• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኢትዮጵያዊያን አሜሪካዊያንና የ2012 ዓመተ ምህረቱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ምርጫ

December 25, 2012 09:53 pm by Editor Leave a Comment

እንደማንኛውም የአሜሪካ ኅብረተሰብ ሁሉ፤ በኢትዮጵያዊ አሜሪካዊነታችን፤ ማንኛውንም ምርጫ ከራሳችን ጥቅም አንፃር መመልከቱ ለሕልውናችን አስፈላጊ ጉዳይ ነው። እናም የ2012 ዓመተ ምህረቱን የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ምርጫ የምንመለከተው፤ ከዚህ ተነስተን ነው።

እኛ ምን ሠራን? ምን ተጠቀምን? ምን ተጎዳን? ምን አገኘን? ምን ቀረብን? ምን ማድረግ ነበረብን? በመጨረሻ ደግሞ፤ ምን ትምህርት ወሰድን? ይህ ነው ለምርጫው ግምጋሜ ጠቅላላ ይዘቱ፤ ከኢትዮጵያዊ አሜሪካዊነታችን አንፃር ሲታይ። የባራክ ኦባማ ከጥቁር ዝርያ መሆኑ ወይንም የሚት ራምኒ ነጭ መሆን ቦታ አልነበረውም። የዴሞክራቲክ ፓርቲው ማቸነፍ ወይንም የሬፑብሊኩ ፓርቲ መቸነፍ፤ ለኛ ትርጉሙ በፓርቲነታቸው ሳይሆን፤ የኛን ጉዳይ በሚመለከት ባላቸው አቁዋም ነው። በአሜሪካን ፓርቲ ስሌት ደግሞ፤ የምንፈልገውን ለማግኘት፤ የሚተማመኑበት የአንድ ፓርቲ ቋሚ ደጋፊ ሆኖ በመገኘት ሳይሆን፤ ጉዳያችንን ሁልጊዜ እያቀረብን በመደራደር ነው። ይህ ደግሞ ለመደራደር የሚያበቃ ድምፅ ሰጪ ነዋሪ ተሰልፎ ሲገኝ ነው።

ከዚህ አኳያ የኛን ሚና ስንመለከተው፤ መኖራችን አንኳ አይታወቅም።

ምን ሠራን? በየቦታው፤ ከተወዳዳሪዎች ጋር የቅርብ ግንኙነት የመሠረቱ ግለሰቦች ተገኝተዋል። ጥሩ ጅምር ነው። ይህ ደግሞ ውጤታማ የሚሆነውና እነኚህ ጅምሮች የሚጠናከሩት፤ በግለሰቦቹ መካከል ባለው መልካም ግንኙነት ሳይሆን፤ ከኛ ወገን ያሉት ታታሪዎች፤ ሊያቀርቧቸው በሚችሉት ድምፅ ሰጪ ነዋሪዎች ቁጥር ሲኖር ነው። ያን ቁጥር ያልያዘች ግለሰብ፤ ያላት ምርጫ፤ በገፍ ገንዘብ ማፍሰስ ይሆናል። ያን ያህል ገንዘብ ለማፍሰስ ያቀደች ካለች፤ የበለጠ ውጤት ሊያስገኝ የሚያስችል ሌላ መንገድ መኖሩን ልጠቁም እወዳለሁ።

ሁለተኛው ጅምር ደግሞ፤ የባራክ ኦባማን የምርጫ አንቀሳቃሽ ክፍል ለመቅረብ የተደረገው ጥረት ነው። ይህ ጥረት በጣም ጥሩና ሊዳብር የሚገባው ጅምር ነው። ያልተዘራ አይታጨርም። ይህ የተፈጥሮ ሕግ ነው። ከሥር ተፈንቅሎ ያልታረሠ ሠርዶ፤ በአረም መልሶ ልብ ከማውለቁ በላይ፤ እህሉን አጫጭቶ ምርት ያሳንሣል። አቋርጭ ፍለጋ ስንሄድ ዋናውን መንገድ ጎድን ትተን፤ መደናበር እንገባለን። በአሜሪካ የፖለቲካ ሂደትም ደግሞ፤ እንደሌላው የተፈጥሮ ሕግ፤ ያልዘሩትን ማጨድ አይቻልም። እንጀራ ስለተፈለገ አይጋገርም። ቡሆ መኖር አለበት። ቡሆው መነሣት አለበት። መቅጠን አለበት። እሳቱ መቆስቆስ አለበት። ምጣዱ መድመቅ አለበት። ከዚያ በኋላ ማፍሰሻውን አንስቶ፣ መጥኖ፣ በጣዱ ላይ መፍሰስ አለበት። ከዚያ በኃላ ነው ሞግዱን ገጥሞ፤ እባክህ እባክህ እያሉ ምጣዱን እንጀራ ለማግኘት አፍጥጦ ማየት ነው። ጥረት ውጤት ያስገኛል። የተጀመረው ግን ጅምር መሆኑን መገንዘብ አለብን። የምንፈልገውን ለማግኘት፤ ጥረቱን ማሳደግ አለብን።

ምን ተጠቀምን? ምን ሠርተን? በልጅነቴ፤ በእንግሊዘኛ ቋንቋ “ ‘success’ ከ ‘work’ በፊት የሚመጣው፤ በመዝገብ ቃላት ውስጥ ብቻ ነው።” የሚል መምህሬ ሲናገር አስታውሳለሁ። ከዚህ ተነስቼ፤ ጥቅም አላገኘንም እላለሁ። ትልቅ ትምህርት ግን አግኝተናል እላለሁ፤ ተሣትፏችንን ማሳደግ እንዳለብን። ይህ በኢትዮጵያዊ አሜሪካዊነት መራመድ ያለበት ግዴታ ነው። እዚህ ሀገር እስከኖርን ድረስ፤ በዚህ ሀገር ፖለቲካ በንቁ መሣተፉ፤ ለግለሰብም ሆነ ለኢትዮጵያዊ አሜሪካዊያኖች በአንድነት፤ አስፈላጊ ጉዳይ ነው። የተሰባሰብ ክፍል አድማጭ ያገኛል። የ2012 ምርጫ ትልቁ መልዕክት፤ የኅብረተሰብ ስብስቦች አቸናፊነትን እንዳገኙ ነው።

ምን ተጎዳን? በጣም ተጎዳን እንጂ! ሱዛን ራይስ ከመሬት ተነስታ አይደለም እንዲያ የተናገረች። ከጀርባዋ የተኮተኮተ ግንኙነትና የዳበረ ስምምነት ተደርድሯል። ኦባማ የቡሽን የኢትዮጵያ መመሪያ አንድም ሳይቀይር የገፋው፤ የሚያየው ሌላ አማራጭ ስላልቀረበለት ነው። ይልቁንም የወያኔ መንግሥት አባሎቹን ሰግስጎ በማስገባት፤ የኦባማን ጀሮ አግኝቷል። አሁንም ካለንበት ፈቀቅ አላልንም። ይልቁንም ወያኔ የእምነት ቦታዎችን ማመስ፤ የኅብረተሰብ ማህበራትን (የአገልግሎትና የስፖርት ማህበራትን) መበጥበጥና ባለንበት መንደር መጥቶ መጨፈር ይዟል። እናም ተጎዳን ማለት እንችላለን።

ምን አገኘን? ምንም። አሁንም ተመልሰን የምንመለከተው፤ ምን ፈልገን ነበር? ምን ጥረት አደረግን? የሚሉትን ስለሆነ፤ ምንም አላገኘንም።

ምን ቀረብን? ብዙ እንጂ። ከተመራጮቹ ጋር መመሥረት ያለብንን ዝምድና ሳናደርግ ቀረን። አጀንዳችንን የሚጨብጡልን ሳንመለምል ቀረን። ከሁሉ በላይ ደግሞ፤ ይኼን አጋጣሚና ይኼን አጀንዳ በመጠቀም፤ በአሜሪካ የምንኖር ኢትዮጵያዊያን መሰባሰብ ስንችል፤ በከንቱ አሳለፍነው።

ምን ማድረግ ነበረብን? ጠንክረን መገኘት ነበረብን። ጥንካሬ ማለት፤ የተሣትፎ ቁጥራችንን ማሳደግ ማለት ነው። በዋናነት በኢትዮጵያ ውስጥ ሊኖር ለምንፈልገው የፖለቲካ ሥርዓት ለምናደርገው ጥረትና ባጠቃላይም በአሜሪካ ለምናደርገው የፖለቲካ ተፅዕኖ፤ የተሣትፎ ቁጥራችንን ማሳደግ ነበረብን። በትልቁ ከመንጠራራት በፊት፤ በትንሹ በየምንኖርበት አካባቢ፣ በግለሰብና እየተሰባሰብን፤ ተመራጮችን ማነጋገር ነበረብን። ጥረታችንን ከኢትዮጵያ ሕልውና ጋር ማዛመድና የሚጠበቅብንን ማበርከት ነበረብን።

ምን ትምህርት ወሰድን? ማንነታችንን ተረዳን። ድክመታችንን በጉልህና በግልፅ ዐየን። የፖለቲካ ቡድኖችን፤ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪክ ማህበራትን ማንጋጋት፤ ጽሑፍ መደርደርና መለፍለፍ ውጤት እንደማያመጣ ተገነዘብን። የድረ ገፆች ጋጋታ፣ የፓልቶክ ክፍሎች መጠራቀምና የሬዲዮ ማሠራጫዎች መንዛዛት፤ የትም እንዳላደሰን ተረዳን። አንገብጋቢ ለሆነው የሀገራችን ጉዳይ የተሠጠንን አጋጣሚ ሁሉ ልንጠቀምባቸው አለመቻላችንን አወቅን። ማጠቃለያው ደግሞ፤ የበለጠ መሥራት አንዳለብን መምህር ሆነን። ውጤት ያለጥረት ዋጋ እንደሌለው ተምረናል። ቁጥር ወሳኝ ነው። ያልተደራጀ ክፍል ተደማጭነት የለውም።

እንዲያው እስከዛሬ ይዘነው ስንጓዝ እንደነበረው፤ ወያኔን ማውገዝ፣ በየቦታው ወያኔ ይኼን አደረግ ብሎ መጮህ፤ የትም አያደርሰንም። ይኼ የትግል መንገድ እዚህ ላይ አራት ነጥብ ተቀምጦበት፤ አዲስ መንገድ መከፈት አለበት። ከምንቃወመው ሳይሆን ከምንፈልገው የመነጨ የትግል መንገድ መተለም አለብን። ፀረ-ወያኔ መሆን የትግል መንገድ አይደለም። የሕዝብ ወገን መሆን ነው ትግሉ። የሕዝብ ወገን ሆነን፤ ለዚህ ወገናዊነታችን፤ ለውጤቱ እውን መሆን፤ አዲስ መንገድ ተልመን መጓዝ አለብን።

ለወደፊቱም፤ ባንድ በኩል ለራሳችን እዚህ ለምንኖርበት የፖለቲካ ሥርዓት፤ በሌላ በኩል ደግሞ በሀገራችን ላይ አሜሪካ እንድትወስደው በምንፈልገው አቋም ላይ ተፅዕኖ ለማድረግ፤ መደራጀትና አስፈላጊ አካል ሆነን መገኘት አለብን። ብዙ ስለፃፍን፣ ብዙ የፓልቶክ ክፍሎች ስለከፈትን፣ ብዙ ድረገፆች ስላንጋጋን፤ ተደማጭነታችንን አንዲት አንቋ አንገፋውም።

አሜሪካ ተወልደው፤ አመለካከታቸውም ሆነ ተግባራቸው የሀገሩን ባህል የተዋሐደ የሆኑ ወጣት አሜሪካዊ ኢትዮጵያዊያንን መመልመል አለብን። እነሱ ናቸው በአሜሪካ የፖለቲካ ምኅዳር የጎላ ሚና ሊጫወቱ የሚችሉት። እነዚህን ኮልኩለን አሳድገን፤ ባንድ በኩል የኢትዮጵያዊነት በሌላ በኩል የአሜሪካዊነት ምንነትን አቅፈው፤ በአሜሪካ ፖለቲካ፤ ለኢትዮጵያ ውል ያለው ሚና እንዲጫወቱ ማድረግ እንችላለን። የቆየነው እዚህ ካደረሰን ያዘልነው ሸክም መላቀቅ አስቸግሮናል። በየኪሳችን የያዝነው ዘውድ፤ ከዕለት ዕለት በእብሪታችንና እኔ ብቻ ትክክል ነኝ በሚለው ጉራችን እንደቦርጭ እያደገ፤ የእኛኑ ወገብ መልሶ እያጎበጠው ነው።

አንዱ ዓለም ተፈራ (በተለይ ለጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ የተላከ)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm
  • ኦነግ ሸኔ አሸባሪነቱ ሳይነሳለት በሽመልስ የሰላምና የእርቅ ጥሪ “በክብር” ቀረበለት February 17, 2023 12:35 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule