ለጎልጉል የእማኝ ዘጋቢ (ireporter) የሆኑ በላኩልን መረጃ መሠረት በኢትዮጵያ የተለያዩ ቦታዎች የተነሣው ንቅናቄ ወደ ሲቪል ሠራተኞች ዘልቆ እንዳይገባ ስጋት ውስጥ የገባው ኢህአዴግ ሠራተኞችን ማባበልና ማንቃት ጀምሯል፡፡
በተያዘው ዕቅድ መሠረት በአዲስ አበባ በሚገኙ ወረዳዎች ውስጥ በሲቪል ሠራተኝነት የሚታወቁ ዜጎችን ኢህአዴግ በየቦታው መሰብሰብ ጀምሯል፡፡ እማኙ በላኩት መረጃ እንደገለጹት ለሁለት ቀን በሚካሄደው ስብሰባ በየወረዳው ለሚሰበሰቡ ሠራተኞች ቢያንስ ብር 300 አበል በመስጠት የማባበያ ስብሰባው እንደሚካሄድ ገልጸዋል፡፡ በየወረዳው ካለው ሲቪል ሠራተኛ አንጻር ለአበል የታሰበው ብር በሚሊዮን ሊቆጠር እንደሚችል እማኙ ጨምረው አስረድተዋል፡፡
ዋናው አጀንዳ ሲቪል ሠራተኛው እየተካሄደ ባለው ንቅናቄ ተሳታፊ እንዳይሆን፤ እንዳይተባበር፤ ድጋፍ እንዳይሰጥ፤ … ሲሆን ተሰብሳቢዎቹ ወደ ስብሰባው የመጡት የህወሃት/ኢህአዴግ ደጋፊ ሆነው ሳይሆን አለመሳተፍ የሚያመጣባቸውን ከመፍራትና በነጻ ስለሚያገኙት አበል በማሰብ እንደሆነ እማኝ ዘጋቢው ጨምረው ገልጸዋል፡፡ ሰብሳቢዎቹ “ንቅናቄውን እንዳትደግፉ” ወይም “ማስተር ፕላኑን በተመለከተ የተነሳውን የኦሮሞ ተቃውሞ እንዳትደግፉ” ወይም መሰል ግልጽ ማስጠንቀቂያ ለተሰብሳቢዎቹ እንዳልሰጡ መረጃውን የላኩት እማኝ ዘጋቢ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ ይልቅ ግን በተዘዋዋሪ ሁኔታ ከጸረ ልማት ኃይሎች ጋር እንዳትተባበሩ፤ ጸረ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎችን እንዳትደግፉ፤ ተገልጋዩን ኅብረተሰብ በጥሩ ያዙ፤ የገቢ ግብር ይቀነሳል፤ … የሚሉ ማባበያና ማስጠንቀቂያ አዘል ንግግሮች ከሰብሳቢዎቹ እንደተደመጡ ዘጋቢው አስረድተዋል፡፡
ይህ በግምገማ ሽፋን የሚካሄደውን የሲቪል ሠራተኞች ስብሰባ ከሌላ ነጻ ምንጭ ለማረጋገጥ ባይቻልም እማኝ ዘጋቢው በላኩልን መረጃ መሠረት ስብሰባው በይፋ እንዳይታወቅ መፈለጉንና ከወረዳ ጽ/ቤቶች ውጪ በሚገኙ ቦታዎች መካሄዳቸውና በዚሁ እንደሚቀጥል አክለው ተናግረዋል፡፡
በአዲስ አበባ ዙሪያ የታቀደውን ማስተር ፕላን በመቃወም በተማሪዎች የተነሳው ተቃውሞ በአገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች በመቀጠሉ ከተማሪዎች አልፎ ነዋሪዎች እየተቀላቀሉት እንደሆነ በስፋት ይነገራል፡፡ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በንቅናቄው ምክንያት እስከ 25 ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል፡፡ ከሞቱት መካከል ከአስር ዓመት በታች የሚሆኑ እንዳሉበት የተነገረ ሲሆን በምዕራብ ሸዋ ነዋሪዎች አንዳንድ ከተሞችን በራሳቸው ቁጥጥር ሥር ማዋላቸው ሲነገር ይህንኑ መረጃ አፍቃሪ ህወሃት/ኢህአዴግ የሆኑ የሥርዓቱ ቀጥተኛ ተጠቃሚዎች፣ ተላላኪዎች፣ አሽቃባጮችና ጭፍን ደጋፊዎች በየፊናቸው አረጋግጠዋል፡፡
ሕዝባዊ ንቅናቄውን የኦሮሞ ብቻ አድርጎ መውሰድና በዚያ መልኩ ፕሮፓጋንዳ መስጠት በኢትዮጵያ ውስጥ በህወሃት ሲረጭ የኖረውን የዘር ጥላቻና መከፋፈል የከፋ ደረጃ ላይ አድርሶ ራስን ለህወሃት መጠቀሚያነት የሚያጋልጥ የሚናገሩ ወገኖች “ኦሮሚያን” እንደ አገር እያሰቡና ሠንደቅ እየያዙ መውጣት በንቅናቄው ላይ ሊጠገን የማይችል አሉታዊ ተጽዕኖ ያመጣል ሲሉ ስጋታችን ይገልጻሉ፡፡ (ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ)
Jaawii says
Hallo Gulgoole,
Good that your covering the current situation in Ethiopia and express the overall fear of a risk that the country is going to face. BUT as media outlet be careful with a message you are passing. Yes, the Oromoo people is right now fiercely raising its voice and being killed day and night by brutal government heavy armed forces. Unless others join the Oromoo to make it a national popular uprising, how can you claim it will be a national uprising. You can not stand passive and say criticize by saying “Oromoo is fighting for itself’. The Oromoo people did not say we are fighting for an oromoo nation alone; they say we are fighting for our right. Do not mess up things, please !! You need to give a message that encourage all other oppressed people to genuinely and immediately act in supporting the Oromoo people.