ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በተደጋጋሚ የተሃድሶን አስፈላጊነት በሚያወጡት ርዕሰአንቀጽ ላይ አስነብበውናል፡፡ ባለፈው ጊዜ “ከፖለቲካ ተሃድሶ በፊት [የእውቀት] ተሃድሶ በአስቸኳይ!!” በሚል ርዕስ የተሃድሶን ጥቅምና አስፈላጊነት አስታውቀውናል፡፡ በቅርቡ ደግሞ “የተሃድሶ ያለህ!!!” በማለት በድጋሚ የሰሚ ያለህ ብለውናል፡፡ እኔም ይህንን በሙሉ ልብ የማምንበትን ሃሳብ በማንሳታቸው ላመሰግናቸው እወዳለሁ፡፡ በዚሁ ርዕስ ዙሪያ “ከአእምሮ ባርነት ነጻ እንውጣ” በሚል ሃሳቤን እንደሚከተለው አቅርቤአለሁ፡፡ ከአእምሮ ባርነት ነጻ እንውጣ የሰውን ልጅ “ሰው” ከሚያሰኙት መካከል ማንነቱን የሚወስኑት የአካላዊ፣ የአእምሯዊና የመንፈሣዊ ኃይላት ውጤት መሆኑ በዋንኛነት ተጠቃሽ ነው፡፡ እነዚህ ዕድገታቸውን በተመጣጠነ መልኩ ካልተጠበቀ የሰው ልጅ “ሰው” ተብሎ ቢጠራና ራሱንም “ሰው ነኝ” እያለ … [Read more...] about ከአእምሮ ባርነት ነጻ እንውጣ!
Opinions
የኔ ሃሳብ
ወርቁ ካዶላ የሚያጌጥበት ሌላ!
ከሁለት ወር በፊት “የለገደንቢ ወርቅ ሽያጭ ድራማ!! ወርቃችን እንዴት አላሙዲ እጅ ገባ?” በሚል ርዕስ ላቀረብነው ጽሁፍ የድረገጻችን የዘወትር ተሳታፊ አሥራደው ከፈረንሣይ “የአላሙዲ ኪስ በወርቅ ሲታጨቅ፤ አዶላ ኑሮ በጭንቅ!” በሚል ርዕስ የመጀመሪያውን ክፍል ጽሁፋቸውን አስነብበውን ነበር፡፡ በዚህ የክፍል ሁለት ጽሁፋቸው ደግሞ ባለፈው ያነሱትን ጉዳይ በመዳሰስ እንደሚከተለው አቅርበውታል፡፡ ወርቁ ካዶላ የሚያጌጥበት ሌላ! በመጀመሪያው ክፍል መጣጥፌ፤ ቡችላው ማነው? ለምንስ ቡችላ ተባለ? በሚል ጥያቄ ነበር የተለየኋችሁ :: የወርቁ ቡችላ በምስሉ የሚያዩትን ይመስላል፤ ቡችላ የተባለበት ምክንያት ተለቅ ያለ የወርቅ ፍንካች በመሆኑ ነው:: እናም: አዶላ ወርቅ ነው፤ አዶላ ማርና ወተት ነው፤ አዶላ የዱር አራዊትና አዕዋፍ በአንድላይ ሆነው የሚዘምሩበት፤ ዛፎች እጅ ለእጅ ተያይዘው … [Read more...] about ወርቁ ካዶላ የሚያጌጥበት ሌላ!
ሉዓላዊነትና መብት
ሶርያ አሮጌ አገር ነው፤ ታሪኩ ረጅም ነው፤ ከሶርያ ጋር ሲወዳደር አሜሪካ ሕጻን ነው፤ ነገር ግን ለብዙ ወራት በሶርያ ውስጥ የሚካሄደውን ጦርነትና በቅርቡ በአሜሪካ የተደረገውን ምርጫ ስንመለከትና ስናነጻጽራቸው፣ የሶርያ ሕዝብ እርስበርሱ ሲጨራረስ አሜሪካኖች በጥቂት ቀናት ውስጥ ሐዝቡ ድምጹን ሰጥቶ ምርጫው ተጠናቅቆ በሰላም የሥልጣን ርክክብ ተደረገ፤ ዕድሜ የመብሰል ምልክት ላይሆን እንደሚችልና ፍሬ-አልባ እንደሚሆን መረዳት እንችላለን፤ ከርሞ ጥጃ እየሆኑ ዕድሜ መቁጠር፤ በሶርያ የሚካሄደው ጦርነት ግን አንድ ሰው፣ በሺር አላሳድ፣ እስቲሞት ድረስ መጋደሉና አገር መፈራረሱ ይቀጥላል፤ ዓለምም፣ የተባበሩት መንግሥታትም፣ የአረብ ማኅበርም ሁሉም ከንፈሩን እየመጠጠ የሶርያን ሕዝብ ስቃይ ያያል፤ የፍልስጥኤማውያንንም ስቃይ እንዲሁ፡፡ ለምን አንዲህ ይሆናል? ምክንያቱ ሉዓላዊነት የሚባል ነገር … [Read more...] about ሉዓላዊነትና መብት
‘Hit the iron when it is hot’
The saying I used as my title here above seems less known in our recent linguistic history. But as we are witnessing the current history of this world, people of different nations other than Ethiopians, even the Burmese, even Libyans and Syrians and Yemenis who had been immersed in untold tyranny for over three and four decades, have been waging a neck and neck struggle for their freedom and among them some have already succeeded while some others are on the way. This happens because they … [Read more...] about ‘Hit the iron when it is hot’
አዲሱ የስልጣን ክፍፍልና አመክንዮው
እንደ መግቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረውን የካቢኒያቸውን ሽግሽግና አዲስ ተሿሚ ሚኒስትሮቻቸውን ትላንት (ህዳር 20፣ 2005 ዓ.ም) በፓርላማ በመገኘት አሹመዋል:: አዲሱ ካቢኔም ሶስት ም/ጠ/ሚኒስትሮች ሲኖሩት የአራት ሚኒስቴሮችን ሽግሽግም ያካተት ነው:: የቀድሞ ሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር ሚኒሰቴር አቶ ጂነዲ ሳዶ ከሃላፊነት በማንሳት በአቶ ሙክታር ከድር ተተክተዋል:: የጤና ጠብቃ እና የንግድ ሚኒስትር ሚኒሰቴር ዲኤታ የነበሩት ዶ/ር ከሰተብርሃን አድማሱና አቶ ከበደ ጫኔ እንደየቅደምተከትል ለሚመሯቸው ተቋሞች ሚኒስቴር ሆነዋል:: የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር ማዕረግ የተሾሙት የሚከተሉት ናቸው:: ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል … [Read more...] about አዲሱ የስልጣን ክፍፍልና አመክንዮው
የእስላም ኢትዮጵያውያን የትግል ስልት
በአለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ እስላም ኢትዮጵያውያን ማካሄድ የጀመሩት ትግል በዓይነቱም፣ በስፋቱም፣ በአስተሳሰቡም፣ በስሜቱም እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ውስጥ ከአገዛዙ ጋር ከተደረጉ ትግሎች በጣም የተለየ ነው፤ በመጀመሪያ ደረጃ ትግሉ ለሃይማኖት ነጻነት ነው፤ ስለዚህም በአገዛዙ በኩል የፖሊቲካ ዓላማና የፖሊቲካ መልክ እየተሰጠው ሲሆን በእስልምና ምእመኖቹ በኩል ግን ትግሉን ከፖሊቲካ የጸዳ ለማድረግ ግሩም የሆነና የተሳካ ጥረት እያደረጉ ነው፤ ሁለተኛ የትግሉ ስልት ፍጹም ሰላማዊ በመሆኑ የአገዛዙን የጉልበት ስልት እያከሸፈ ያጋለጠው ይመስላል፤ አንዱና ዋነኛው የትግሉ ሰላማዊነት መግለጫ በቤተ መስጊድ መወሰኑ ነው፤ ይህ ስልት አዲስ አይደለም፤ በብዙ የአረብ አገሮች የሚጠቀሙበት ነው። ተፋላሚዎቹ ያልተገነዘቡዋቸው አንዳንድ ጉዳዮች ይታዩኛል፤ አንደኛ እስልምና በጎሣ የታጠረ ባለመሆኑ … [Read more...] about የእስላም ኢትዮጵያውያን የትግል ስልት
በጉዲፈቻ ስም የህፃናት የውጭ ንግድ
የጉዲፈቻ ታሪክ በኢትዮጵያ በባህላዊ መንገድ ሲደረግ የቆየ ነው መቼ እንደተጀመረ በእርግጠኝነት ለማወቅ ባይቻልም በ18 ክፍለ ዘመን በኦሮሞ ብሔረሰብ እንደተጀመረ ይታሰባል። ጉዲፈቻ የሚለው ቃል የመጣው ከኦሮሚኛ ቋንቋ ሲሆን ትርጓሜውም ተፈጥሮዓዊ የወላጅነትና የልጅነት የሥጋ ዝምድና ሳይኖር ከሌላ ሰው አብራክ የተወለደን ልጅ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ ጥቅሙን ጠብቆ እንደ አብራክ ክፋይ ልጅ ማሳደግ ማለት ነው። በኢትዮጵያ የጉዲፈቻ ሕግ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1952 ዓ.ም በወጣው የፍትሐብሔር ሕግ ማዕቀፍ ተሰጥቶታል ይህም ሕግ የሕፃኑን መብት የሚያስጠብቅ ሆኖ የተዘጋጀ ነው። የጉዲፈቻ ዓላማ ከውርስ ሥርዓት ጋር በተያያዘ የዘር ሃረግን ለመቀጠል፤ የዝምድና ትስስር ለማጠናከር፤ ፖለቲካዊ ሃይማኖታዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞችን ለማግኝት፤ … ጥቂቶቹ ናቸው። ለምሳሌ በሀገራችንም የተለያዩ ጦርነቶች በጎሳዎች … [Read more...] about በጉዲፈቻ ስም የህፃናት የውጭ ንግድ
Statue of bishop, Abune Petros, to be removed
“My countrymen… do not believe the fascists if they tell you that the patriots are bandits. The patriots are people who yearn for freedom from the terrors of fascism...” (Read more) … [Read more...] about Statue of bishop, Abune Petros, to be removed
የእምነትና የሞራል ግዴታ
በአገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ በመንግስትና በቤተ ክርስቲያን አካባቢ ያሉ ሰዎች ስለየሚያደርጓቸው ተደጋጋሚ በደሎች ዘወትር የሚነገሩትና የሚጻፉት ነገሮች እንደሚያሰለቹ የታወቀ ነገር ነው። በሆንም ቀድሞ በባህላችን ሲደረጉ አስገራሚና አስደንጋጭ የነበሩ ስህተቶች ተደጋግመው በመደረጋቸው እየተለመዱ፤ ስለነሱም በተደጋጋሚ የሚነገሩትና የሚጻፉት አሰልችተውናል። ቢሆንም፤ ሰልችተን ርግፍ አርገን ከተውናቸው፤ ስሀተተ ፈጻሚዎች በስህተታቸው ስለሚቀጥሉና ስህተቶችም የባህል ውርስ ሆኖነው እንዳሸገሩ፤ ስህተተኞችም ከስህተታቸው እንዲገቱ ለማሳሰብ፤ የእምነትና የሞራል ግዴታ በሚል ርእስ ይህችን ጦማር አዘጋጀሁ። (ሙሉው ጽሑፍ እዚህ ላይ ይገኛል) … [Read more...] about የእምነትና የሞራል ግዴታ
“ለትግል እንነሳ”
በዛሬው እለት በ14/11/2012 በእስራኤል አገር በእየሩሳሌም ከተማ ቁጥራቸው ከ10000 እስከ 15000 የሚገመቱ ኢትዮጵያውያን ቤተ እስራኤላውያን በተገኙበት የስግድ በአል በከፍተኛ ድምቀት ተከብሯል። የበአሉ አብይ ትርጉም ኢትዮጵያዊ አይሁዳውያን በኢትዮጵያ በነበሩበት ጊዜ አምላካቸው ቅድስት አገር እየሩሳሌም ያደርሳቸው ዘንድ ተሰባስበው የምኞት ፀሎታቸውን ሲያደርሱ የነበረው በፀሎት ያሰሙት ልመና ፈጣሪ ሰምቷቸው በቅድስት አገር እስራኤል መሰባሰባቸውን ምክንያት በማድረግ በየአመቱ የምስጋና ፀሎት ከተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች በመምጣት ሲያከብሩት አመታት ተቆጥሯል። ሆኖም በተጠቀሰው የበአል አከባበር እለት የኢትዮጵያን መንግስት የሚያወግዝ ባለ 14 ነጥብ የተቃውሞ ሀሳብ የያዘ “ለትግል እንነሳ” በሚል ርእስ በርካታ ወረቀቶች ተበትነው በበአሉ ታዳሚዎች እጅ የደረሱ ሲሆን በፅሁፉ ላይ … [Read more...] about “ለትግል እንነሳ”