ይህ ቃለ ምልልስ “መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ” በሚል ርዕስ May 20, 2013 አትመነው ነበር፡፡ የኢትዮጵያን የውድቀት ጉድጓድ ሲቆፍሩ የነበሩትና በአገዛዝ ሥልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ ጉድጓዱን በጥልቀት ሲቆፍሩ የነበሩት መለስ ከኢትዮጵያ ቀድመው ጥልቁ ጉድጓድ ገብተዋል፡፡ ዛሬ በሙት መንፈስ የሚመሩት “ተዝካራቸውን” የሚያወጡበት ቀን ነው፡፡ ለዝክሩ ይህንን ደግመን አቅርበነዋል፡፡ ይህንን ቃለምልልስ ያደረግነው ለበርካታ ዓመታት ለኢህአዴግ ሲሰራ ከነበረና በአሁኑ ወቅት ለከፍተኛ ትምህርት ውጪ አገር ከሚገኝ ኢትዮጵያዊ ጋር ነው፡፡ ለደኅንነት ሲባል ስሙን ከመጥቀስ ተቆጥበናል፡፡ ጎልጉል ፦ የጠ/ሚኒስትር መለስ መታመም ድንገተኛ ነው የሚሉ አሉ፤ አሟሟታቸውም ድንገት ነው የሚሉ አሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ አጋጣሚው መልካም እንደሆነ የሚጠቁሙ አሉ አንተ ከየትኛው ወገን ነህ? መልስ፦ … [Read more...] about “ለባለ ራዕዩ” 4ኛ ሙት ዓመት “ተዝካር”
Politics
ወልቃይት የማን ነው? የማይረባ ጥያቄ!
አንድ በነገረ አስተሳሰብ ወይም በአስተሳሰብ ሕግ (ሎጂክ) ትምህርት ላይ አንድ የማስታውሰው ምሳሌ አለ፤ ‹‹ሚስትህን መደብደብ ትተሃል ወይ?›› የሚል ጥያቄ ነው፤ ጥያቄው የሚነሣው ጠያቂው አውቃለሁ ብሎ ከያዘው እውቀት ወይም እምነት ነው፤ ስለዚህም ጠያቂው የሚፈልገው ጥያቄ ለማስተላለፍና መልስ ለማግኘት አይደለም፤ ጠያቂው የሚፈልገው በጥያቄ መልክ የራሱን ‹‹እውቀት›› ወይም እምነት ለተጠያቂው ለማስተላለፍና ተጠያቂውን የጠያቂው ደቀ መዝሙር ለማድረግ ነው፡፡ ሚስትህን መደብደብ ትተሃል ወይ? መልስ የሌለው ጥያቄ ነው፤ ‹‹አዎ›› የሚል መልስ ሰውዬው ሚስቱን ሲደበድብ እንደነበረ አመነ ማለት ነው፤ ‹‹አልተውሁም›› ከአለ በራሱ ላይ መሰከረ፤ ሁለቱም መልሶች ተጠያቂውን የሚያስወነጅሉ ስለሆኑ መልስ አይደሉም፤ ከዚያም በላይ ጥያቄው ትክክል አይደለም፤ የማይረባ መጥፎ ጥያቄ … [Read more...] about ወልቃይት የማን ነው? የማይረባ ጥያቄ!
መጪው ቅዳሜ ለት በመላው ኦሮሚያ ሰላማዊ ሰልፍ ይካሄዳል
እሁድ እለት በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ በአስርታት ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥቶ ወያኔን ተቃውሞ በሰላም ወደ ቤቱ ተመለሰ። በጣም ጥሩና ታሪካዊ ሰልፍ ነበር። በእለቱ ከጥቂት ሰዓታት በኋል ግን በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ አወዳይ ከተማ ወጣቶች ሰልፍ ወጥተው በአጋዚ አልሞ ተኳሾች 26ቱ ቆስለው እስከ አሁን 6 ሞተዋል። ይሄንን እንደምሳሌ ጠቀስኩ እንጂ ኦሮሚያ ውስጥ ወያኔ ሰላማዊ ሰልፈኞችን በጥይት እሩምታ ሲፈጅ አዲስ አይደላም። ባለፉት 9 ወራት ካ600 በላይ ዜጎች ተገድለዋል፣ 5000 የሚሆኑ የመቁሰል ጉዳት ደርሶባቸውል። ይሄንን ቁጥር ወስደን ብናሰላው፣ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ በየእለቱ ባማካይ ከሁለት እስከ ሶስት ሰዎች ኦሮሚያ ውስጥ በመንግስት ታጣቂ ሃይሎች ሲገደሉ እንደነበረ ማየት ይቻላል። ይህ ሁሉ ግፍ ሲፈጸም የአምባገኖች ጸባይ ነው ተብሎ ሲታለፍ ነበር። … [Read more...] about መጪው ቅዳሜ ለት በመላው ኦሮሚያ ሰላማዊ ሰልፍ ይካሄዳል
የነፍጠኞች ፖሊቲካ
ነፍጠኛነት ባህላችን ነው፤ ፖሊቲከኛነት አዲስና ባዕድ የትግል ዘዴ ነው፤ ፖሊቲከኛነትና ነፍጠኛነት ተቃራኒ ተግባሮችን ያመለክታሉ፤ ተቃራኒ ተግባሮች አብዛኛውን ጊዜ ተቃራኒ ዘዴዎች ያስፈልጋቸዋል፤ ለምሳሌ መፍጨትና መቡካት ተቃራኒ ተግባሮች ናቸው፤ መፍጨት ሲበታትን፣ ማቡካት ሰብስቦ ያያይዛል፤ የሚፈጭ ሰው ማቡካት ይችላል፤ እንዲሁም ማቡካት የሚችል ሰው መፍጨት ይችላል፤ ፈጪ አቡኪ መሆን የሚችለውን ይህል ወይም አቡኪ ፈጪ መሆን የሚችለውን ያህል ነፍጠኛ ፖሊቲከኛ ወይም ፖሊቲከኛ ነፍጠኛ መሆን ይችላል ወይ? መልሱ ግልጽ ነው፤ አይችልም፤ የነፍጠኛ ትግል በጠመንጃ ነው፤ የፖሊቲከኛው ትግል በቃላት፣ በንግግር ነው፤ በሌላ አነጋገር የነፍጠኛ በዱላ፣ የፖሊቲከኛ ትግሉ በመላ ነው፡፡ የፖሊቲካ ሥልጣንን ነክሶ ይዞ ሕዝብን በሕዝብ በዱላ እያደባደቡ በማሸነፍም ሆነ በመሸነፍ የሥልጣንን ክብር ማግኘት … [Read more...] about የነፍጠኞች ፖሊቲካ
ምስለ – ብአዴን
ለፖለቲካ ስልጣን ሁለተኛነት ሁሌም የሚጫወተዉ ብአዴን፤ ኢሕኢፓ በገጠመው የመበታተን አደጋ ለኢሕዴን ጥንሰሳ ምክንያት የሆነው የበለሳ ንቅናቄውን በመጀመር ብዙዎች ወደ ደርግ ሲኮበልሉ፣ እልፎች ወደ ሱዳን ሲሰደዱ ‹‹ጥቂቶች ቆራጦች›› ህዳር 11/1973 ዓ.ም በህወሓት አጋፋሪነት ኢሕዴንን እንደመሰረቱ በግነታዊ ቃላት የታጀበው የድርጅቱ ታሪክ ያትታል፡፡ የዘመናዊው አርበኛ (ኢሕአፓ) ኃይል በደርግ፣ ሻዕብያና ወያኔ ታክቲካል ህብረት ውልቅልቁ በወጣበት ሂደት ውስጥ የተፈጠረው ኢህዴን ደርግን ለመጣል ካደረገው ወታደራዊ አበርክቶ ይልቅ የፖለቲካ አበርክቶው እጅግ ላቅ ያለ እንደነበር ይነገርለታል፡፡ በተለይም በሰሜን ምዕራብ፣ ደብረታቦር፣ ጎጃም፣ ወሎና ሰሜን ሸዋን የመሳሰሉ የደርግ ጠንካራ ወታደራዊ ቤዞች የነበሩትን ቦታዎች ሰብሮ ለመግባት የኢሕዴን ውስን ሰራዊትና አመራሮች የየአካባቢውን … [Read more...] about ምስለ – ብአዴን
የአቶ ዠ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ጉዳይ
አቶ ዠ፣ ከ Fast Lane ዩኒቨርስቲ በተልዕኮ በአራት ወራት እድሜ የዶክትሬት ድግሪ የተጫነባቸው የክብር ዶክትሬት እንደሚጫንባቸው ጭምጭምታ ተሰማ። ጭምጭምታው ደግሞ ከሁነኛ ምንጮች ነው። በ“ተልዕኮ” ማለት ለ Fast Lane ዩኒቨርሲቲ ደብዳቤ መጻፍና ገንዘብ መላክ ነው ተብሎ ይታማል። ይህን ሃሜት እኔ ጭምጭታ ነው የሰማሁት። ጭምጭምታው ግን ከሁነኛ (አስተማማኝ) ሰው ነው። አቶዠ፣ቀድሞ በደርግ ጊዜ መፈክር ጸሃፊ፣ በኋላም በኢሃዲግ ጊዜ ልማታዊ ጸሃፌ ተውኔት፣ቀድሞ የኢሃዲግ ፍቅር ቤት ሥራ አስቀማጭ፣ ይቅርታ ሥራ አስኪያጅ፣ በዩናይትድ ኔሽንስ የኢትዮጵያ ተወካይ፣ ለዩናይትድ ኔሽንስ ዋና ጸሃፊነት በራስ አነሳሽነት ተወዳዳሪ፣ ወዘተርፈ...ወዘተርፈ....ወዘተርፈ....እንዳልኩት የክብር ዶክትሬት እንደሚጫንባቸው ጭምጭምታ ተሰማ። ጭምጭምታው ደግሞ ከሁነኛ ምንጮች ነው። ሆኖም ችግር … [Read more...] about የአቶ ዠ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ጉዳይ
“ወልቃይትና ጠግዴ በኢትዮጵያ ታሪክ በትግራይ ስር ሆነው አያውቁም” ታሪክ
የወልቃይት ጉዳይ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ ደም እያፋሰሰ ባለበት በሁኑ ወቅት ቴድሮስ አድሃኖም ወልቃይትን የትግራይ ግዛት አድርገው በመቁጠር "የአማራ ብሔር ተወላጆች ወልቃይት መጥተው መኖር ከፈለጉ የትግራይ ሕዝብ በደስታ ይቀበላቸዋል" በማልተ የትግራይ ሕዝብ ወክለው ስለ ወልቃይት የትግራይ ክልልነት በድፍረት በፌስቡክ ላይ ይህንን ብለዋል - ሙሉው ቃል ከዚህ በታች ይገኛል:- በጎንደር የተከሰተውን የማንነት ጥያቄ ሰበብ በማድረግ አንዳንድ ግለሰቦች ብጥብጥ ለማስነሣት ቢሞክሩም መንግሥታችን በሰከነ ዘዴ በአጭር ጊዜ ውስጥ በቁጥጥር ሥር አውሎታል:: የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከአማራ ተወላጆች ጋር በመወያየትና በማሳመን የወልቃይትን መሬት የትግራይም ሆኑ የአማራ ተወላጆች በጋራ እንዲኖሩበት በማግባባት ላይ ይገኛል፡፡ ወልቃይት የአማራ ነው በማለት የሚነዛው ፕሮፓጋንዳም የሐሰት መሆኑና … [Read more...] about “ወልቃይትና ጠግዴ በኢትዮጵያ ታሪክ በትግራይ ስር ሆነው አያውቁም” ታሪክ
በጎንደር የተነሳው አመጽ እየሰፋ ነው!
በጎንደር የሰዎች ህይወት ከማለፉ በተጨማሪ ሕዝብ የማያምንባቸውንና ከትግራይ ተገንጣይ ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው ባላቸው ንብረቶች ላይ ርምጃ መውሰዱ ታውቁዋል። ማክሰኞ ሊነጋጋ አካባቢ ተነሳ የተባለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለመቀላቀል ወደ ጎንደር ያመሩ ወገኖችም መበራከታቸው እየተሰማ ነው። ለዓመጹ ውጤታማነት የዘር ትግል ሳይሆን ኅብረብሔራዊ እንቅስቃሴ እንደሚበጅ ተገለጸ። አመጹ የተቀሰቀሰው የማንነት ጥያቄ ባነሱና "እኛ አማራ እንጂ ትግሬ አይደለንም" በሚል የተነሳውን ጥያቄ ከውጤት ለማድረስ ከተመረጡት የኮሚቴ አባላት መካከል አራት የሚሆኑትን ከትግራይ የመጡ ነፍጥ አንጋቾች ከያዟቸው በኋላ እንደሆነ ለኢሳት በድምጽ ማብራሪያ የሰጡ አረጋገጠዋል። ከዚያም ኮሎኔል ዘውዱ ደመቀን ለመያዝ ሙከራ ተደረገ። ይህን ጊዜ ኮሎኔሉ "በሬን አልከፍትም ጥዬ እወድቃለሁ" በማለት ሊያስሯቸው ከመጡት ሃይሎች … [Read more...] about በጎንደር የተነሳው አመጽ እየሰፋ ነው!
“የማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች እስካልተቀየሩ ድረስ ሕይወታችን የከፋ አደጋ ላይ ነው”
ዛሬ አቶ በቀለ ገርባ በውስጥ ከነቴራ፣ በቁምጣና በባዶ እግራቸው ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ ጉዳዩን የተከታተለው ኤሊያስ ገብሩ ጎዳና ይህንን የአቶ በቀለን ንግግር በፌስቡክ ገጹ ላይ አትሞአል፡፡ ይህ ምስክርነት በፍርድ ቤት ካሰሙ በኋላ በአማርኛ በኦሮሚኛ እና በ እንግሊዝኛ በየማህበራዊ ገጾችና ድረገጾች ተሰራጭቶዋል፡፡ "በባለፈው ቀጠሯችን ለብሰን ፍርድ ቤት ልንቀርብ የነበረውን ጥቁር ልብስ አውልቁ ተባልን፡፡ አናወልቅም አለን፡፡ የፈለግነውን የመልበስ ሕገ-መንግስታዊ መብታችን ነው፡፡ ጥቁር ልብስ የለበስነውም፤ ከ50ሺህ በላይ የአንድ ብሄር ተወላጆች እስር ቤት መገኘታቸውንና በዚህ ዓመትም በጥቂት ወራት ውስጥ ከ200-300 የሚደርሱ የኦሮሚያ ክልል ተወላጆች መገደላቸውን በማዘን ለመግለጽ ነው፡፡ ድርጊታችንም ይሆን የነበረው የፍርድ ቤትን አሰራርን ምንም በማይነካ መልኩ በሰላም … [Read more...] about “የማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች እስካልተቀየሩ ድረስ ሕይወታችን የከፋ አደጋ ላይ ነው”
አድዋ! 120 ዓመት!
“… የተተከለው ድንኳን ሲታይ ከብዛቱ የተነሳ አፍሪካ ኤሮጳን ለመጠራረግ የተነሳች ይመስላል፡፡ የጦርነቱ ዕለት ኢትዮጵያውያኑ ደማቅ ቀለም ያለው ካባ ለብሰው፤ ጠመንጃና ጦር ይዘው፤ ጎራዴ ታጥቀው፤ የነብር ያንበሳ ቆዳ ለብሰው፤ አዝማሪዎቹ እየዘፈኑ፤ ቄሶች፤ ልጆች፤ ሴቶች ሳይቀሩ ፀሐይዋ ፈንጠቅ ስትል በተራራው ላይ በታዩ ጊዜ የኢጣሊያን ክፍል አሸበሩት” የበርክለይ ምስክርነት፤ አጤ ምኒልክ በጳውሎስ ኞኞ፤ ገጽ 195 … [Read more...] about አድዋ! 120 ዓመት!









