• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

”እናቴ አልዳነችም!…….‏’’

November 11, 2012 10:00 am by Editor 2 Comments

እናት ለልጇ ያላትን ፍቅር መለኪያ፣ ወሰን፣ ድንበርና ግዜ ይኖረው ይሆን?……. በእግዚአብሄር ፈጣሪነትና ፈቃድ፤ ዘጠኝ ወር በመሀጸኔ ተሸክሜ፣በጭንቅና በጣር አምጨ ወለድኩት። አርባ ቀን ሲሞለው እምነታችን በሚያዘው መሰረት ክርስትና አስነሳሁት። በክርሰትና ስሙ ኅይለማርያም ብዩ ስም አወጣሁለት። ጡቶቸን እያጠባሁ፣ የምችለውን ሁሉ እያደረኩና የማይጠገበውን የእናትነትን ፍቅር እየመገብኩ አሳደኩት። ወደ ዘመናዊ ትምህርት ቤትም ላኩት። ልጀም ለቁምነገር በቃ። ከስልጣን ወደ ስልጣን ተሸጋገረ። ከትልቅ ደራጃም ደረሰ።  የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒሰተርም ተባለ። ኅይለማርያም ደሳለኝ፤ የኔ ልጅ። መቼም የእናት ፍቅርና ስቃይ መሳ-ለመሳ ነው። ትልቅ ደረጃ ላይ መድረሱ የሚያስድስተኝን ያህል፤”ምን ይሆን? ወይስ ምን ይደርስበት ይሆን?….”የሚለው የሌት-ተቀን ሀሳብና ጭንቀቴን እናት ብቻ ነው ሊረዳው የሚችለው። የጭንቀታችን አይነት ይለያይ እንጅ፤ ልጅ ኅይለማርያምም ለ’ኔ ይጨነቃል። ”እናቴ አልዳንሽም!….እጸልይልሻለሁ!…..” እያለ።

የተማረውና ብዙ ያውቃል የምለውን ልጀ የሚለኝ ባይገባኝም፤ ዝም ብየ አልፍው ነበር። እየዋለ እያደረ ሲሄድ ግን ”ጀሮ ለባለቤቱ ባ’ድ ነው!”እንደሚባለው ሆነና ከጉረቤቶቸ ”ልጅ ሃይማኖቱን ከድቶ”፤ ከባህር ማዶ በመጣ አዲስ ሃይማኖት እንደለወጠ ተነገረኝ። ደነገጥኩ። ተጠራጠርኩም። ተቆጣሁም። ተናደድኩም። ተገናኝተን እስካናግረው ድረስ ቀኑ ‘ረዘመብኝ። ለነገሩ እስካገኘው  ሁሌም ቀኑ እንደረዘመብኝ ነበር። ይህ ግን የተለየ ነው። እናም ”ምን ቢቃጠሩ ደረሰ ቀኑ!” ነውና ልጅን አገኝሁት። ነገር ግን ገና ሳየው ቁጣየና ንደቴ ሁሉ ናፍቆቱ አጠፋብኝ። እንዴት አድርጌ ልቆጣውስ? እንዴት በዬ ልናደድስ?… ደስ ሲለው ደስ ብሎኝ፣ የከፋው ሲመስለኝ ከፍቶኝ፣ የራበው ሲመስለኝ እርቦኝ፣ የጠማው ሲመስለኝ ጠምቶኝ፣ ወ’ቶ እስኪመለስ ድረስ ”የሆነ ነገር ይደርስበት ይሆን?’ እያልኩ ፈጣሪን እየተማጸንኩና ለአርባ አራቱ ታቦት እየተሳልኩ፤ መገቢያ በሩን እያየሁ በጭንቀተና በስስት ባሳደኩት ልጀ ለምናደድና ለመቆጣት የእናትነት ልቤ እንዴት ይፍቀድልኝ?። አሁን እነዲህ ትልቅ ሰው፣ ባለስለጣንና ባለ ሀብት ሆኖ እንኳ’ በልቶ የሚጠግብ፣ ለበሶ የሚያጌጥና ወ’ቶ በሰላም የሚመለስ ይመስለኝም።

የቤተሰብ ጉዳይ አንስተን ብዙ ስንጫዋውት ከቆየን በኋላ ግን፤ ስለሰማሁት ነገር ስፈራ ስቸር አነሳሁበት።

”ልጅ!… ለመሆኑ የምሰማው ነገር እውነት ነው?”

 “ምን ነገር ሰምተሽ ነው?’’

”ጠፍቶህ ነው?…ሀገሩ ሁሉ ስለ አንተ አይደለም እንዴ ሲያወራ የከረመው። መቼም አሮጊት እናት ምን ታመጣለች ብለህ ነው? ለነገሩማ እኔ ባይገባኝ እንጅ አንተማ ልትነግረኝ ሞክረህ ነበር።”

ሳላስበው እምባዬ በጉንጮቸ ላይ መፍሰስ ጅመረ። ልጀ በድንጋጤ ” ምነው በደህናሽ ነው?” አለና አቅፎ ሊያባብለኝና ምክንያቴን ለማወቅ ተጠጋኝ።

”ለመሆኑ ልጀ..” አልኩ ለቅሶየን ለመግታት እየሞከርኩ። ” ለመሆኑ…ሃይማኖታችን  ከድተህ፣ ሌላ ሃማይኖት መከተል ጀምረሀል የሚባለው እውነት ነው?”

እንደማስቅ አለና፤ መሀረም ከኪሱ አው’ቶ እምባዬን እየጠረገ፤  እኔ ወይም ሌላው ሰው እንደሚለው ሃይማኖታችን ሳይሆን የከዳ፣ ትክክለኛውን የክርስቶስን መንገድ እንደተቀበለና እኔም ብቀበል ዘላለማዊ ህይወትእንደማገኝ መከረኝ። የ’ኛ ወይም የ’ኔ ሃይማኖት ትክክል እንዳልሆነና ገና ያልዳን መሆናችን ጨምሮ የመጸሀፍ ቅዱስ ቃል “እየጠቀሰ” ሊያስረዳኝ ሞከረ። ”እናቴ አልዳንሽም!….እጸልይልሻለሁ!…..” አለኝ። እኔም ሁሉ ነገር ግልጽ ሆነልኝ። ለግዜውም ቢሆን እምባዬ  መፍሰሱን አቆመ። ልቤ ግን ያለቅስ ነበር።

 በራሴ ሀሳብ ውስጥ ገባሁ። ልጀ እኔን ”አልዳንሽም!” ሲለኝ፤ ስለ እግዚአብሄር እናገራለሁ እያለ ” …..በማንም ሰው ላይ አትፍረዱ!…….” የሚለውን ህያው ቃል ዘነጋው ይሆን? ምን አልባት መጸሀፍ ቅዱሳቸው ከ’ኛ የተለየ ይሆን? ወይስ ፈረንጆች የ’ነሱን እምነት እንድንከተል ሆን ብለው አሳስተው ተርጉመው ልጅንም አሳሳቱብኝ ይሆን?

ልጀ ኀይለማርያም ደሳለኝ፤ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር እንደሚለኝ ከሆነ፤ እሱ የሚከተልውን ሃይማኖት ያልተከተለ ሁሉ ”ያልዳነና የጠፋ ነው።” ታዲያ ይህን ሳስብ ልቤን ሀዘን ተሰማው። በማን እንዳዘንኩ ግን በትክክል አላወኩትም። አእምሮዬ በሀሳብና በጭንቀት ናወዘ። እንድሰማውትና እውነት ከሆነ፤ ልጀ አሁን የሚከተለው ሃይማኖት ከተጀመረ ሶስትና አራት ሞቶ ዓመት ቢሆነው ነው። ታዲያ ከዚህ በፊት የነበረው የሰው ልጅና አሁንም ከ’ሱ እምነት ውጭ የሚከተለው የአምላክ ፍጡር ሁሉ የጠፋና ያልዳነ ነው። ይህ ደግሞ እንዴት ሊሆን ይችላል?

ሃይማኖት የግል ነው። ይህ የሰው ልጅ የተፈጥሮ መብቱ ይመስለኛል። የልጀ ሃይማኖታዊ ግንዛቤ በ’ኔ በእናቱ ”አልዳንሽም!…” ብቻ ብሎ የሚያቆም አይመስለኝም።  ፈረንጆች  እምነትቸውን በዚች ሀገር ለማስፋፍት ስለሚጥሩ፤ ልጀ የያዘውን ስልጣን ከለላ በማድረግ  በሌሎች ዜጎች ላይ ተጽኖ ላማሳድር እንዳይጠቅሙበት ፈራሁ።  ”ያ’ገሩን በሬ ባ’ገሩ ሰርዶ!” አይደል የሚባለው።  ‘’ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ይጋጭብኝ ‘’ይሆን ብዬ  የእናትነት ነፍሴ ተጨነቀች።  ጭንቀቴን ዋጥ አድርጌ ልጅን ቀና ብየ አየሁትና ሁሉንም ባይሆን የተውሰነውን ስሜቴን ልገልጽለት ወሰንኩ።

”እንደ አ’ተ የዚያን ከዚህ አጣቅሸ ማስረዳት ባልችልም ‘የጠፋው በግ’ ማለት አንተ ነህ። ከልጅነትህ ጅምሮ እንድትማር ሌት-ተቀን የደከምኩት እምነትክን አጥብቀህ እንድትይዝ፣ ወገንህን ከድህነት እንድታወጣና ሙያህን ለሀገርህ ህዝብ እንድታስተምር ነበር እንጅ፤ የራስህን እምነት ንቀህና ከድተህ እኔን እናትህን ደግሞ ለማስካድ አልነበረም። መዳን የሚያስፈልግህስ አንተና ያንተ ብጤዎች ናችሁ።”

እምባዬ እንደገና መፍሰስ ጀመረ። የተናገርኩት ልጅን ያስከፈው ይሆን ብዬ ጨነቀኝ። በጥፋተኝነት ስሜት ዓይን-ዓይኑን እያይሁ  መለሳለስ ጀመርኩ።

 ”ዋናው ነገር ለ’ኔ ለእናትህ ኑርልኝ። ደህና ሁንልኝ እንጅ ደስ ያለህን አድርግ።” አልኩት።

እምባዬን እየጠረገ ”ደህንነት ከክርስቶስ ነው!” አለኝ።

የሆነ ነገር ብልጭ አለብኝ ።”እኔ ደህንነት ከድንጋይ ነው አልኩ  እንዴ ? በክርስቶስ ስለማምለክ ደግሞ….”ከ’ኛ ወዲያ….። ” አስቤ የተናገርኩት አይመስለኝም። እናም በእናትና በልጅ መሀ’ል ዝምታ ሰፈነ። የኔ ልብ ግን ማንጎራጎር ጀመረ።……

”ከሁሉ – ሁሉ፣ ጤፍ ታንሳለች

ከጭቃ ወድቃ  ትነሳለች::”…..

እናት ምን ግዜም፣ እናታ‘ለም ነች!

ሀገር ምን ግዜም ፣ ሀገር ነች!

”ስልጡን” ኢትዮጵያዎያኖች…..

ዘመናዊ ”ልሂቃኖች”….

አምላካቸውን  ዘነጉና

ለባእድ አምልኮ ተገዙና፤

ህዝብ–ወገናቸውን ‘ረሱና

ማንነታቸውን ናቁና፤……..

”እኛ ብቻ እናውቃለን”

አጠፋን አንጅ፣ አላለማን

ለያየን አንጅ፣ አላፋቀረን።…….

ተው! ተመከሩ…ተመከሩ!

ከትላንቱ ተማሩ…..ተመራመሩ!

ኢትዮጵያ ግን፤ እጆቿን ወደ እዚአብሄር ትዘረጋለች

እየነጋ እንጅ እየመሸ አይሄድም፣ በጽናት ለቆሙ ለአምላክ ልጆች።

የልቤን እንጉርጉሮ ስጨርስ፤ ልጀን አስተውልኩት። ያልጠበቀው ነበርና ድንጋጤና ሀዘን ፊቱ ላይ አነበብኩ።

“በል አሁን ‘ይቅር በለኝና’ የእናትና የልጅ ወግ እናውጋ።” ስለው ወዲያውኑ እሻታውን አሳየኝ። በውስጡ ግን ”እናቴ አልዳንሽም!… አጸልይልሻለሁ!…” የሚል መሰልኝ። በእርግጥ የኔም መንፈስ  “የጠፋው በግ!… የጠፋው   ልጅሽ!……”  እያለኝ ነበር።

ለማንኛውም አስተያየት፡ e-mail: philiposmw@gmail.com

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions

Reader Interactions

Comments

  1. Eyob says

    November 13, 2012 12:55 pm at 12:55 pm

    እጅህ ይባረክ ወንድም ፊሊጶስ

    አውሮፓዊያን ክርስትናን፣እስልምናን ፣የአይሁድ አምልኮን ሳያውቁት
    አገራችን ኢትዮጵያ ግን ሶስቱንም መሰረታዊ አምልኮዎች አስተናግዳለች።
    የነ አቶ ኃ/ማሪያም ሃዋርያት(ኢየሱስ ብቻዎች)አምልኮንም ጨምሮ አሁን
    ሕገ – መንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት ዕምነት የግል ነው።የሚደንቀው ግን
    ልጅ ለእናትዋ ምጥ አስተማረቻት እንደተባለው ተረት ዕምነት ፈረንጅ
    አገር አገልግሎት ዘመኑ አልቆ በተተወበት ዘመን ለእኛ መጥነው ዳኝና
    ተኮናኝ፣ፀዳቂና በቃይ ሲለዩልን ይስደምማል።አቶ ኃ/ማሪያም ምንም
    ማመን መብቱ ነው ስልጣኑን ተገን አድርጎ ግን የሚሰጣቸው ቃለ-ምልልሶች
    በማር የተለወሱ መርዞች ናቸው።””የኢሕአዴግ አሰራር እና የኔ ዕምነት አንድ
    ነው” ብሎናል።ፈጣሪንና ሃያ አንድ አመት ያልሞላውን ገዳይ ፓርቲ ደርቦ
    የሚያምን ግለሰብ መሆኑንም በአደባባይ ነግሮናል።ስብሃት ነጋ ያለውን
    ከአማራና ኦርቶዶክስ ስልጣንን አወጣናት ነጠላ ዜማ አኳያ ስናየው
    ተጠንቀቁ የሚያስብል ነው።ኦርቶዶክስ ዕምነት የአገራችን መሰረት ናትና!
    መሰረት የሌለው ቤት አይቆምም።የትናውም አምልኮ ሌላውን ማንቋሸሽ
    የለበትም።ጥያቄ አለኝ በጠቅላዩ ላይ ከመነኮሳት ደብሮች እስከ ሰላማዊ
    ሙስሊሞች እስራት ጀርባ ሌላ ነገር አለ ጊዜ የማይፈታው የለምና ሁሉን
    ያሳየናል።
    እስከዛው ግን አቶ ኃ/ማሪያም ሆይ የአምልኮ ዲስኩርዎን ቤትዎት ለልጆችዎ
    ወይ የዕምነት ቦታ ያስተምሩት ለእኛ ፍትሕና ሚዛናዊ ዳኝነትን ይስጡን።
    አዳኝና ኮናኝ ፈጣሪ እንጂ ግብረሰዶምነትን የሚፈቅደው፣ሴት ጳጳስ የሚሾም
    የእርስዎ የነጭ አምልኮ አይደለምና!

    ኢትዮጵያ ለዘላለሙ ፀንታ ትኖራለች!!!!

    Reply
  2. Yonas says

    November 14, 2012 12:44 am at 12:44 am

    A Biased Article and doesn’t reflect the reality !

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am
  • የኦነግ ሸኔ አባላትን ዕድሜ ለማሳጠር የጂፒኤስ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው December 7, 2020 12:38 am
  • የቆሰሉ ወታደሮች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጎበኙ December 6, 2020 11:41 pm
  • “ከዚህ በኋላ ይዘን እንታገላለን እንጂ ሠጥተን አንጠይቅም” ኮሎኔል ደመቀ December 2, 2020 12:24 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule