• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ፈረንሳይ እስከ 160 የሚሆኑ መስጊዶችን ልትዘጋ ነው!

December 4, 2015 11:00 am by Editor Leave a Comment

በመጪው ጥቂት ወራቶች ፈረንሳይ እስከ 160 የሚጠጉ መስጊዶችን ለመዝጋት መወሰኗ ተሰማ፡፡ የአገሪቱ ከፍተኛ ኢማም እንዳሉት በሥራ ላይ በዋለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሠረት ጽንፈኛ አመለካከት የሚያራምዱ የእምነት ቦታዎች መዘጋት አለባቸው፡፡

በኅዳር ወር መጀመሪያ አካባቢ በፓሪስ የተከሰተውን ጥቃት ተከትሎ እስካሁን ጽንፈኛ አቋም አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ ሦስት መስጊዶች መዘጋታቸውን የአገር አቀፍና የአካባቢ ኢማሞች ለመምረጥ ኃላፊነት የተሰጣቸው ኢማም ሃሰን ኤል-አላዊ ለአልጃዚራ መናገራቸው ተዘግቧል፡፡ እርሳቸው እንደሚሉት በቀጣይ ወራቶች በርካታ መስጊዶች እንደሚዘጉ አስረድተዋል፡፡

“ከአገር ውስጥ ሚኒስቴር ጋር በምናደርገው ውይይት እና ይፋ በሆኑት መረጃዎች መሠረት ሕጋዊ ፈቃድ የሌላቸው፣ ጥላቻን የሚሰብኩ፣ ታክፊሪ ንግግር የሚደረግባቸው ከ100 እስከ 160 መስጊዶች ይዘጋሉ” በማለት ኢማም ሃሰን ተናግረዋል፡፡ ታክፊሪ ንግግር ማለት በእምነቱ ውስጥ ያሉትን ሌሎች ሙስሊሞችን በከሃዲነት የሚነቅፍ ንግግር ነው፡፡ “እንዲህ ዓይነቱ ንግግር ዓለማዊ በሆነችው ፈረንሣይ ብቻ ሳይሆን በእስላማዊ አገራትም ቢሆን መፈቀድ የለበትም” በማለት የመጀመሪያው የእስርቤት ኢማም (ቻፕሊን) ለመሆን የበቁት ሃሰን ኤል አላዊ ተናግረዋል፡፡

franceይህ በፈረንሳይ አገር በቤተ እምነት ላይ የተወሰደ የመጀመሪያው የተባለለት እርምጃ የተወሰደው “አንዳንድ ሕገወጥ ነገሮች በመገኘታቸው” መሆኑን የጠቀሱት ኢማም ድርጊቱ ባለሥልጣናት ማድረግ የሚገባቸው ሕጋዊ እርምጃ ነው ማለታቸውን አልጃዚራ ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

ለ130 ሰዎች መሞት ምክንያት የሆኑትን “አሸባሪዎች” በማለት የጠቀሷቸው ኢማም ሃሰን “እነዚህ የሃይማኖት ልብስ የተጎናጸፉ ሌቦችና አደንዛዥ ዕጽ አዘዋዋሪዎች ናቸው፤ ነገሩ የአሸባሪዎች ጉዳይ ነው እንጂ ከሙስሊሞች ጋር ምንም ግንኑነት የለውም፤ የሁሉንም ሰው ደኅንነት ማስፈን የመለከተ ነው” በማለት ኢማም ሃሰን በጥቃት አድራሾቹ ላይ ያላቸውን አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

ሌላው ለአልጃዚራ አስተያየታቸውን የሰጡት የአል-ካዋኪቢ ድርጅት ተባባሪ መሥራች የሆኑት የፋርሱ ሙስሊም ፊሊክስ ማርቃርት የመስጊዶቹ መዘጋት እንዳላስደነቃቸው ተናግረዋል፡፡ ይልቁንም በተለያዩ የፈረንሳይ ከተሞች በተካሄዱ እስላማዊ የጸሎት ሥነ ሥርዓቶች ላይ የሰሙት ነገር በእጅጉ እንዳስደነገጣቸው ተናግረዋል፡፡ “እስልምናን ከፖለቲካ ጋር በማያያዝ እስልምናን አስፈሪ የማስደረግ ሥራ በፈረንሳይ መንግሥት እንደሚሠራ አንዳንድ ቦታዎች በይፋ ሲነገር ሰምቻለሁ” ብለዋል፡፡

ሆኖም ግን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ከጥቃቱ በኋላ ፈረንሳይ ሙስሊሞች ላይ ያነጣጠረ የመብት ጥሰት እየፈጸመች መሆኗን ይናገራሉ፡፡ የቤት አሰሳ፣ እስራት፣ ሙስሊሞች ባለቤት የሆኑባቸው ድርጅቶችን የመዝጋት፣ ወዘተ የመብት ጥሰት ተከስቶባቸዋል የተባለባቸው ናቸው፡፡

“በአሁኑ ጊዜ በፈረንሳይ ሙስሊም ሆኖ መኖር ቀላል አይደለም” ያሉት ማርቃርት “በተለይ የፊት መሸፈኛ የሚያደርጉ ሴቶች የመድልዖ ሰለባ ሲሆኑ ለወንዶች ደግሞ ሥራ ማግኘት እጅግ ከባድ ነው” በማለት አስረድተዋል፡፡

በፈረንሳይ ውስጥ በድምሩ 2,600 መስጊዶች ይገኛሉ፡፡


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule