ተማሪዎችና የፖለቲካ ተቋዋሚ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ፖሊሲ ላይ ያተኮረው ለከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት ተማሪዎች የሚሰጠውሥልጠና ከጥሪው አንስቶ በግዳጅ የሚካሄድ መሆኑን ነው የሚናገሩት የኢትዮጵያ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የሁለት ሳምንታት የፖሊሲ ስልጠና ላይ መሆናቸውን መንግስት አስታውቋል ።
ነሐሴ የተጀመረው ይኽው ስልጠና ተማሪዎች በግዳጅ የሚሳተፉበት መሆኑን አንዳንድ ተማሪዎችና ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ይናገራሉ። መንግሥት ግን ይህን ያስተባብላል።
ተማሪዎችና የፖለቲካ ተቋዋሚ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ፖሊሲ ላይ ያተኮረው ለከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት ተማሪዎች የሚሰጠውሥልጠና ከጥሪው አንስቶ በግዳጅ የሚካሄድ መሆኑን ነው የሚናገሩት። በተለይ በስልጠናው የማይሳተፉ ተማሪዎች በመጪው አመት የትምህርት እድል እንደማያገኙ ይገልፃሉ ።ከዚህ በተጨማሪ የትምህርት ነጻነትና ፖለቲካዊ ሰበካ በመርህ ደረጃ አብረው የማይሄዱ ሆኖ እያለ ተማሪዎችም ይህን አስመልክቶ ቅሬታቸውን እንዳያሰሙ ተቃውሞ እንደገጠማቸው ነው የሚገልፁት። በትምህርት ላይ ሳሉ የኢህአዴግ አባል የሆኑ ተማሪዎች በኩል መመዝገባቸውንና የስልጠና ቅጽ መሙላታቸውን በስልጠናው የሚሳተፉ ተማሪዎች ይናገራሉ። ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ አንድ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ የስልጠናውን አጀንዳዎች ያብራራል።
ካሁን ቀደም ምላሽ ያላገኘው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጥያቄ በቅድሚያ ምላሽ ሊሰጥበት ይገባል የሚል ተቃውሞ መነሳቱን ይኽው የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ተናግሯል። ተማሪው ስልጠና የሚሰጥባቸው አካባቢዎች በፌዴራል ፖሊስ መከበባቸውንና ተማሪዎች ከቅጥር ግቢው መውጣት መከልከላቸውንም ገልጿል። ተማሪው እንዳለው በስልጠናው የሚሳተፉ ተማሪዎች የተሰጣቸውን የስልጠና ሰነድ በማቃጠል ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።
ካልተመዘገቡና ካልተሳተፉ በመጪው አመት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የጀመሩትን ትምህርት ለመቀጠል እንደማይችሉም ጨምረው ተናግረዋል።
ተቃዋሚው የፖለቲካ ፓርቲ ሰማያዊ ፓርቲ ባለፈው ሳምንት ይህን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ በስልጠና አመካኝቶ የራሱን አስተሳሰብና ርዕዮተ ዓለም በተማሪዎች ላይ እየጫነ መሆኑን አስታውቋል። የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ስለሺ ፈይሳ ስልጠናውን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት የትምህርት ተቋማት ከፖለቲካ ጫና ነፃ መሆን እንዳለባቸው ይናገራሉ። እሳቸው እንደሚሉት ከሆነ አገሪቱ ካለችበት አስቸጋሪ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ አኳያ ይህን አይነት ስልጠና ትልቅ ወጪ የሚጠይቅ ስለሆነ ከየትኛው በጀት ተወስዶ እየተካሄደ መሆኑ ግልጽ ስላልሆነ ሃብት ማባከን ነው ።
መንግስት በበኩል ሥልጠናው በግዳጅ የሚስጥ እንዳልሆነና የትምህርት ነጻነትን እንደማይጋፋ ነው ያስታወቀው። በአምቦ፤ ወለጋ፤መዳወላቡና ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲዎች ተቃውሞዎች አሉ ቢባልም አቶ ሬድዋን ሁሴን ግን የፖሊሲ ስልጠናው ያለምንም እንከን እየተካሄደ መሆኑን ይናገራሉ።
በአሁኑ ወቅት በሃገሪቱ ባሉ ከ30 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ከስምንት መቶ ሺ በላይ ተማሪዎች በስልጠናው እንደሚሳተፉ ተገልጿል። (ፎቶ ከፋይል ማህደር)
bini negn says
temariw tmhrtun cherso wede sera sigeba yemiyasfetsmew yezihn ager polici new tadiya gnzabe endinorachew madregu mnu lay new metfonetu,,uof were telan