ሰሞኑን ኢህአዴግ በፈለፈላቸው ድርጅቶች ታጅቦ የ"ባንዲራ ቀን" በሚል የመለስን ፈረጀ ብዙ ዝክር ሊደግስ ከወዲያ ወዲህ እያለ ነው። አቶ መለስ “ጨርቅ” ብለው ሲያነሱና ሲጥሉት የነበረውን ያገር መለያ ለፈጠራና ከጀርባው ተንኮል ያዘለ ዓላማቸው ሲሉ ቀኑ እንዲዘከር አድርገዋል፤ የምዕራባውያን ጉዳይ አስፈጻሚ እንደመሆናቸውም የታዘዙትን በሠንደቅ ዓላማው ላይ ጨምረዋል። በዚሁ የ"ባንዲራ ክብር" ሳይሆን በሌላ አህጉራዊ ክስተት ራሳቸው ያሰፉትን ጨርቅ ገልብጠው ባደባባይ ሰቅለውት ነበር። በወቅቱ ራሳቸው ያሰሩትን ባንዲራ አናትና ግርጌ መለየት ባለመቻላቸው ተወግዘውበታል፤ የትግራይን ቢሆን እንዲህ ያደርጉት ነበር ተብሎም ተጠይቋል። ባድመ ስትወረር "ደርግ ኢሰፓ" ተብለው ጎዳና ላይ የተጣሉት የቀድሞው ሰራዊት አባላት ለዳግም ዘመቻ "እናት አገር ጥሪ" ሲተም በገጸ በረከትነት የተሰጠው ያደራ ቃል … [Read more...] about ውርደት! – መለስ ፣ ስብሃት፣ የኢህአዴግ ኤምባሲ ከዚያስ?
Middle Column
በህወሃት “የትግራይ ኩራት ተነክቷል” ባዮች አይለዋል
የሰሞኑ የጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ካቢኔያቸውን "ከኋላ" አስከትለው ከፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ያካሄዱት የፊት ለፊት ንግግር ያስደሰታቸውና ያስኮረፋቸው ክፍሎች አሉ። “በህወሃት መንደር ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ የመወከል ባለጊዜው ህወሃት ነው። ህወሃት የኢትዮጵያ ምልክትና ተምሳሌት ነው” የሚሉት ወገኖች ቀደም ሲል ሲሰማ የነበረውን “የትግሬ ኩራት ተነክቷል” ስሜት በገሃድ ሲያንጸባርቁ ታይቷል። አስገድደው ከሚመሩት ህዝብ ይልቅ ለውጪው ዓለም በመስገድና በማጎብደድ ወደር እንደሌላቸው የሚነገርረላቸው አቶ መለስ ሰሞኑን አቶ ሃይለማርያም ያገኙትን ዕድል አላገኙም። ከታላቋ አሜሪካ መሪ ጋር በግል የፊት ለፊት ወግ አላደረጉም። በተለያዩ መድረኮች ላይ በጅምላ ተገኝተው ከመጨባበጥና ውስን ቃላቶችን ሲለዋወጡ ከመታየቱ ውጪ ያላገኙትን ይህንን ዕድል አቶ ሃይለማርያም ማግኘታቸው … [Read more...] about በህወሃት “የትግራይ ኩራት ተነክቷል” ባዮች አይለዋል
ለህወሃት የማስጠንቀቂያ ደወል!
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር ለህወሃት ሊቀመንበር በቀጥታ ወደ ዕርቅ ሊያመጣ የሚችል ደብዳቤ ላኩ፡፡ በደብዳቤው ለህወሃት ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ለትግራይ ተወላጆች በግልጽ ማስጠንቀቂያ የተሰጠ ሲሆን ህወሃት የፈጸመው ወንጀልም በተወሰነ መልኩ ቀርቧል፡፡ መግለጫው ጥፋትን ዘርዝሮ ወደ እውነተኛና ፍትሃዊ የተሃድሶ ዕርቅ ለመምጣት ነው፡፡ ሙሉቃሉ ከዚህ በታች ይነበባል፡፡ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ግልጽ ደብዳቤ ለህወሃት! “ጊዜ መልኩን ሳይቀይር አሁን ባላችሁ ዕድል ተጠቀሙ! … ቀናነት ነጻ ያወጣችኋል!” አባይ ወልዱ የህወሃት ሊቀመንበር መቀሌ፤ ትግራይ አቶ አባይና መላው የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት፤ ይህንን ደብዳቤ የምጽፍላችሁ ከተለያዩ ኢትዮጵያውያን በተውጣጣው የማኅበራዊ ፍትሕ እንቅስቃሴ ከሚመራው … [Read more...] about ለህወሃት የማስጠንቀቂያ ደወል!
በጎደሬ ወረዳ የዘር ግጭት ተነሳ፤ መከላከያ ገብቷል
በጋምቤላ ዞን በጎደሬ ወረዳ ነጋዴዎችና ሰፋሪዎች ከአካባቢው ተወላጅ የመዠንገር ጎሳ አባላት ጋር ተጋጩ። በግጭቱ ከ17 ሰባት በላይ ሰዎች ተገድለዋል። በግጭቱ የመዠንገር ዞን አስተዳዳሪና የጎደሬ ወረዳ ዳኛ ከነቤተሰቦቻቸው የግጭቱ ሰለባ መሆናቸው ታውቋል። ግጭቱን ለማብረድ የመከላከያ ሠራዊት የገባ ሲሆን፣ የጋምቤላ ክልል ልዩ ኃይል ግጭቱን ለማብረድ በጉዞ ላይ እንዳለ በተሰጠ መመሪያ እንዲመለስ ተደርጓል። ስማቸው እንዳይገለጽ የፈሩ የአካባቢው ነዋሪዎች ለጎልጉል እንደገለጹት በወረዳው በመሬት ባለቤትነትና በመሬት ይገባኛል ጥያቄ ከመሀል አገር በመጡ ሰፋሪዎችና ነጋዴዎች መካከል አለመግባባት ከተፈጠረ ዓመታትን አስቆጥሯል። የፌዴራል አገዛዙም ሆነ የክልሉ አመራሮች ችግሩ ሳይሰፋ ሰላማዊ መፍትሄ ባለማፈላለጋቸው ችግሩ ሊካረር ችሏል። ኢህአዴግ የሚከተለው በዘር ከፋፍሎ የመግዛት ፖሊሲ ለችግሩ … [Read more...] about በጎደሬ ወረዳ የዘር ግጭት ተነሳ፤ መከላከያ ገብቷል
የኢትዮጵያ ህዝብ ፍርድህ ምንድነው?
ከአኝዋክ ጀስቲስ ካውንስል የተሰጠ መግለጫ የህወሃት ፍጹም ታማኝ ነበር። በተለያዩ ሃላፊነቶች በህጻናት፣ በወንድሞቹ፣ በእህቶቹ፣ በእናቶቹ፣ በአባቶቹ አጠቃላይ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በሰራው ወንጀል በህግ ይፈለጋል፣ በህግ የሚፈልጉት ኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆኑ ዓለም አቀፍ የፍትህና የመብት ተሟጋቾች ናቸው። ህወሃትን ክዶ በስደት ከሚገኝበት አገር እጁን እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቦለታል። ይህ "ሰው" በጋምቤላ ክልል የፖሊስና የጸጥታ ሃላፊ የነበረ። የደህንነት አመራር ነበረ። ክልሉን በፕሬዚዳንትነት ለዓመታት የመራ፣ በጅምላ ለተጨፈጨፉት የአኝዋክ ንጹሃን ደም ቀዳሚ ተጠያቂ ነው - ኦሞት ኦባንግ !! ኦሞት በዴሰምበር 13/2003 በጅምላ ጄኖሳይድ ለተፈጸመባቸው ከ424 በላይ የአኝዋክ ንጹሃን ዜጎች፣ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች ስደት፣ መሬታቸው በግፍ ለተነጠቁና በጠመንጃ ለተፈናቀሉ ዜጎች … [Read more...] about የኢትዮጵያ ህዝብ ፍርድህ ምንድነው?
ህወሃት “በህወሃት ወዳጆች” ለእርቅ እንዲነሳሳ እየተሸመገለ ነው!
በኢትዮጵያ ከቀን ወደ ቀን እየከረረ የሚሄደው የጥላቻ ደረጃ ያሳሰባቸው “የህወሃት ወዳጆች” ህወሃት ለእርቅ እንዲነሳሳ የማግባባት ስራ እየሰሩ መሆናቸው ተሰማ። የአቶ መለስና “የህወሃት ወዳጅ” ወይም ቅርብ ናቸው የሚባሉት ራስ መንገሻ ስዩም ጉልህ ሚና ይዘዋል። የጎልጉል የአዲስ አበባ ተባባሪዎች እንደዘገቡት ከሆነ በህወሃት መንደር እርቅ አስፈላጊ እንደሆነ የሚያምኑ ወገኖች በህወሃትና በተቀረው ህዝብ መካከል እየሰፋ የሄደው ጥላቻ መልኩን እንዳይቀይር ከፍተኛ ስጋት አላቸው። በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የሚሰማው ቅሬታና የተቋጠረው ቂም ማየሉ ያሳሰባቸው እኚህ ወገኖች ህወሃት ደጁን ለእርቅ መክፈት እንዳለበት በማሳሰብ መጎትጎታቸው እንጂ የእርቁ መሰረትና እርቁ የሚያካትታቸውን ወገኖች በዝርዝር አልገለጹም። “ኢህአዴግ ናቸው” በሚል የሚታሙት ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅና ፓስተር ዳንኤል … [Read more...] about ህወሃት “በህወሃት ወዳጆች” ለእርቅ እንዲነሳሳ እየተሸመገለ ነው!
በስዊድን የኤርትራ ኤምባሲ አጣብቂኝ ውስጥ ገባ
በስዊድን የኤርትራ ኤምባሲ በስደት አገራቸውን ጥለው የወጡ የኤርትራ ስደተኞችን እንደሚሰልል ተረጋገጠ። የስዊድን መንግሥት በደረሰው ጥቆማና ማስረጃ መሰረት ባደረገው ማጣራት ኤምባሲው በስለላ ስራ ተሰማርቶ ስዊድን ከለላ የሰጠቻቸውን የኤርትራ ተወላጆች አንደሚከታተልና እንደሚሰልል ማስረጃ ተይዞበታል። ተቀማጭነታቸው ስዊድን የሆነ የጎልጉል ተባባሪዎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር በመነጋገር እንዳመለከቱት፣ የስዊድን ዜግነት ያላቸውንና ሻዕቢያን ለማስወገድ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶችን የሚደግፉ፣ አክቲቪስት የሆኑትን የኤርትራ አገዛዝ በኤምባሲው አማካይነት እንደሚስልላቸው የታወቀው በጥቆማ ነው። ውስን ቁጥር ያላቸው በስዊድን የሚኖሩ የኤርትራ ተወላጆች ባቀረቡት ጥቆማ መሰረት የስዊድን መንግሥት ባካሄደው ማጣራት የኤርትራ ኤምባሲ የተከሰሰበትን ተግባር እንደሚፈጽም ተረጋግጧል። የመረጃው … [Read more...] about በስዊድን የኤርትራ ኤምባሲ አጣብቂኝ ውስጥ ገባ
ፑንትላንድና ሶማሌላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የመዋሃጃ ሰነድ አቀረቡ
ራሳቸውን ራስ ገዝ አገር አድርገው በማስተዳደር ላይ ያሉት ሶማሌላንድና ፑንትላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ውህደት ለመፈጸም የሚያስችላቸውን ሰነድ ለአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት (ስቴት ዲፓርትመንት) ማቅረባቸው ተሰማ። ሰነዱ ለእንግሊዝና ለሌሎች የአውሮፓ ሃያል አገራት መቅረቡም ታውቋል። ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ክፍሎች "እንሰጋለን" ሲሉ የውህደት ጥያቄው ሊተገበር የሚገባው እንዳልሆነ አመልክተዋል። ከኢትዮጵያ ጋር ለመዋሃድ ጥያቄ ያቀረቡት ሁለቱ የሶማሌ ጠቅላይ ግዛቶች የተጠቀሰውን ሰነድ ማቅረባቸውን የተናገሩት የጎልጉል ምንጮች፣ የሰነዱን ዝርዝርና ውህደቱ በምን መልኩ ሊከናወን እንደሚችል ዝርዝር መረጃ ለጊዜው ከመስጠት ተቆጥበዋል። ፑንትላንድና ሶማሌላንድ ራሳቸውን ከተበጠበጠችው እናት አገራቸው ነጥለው አገር ማስተዳደር ከጀመሩ ዓመታት ቢያስቆጥሩም እስካሁን ድረስ በአገርነት እውቅና … [Read more...] about ፑንትላንድና ሶማሌላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የመዋሃጃ ሰነድ አቀረቡ
ለነዋሪዎች አማራጭ የለም!
በአዲስ አበባ ያለው የመጸዳጃ ቤት ችግር ከልክ ያለፈና መሆኑን የእንግሊዙ ዘ ጋርዲያን ጋዜጣ ዘገበ። ሐሙስ በወጣው የጋዜጣው ድረገጽ ላይ እንዳስነበበው ከ3 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በሚኖርባት አዲስ አበባ ውስጥ ለሕዝብ መገልገያነት የዋሉት መጸዳጃ ቤቶች 63 ብቻ መሆናቸውን ዘግቧል። አማራጭ ያጡ የከተማዋ ነዋሪዎች ደግሞ ከተማዋ ወደ መጸዳጃ ቤትነት እየተለወጠች መሆኗን በምሬት ገልጸዋል። ጋርዲያን “Wash Ethiopia Movement” የተባለ አገር በቀል ድርጅት ጠቅሶ እንደዘገበው በከተማዋ ከ10 ቤተሰቦች 9ኙ የጉድጓድ መጸዳጃ ቤት እንደሚጠቀሙና መቀመጫ ባለው መጸዳጃ ቤት የሚጠቀሙት ከ25 ቤተሰቦች አንዱ ብቻ መሆኑን ተናግሯል። በዘገባው መሠረት የከተማዋ ባለሥልጣናት የዛሬ ዓመት ይገነባሉ በሚል የ100ሚሊዮን ብር ዕቅድ የተያዘላቸው መጸዳጃ ቤቶች እንዳሉ መናገራቸውን … [Read more...] about ለነዋሪዎች አማራጭ የለም!
አነጋጋሪው የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የፖሊሲ ስልጠና
ተማሪዎችና የፖለቲካ ተቋዋሚ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ፖሊሲ ላይ ያተኮረው ለከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት ተማሪዎች የሚሰጠውሥልጠና ከጥሪው አንስቶ በግዳጅ የሚካሄድ መሆኑን ነው የሚናገሩት የኢትዮጵያ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የሁለት ሳምንታት የፖሊሲ ስልጠና ላይ መሆናቸውን መንግስት አስታውቋል ። ነሐሴ የተጀመረው ይኽው ስልጠና ተማሪዎች በግዳጅ የሚሳተፉበት መሆኑን አንዳንድ ተማሪዎችና ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ይናገራሉ። መንግሥት ግን ይህን ያስተባብላል። ተማሪዎችና የፖለቲካ ተቋዋሚ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ፖሊሲ ላይ ያተኮረው ለከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት ተማሪዎች የሚሰጠውሥልጠና ከጥሪው አንስቶ በግዳጅ የሚካሄድ መሆኑን ነው የሚናገሩት። በተለይ በስልጠናው የማይሳተፉ ተማሪዎች በመጪው አመት የትምህርት እድል እንደማያገኙ ይገልፃሉ ።ከዚህ በተጨማሪ የትምህርት ነጻነትና ፖለቲካዊ … [Read more...] about አነጋጋሪው የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የፖሊሲ ስልጠና










