ኤርትራ የትግራይ አካል ናት የሚል አስተምህሮና የፖለቲካ ዝግጁነት ቅስቀሳ መጀመሩ ተሰማ። የጎልጉል ታማኝ ምንጮች ኤርትራ የትግራይ አካል ስለነበረች እንደገና መልሶ በመቀላቀል ታላቋን የአክሱም መንግስት ለመመሥረት የተያዘው አጀንዳ ተግባራዊ ለማድረግ ይቻል ዘንድ አስፈላጊው ሥራ እየተሰራ መሆኑንንም ጠቁመዋል። ለኢትዮጵያ እንደሆነ የሚጠቀሰው “ትልቅ ነበርን ትልቅ እንሆናለን” የሚለው የህወሃት መፈክር ኤርትራን ከትግራይ በመቀላቀል የአክሱምን “ዳግም ልደት” (ህዳሴ) ለመተግበር የታቀደ ነው ተብሏል፡፡
አጀንዳው ባልታሰበ ወቅት ብቅ ያለው በመሃል አገርና በተለያዩ አካባቢዎች እየተነሳ ያለው ተቃውሞ መበራከቱ ያሳሰባቸው ለሚያነሱት የስጋት ጥያቄ መልስ ለመስጠት ነው። የሻዕቢያን ተቃዋሚዎች በማደራጀት፣ በመደገፍና የስደት ፓርላማ በማቋቋም በህወሃት እየተካሄደ ያለው ሥራ የዚሁ ዕቅድ አካል እንደሆነ መረጃውን የሰጡት ክፍሎች አመልክተዋል። ህወሃት ውስጥ ያሉ ኤርትራዊ ደም ያላችው ባለሥልጣኖች የዚህ ዓላማ አካል ናቸው ተብሎ እንደሚገመትም አክለው ይናገራሉ።
ስለ ኤርትራ ከተወላጆቹ በበለጠ በልበሙሉነትና ባለቤትነት መንፈስ በገሃድ የሚሟገቱት የቀድሞው የህወሃት መሪና የነፍስ አባት ስብሃት ነጋ አሁን የሚመሩት የሰላምና የልማት ዓለም አቀፍ ተቋም “የሃገሪቱን ገፅታ ለመገንባት የኢትዮ-ኤርትራን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማድረስ የሚያስችሉ ስራዎችን እያከናወነ” ሲሉ ኢህአዴግ በፓርላማ ስም ለሚመራው የምክርቤት ኮሚቴ መናገራቸውን ሰኔ 5፣2007 የታተመው የኢቲቪ (ኢብኮ) ዘግቧል፡፡ የውጭ መከላከያና ደህንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮቴውም የስብሃትን ዘገባ ካደመጠ በኋላ “ኢንስቲትዩቱ የኢትዮ-ኤርትራ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ የጀመረውን ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል” ማሳሰቡ ጨምሮ ተገልጾዋል፡፡
“የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ የሚለውን ስም የማትቀይሩት ለምንድን ነው?” የሚል ጥያቄ ለሴት ጓደኛው ሲያቀርብ “መጀመሪያ ኤርትራን ወደ ውድ እናት አገሯ መመለስ ይቀድማል” የሚል መልስ ማግኘቱን ትምህርት ሚኒስቴር እንደሚሰራ የተናገረ የጎልጉል ደንበኛ ከሁለት ወር በፊት ገልጾ ነበር። ይህ ለትግራይ ሕዝብ የማይጠቅም እንዲያውም ለከፍተኛ ችግር የሚዳርግ እና በስሙ የሚፈጸም ሤራ ተቃዋሚዎች እንዳሉት ቢገመትም በግልጽ ደጋፊዎችም አሉት፡፡
በዴንማርክ የምትኖር አንዲት የትግራይ ተወላጅ እዚያው ለሚገኝ የጎልጉል አምደኛ ተመሳሳይ መልስ ሰጥታለች። “ደሚት (የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ) የሚባለው ሃይል የህወሃት ልዩ አጀንዳ አስፈጻሚ እንጂ የህወሃት ተቃዋሚ አይደለም” ስትል ስሜት በተቀላቀለበት ሁኔታ ተናግራለች። ስዊድን አገር ለትምህርት ተልካ ዴንማርክ የቀረችው ይህቺው የትግራይ ልጅ “ኢሳያስ በቅርብ ይወገዳል” ስትል መሃላ የተቀላቀለበት ትንቢት ተናግራለች። “እጁን ሰጥቷል፤ ፈርሷል፤ ወደ ልማት ተመልሷል፤…” የሚባልለት የሞላ አስገዶም ደሚት በቃል ለኢትዮጵያ ነው የምታገለው እያለ በትግራይ ስም መቋቋሙና መቀጠሉ ገና ከጅምሩ ለብዙዎች ጥያቄ የፈጠረ ጉዳይ ነበር፡፡
ህወሃት ደሚትን “አሸባሪ” በሎ ያላስፈረጀው ብቸኛ ነፍጥ ያነገበ ድርጅት መሆኑ የዘወትር መወያያ መሆኑ ይታወቃል።
የኢትዮጵያን ታሪካዊ ታላቅነት በማሰብ እንደገና ገናና አገር እንደምትሆን የሚያመላክቱ ናቸው የሚባልላቸው ሕዝብን ቀስቃሽ መፈክሮች ህወሃት ለራሱ ድብቅ ዓላማ ሊጠቀምበት ያሰበ ስለመሆኑ ሲነገር ቆይቷል፡፡ “ህዳሴ” (ዳግም ልደት – renaissance)፣ “ትልቅ ነበርን ትልቅ እንሆናለን”፣ … እየተባሉ የሚለፈፉ መፈክሮች የኢትዮጵያን ሳይሆን የአክሱምን ገናናነት እንደገና እንዲወለድ በማድረግ በድጋሚ ትልቅ ለመሆን የተወጠነ ነው በማለት የሚከራከሩ፤ ትግራይ ካለ ዓቅሟ የምታካሂደው የኢኮኖሚ፣ የትምህርት፣ የወታደራዊ፣ ወዘተ “ልማታዊ እንቅስቃሴ” በተያያዥነት ሊጠቀስ እንደሚገባ በአስረጂነት ይጠቅሳሉ፡፡
ኤርትራ የትግራይ ታሪካዊ አካል ስለመባሏ አስተያየት የተጠየቀ በአውሮፓ የኢሳያስ ተቃዋሚ ኃይሎች አመራር አባል የሆነ የኤርትራ ተወላጅ የዴንማርክ ነዋሪ “እኛና የትግራይ ህዝብ አብርን ልንኖር አንችልም። ምኞታቸው ይገርማል። ከሚመለከታቸው ጋር ተነጋገሬ አስተያየት እሰጣለሁ” የሚል መልስ ሰጥቷል።
ህወሃት ታላቋን ትግራይ የመመስረት (ነጻ የማውጣት) ፕሮግራም ይዞ የሚንቀሳቀስ ተገንጣይ ድርጅት ነው።
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
Tomi says
Kkkkkkk nice comedy after what they say Arab is for them.Dirtyilless Tplf time finish for them
Eri Anbesa says
Hi eye Weyane man benante yemitalel ale y Eritrea hone y Etiopia hizd yenant tenkol kifat minknga leba yemayawek yelemna yetigray hizb lb ystew
dongolo says
ye 3000 amet kijet tenesabachu
koster says
I knew the evil Agenda of the fascists for Long. They are in Menelik Palace because of the power vaccum and since it is ideal to loot and build greater TIGRAI but the fascists have never and ever said that they are Ethiopians. http://vimeo.com/18242221
Tamirat says
Melese Zenawi openly said the following regarding his longterm ambition:
1. When asked haw he wanted to be remembered, he said as the founding father of the nation (tigray)
2. He once openly invited OLF to come to the negotiation tableby stating that “at the end of the day, we dont have differences in longterm objective”
3. Regarding port of Asab “we will not take it even if Shabia agree to give the port”
4. Why he hate Amharas? You know the answer.
5. “We will fight to Eritrian freedom if forces from ethiopia try to invade that country”
6. Why he keeps absolute monoply of power and wealth?
7. Why he wants to create contradiction between tigryans and the rest of ethiopians?
Why he inserted article 39?
8.why ethinic based fedralism?
………
Ramedan says
Historical poropoganda is nothing to change tigry poeple because the are corrupting in any area
lose ertira land and unethiopian!! !!
Semka says
Nice joke of 2015, አንዃን ኤርትራ ይልቅ ትግራይን የትግራይማረግ ይሞክሩ መጀመሪያም ታሪካጽቸው በደም ኣያውቁም።
Semka says
ኣክሱም ውን ሲሆን በዛን ግዜ የትግራይ ኣልነበረም። የነሱ የታሪክ ትንታኔ ሲተት ስለሆነ ስህተትም አንዳስቡ ያረጋቸዋል፣ ለምንድነው አንደዛ ያልኩት፣ በኣክሱሜት ወይ ኣፕሲኒኣን ማለት ህበሻ ብሎ የሚጠራው ግዜ ወይም ክፍለዘመን አትዮጵያ፣ ትግራይ፣ አርትራ የሚል ስም ኣልነበረም። እነሱ የሚሉት ኣክሱም ባሁኑ ባለው የትግራይ ክፍለሃገር ወይም ክሊል ስለሚገኝ ኣክሱም የትግራይ ነው የሚሉት እንጂ ኣነሱም አኮ በዛም ግዜ ኣልነበሩም። ለዚህ ነው አኔ የስህተት ታሪክ ትንታያቸው ስህተት አንዲኣስቡ ያረጋቸው ያልኩት። አንድያው ኣክሱም ሃወልት በነሱ ክሊል መሰራቱ አድለኞች ናቸው አንጂ አነሱም የዛን ግዜ ኣክሱም ኣይመስሉም።
tarik says
weyane is day dreaming, Eritreans and Tigrians can never be one country!!
1 They do not like each other
2 Eritreans do not believe they are Tigrians
3 There are about eight tribes in Eritrea
4 Tigrina people in Eritrea never believe they are Tigrians
Amman says
የማይጨበጥ የሕልም ተስፍ ነው። ወያነ ሲረገዝ እና ሲወለድ ጀማሮ በሕልም እየዋኘ ነው የሚነረው ወያነ ትንሽዋን ትፍግራይ በሐይል የሊላ ሰው መሬት በመዝረፍ ታላቅዋን ሪፓብሊክ ለመመስረት ይፈልጋል የሕ ግን ሕልም ብቻ ነው.ወያን እንካን ሪፓብሊክ ትግራይ ለመመስረት ይቅር ባሐይል የዘረፈውን የበገመድር መሬት አንድ ቀን ይመለሳል። ያለንበት ዘመን 21 ከፍለዘመን በሐይል እንደ ፈለግ ማድረግ አይችልም። ደግሞ ወያነ በመጨረሻ ሳዓት ነው የለው በሞት አፋፍ ነው የሚገኘው የማድረግ ብቃት የለውም ። ለማይቀረው ሞት መዘጋጀት ነው።
Geresu duki says
ofcourse seraye was part of tigray before the italian occupation of ertra, the other part of ertrea was midere bahiri ( bahere negash was the prince of the area. Bahere negash was one of the princes of Ethiopia. The axumite empire was an Ethiopian empire , axum was the capital city of Ethiopia. Ertrea belongs to Ethiopia. and ertreans are Ethiopians, this is the reality, period. any how at this time the two bandits shabya and woyane , mischieviousily they are twisting history, they are serving the interest of anti-Ethiopians . Most of them are the son of traitors. Their objective is to dismantle Ethiopia. Their strategy is 1. to secede province Ertrea from Ethiopia, then to put ertrea in continuous war ., to be instrumental for the immigration of ertrean youth out of ertrea , in other words to sell the youth of ertrea to the arabs and europeans . At the end the future generation would not be there , then the arabs would have an access to control ertrea and the sea cost at large. 2. To create an ethnic animosity between ertreans and tigreans to put them in a continuous war , the two provinces of Ethiopia are the base of Ethiopianism , if you put them in to antagonistic situation , they think that they can create a base to dismantle Ethiopia
3. to propagate the Four provinces of ethiopia , gondor, gojam , shewa and wollo as Amhara the enemy of the other tribes of Ethiopia
4. wellega, bale,arsi,harerege shewa ,…as oromos to categorize them as the enemy of Ethiopianism
5.To create a favourable condition to dismantle, and loot Ethiopia , such as allowing Ethnic federalism , the right to secede .
6, To create religious animosity between the christians and islams
Neverthless , the Ethiopian people is strong. A nation which has been there for the last three thousand years , has proved that he is beyond the tribal divisions. Ethiopianism is love , this nation will prevail.
Amman says
ሰራየ የትግራይ ግዛት ሆኖ አይቅም ከጣልያን በፊት ሆነ በሃላ በሰራየ በኩል መረብ ወንዝ ነው የሚለያቸው ወያነ ግን ኤርትራ እንደወልቃይት አይደለችም በደንብ ያቃል።ከትግራይ ሕዝብ ምንም ጥላቻ የለንም አንድ አገር መሆን ግን አንፈልግም። ወያነ የሞተ ውሻ በሁለም የተጠላ ፍሽት ነው ጨካን ነው 3 ሜላን አማራዎች የገደለ ዘረኛ ማን ይፈልገዋል?