መንግሥት በምርጫ ዙሪያ በመቶ ሺሕ የሚቆጠር ካድሬ እስካለፈው እሑድ ድረስ ማሠልጠኑን፣ ማክሰኞ መጋቢት 21 ቀን 2013 ዓ.ም. በተካሄደው የአዲስ ወግ ውይይት ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ተናግረው፣ ዘንድሮ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው አገራዊ ምርጫ ፓርቲያቸው ብልፅግና ከተሸነፈ ሥልጣን ለማስረከብ ዝግጁ መሆኑን አስታወቁ። “እንደ ብልፅግና ፓርቲ ከተሸነፍን ሥልጣን ለማስረከብ ተዘጋጅተናል። ይህንን ካደረግን ደግሞ ከምርጫ በኋላ ሰላም የማይኖርበት ምክንያት አይኖርም። አሁን ሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት በመቶ ሺሕ የሚቆጠር ካድሬ እስካለፈው ቅዳሜና እሑድ ድረስ ሥልጠና ላይ ነበር። ዋናው መልዕክት ኢትዮጵያ አሸናፊ መሆን አለባት ነው” ብለዋል። ኢትዮጵያ አሸናፊ የምትሆነው ሽንፈት ሲኖር በማመሥገንና መልካም በመመኘት ሥልጣን መስጠት ከተቻለ መሆኑን … [Read more...] about “እርግጠኛ ሆኜ የምነግራችሁ መንግሥት ኮሮጆ አይሰርቅም” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
election 2013
ባልደራስና የአብን የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲና የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) በሀገሪቱ ፍትህና ዴሞክራሲ እንዲሰፍን በጥምረት ለመስራት ያስችላል ያሉትን የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል። ትብብሩ በቀጣይ በአገሪቱ እንዲፈጠርና እንዲጎለብት የሚፈለገው የአገራዊ በጎ ሀይሎች ጥምረት መሰረት እንዲሆን ያለመ መሆኑም ተገልጿል። በመጪው አገራዊ ምርጫ የመራጮች የጋራ ፍላጎትና ራዕይ ለማሳካት ፓርቲዎቹ በጋራ ለመስራት በማሰብ የተመሰረ የፖለቲካ ትብብር መሆኑንም ነው ፓርቲዎቹ የገለፁት። በአገሪቱም ሆነ በዜጎች ላይ የተጋረጡ ፈተናዎች እንዳሉ የገለጹት ፓርቲዎቹ፣ ይህንን ከመቼውም ጊዜ በላይ በትብብር ለመታገል በቁርጠኝነት እንደሚሰሩና ትብብሩ ከምርጫው በኋላም እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። (ኢቢሲ) የባልደራስ መሪና በአሁኑ ጊዜ በእሥር ላይ የሚገኙት አቶ እስክንድር ነጋ ከአማራ ድርጅቶች በተለይ … [Read more...] about ባልደራስና የአብን የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ
ምርጫ ቦርድ ከፈቀደለት ኦነግ በምርጫው እንደሚወዳደር አስታወቀ
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/ ምርጫ ቦርድ ከፈቀደለት በምርጫው እንደሚወዳደር አስታወቀ። ለሁለት ቀናት አጠቃላይ ጉባዔውን ያካሄደው ፓርቲው አዲስ ሊቀመንበርም መርጧል። ፓርቲው ባደረገው ጉባኤ የቡድኑን መሪ አራርሶ ቢቂላን የግንባሩ ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል። አቶ ብርሃኑ ለማ እና አቶ ቀጄላ መርዳሳን ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር ሆነዋል። ጉባዔው 43 ቋሚ እና 5 ተለዋጭ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትንም መርጧል። በጠቅላላ ጉባኤው ህገ ደንቡን ያሻሻለው ፓርቲው የስነ ስርዓትና ቁጥጥር ኮሚቴም አቋቁሟል። ፓርቲው እራሱን ከምርጫ ማግለል እንደማይፈልግ የገለጸ ሲሆን የዕጩዎች መዝገባ ከመጠናቀቁ ጋር በተያያዘ ግን ምርጫ ቦርድ ከፈቀደ ወደ ምርጫው እንደሚገቡም አስረድተዋል። (ፋና) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ምርጫ ቦርድ ከፈቀደለት ኦነግ በምርጫው እንደሚወዳደር አስታወቀ
ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን ወሰዱ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው አገር አቀፍ ምርጫን ለማከናወን በጊዜ ሰሌዳው ላይ ካስቀመጣቸው ተግባራት መካከል አንዱ በሆነውና የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ምልክቶቻቸውን የሚመርጡበት/ የሚያስገቡበት መርሃ ግብር መሰረት ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን የመረጡ ሲሆን በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፀድቋል። በዚህም መሰረት የፖለቲካ ፓርቲዎቹ የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን መውሰዳቸውን የኢትዮጵያ የምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡ (ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን ወሰዱ




