በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የዓለምአቀፍ ልማት ትምህርት ክፍል ሥር የኢኮኖሚ ጥናት የሚያካሂደው የኦክስፎርድ የድህነትና የሰብዕ ልማት ማዕከል (The Oxford Poverty and Human Development Initiative (OPHI)) ሰሞኑን ባወጣው የ2014 የጥናት መረጃ ደሃ ከሚባሉት አገራት ዝርዝር ኢትዮጵያ ከመጨረሻው ሁለተኛ መሆኗን ገለጸ፡፡ የጥናቱ ዘገባ ኢህአዴግ በየጊዜው ከሚያቀርበው የዕድገት ስሌት ጋር በግልጽ የሚጋጭ መሆኑ ተነገረ፡፡ በዓለማችን በሚገኙ 108 በማደግ ላይ ባሉ አገራት በየጊዜው ጥናት የሚያካሂደው ማዕከል ጥናቱን በሚያካሂድበት ጊዜ 10 መለኪያዎችን እንደ ግብዓት እንደሚጠቀም ይናገራል፡፡ እነዚህም በሦስት ዘርፎች የተጠቃለሉ ናቸው - ትምህርት፣ ጤና እና የኑሮ ሁኔታ፡፡ በተለይ በኑሮ ሁኔታ ሥር ኤሌክትሪክ፣ ጽዳት፣ የሚጠጣ ውሃ፣ የንብረት ባለቤትነት፣ ወዘተ … [Read more...] about ድርብ አኃዝ ዕድገት ወይስ ድርብ ድህነት?
Middle Column
ኦባንግ “ከምርጫው” በፊት ለተቃዋሚዎች “ምርጫ” አቀረቡ
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ በአገር ውስጥ ለሚገኙ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችና አግባብ አላቸው ለሚሏቸው አካላት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ተቀምጠው እንዲመክሩ ማሳሰቢያ ሰጡ፡፡ ኢህአዴግ በውስጥ ችግሩ፣ በውጭ ተጽዕኖ ወይም በፖለቲካው የተፈጥሮ ባህርይ የሚከስምበት ደረጃ መድረሱን ያሳሰበው በ"ጥቁሩ ሰው" ኦባንግ ስምና ፊርማ የተበተነው የአኢጋን ደብዳቤ፤ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ልዩነታቸውን አጥብበው እንዲሠሩ ጠይቋል፡፡ ይህንን ለኢትዮጵያና ለሕዝባቸው ሲሉ መሥራት የማይችሉ ከሆነ ከኢህአዴግ በላይ ተጠያቂ ሊሆኑ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል፡፡ የፖለቲካ ዕርቅ በመጀመሪያ በተቃዋሚዎች ደጅ ሊተገበር እንደሚገባው ያሳሰበው አኢጋን፤ ይህንኑ ዕርቅ መሠረት በማድረግ ወደ ኅብረት እንዲመጡ በደብዳቤው ገልጾዋል፡፡ ወደ ኅብረት ሲመጡ የፖለቲካ ሥልጣን … [Read more...] about ኦባንግ “ከምርጫው” በፊት ለተቃዋሚዎች “ምርጫ” አቀረቡ
የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ጉዳይ ለምን አይቋጭም?
መለስ በሁለቱ አገሮች ድንበር ላይ “የጅራፍ ድምጽ እንኳን አይሰማም” በማለት ሲመጻደቁበት የነበረው የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በ"ወረራ" እና "ወረራን መቀልበስ" በሚል ድራማ ተጀምሮ ከተቋጨ አስራ አምስት ዓመት አልፎታል። ኢህአዴግና ሻዕቢያ ጉዳያቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ ወይም በጡንቻ መቋጨት ያልቻሉበት ምክንያት ለብዙዎች እንቆቅልሽ ሆኖ እስካሁን አለ። ሁለቱም ወገኖች ድንበር ላይ ወታደር አፍስሰው መቀመጣቸውን አስመልከቶ "አውቀው ነው" ከሚለው ውሃ የማይቋጥር አስተያየት ጀምሮ በርካታ ጉዳዮች በገሃድና በሹክሹክታ ሲሰማ ቆይቷል። የጎልጉል የዜና ምንጮች ሰሞኑን ከአዲስ አበባ የላኩት መረጃ ግን በይዘቱ የተለየ ነው። ይህንኑ አዲስ ጉዳይ የሚመለከታቸው ክፍሎች አስተያት እንዲሰጡበት ያደረግነው ሙከራ ባይሳካም ዜናው ለውይይት የሚጋብዝ በመሆኑ አትመነዋል። የድንበር ውዝግቡ አንዲቋጭ … [Read more...] about የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ጉዳይ ለምን አይቋጭም?
አባ ዱላና ከንቲባ ድሪባ የቁም እስረኛ ሆኑ፣ ፓስፖርታቸው ተቀማ
አባ ዱላ ገመዳና የአዲስ አበባ ከንቲባ ድሪባ ኩማ ፓስፖርታቸውን ተነጥቀው የቁም እስረኞች መሆናቸው ከተለያዩ ምንጮች እየወጡ ያሉ መረጃዎች አመልከተዋል። የጎልጉል ምንጮች ግን ኦህዴድ ውስጥ በከፍተኛ አመራሮች ደረጃ እየተካሄደ ያለው ግምገማ ሲጠናቀቅ በርካታ ባለስልጣኖች ክስ እንደሚመሰርትባቸው ተናግረዋል። በቀድሞው የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት አባ ዱላ ገመዳና በአቶ ድሪባ ላይ ይህ ውሳኔ የተላለፈው አገር ጥለው እንዳይወጡ በሚል ነው። ጎልጉል በቅርቡ ካገር መውጣት የማይችሉ ባለሥልጣኖች እንዳሉ ጠቅሶ መዘገቡ ይታወሳል። ውሳኔው የተላለፈው ሰሞኑን የአዲስ አበባን አዲስ ማስተር ፕላን ለመተግበር የኦሮሚያ ክልል ከተሞች መካተታቸው ይፋ መሆኑን ተከትሎ ከተነሳው ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ነው። ከሁለቱ ባለስልጣናት በተጨማሪ ከፍተኛ የክልልና የዞን የኦህዴድ አመራሮችም በደህንነት ቅርብ ክትትል … [Read more...] about አባ ዱላና ከንቲባ ድሪባ የቁም እስረኛ ሆኑ፣ ፓስፖርታቸው ተቀማ
40 – 23 የኢህአዴግ የጎሳና የመጥበብ ሰረገላ ሐዲዱ ላይ ነውን?
ህወሃት በነጻ አውጪ ስም ታግሎ ኢትዮጵያን መግዛት የጀመረበትን 23ኛ ዓመት በዓሉን እያከበረ ነው። ወዳጆቹና መሪዎቹ ባስቀመጡት እቅድ መሰረት ኢትዮጵያን "በመተካካትና በተሃድሶ" ስም ራሱን እያገላበጠ ለመግዛት የቆረጠው ጊዜ በትንሹ 40 ዓመታት እንደሆነ ይታወቃል። አሁን ባለው የሰረገላው ጉዞ ኢህአዴግ ከ40 - 23 ከመቀነሱ ውጪ አሰበበት ስለመድረሱ መገመት የሚያስችል ምልክት የለም። እንደውም ስጋት እንጂ። ሲጀመር "የገበሬ ተሟጋች" ነኝ በማለት ራሱን የአርሶ አደሩ ወኪል አድርጎ የተነሳው ህወሃት፣ ኢህአዴግ ሆኖ አገር መግዛት ሲጀምር ያስቀደመው የብሄር ብሄረሰቦችን የመብት ጥያቄ እንደ ውዳሴ ጸሎት በመደጋገም ነበር። በዚሁ በጎሳ ላይ ተመስርቶ በቋንቋ የተቆለፈው የአገዛዝ ስልት ሲጀመር ማስጠንቀቂያ የሰጡ፣ ለመታገል የሞከሩ፣ የታገሉ፣ ያስተባበሩ፣ ያደራጁ የህወሃት የ40 ዓመት ጉዞ … [Read more...] about 40 – 23 የኢህአዴግ የጎሳና የመጥበብ ሰረገላ ሐዲዱ ላይ ነውን?
ስብሃት “እርቅን” እንሞክራለን፤ ከባልደረቦቼ ጋር እመክራለሁ አሉ
ባለፈው ሳምንት የጀርመን ድምጽ ሬዲዮ የተቃዋሚ ፓርቲ ወኪሎችንና አቶ ስብሃትን ባንድነት በየተራ አናግሮ ነበር። ከውይይቱ የተለመደ ክርክር በዘለለ አቶ ስብሃት እርቅ አስፈላጊ መሆኑንን ማመናቸው የተለየ ጉዳይ ነበር። እንደ እርሳቸው አነጋገር አሁን የተጀመረውን መልካም የልማት ስራ ለማስቀጠል እርቅ አስፈላጊ ነው። የእርቅን አስፈላጊነት በማመን ከባልደረቦቻቸው ጋር በመምከር የእርቅ ጉባኤ ለማዘጋጀት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል። አቶ ስብሃት “የተቃዋሚ ፓርቲ አለ ብዬ አላምንም” በማለት ተቃዋሚዎችን እንደወትሮው ሁሉ ዘልፈዋል። “መደብ የላቸውም” ሲሉ ተቃዋሚዎችን ጭራሽ እንደ ፓርቲ እንደማይቆጥሯቸው የተናገሩት አቶ ስብሃት ከዘለፋቸው በኋላ ስለ እርቅ አግባብ መናገራቸውን፣ ጠያቂው እሳቸው ባነሱት አዲስ ሃሳብ ላይ በመንተራስ ማረጋገጫ ሲጠይቃቸው “ከጓደኞቼ ጋር መክሬ” በማለት በቅርቡ … [Read more...] about ስብሃት “እርቅን” እንሞክራለን፤ ከባልደረቦቼ ጋር እመክራለሁ አሉ
በኢትዮጵያ የኤርትራ ስደተኞች የትጥቅ ትግሉን ለመቀላቀል ወሰኑ
በሺህ የሚቆጠሩ የኤርትራ ስደተኞች የፕሬዚዳንት ኢሳያስን አስተዳደር በትጥቅ ትግል ለማስወገድ ጠመንጃ ካነሱ ተቃዋሚዎች ጋር ለመቀላቀል መወሰናቸውን ሱዳን ትሪቢውን ገለጸ። ውሳኔው የተላለፈው ኤርትራ ለ23ኛ ዓመት ድል በዓልን ተንተርሶ ነው። ሱዳን ትሪቢውን እንዳለው የኤርትራን ስደተኞች መግለጫ በመጥቀስ እንደዘገበው ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ አገሪቱን በአንድ ፓርቲ “በረግጠህ ግዛው” አስተዳደር ላለፉት 23 ዓመታት ገዝተዋል። ተያይዞም የአስመራው አገዛዝ በአገሪቱ ዴሞክራሲን፣ የሰብአዊ መብትን፣ ነጻነትን ማጎናጸፍ ባለመቻሉ ስርዓቱ በዚህ መቀጠል እንደሌለበት መስማማታቸውን አመልክቷል። "ከነጻነት" ማግስት የኤርትራ ተወላጆች እጣ ፈንታቸው ስደት፣ መሰወር፣ ጭቆና፣ እስር፣ ውርደት፣ ማስፈራራት እንደሆነ በመግለጫቸው ያመለከቱት ስደተኞች፣ "የኤርትራ ምድር እንጂ ህዝቦቿ … [Read more...] about በኢትዮጵያ የኤርትራ ስደተኞች የትጥቅ ትግሉን ለመቀላቀል ወሰኑ
በአባይ ጉዳይ ኃያላኑ በግብጽ ላይ ጫና እየፈጠሩ ነው
ምዕራባውያን ሃያላን አገሮች ግብጽ በአባይ ዙሪያ የድርድር ጠረጴዛ ላይ እንድትቀመጥ ጫና እያደረጉ መሆኑ ተሰማ፡፡ ዜናውን የዘገበው አልአህራም ቃል በቃል ግብጽ ላይ ጫና ተፈጠረ ብሎ ባይጽፍም ከዜናው ለመረዳት እንደተቻለው ግብጽ ላይ ጫና እየተደረገባት ነው፡፡ ሃያላኑ ግብጽ ላይ እያሳደሩት ያለው ጫና መነጋገሪያ ሆኗል፡፡ እንደ ጋዜጣው ዘገባ ያለፈው ቅዳሜ የግብጹ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ከኢትዮጵያ ጋር በአባይ ጉዳይ ለመደራደር አገራቸው ፈቃደኛ መሆኗን ማሳወቃቸውን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ ይህንን መግለጫ ከመስጠታቸው በፊት የግብጹ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር መ/ቤት የውሃ ሃብት ልዩ አስተባባሪ ከሆኑት አሮን ሳልዝበርግ እንዲሁም ከአውሮጳ ኅብረት ልዩ ልዑክ አልክሳንደር ሮንዶስ ጋር ውይይት ማድረጋቸው ታውቋል፡፡ በተለይ የአሜሪካው ተወካይ ሳልዝበርግ ወደ ግብጽ ከመሄዳቸው … [Read more...] about በአባይ ጉዳይ ኃያላኑ በግብጽ ላይ ጫና እየፈጠሩ ነው
ደቡብ ሱዳን – የሰላም ድርድር ወይስ ቁማር?
የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ስምምነቱን የማይፈርሙ ከሆነ ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም ለዓለምአቀፉ የወንጀለኞች ፍርድቤት (ICC) አሳልፈው እንደሚሰጧቸው መግለጻቸውን በጁባ የጎልጉል ምንጭ አስታወቁ፡፡ ሱዳን ትሪቢዩን በበኩሉ ስምምነቱ የማይፈረም ከሆነ እስር እንደሚጠብቃቸው ሃይለማርያም ለሳልቫ ኪር መናገራቸውን ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ አርብ የተፈጸመው የስምምነት ፊርማ ገና ሳይደርቅ ሁለቱም ኃይላት ወደ እርስበርስ ውጊያው ተመልሰው በመግባት እየተካሰሱ ነው፡፡ እጅግ ደም አፋሳሽ በሆነውና ለበርካታ ዜጎች መፈናቀል ምክንያት የሆነው የደቡብ ሱዳን የእርስበርስ ጦርነት ከጥቂት ቀናት በፊት አዲስ አበባ ላይ በፊርማ ሲጸድቅ ብዙ ተስፋ የተጣለበት ነበር፡፡ ሆኖም ስምምነቱ ከተጽዕኖ ባለፈ መልኩ በዕለቱ በፊርማ ካልጸደቀ ሳልቫ ኪርንም ሆነ ሬክ ማቻርን ሃይለማርያም ደሳለኝ ለዓለምአቀፉ … [Read more...] about ደቡብ ሱዳን – የሰላም ድርድር ወይስ ቁማር?
የወያኔ ጥላቻ ፍሬ
ወያኔ ለትግራይ ሕዝብ ሀብትንና ብልጽግናን አመጣ ብለው የሚያምኑ ሰዎች ብዙ ናቸው፤ ወያኔ የሥልጣን ወንበሩ ላይ በመውጣቱ ትግሬዎች ሁሉ አልፎላቸዋል ተብሎ ይታመናል፤ በተለይ በአውሮፓና በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዚህ ላይ የጠነከረ እምነት አላቸው፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ውጭ ብዙ ውይይትም ይሁን ንትርክ ይደረጋል፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ግን የተፈራ ርእስ ነው፤ ውስጥ-ውስጡን እንጂ አደባባይ አይወጣም፤ ይህንን ጉዳይ በኢትዮጵያ ውስጥ አደባባይ ለማውጣት ጊዜው የደረሰ ይመስለኛል፤ አረጋዊ በርሄ፣ ገብረ መድኅን አርአያ፣ አስገደ ገብረ ሥላሴ፣ አብርሃ ደስታ (አሥር ቢሞሉልኝ ደስ ይለኝ ነበር!) እየደጋገሙ ቢያነሡትም ሌሎች በቁም-ነገር የተቀበሉት አይመስልም፤ ሕዝቡ ግን በራሱ መንገድ እየተናገረና ምስክርነቱን እየሰጠ ነው፤ በመቀሌ የተሠራውን የመኳንንት መንደር ሕዝቡ አፓርቴይድ ብሎ … [Read more...] about የወያኔ ጥላቻ ፍሬ










