

    This is a sad story. The only solution that will bring to an end the suffering and humiliation of our brothers and sisters in the hands of Israelis and Arabs is to build a peaceful and prosperous Ethiopia and Eritrea with ample opportunity to fulfill the aspirations of their citizens.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሤራ አክሻፊው ጎንደር ለሦስተኛ ጊዜ ታሪክ ሠራ May 10, 2023 09:25 am
  • ማር በከፍተኛ ደረጃ የኮንትሮባንድ ሰለባ ሆኗል May 9, 2023 09:24 am
  • ኦነግ በኦሮሚያ ሪፈረንደም እንዲካሄድ መጠየቁ ለሰላም ንግግሩ ዕንቅፋት ሆነ May 4, 2023 01:12 am
  • መረጃ ቲቪ ያጋራው አሳሳች መረጃ May 2, 2023 12:37 pm
  • “ከፈጣሪ በታች መከላከያ የሁላችን ዋስ ጠበቃ ነው፤ ትልቅ ይቅርታ እንጠይቃለን” April 13, 2023 10:19 am
  • በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው April 13, 2023 08:56 am
  • በትህነግ የፈረሰው የአክሱም ኤርፖርት ያስከተለው ዘርፈብዙ ኪሣራ April 13, 2023 03:21 am
  • “የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” ገጥሟቸዋል April 12, 2023 09:23 am
  • ከዕድሜ ልክ እስከ 20 ዓመት ቅጣት ተበይኖባቸዋል April 11, 2023 02:58 pm
  • የኡጋንዳ የክልሎች ሚኒስትር በቆርቆሮ ሌብነት ተጠርጥረው ታሰሩ April 10, 2023 03:59 pm
  • ታከለ ከተነሳ በኋላ የመዐድን ሌቦች እየተያዙ ነው April 6, 2023 02:53 pm
  • አገር ለማተራመስ ያለመ የምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶች ህቡዕ ቡድን ተያዘ April 4, 2023 10:07 am
  • በ10 ዓመት ውስጥ ከ44 ቢሊየን ዶላር በላይ ሸሽቷል April 4, 2023 09:26 am
  • አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም March 29, 2023 09:47 am
  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule