መለስ በሁለቱ አገሮች ድንበር ላይ “የጅራፍ ድምጽ እንኳን አይሰማም” በማለት ሲመጻደቁበት የነበረው የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በ”ወረራ” እና “ወረራን መቀልበስ” በሚል ድራማ ተጀምሮ ከተቋጨ አስራ አምስት ዓመት አልፎታል። ኢህአዴግና ሻዕቢያ ጉዳያቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ ወይም በጡንቻ መቋጨት ያልቻሉበት ምክንያት ለብዙዎች እንቆቅልሽ ሆኖ እስካሁን አለ። ሁለቱም ወገኖች ድንበር ላይ ወታደር አፍስሰው መቀመጣቸውን አስመልከቶ “አውቀው ነው” ከሚለው ውሃ የማይቋጥር አስተያየት ጀምሮ በርካታ ጉዳዮች በገሃድና በሹክሹክታ ሲሰማ ቆይቷል።
የጎልጉል የዜና ምንጮች ሰሞኑን ከአዲስ አበባ የላኩት መረጃ ግን በይዘቱ የተለየ ነው። ይህንኑ አዲስ ጉዳይ የሚመለከታቸው ክፍሎች አስተያት እንዲሰጡበት ያደረግነው ሙከራ ባይሳካም ዜናው ለውይይት የሚጋብዝ በመሆኑ አትመነዋል።
የድንበር ውዝግቡ አንዲቋጭ ይፈለጋል?
የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ውዝግብ ጦርነት ከኢትዮጵያ ወገን ብቻ ከ100 ሺህ በላይ ጉዳዩ በውል ያልገባቸው ወገኖች ህይወት የተገበረበት ነው። የአይደር ትምህርት ቤት ህጻናትን ጨምሮ የበርካታ ሰላማዊ ዜጎችንና ህጻናትን ህይወትም ቀጥፎ አልፏል። አቶ መለስ ለዚህ ሁሉ ቀውስ ተጠያቂ ቢሆኑም በድንገት ተስፈንጥረው ፍርድ ቤት ህግ ሳይጠቀስባቸው አልፈዋል። “ታላቁ መሪ” በህይወት እያሉ በኤርትራ ጉዳይ በተፈጠረ አለመግባባት ትግራይ ውስጥ እስከመታገት ቢደርሱም ከጥንቃቄ ጉድለት በአንጋቾቻቸው ፈጥኖ ደራሽነት ተርፈው ተቃዋሚዎቻቸውን “ውህዳን” በማለት በየተራ አራግፈው ብቻቸውን “ውርስና ቅርስ” ለመሆን በቅተዋል።
ከህንፍሽፍሽ፣ የልዩነት ጊዜ ጀምሮ አደባባይ የወጣው የልዩነት መሰረት በወቅቱ ይፋ ሲደርግ ኢትዮጵያውያንን አሳዝኖና አስቆጥቶ እንደነበር በወቅቱ በስፋት የተዘገበበት ጉዳይ ነው። ዛሬም ይህ ወቅት ዳግም እየተመለሰ እንደሆነ እየተሰማ ነው። “የኤርትራን ጉዳይ እንቋጭ” የሚሉ የከረረ አቋም ያላቸው ተነስተዋል። እነዚህ ወገኖች ሁለት አማራጭ በማቅረብ ሃሳባቸው ተግባራዊ ሊሆን እንደሚችል እየወተወቱ ነው።
የመጀመሪያው አሁን ያለው የመከላከያ አቅም የድንበሩን ውዝግብ በሃይል ለመቋጨት አቅም እንዳለው እየታመነ ለምን “ቸልተኛነት ተመረጠ” በሚል በቂ ጡንቻ ስለመገንባቱ አበክረው የሚከራከሩበት አግባብ ነው። ሁለተኛው ደግሞ “የኤርትራን ተቃዋሚዎች አደራጅተናል፤ ለምን እነሱ ወደ ኦፕሬሽን አይገቡም” የሚል እንደሆነ መረጃዎቻችን ያስረዳሉ።
ቸልተኞቹ ምን ይላሉ?
በዚህ ጉዳይ ቸልተኛ የሚባሉት የተለየ ምክንያት ያላቸው፣ ነገር ግን “ጦርነት አያዋጣም” በሚል በገሃድ የሚከራከሩ ወገኖች ናቸው። እነዚህ ውስን የብአዴንና የህወሃት ቁልፍ ሰዎች በትግራይ ድንበር አካባቢ አስተዳደር የሚሰሩትን ጨምሮ የኤርትራ ደም አላቸው። በደህንነትና በጸጥታ ክፍሉ አጠቃላይ መዋቀር ላይ ቁልፍ ቦታ ተጎናጽፈዋል። የመረጃ ምንጮቹ ማብራሪያ እንደሚያመለክተው እነዚህ ወገኖች “ኢሳያስን የክፉ ቀን መጠባበቂያ” ነው የሚሏቸው። ሰዎቹ ኢህአዴግ ላይ አንዳችም አይነት ስጋት እንደማይሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ዋና ዓላማቸው “ከመሃል አገር ወይም ከመካከል ለውጥ ካልተነሳ አርፈህ ተቀመጥ” የሚል ዓይነት መንገድ የሚከተሉ ናቸው።
ሃሳቡን ሲያብራሩ “ጉዳዩ ስትራቴጂክ ነው” በሚል ነው የሚጀምሩት። ኢትዮጵያዊነት ለሚያንገበግባቸው ህወሃቶች የማይገባቸው ይህ “ቁልፍ ስትራቴጂ” ለማመን የሚከብድ መረጃ ነው። እንደ መረጃው ምንጮች ከሆነ “የመሀሉ አገር ለለውጥ ከተነሳ የመጨረሻ መመሸጊያችን ኤርትራ ናት” የሚል ነው፡፡ እነዚህ የተቀላቀለ ደም ያላቸው ክፍሎች የሚያራምዱት “ቁልፍ” የተባለው ስትራቴጂ “የከፋ ቀን ከመጣ ወንድሞቻችን አይጥሉንም” የሚል ነው። ይህም ተግባራዊ የሚሆነው የቁርጥ ቀን ሲመጣ ለኢሳያስ የሚፈልጉትን በማድረግና በመስጠት ሰላም አውርዶ ህወሃት በገነባው ኢኮኖሚ አማካይነት የንግድ ትስስር መፍጠርና መኖር ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ “በማንምና በምንም የማይገሰስ” የንግድ ኤምፓየር በመገንባት ኤርትራን በኢኮኖሚ ድቀት እንድትቀጥል የማድረጉ አካሄድ የ“ቁልፉ” ስትራቴጂ አንደኛው ግብዓት እንደሆነም ይነገራል፡፡
ኢሳያስን “አስልሎ መጣል” በሚለው መርህ ሻዕቢያን መጣል ከተቻለ ኢህአዴግ ያደራጃቸውን ተቃዋሚዎች በመያዝ የሚፈልገውን መንግስት ኤርትራ ላይ የመትከልና ከህወሃት ጋር ተዳቅለው የኖሩት የኤርትራ ደም ያላቸው የኤርትራ ተወላጆችን ወደ ግንባር ማምጣት ነው። በነዚህ ሁለት አማራጭ ሃሳቦች የተተከሉት ከላይ የተጠቀሱት ዓይነት “ለዘብተኞች” ይህንን ሃሳብ ይፋ አውጥተው መከራከርና ማሳመን ስለማይችሉ ጉዳዩ ውስጥ ውስጡን እየተብላላ ወደ ልዩነት እንዳያመራ ስጋት አለ። እነዚህ ስጋት የገባቸው ክፍሎች “ቁልፍ” የሚባለውን ስትራቴጂ “የህወሃት የለዘብተኞችና የእስስት ፖለቲካ” ሲሉ ይጠሩታል።
ከኤርትራና ከኢትዮጵያ የሚንደረደሩ ኃይሎች
ህወሃት/ኢህአዴግና ሻዕቢያ/ኤርትራ አንዱ የሌላውን ተቃዋሚ በይፋ በመደገፍ ሃይል ማደራጀት ከጀመሩ ቆይተዋል። ከሁለቱም ወገን ከፍተኛ የሚባል ሃይል ያላቸው የተቃዋሚ ክፍሎች፣ ድርጅቶች፣ ፓርቲዎች አሏቸው በሚባለው ሃይል ተጠቅመው አንዱ ሌላውን በማጥቃት ነጻ መሬት እስካሁን መያዝ አልቻሉም። ከዚህም ከዚያም ከሚሰሙት መጠነኛ የጦርነት ሪፖርቶች ውጪ ተለቅ ያለ ድል ስለመገኘቱ ከሁሉም ወገን አልተሰማም። ሰፊ ሃይል አለው የሚባለው ደሚትም ሆነ ኤርትራ ላይ መሳሪያ አነሳ የሚባለው የአፋር ቀይ ባህርና ኩናማ ንቅናቄ ስለ ሃይል ግንባታ ከመናገር ውጪ ይህ ነው የሚባል ድል እስካሁን አልጨበጡም።
ምንም እንኳን ጥንቃቄና ማስተዋል የሚጠይቅ ቢሆንም ከኤርትራ የሚንደረደሩት የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሃይሎች፣ ከኢትዮጵያ ይወናጨፋሉ የተባሉት የኤርትራ ተቃዋሚዎች ወደ ተግባር ሳይገቡ ጊዜ መፍጀታቸው “ቁልፍ” የተባለው ስትራቴጂ ሊመረመር የሚገባው እንደሆነ አመላካች እንደሆነ የመረጃው ምንጮች ይጠቁማሉ። የኤርትራ ተቃዋሚዎች አዲስ አበባ ላይ የሽግግር መንግስት አቋቁመው፣ መሪያቸውን ሰይመው፣ ህገ መንግሰት አዘጋጅተው፣ ሽግግር ወቅት መተዳደሪያ አርቅቀው፣ የሃይማኖትና የሲቪክ ተቋማትን አካትተው በዝግጅት ላይ እንዲቀመጡ መደረጉ፣ ምናልባትም በኢህአዴግ በኩል ያለው ዝግጅት “ቸልተኛ” በሚባሉት “እስስት ፖለቲከኞች” ታልሞና ታቅዶ የሚከናወን ስለመሆኑ አመላካች አይመስልም? በኢትዮጵያ ወገን ግን ተቃዋሚዎች “እኔ በጠራሁት ሰልፍ ላይ አትገኝም” እየተባባሉ እርስበርስ እየተቆራቆሱ፣ በገጽ ብዛት ብቻ የሚለያይ ተመሳሳይ ማኒፌስቶና ፕሮግራም ይዘው ትግሉን የርስ በርስ አድርገውታል። ከኢትዮጵያ ውጪ ያሉትም በመቀዳደምና በመጠላለፍ ፖለቲካው ተክነውበት የኢትዮጵያ ነጻነት ያደላደሉትን መደብ የሚያፈርስባቸው ይመስል አትላንቲክን ማቋረጥ አስግቷቸዋል፡፡ ሁሉም “እስስት ፖለቲከኛ” መሆን አልቻሉም። የአብዛኛዎቹ የትግል ሁሉ መጀመሪያና መጨረሻ “የምትታገለውን ዋና ባላንጣ ትተህ ያንተው ቢጤውን በመቃረን ዕድሜህን አርዝም” የሚል ያልተጻፈ የፖለቲካ ፕሮግራም፣ የጸና እምነትና ግብ ያላቸው ይመስላሉ።
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
Azieb SeneMariam says
Tor Am-tta honachu endie? Ye Helm Injerra Malamet Tewu, Yibekal. Let the new generation start having a peaceful life.
Ene says
Azieb SeneMariam, ሰላም አልሽ? good word by itself. But it seems ironic in this context.
Tesfa says
የኤርትራና የኢትዮጵያ ፍትጊያ ዓላማ የለሽ፤ ትርፍ አልባ እንዲሁ ከበሮና ክራር እየተመታ የድሃ ልጅ እሳት ገብቶ ያለቀበት ፍጅት ነበር አሁንም ነው። የወያኔና የሻብያ እብደት ማርከሻ ያጣ ነው። ባድመ ሁለት ጽጉር አልባ ሰዎች ለማበጠሪያ የሚፋተጉባት የፓለቲካ አቲካራ ናት። ድባ የማይበቅልበት ጠፍ መሬት ነው። ሃገርን ቆርሶ ለሱዳንና ለኤርትራ ያስረከበ መንግሥት ነኝ ባይ የድንበር ማካለሉን ዘይቤ ለእድሜ ማራዘሚያ እየተጠቀመበት ነው። የጨነቀው እርጉዝ ያገባል እንዲሉ እንጂ የኤርትራው ነጻነትም የበየደው ነገር የለም። የልጆች ጫዋታ። በህይወት መቀለድ። ትላንትም ዛሬን ሲመስል እንዴት ያሳዝናል። መቆሚያ የሌለው የግፈኞች በትር መቼ ይሆን ከህዝባችን ላይ የሚወርደው? እየሳቁ ማልቀስ ይሉሃል እንደ ኤርትራና ኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ ጥልልፍ የፈጠረው ትራጄዲና ኮሜዲ ግብ የለሽ እሰጣ ገባ ነው። ያተረፈ የለም። የከሰረ ግን በህይወትም ከመቃበር በታችም አሉ። አተረፍን የሚሉትም ለጊዜው ነው። አይበሉትም። በደም የተለወሰ እንጀራ አይጣፍጥምና!
andnet berhane says
በድንበር አከላከል ለመቋጨት ያልተቻለበት ሁኔታ በሁለቱ ማለትም በወያኔና በሻእቢያ ሁለቱም ሕዝቦች ግልጽ ያልሆነ ውስጣዊ ተንኮል በግልጽ እንዳይወራ በድብቅ የሚያደርጉት ግንኙነት ማስተዋል ያስፈልጋል፡ ከመሰረቱ አባትና ልጅ ሆነው በበረሃ ባሉበት ወቅት የተማማሉት ሴራ ቀጣይ ሆኖ ሕዝቦችን አለያይቶና አናቁሮ ኢትዮጵያ የጋራችን ኤርትራ የግላችን ተባብለው ተማምለው ይህን ሁሉ ችግር ጭነውብን ተመልሰው ጠላት ለመምሰል የሚያደርጉት ሸፍጥ ውሃ አይቋጥርም፡ የሆኖ ሆኖ ኢሳያስ ማነው መለሰ (ለገሰ) ብለን ራሳችንን መጠየቅ እና እውነቱን መመርመር ያስፈልጋል በሁለቱም ቡድኖሽች ያመራር አወቃቀር ምንም አይነት ልዩነት የለም በኤርትራ አመራር ከኢሳይስ ጀምሮ የገንዘብ ሚንስትሩ የኢሳያስ አፈቀላጤ የትግራይ ተወላጆች ሲሆኑ የመከላከያ ሚንስትሩ ስብኃት ኤፍሬም ባለቤት የስብሃት ነጋ እህት ነች እንግዲህ ያለውን ትሥርና እቅዳዊ ስሌት ማየት ያስፈልጋል በወያኔ ስልጣን ውስጥ ካሉት ብናይ አባይ ወልዱ ጸጋይ በርሄ በረከት ስምኦን ሕላዌ ዮሴፍ የማነ ኪዳኔ(ጀማይካ) ኤሬትራውያን ናቸው ሌሎችም ስለዚህም ያልተቋጨው በስልጣን በዘረፋ የተሰማሩ ማፍያዎች ሃገሪቱን ድምጥማጣን አጥፍተው ታላቅ ትግራይ ኤርትራ በማለት (ምንፍስቲ ትግራይ ትግርኛ) የሚል ለመመስረት ሕልም (ቅዠት) እንዳላቸው የሚያሳይ ተግባር ስላላቸው የድምበር ውዝግብቡ ቀጣይ እንዲሆን ሁሉቱም ይፈልጋሉ፡ በድንበሩ ያሉት ከዛም አልፈው በአድዋና አዲግራት በባደሜ እስከ ሽራሮ ያሉት ሕዝቦች በጋብቻ የተሳሰሩ የቅርብ ዝምድና አንድ ቤተሰብ በመሆናቸው ድምበሩን እያቋርጣሉ ያልፋሉ በሕዝቡ መካከል ምንም አይነት ቅራኔ እንደሌለ የሚያሳይ ብዙ ምልክቶች አሉ፤ ተቅዋሚዎች ተብለው በአዲስ አበባ ተቀምጠው ሙት ፖለቲካ የሚያካሂዱት የመለሰ የስጋ ዘመድ ሕሩይ ተላባይሩ የህዝብ እውቅና የሌለው በስደት ያሉትን ኤርትራውያንን ለማዳን ያልቻለ የወያኔ አሻጉሊት በተቃዋሚው ምንም አይነት እንቅስቃሤ የሌለው፡ በየአመቱ በኢትዮጵያ ሕዝብ ታክስ ገንዘብ፡ ከየአውሮፓ ከኖርዝ አሜሪካ በመሰባሰብ ፍሬ የሌለው የሽግግር መንግስት በማለት ይጨፍራሉ፡ አጠቃላይ የወያኔ ና የሻእቢያ ጫወታ ቀጣይ ሆኖ እስከውድቀታቸው ይዘልቃል፡ ነገርግን የአንዱ መውደቅ ሳይሆን ሁለቱም መውደቅ እንዳለባቸው ማመን ይኖርብናል፡ ይህንንም ለማድረግ እውነተኛ የሃገርና የወገን ፍቅር ያላቸው ሁሉ፡ በመተባበር ያለውን ቅራኔ ንትርክ በመወያየት መፍታትና አንድ ወጥ ትግል በማድረግ ይህንን ስራአት መገርሰስ ያስፈልጋል፡
me says
The writer must have been away
From home long ago.great deficiency of
Info shows that.
Cyber lion kikik