የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ስምምነቱን የማይፈርሙ ከሆነ ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም ለዓለምአቀፉ የወንጀለኞች ፍርድቤት (ICC) አሳልፈው እንደሚሰጧቸው መግለጻቸውን በጁባ የጎልጉል ምንጭ አስታወቁ፡፡ ሱዳን ትሪቢዩን በበኩሉ ስምምነቱ የማይፈረም ከሆነ እስር እንደሚጠብቃቸው ሃይለማርያም ለሳልቫ ኪር መናገራቸውን ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ አርብ የተፈጸመው የስምምነት ፊርማ ገና ሳይደርቅ ሁለቱም ኃይላት ወደ እርስበርስ ውጊያው ተመልሰው በመግባት እየተካሰሱ ነው፡፡
እጅግ ደም አፋሳሽ በሆነውና ለበርካታ ዜጎች መፈናቀል ምክንያት የሆነው የደቡብ ሱዳን የእርስበርስ ጦርነት ከጥቂት ቀናት በፊት አዲስ አበባ ላይ በፊርማ ሲጸድቅ ብዙ ተስፋ የተጣለበት ነበር፡፡ ሆኖም ስምምነቱ ከተጽዕኖ ባለፈ መልኩ በዕለቱ በፊርማ ካልጸደቀ ሳልቫ ኪርንም ሆነ ሬክ ማቻርን ሃይለማርያም ደሳለኝ ለዓለምአቀፉ የወንጀለኞች ፍርድቤት አሳልፈው እንደሚሰጧቸው የተነገራቸው መሆኑን የጎልጉል ምንጭ ከጁባ አስረድተዋል፡፡ ሳልቫ ኪር ወደ ጁባ ከተመለሱ በኋላ ከካቢኔያቸውና ቅርብ አማካሪዎቻቸው ጋር በተነጋገሩ ወቅት በስምምነቱ ወቅት የነበረውን ሁኔታ ባስረዱበት ወቅት መናገራቸውን የመረጃው አቀባይ ለጎልጉል አስታውቀዋል፡፡ ሁኔታው ለደቡብ ሱዳን እጅግ አሳፋሪ ከመሆኑ የተነሳ ደቡብ ሱዳን አምባሳደሯን ከኢትዮጵያ እስከማስወጣት እንዳሳሰባት ጨምሮ ተገልጾዋል፡፡
በበርካታ ወንጀሎች የሚጠየቁት ኪርና ማቻር ማስፈራራሪያውን በቀላሉ እንደማይመለከቱት መገመት የሚቻል ሲሆን በሌላ በኩል ኢህአዴግ ወንጀል በመሥራትና በማሰራት አገር ውስጥ የለመደውን የማጠልሸት ዘዴ በጎረቤት አገሮችም ላይ በመጠቀም የበላይነቱን መግለጹ ስምምነቱን “የሰላም ድርድር ወይስ ቁማር?” ተብሎ እንዲጠየቅ የሚያስገድድ መሆኑን አንዳንድ ወገኖች ያስረዳሉ፡፡
ሱዳን ትሪቢዩን በበኩሉ ሳልቫ ኪርን ጠቅሶ እንደዘገበው ስምምነቱ በማስፈራራትና በተጽዕኖ የተካሄደ መሆኑን ዘግቧል፡፡ “ጠ/ሚ/ሩ ለሬክ ሲነግረው ስምምነቱን ዛሬ ሳትፈርሙ ከዚህ አትወጡም ብሎት ነበር ለእኔ ደግሞ ሰነዱን ካልፈረምክ አስርሃለሁ” በማለት አስፈራርተዋቸው እንደነበር ሳልቫ ኪር መናገራቸውን ዘግቧል፡፡ ሳልቫ ኪር ከሬክ ማቻር ጋር ፊት ለፊት ተገናኝተው ምንም ዓይነት ውይይት ሳያደርጉ ለፊርማ ብቻ መተያየታቸውንም ተናግረዋል፡፡
የሃይለማርያም ደሳለኝ እውነተኛ ባለሥልጣንነትና ተጽዕኖ አድራጊነት የታየበት ይህ ስምምነት በኢህአዴግ ውስጥ በምን ዓይነት መልኩ እንደሚቀጥል የሚያወያይ እንደሆነ አስተያየት ተሰጥቶበታል፡፡ አስተያየቱን ከሰጡ መካከል እንዳሉት “ሃይለማርያም ይህንን ማስፈራሪያ ሲሰጡ በአጠገባቸው የነበሩት የህወሃት ባለሥልጣናት እነማን ይሆኑ በማለት በዓይነ ልቦናዬ ሳስብ ነበር፡፡ እነ በረከት፣ ደብረጽዮን፣ … ሳልኳቸው” የሚሉት አስተያየት ሰጪ ሲቀጥሉ “ጠ/ሚ/ሩ በነካ እጃቸው የሕዝብን ድምጽ የሚያፍኑትን፣ ኦሮሞውን በየቦታው እየገደሉ ደሙን የሚጠጡትን፣ አማራውን ለዘመናት ከኖረበት እያፈናቀሉ መሄጃ ያሳጡትን፣ አኙዋኮችን ያረዱትን፣ ኦጋዴኖችን ያጋዩትን፣ ተናገራችሁ፣ ጻፋችሁ በማለት እስርቤት እስኪጠብ ሃሳቡ የገለጸውን ሁሉ ለስቃይና ስደት የዳረጉትን፣ … ወንጀለኞች እንዲሁ ግፋችሁን ካላቆማችሁ ቃሊቲ ወይም ዝዋይ ወይም … እወረውርሃለሁ ብለው አንዴ እንኳን በማስፈራራት ጠ/ሚ/ር መሆናቸውን ቢያሳዩን ብዬ ተመኘሁ” ብለዋል፡፡
በተጽዕኖና ማስፈራሪያ የተፈረመው የደቡብ ሱዳን ስምምነት ፊርማ ገና ሳደርቅ ሁለቱም ወገኖች ተኩስ አቁሙን ጥሰው ፍልሚያቸውን ቀጥለዋል፡፡ እርስበርስም እየተካሰሱ ይገኛሉ፡፡ እሁድ ዕለት የሳልቫ ኪር ኃይሎች በከባድ መሣሪያ የታገዘ የምድር ጥቃት እንደሰነዘሩባቸው የማቻር ኃይሎች ይናገራሉ፡፡ የኪር መንግሥት በበኩሉ ማቻር ስምምነቱን ላለመፈረም በመፈለግ ተቃውሞ ሲያሰማ የነበረ ነው በማለት ዶ/ር ሬክ ማቻርን ይከስሳሉ፡፡
ማቆሚያ የሌለው የሚመስለውና እስካሁን በሺዎች የሚቀቆጠር ህይወትን የቀጠፈውና ለ1.2 ሚሊዮን ዜጎች መፈናቀል ምክንያት የሆነው ጦርነት ወደ ሰላም የመድረሱ ምኞት እየራቀ የሄደ ይመስላል፡፡ ኢህአዴግ ማስፈራሪያ፣ ዛቻ፣ ቁማር፣ … ቢጠቀምም ህልሙ ቅዠት ሆኖበታል፡፡
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
ፋአድ says
በመሰረቱ የምስራቅ አፍሪካ አገር መሪዎች ከሀገር መውደምና ከሰው ልጅ ህይወት መጥፋት ይልቅ የሚያስጨንቃቸው የያዙትን ስልጣን መለቀቅ ነው
በመሆኑም ሁሉንም ብንል ይቀላል /ኬንያ ብቻ ስተቀር / ስልጣን ለህዝቡ እንዲሆን ሊያደርጉት ይቅርና አያስቡትም
እንደተባለውም ኢህአዴግ አዲስ ፎርሙላ ጀመረ ማለት ነው የሀገር ውስጡ ትግል እየከረረ ሲመጣ ለዓለም ዓቀፍ መንግስታት አፍ ማስያዣ ነው። ቢሆንም የሀገር ውሰጥ ትግል የሚያመጣው ውጤት ታይቶ የኢህአዴግም አንባገነኖችን ፍርዳቸው የሚያገኙ ይሆናሉ
aradaw says
ከሆነ ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም ለዓለምአቀፉ የወንጀለኞች ፍርድቤት (ICC) አሳልፈው እንደሚሰጧቸው መግለጻቸውን በጁባ የጎልጉል ምንጭ አስታወቁ፡፡
How irony is this. Yesterday the TPLF ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም and the Woyane government openly saying that they do not accept ICC and they showed their support to Uhuru Kenyatta and Beshir. Here today the confused ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም is recognizing ICC and willing to hand over ኪርና ማቻር to ICC.
በለው ! says
>>>እንቡሼ ገላ…የፊርማ ገለባ..
ሰላም ነው ብለው ተነፍቶ ጡሩንባ
በልተው ጠጥተው ተዘምሮ ተጨፍሮላቸው
የእንባይ ካብ ጦርነት ላይ መዋላቸው!?
ፊርማ ፈርሞ አገሩ ሲደርስ
ኀይሌን ለማስከፋት መክሰስ !?
እረ በስንቱ እንወቃቀስ?
ስንት አለ የቤታችን ጉድፍ የሚነቀስ!?
…”Kiir immediately denounced the deal, claiming that he was coerced into signing it through threats from the Ethiopian prime minister. “[Ethiopian PM Hailemariam Dessalegn] told me that ‘if you don’t sign this, I will arrest you here’,” !! *** ኀይለመለስ አይልም! አያደርገውም!የነፍስ አባቱ ማን ሆነና..ዘመኑ ሰጥቶ መቀበል እኮ ነው፡፡ እነሱ ካልበሉ ኀይሌ አያገሳም!ለመሆኑ ሰልቫ ኪር ቢታሰር ምን ይሆናል? ኢህአዴግ ዓለም በቃኝ ዘግቶ ኢትዮጵያ በቃችኝ ከፍቷል ጭራሽ ቃሊቲም ሆነ ቂልንጦ ከሲዊዲን ጋዜጠኞች የነጭ ደም በተለይ የደማቅ ጥቁር ደም አሰረች ተብላ ትደነቅ ነበር። ኢህአዴግ በአፍሪካ ከፍተኛ የፖለቲካ ተምሳሌነቱን ለማረጋገጥ በፋውንዴሽኑ ብዙ አህትና ወንድም ፓርቲ መሪዎችና ካድሬ ቤተሰቦች የምርምር ጥናት ማዕከል እየመጡ እንደሚሰለጥኑ ተነግሮን ነበር። ክፍል አንድ፦ቃል ማፍረስ! አህአዴግ ስንት ግዜ ቃሉን አጥፏል?ለምሳሌ፤ የምርጫ ሥርዓት ህጉን ተፈረመና ምን ተገኘ?00 ከተቃዋሚ አጋር..አጃቢና..አዳናቂ..ፓርቲዎች ሆኑ ምን አተረፉ?
**…” Kiir said before a crowd at Juba International Airport. “I said ‘if you arrest me in this good place, I am sure I will get good food. So there will be no need to return to Juba. You will feed me for free here.’”አዎን ምን ጠፍቶ!?እንኳን መጥታችሁልን እቤታችሁ ድረስ አምጥተን እናበላችኋለን አደለምን!? ግን ይህ የቀጠናው ጥልቅ ብዬነታችን እሰከመቼ ነው? “የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች” አሉ። ግን ይህ አስገድዶ መሬት መንጠቅና አስገድዶ ማስፈረም ለመደብን ወይስ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ልማታዊ የሙስና መር ፖለቲካ ባሕል ይሆን!? ኢህአዴግ ለሱማሊያ ያወጣውን የሰው ኀይል ለሱዳን ሰላምና የተቀናቃኝ ፓርቲ ድርድር የከፈለውን መስዋትነት ለምን ለሀገር ውስጥ ‘ተፎካካሪና ተወዳዳሪ’ ፖለቲካ ፓርቲዎች የሰላም ድርድር ላይ ተግቶ መስራት ተሳነው!? ትርፋማነት የለውም ማለት ነው? ለደቡብ ሱዳን መጨነቅ የነበረባቸው የነዳጁ ባለቤቶች አውሮፓውያንና ካናዳውያን መሆን አልነበረባቸውም? ምን አልባት ኢህአዴግ ንብረት ኣስጠባቂ ሆኖ ሥልጣኑን እንዲጠብቁለት መማፀኛ(አጅ መንሻ) ይሆን? ለማናቸውም ሲልቫ ኪር ጎረቤት፣ ወዳጅ፣ ተቃዋሚን ጠባቂ ብቻ ሳይሆን ከባለሥልጣን ቤተሰብ ጋብቻም ነውና ኅይሌ ጠንቀቅ…እየተስተዋለ ይች በፓርላማ የለመደች እጅ ማወናጨፍና ደማቅ ጩኽት ውጭ ትወጣና መግቢያ እንዳይጠፋ ዋ በለው!