ኤርትራ የትግራይ አካል ናት የሚል አስተምህሮና የፖለቲካ ዝግጁነት ቅስቀሳ መጀመሩ ተሰማ። የጎልጉል ታማኝ ምንጮች ኤርትራ የትግራይ አካል ስለነበረች እንደገና መልሶ በመቀላቀል ታላቋን የአክሱም መንግስት ለመመሥረት የተያዘው አጀንዳ ተግባራዊ ለማድረግ ይቻል ዘንድ አስፈላጊው ሥራ እየተሰራ መሆኑንንም ጠቁመዋል። ለኢትዮጵያ እንደሆነ የሚጠቀሰው “ትልቅ ነበርን ትልቅ እንሆናለን” የሚለው የህወሃት መፈክር ኤርትራን ከትግራይ በመቀላቀል የአክሱምን “ዳግም ልደት” (ህዳሴ) ለመተግበር የታቀደ ነው ተብሏል፡፡ አጀንዳው ባልታሰበ ወቅት ብቅ ያለው በመሃል አገርና በተለያዩ አካባቢዎች እየተነሳ ያለው ተቃውሞ መበራከቱ ያሳሰባቸው ለሚያነሱት የስጋት ጥያቄ መልስ ለመስጠት ነው። የሻዕቢያን ተቃዋሚዎች በማደራጀት፣ በመደገፍና የስደት ፓርላማ በማቋቋም በህወሃት እየተካሄደ ያለው ሥራ የዚሁ ዕቅድ አካል … [Read more...] about “ኤርትራ የትግራይ ናት”
Middle Column
ጨለማው በረታ!! የትግራይ ተገንጣዮች ወስኑ!!
ወተት ሊገዛ የወጣ ልጅ በድንገት መሃል ግንባሩን በአልሞ ተኳሾች ይመታና ይወድቃል። ግማሹ ይሸሻል። አላስችል ያለው ርዳታ ለመስጠት ይሞክራል። በመካከል እናት የልጇን መውደቅ ትሰማለች። ጨርቋን ጥላ እያለቀሰች አስፋልት መሃል ተዘርሮ የወደቀው ልጇ ላይ ተጠመጠመች። በደም ተጨማልቃ እያነባች ህይወቱን ለመመለስ ፈለገች። ልጅ መሃል ግንባሩን ተወግቶ ነበርና ሕይወቱ አልፋለች። እናት አበደች። “እኔን፣ እኔ ልደፋ … …” አነባች። አስከሬኑን ለመውሰድ ሚኒሊክ ሆስፒታል ተሰለፈች። ብዙዎች በተመሳሳይ አንብተዋል። በርካታ እስካሁንም እያነቡ ያሉ አሉ። ይህ የሆነው 1997 ዓም የህዝብ ድምጽ ከተሰረቀ በኋላ ህዝብ ለምን ድምጼ ተሰረቀ ብሎ ስለጠየቀ ነው። በገዳዮቹና ባስገዳዮቹ ዘንድ ይህ ልጅ “ጸረ ሰላም ኃይል” ነው። ይህንን አጭር መልዕክት ያስታወሱን አንድ የራስ ደስታ ሆስፒታል ሠራተኛ … [Read more...] about ጨለማው በረታ!! የትግራይ ተገንጣዮች ወስኑ!!
በሕዝባዊው ንቅናቄ ኢህአዴግ ሠግቷል
ለጎልጉል የእማኝ ዘጋቢ (ireporter) የሆኑ በላኩልን መረጃ መሠረት በኢትዮጵያ የተለያዩ ቦታዎች የተነሣው ንቅናቄ ወደ ሲቪል ሠራተኞች ዘልቆ እንዳይገባ ስጋት ውስጥ የገባው ኢህአዴግ ሠራተኞችን ማባበልና ማንቃት ጀምሯል፡፡ በተያዘው ዕቅድ መሠረት በአዲስ አበባ በሚገኙ ወረዳዎች ውስጥ በሲቪል ሠራተኝነት የሚታወቁ ዜጎችን ኢህአዴግ በየቦታው መሰብሰብ ጀምሯል፡፡ እማኙ በላኩት መረጃ እንደገለጹት ለሁለት ቀን በሚካሄደው ስብሰባ በየወረዳው ለሚሰበሰቡ ሠራተኞች ቢያንስ ብር 300 አበል በመስጠት የማባበያ ስብሰባው እንደሚካሄድ ገልጸዋል፡፡ በየወረዳው ካለው ሲቪል ሠራተኛ አንጻር ለአበል የታሰበው ብር በሚሊዮን ሊቆጠር እንደሚችል እማኙ ጨምረው አስረድተዋል፡፡ ዋናው አጀንዳ ሲቪል ሠራተኛው እየተካሄደ ባለው ንቅናቄ ተሳታፊ እንዳይሆን፤ እንዳይተባበር፤ ድጋፍ እንዳይሰጥ፤ … ሲሆን … [Read more...] about በሕዝባዊው ንቅናቄ ኢህአዴግ ሠግቷል
ማስጠንቀቂያውን እንስማ፤ ኢትዮጵያ በአደጋ ላይ ናት!
በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን የተማሪዎች ተቃውሞ እንቅስቃሴና የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) ያሰማራው ጦር እየፈጸመ ያለውን ግድያና እየወሰደ ያለውን አሰቃቂ እርምጃ እንዲሁም የተማሪዎቹን እንቅስቃሴ የሕዝብ እንዳይሆን ለራሳቸው ጠባብ አላማ ለመቀልበስ የሚጥሩ ሃይላትን በተመለከተ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መግለጫ አውጥቶዋል - ሙሉው ቃል እንዲህ ይነበባል፡፡ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መግለጫ ታኅሣሥ 1፤2008ዓም አንዲት ኢትዮጵያዊት እናት ስለ ልጇ እንዲህ አለች፡ “ልጄን በጥቅምት ወር ለትምህርት ላኩት በኅዳር ሬሣውን ለቀብር ተቀበልኩ!” ይህች እናት የሁላችንንም ወላጅ እናት የምትወክል ናት፤ ኢትዮጵያን እና በአሁኑ ጊዜ በአገራችን ላይ ያለውን ሁኔታም በግልጽ የምታሳይም ናት፡፡ ሟች ልጇ የሷ ልጅ ብቻ ሳይሆን የሁላችንም ወላጆች … [Read more...] about ማስጠንቀቂያውን እንስማ፤ ኢትዮጵያ በአደጋ ላይ ናት!
ተቃውሞ በዝምታ
* እስካሁን አምስት ሰዎች ሞተዋል ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም እየገዛ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) ጋዜጠኝነት “አሸባሪነት” በመሆኑ መረጃ እንደልብ ባይገኝም ከተለያዩ የማኅበራዊ ገጾች የተገኘው ዜና እንደሚያመለክተው የተማሪዎች ሰላማዊ የዝምታ ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፡፡ እንደሚነገረው ዘገባ ከሆነ ስማቸውና የመኖሪያ ስፍራቸው የአንዳንዶቹም ከነፎቶዋቸው ይፋ የተደረገው መረጃ ላይ እንደሰፈረው የተማሪዎች ንቅናቄ ከተጀመረ እስካሁን የአምስት ወገኖች ህይወት በህወሃት ታጣቂዎች አልፏል፡፡ ዛሬ የተደረገው ተቃውሞ በበርካታ የተለያዩ ከተሞች መቀጠሉ ሲሰማ በእንቅስቃሴው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ጨምሮ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችም እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች እና ነዋሪዎች ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡ በተለይ በአዲ አበባ ዩኒቨርሲቲና በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ … [Read more...] about ተቃውሞ በዝምታ
ፈረንሳይ እስከ 160 የሚሆኑ መስጊዶችን ልትዘጋ ነው!
በመጪው ጥቂት ወራቶች ፈረንሳይ እስከ 160 የሚጠጉ መስጊዶችን ለመዝጋት መወሰኗ ተሰማ፡፡ የአገሪቱ ከፍተኛ ኢማም እንዳሉት በሥራ ላይ በዋለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሠረት ጽንፈኛ አመለካከት የሚያራምዱ የእምነት ቦታዎች መዘጋት አለባቸው፡፡ በኅዳር ወር መጀመሪያ አካባቢ በፓሪስ የተከሰተውን ጥቃት ተከትሎ እስካሁን ጽንፈኛ አቋም አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ ሦስት መስጊዶች መዘጋታቸውን የአገር አቀፍና የአካባቢ ኢማሞች ለመምረጥ ኃላፊነት የተሰጣቸው ኢማም ሃሰን ኤል-አላዊ ለአልጃዚራ መናገራቸው ተዘግቧል፡፡ እርሳቸው እንደሚሉት በቀጣይ ወራቶች በርካታ መስጊዶች እንደሚዘጉ አስረድተዋል፡፡ “ከአገር ውስጥ ሚኒስቴር ጋር በምናደርገው ውይይት እና ይፋ በሆኑት መረጃዎች መሠረት ሕጋዊ ፈቃድ የሌላቸው፣ ጥላቻን የሚሰብኩ፣ ታክፊሪ ንግግር የሚደረግባቸው ከ100 እስከ 160 መስጊዶች ይዘጋሉ” … [Read more...] about ፈረንሳይ እስከ 160 የሚሆኑ መስጊዶችን ልትዘጋ ነው!
ስለ ችጋር
• ችጋር ምንድን ነው? ሰፊ ቦታንና ብዙ ሕዝብን የሚሸፍን፣ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ፣ ምንም የሚላስ የሚቀመስ ጠፍቶ እንስሳት (ሰውንም ጨምሮ) ዕለት በዕለት የራሳቸውን አካል እስኪያልቅ ድረስ "እየበሉ" በመጨረሻም የሚሞቱበት ሁኔታ ነው፤ ረሀብ አካል ሲዳከም አካልን ለመገንባት የሚደረግ ጥሪ ነው፡፡ • ችጋር የሚያጠቃው ማንን ነው? ትልቁና ዋናው የችጋር እንቆቅልሽ የዚህ ጥያቄ መልስ ነው፤ አብዛኛውን ጊዜ ችጋር የሚያጠቃው ከገበያ ጋር የማይገናኙትን ምግብ አምራቾችን ገበሬዎችን፣ በተለይም እያመረቱ ከእጅ ወዳፍ ብቻ የሚኖሩትን ነው፤ እነዚህ ገበሬዎች የገጠሩ ሕዝብ፣ ማለትም የአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ የመጨረሻ ደሀዎች ናቸው፤ ኑሮአቸው ሁልጊዜም በችጋር አፋፍ ላይ ነው፡፡ • ችጋር ከተፈጥሮ ጋር ያለው ግንኙነት እንዴት ነው? ከላይ እንደተባለው በችጋር ላይ የሚወድቁት ገበሬዎች ከገበያ … [Read more...] about ስለ ችጋር
“ገበሬው ነፃነት ካላገኘ ችጋር ሁልጊዜ በኢትዮጵያ ይኖራል” ፕሮፌሰር መስፍን
* “ችጋር የሰው ልጅ እንደ ማገዶ እንጨት ተለብልቦ የሚያልቅበት የውርደት ሞት ነው” ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (Institute of Development Research) ሥር ከ1967 ዓ.ም. ጀምሮ ለ10 ዓመታት ያህል በ102 የኢትዮጵያ አውራጃዎች ላይ ምርምር አድርገው ስለ ድርቅ በእርሳቸው አጠራር (ስለ ችጋር) (Rural vulnerability to famine in Ethiopia 1958-1977) የሚል መጽሐፍ ጽፈዋል። የእንቢልታ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል በዛሬው እትማችን ለበርካታ ዓመታት በድርቅ ጉዳይ ያካሄዱትን የምርምር ሥራ መሠረት አድርገን በወቅታዊው የአገሪቱ የድርቅ ሁኔታ ላይ ከጽዮን ግርማ ጋር ቆይታ አድርገዋል። (ዓርብ መጋቢት 26 ቀን 2000 ዓ.ም) ድርቅን በሚመለከት በርካታ ጥናቶች አድርገዋል። ለምን ያህል ዓመት ነው በጉዳዩ ዙሪያ … [Read more...] about “ገበሬው ነፃነት ካላገኘ ችጋር ሁልጊዜ በኢትዮጵያ ይኖራል” ፕሮፌሰር መስፍን
ከ9ሺህ በላይ ፈላሻ ሙራዎች ወደ እስራኤል ሊጓዙ ነው
ከ25 ዓመታት በላይ ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል ለመጓዝ እየጠበቁ ያሉ በተለየ ፈላሻ ሙራ ተብለው የሚጠሩት ቤተ እስኤላውያን ወደ “ቅድስት አገራቸው” እንዲመጡ የእስራኤል መንግሥት ወሰነ፡፡ እስኤል እንደገቡም የአይሁድ እምነትን በተመለከተ የተሃድሶ ትምህርት እንደሚሰጣቸው ተመልክቷል፡፡ በእስራኤል ያሉ እና ሌሎች ዓለምአቀፋዊ የዜና ምንጮች እንደዘገቡት የጠ/ሚ/ር ቢኒያም ኔታንያሁ መንግሥት ውሳኔውን ያስተላለፈው እሁድ ዕለት በሙሉ ድምጽ ነበር፡፡ ይህ የአሁኑ ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊት የዛሬ ሁለት ዓመት እስራኤል ምንም ዓይነት ዜጋዋ በኢትዮጵያ እንደሌለ ይፋ ነበር፡፡ “ዛሬ ጠቃሚ ውሳኔ አስተላልፈናል” በማለት የተናገሩት ኔታንያሁ ውሳኔው በእስራኤል እየኖሩ ከቤተሰቦቻቸው ለተለያዩት ኢትዮጵያውያን ተስፋ ሰጪና ጠቃሚ እንደሆነ በላኩት መግለጫ አመልክተዋል፡፡ ከዚህ በፊት እስራኤል “የተስፋዋ … [Read more...] about ከ9ሺህ በላይ ፈላሻ ሙራዎች ወደ እስራኤል ሊጓዙ ነው
ለድርቁ አስቸኳይ ብሔራዊ ግብረኃይል ይቋቋም!
* ከአገዛዝ ለውጥ በፊት ችጋር ይቀድማል? * “በአሁኑ ጊዜ ችጋሩ እንደ 1977 ሆኗል!” በኢትዮጵያ ላለፉት ፴ ዓመታት ያለታየ ችጋር ተከስቷል። ድርቁና ረሃቡ ከዚህም በላይ የከፋ ሊሆን እንደሚችል ኢህአዴግን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ተቋማት ይፋ እያደረጉ ነው። “የምግብ ዋስትናን አረጋግጫለሁ” በማለት ሲወተውት የኖረው ህወሃት ተገዶ ያመነው ችጋር ከ፩፱፯፯ ድርቅ በላይ የከፋ እንደሚሆን ስጋት አይሏል። ከዚህ በፊት እንደተከሰቱት ለውጦች ይህኛውም የአገዛዝ ለውጥ ሊያስከትል እንደሚችል ተነገረ። በአስቸኳይ ብሔራዊ ግብረኃይል መቋቋም እንደሚገባ ተገለጸ፡፡ ህወሃት ከድርቅ እና ድርቅን ተከትሎ ከሚገኝ ዕርዳታ ጋር በተያያዘ ካለው አስጸያፊ ተሞክሮ በመነሳት ለጎልጉል አስተያየታቸውን የሰጡ እንደሚሉት ከድርቁ ጋር በተያያዘ ፍትሐዊነት ያሳስባቸዋል፡፡ ሲያብራሩም በከፍተኛ የሙስና እና የአድልዖ … [Read more...] about ለድርቁ አስቸኳይ ብሔራዊ ግብረኃይል ይቋቋም!










