• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በኢትዮጵያ የኤርትራ ስደተኞች የትጥቅ ትግሉን ለመቀላቀል ወሰኑ

May 23, 2014 02:54 am by Editor 1 Comment

በሺህ የሚቆጠሩ የኤርትራ ስደተኞች የፕሬዚዳንት ኢሳያስን አስተዳደር በትጥቅ ትግል ለማስወገድ ጠመንጃ ካነሱ ተቃዋሚዎች ጋር ለመቀላቀል መወሰናቸውን ሱዳን ትሪቢውን ገለጸ። ውሳኔው የተላለፈው ኤርትራ ለ23ኛ ዓመት ድል በዓልን ተንተርሶ ነው።

ሱዳን ትሪቢውን እንዳለው የኤርትራን ስደተኞች መግለጫ በመጥቀስ እንደዘገበው ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ አገሪቱን በአንድ ፓርቲ “በረግጠህ ግዛው” አስተዳደር ላለፉት 23 ዓመታት ገዝተዋል። ተያይዞም የአስመራው አገዛዝ በአገሪቱ ዴሞክራሲን፣ የሰብአዊ መብትን፣ ነጻነትን ማጎናጸፍ ባለመቻሉ ስርዓቱ በዚህ መቀጠል እንደሌለበት መስማማታቸውን አመልክቷል።

“ከነጻነት” ማግስት የኤርትራ ተወላጆች እጣ ፈንታቸው ስደት፣ መሰወር፣ ጭቆና፣ እስር፣ ውርደት፣ ማስፈራራት እንደሆነ በመግለጫቸው ያመለከቱት ስደተኞች፣ “የኤርትራ ምድር እንጂ ህዝቦቿ ነጻ አልወጡም” ብለዋል። ጨቋኙ የኤርትራ አገዛዝ አሁንም በዜጎቹ ላይ አረመኔያዊ ተግባሩን ስለገፋበት ጊዜው በህብረት ወታደራዊ ርምጃ የሚወሰድበት እንደሆነ ጠቁመዋል።

ሜይ 22፣ 2014 የወጣው የሱዳን ትሪቢውን ዜና ከላይ በተጠቀሱት ምሬቶች ሳቢያ በኮሌጅ የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችም ትግሉን ጠመንጃ በማንሳት እንደሚቀላቀሉ ማረጋገጣቸውን አመልክቷል።

“በዲሞክራሲያዊ መርህ የሚመራ መንግስት በኤርትራ በተአምር ይመሰረታል ብለን መጠበቅ አንፈልግም” ማለታቸውን የጠቆመው ሱዳን ትሪቢውን፤ ባለፉት አስር ኣመታት የኤርትራ የጦር ሰራዊት አባላት፣ የባህር ሃይል፣ ጨምሮ በ100 ሺህዎች የሚቆጠሩ የኤርትራ ተወላጆች ወደ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ጅቡቲና የመን መሰደዳቸውን ዘግቧል።

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን የአዲስ አበባ ተወካይ የሆኑትን ኪሱት ገብረእግዚአብሔርን ጠቅሶ ዜናው እንደ ገለጸው እስከ ሚያዚያ (ኤፕሪል) መጨረሻ ወደ ኢትዮጵያ የተሰደዱት የኤርትራ ተወላጆች 92,460 መሆናቸውን ዘግቧል፡፡

በአማካይ ቁጥራቸው 2000 የሚጠጋ የኤርትራ ዜጎች በየወሩ የኢትዮጵያን ድንበር እየተሻገሩ እንደሚገቡ፣ እነርሱም ከ18 – 50 ዓመት እድሜ ያላቸው ሁሉ እንዲሳተፉ የሚያስገድደውን ብሔራዊ ውትድርና የሚሸሹ መሆናቸውን ያመለከቱት ሃላፊ፣ ስደተኞቹ ከአስገዳጁ የወታደራዊ አገልግሎት ሌላ የፖለቲካ ጭቆና ሽሽት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚያሰድዳቸው ተናግረዋል።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. በለው ! says

    May 25, 2014 12:08 am at 12:08 am

    >>በምሥራቅ አፍሪካ ቀንዱን አሹሎ ጦርነት የሚያሻ ድንቅ ሀገርና ሕዝብ! ግን እኛ በሰው ሀገር ሉዓላዊነት ጣልቃ አንገባም ብለን አልነበር!? ህወአት አቶ ኢሳያስን ራዕይ ሲያስፈፅም ኤርትራ ተቃዋሚ የአቶ መለስን ራዕይ ሊያስፈፅም ነው!?
    **Ethiopia and Ertiria “one-party state which is considered as one of the most repressive regimes in the world.

    **the regimes in Asmara and in Addis Ababa have failed to bring democracy, human rights and freedom to its people and they don’t want to see the regime prolonging its grip on power.

    ***During the past 23 years become the victim of executions, imprisonment, disappearances, harassment and intimidation.(source awramba times bay Tesfa-Alem Tekle)

    ***In Ethiopia alone, there are 92,460 Eritrean refugees at end of April,2014 Kisut Gebregzabiher a United Nations refugee agency (UNHCR) representative in Addis Ababa told Sudan Tribune.Ethiopia had 150,000refugees only in soudi Arabia.

    ***An average of 2,000 Eritreans cross into Ethiopia every month fleeing political repression or to escape military service which is mandatory to all citizens aged between 18 and 50 and can last a lifetime.(what about Ethiopians in four directions fleed the country every day ?)

    ***International human rights organisations say that Eritrea and Ethioia stands amongst world’s top worst human rights and press freedom records. The regimes are also accused of turning the country into a “giant prison”.(kaliti,klinto)Ethiopia bekage!

    >>>welcome to famaily, group, collective ledereship,the same teacher one book many kaders and blood suckers opportunist (elite) abusing innocent and poor people.(ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተቀምጦ መነጋጋር አንድ ቤተ መፃሕፍት ቤት ውስት ውሎ እንደማደር ነው” ያለው የህወአት ሊቅ፣ የኢህአዴግ አዛዥ፣ የብሔር ብሔረሰቦች ፈጣሪ ማን ነበር?

    ***In Ertirea there are up to 10,000 political prisoners languishing in the country’s harsh and secret detention centers, which are sometimes shipping containers.(wow! እሥር ቤቱ ኦሮምኛ ይናገራል ያለው የህወአት ፈላስፋ ማን ነበር!?)
    ***The Eritrean refugees in Ethiopia further called up on those forces of change within the Eritrean(Ethiopian) ruling party, including the army to join them in the struggle to topple the regime so that democratic change is achieved.the two nations will be free. peace love a better life for mutul benefit in 21st centuary.
    **ራሳችን አንቅልፍ ተኝተን ለጎረቤት ኤርትራ፣ ሱዳን፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ሱማልያ እንቅልፍ ያጣነው፣ለራሳችን የሻማና የጧፍ ጉልበት ለእነሱ የኤሌትሪክ ኀይል ሆነን ሕዝባችንን የምናሸብረው ለመሆኑ አሜሪካና አውሮፓውያን ስንት ቢከፍሉን ነው? ሰበር ዜና “ግንቦት ፳ ሺ፳ የአካባቢው አሸባሪና የቀጣናው አተራማሽ አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ የኅያለመለስን ራዕይ አፈፃፀም ተቃውመው ለብሔር ብሄረሰቦች እና በሊዝና በኢንቨስትመንት ሀገሪቷን ለተቀራመቱ(ሕዝቦች) እንዲሁም ከትጥቅ ትግሉ ጀምሮ አሁንም በኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር ላይ ላሉ ለኤርትራውያንና ትውልደ ኤርትራውያን ዕድገትና ብልፅግና ሲባል እራሳቸው ለማስቀጠል በቁጭት ተነሰሳስተው ከዛሬ ጀምሮ የምኒሊክን ቤተመንግስት የራሳቸው አድርገው ተቆጣጥረውታል።ታዘበኝ በለው!!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule