
ኦሮሞ እና አማራ “እሣት እና ጭድ ናቸው” ብላችሁ ክብሪት ለመጫር ለምትቋምጡ የወያኔ ሎሌዎች የሚከተለውን ብትገነዘቡ መልካም ነው፡፡
1) ኦሮሞ እና አማራ መታየት ያለባቸው እንደ እሳት እና ጭድ ሳይሆን ጎን ለጎን በቅለው ለረጅም ጊዜ አብረው እንዳደጉ ትልልቅ ዛፎች ነው። እነዚህ ዛፎች ለረዥም ጊዜ ተጎራብተው ከመኖራቸውና ከግዙፍነታቸው የተነሳ በመሬት ውስጥ የተሳሰሩት ሥሮቻቸው ምግብ ሊሻሙ ይችላሉ። በአየር ላይ የሚነካኩት ቅርንጫፎቻቸው በንፋስ ጊዜ እርስበእርስ ሊላተሙ ይቻላሉ። ነገር ግን ዛፎቹ ሥር የሰደዱና የተዋሃዱ እንደመሆናቸው መቼም ውሃ አያጡምና፣ እንደ ጭድ ደርቀው በክብሪት እሣት አይቀጣጠሉም።
2) ምናልባት ከሁለቱም ዛፎች ደርቀው የረገፉ ቅጠሎችን እና ጭራሮዎችን ተጠቅማችሁ እሳት መለኮስ ካሰባችሁም ጉዳቱ ለናንተው እንደሚያመዝን እውቁ። የምትለኩሱትን እሳት የንፋስ አቅጣጫው በማስቀየረ የወያኔን ስርዓት ወደሚያወድም ወላፈን መለወጥ እንደሚቻል ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን። Jawar Mohammed
Well said Jawar! This is the answer to those who want to exploit our difference for their benefit.
A great maturity stride of Jawar M: from his slogan, “Abysinea go out of Oromia” to this magnificent metaphore about the deep and historical brotherhood of the Oromos and Amharas. I hope Jawar keeps on using his bright mind to work for the grand cause of making Ethiopia a country of equaliy, justice, freedom, mutual respect and prosperity in real peace.
* እራስን በራስ ማስተዳደር . እራስ ገዝ ክልላችን ባሕላችን ቋንቋችን እንዳይበከል እኛ ልዩ ነን የሚሉ ቱማታ የትም እንደማያደርስ በአንድ እጅ ማጨብጨብ እንደሆነ ተረዳችሁ? ከአሜሪካ ፖለቲካ ሳይንስ የሕብረተሰብ ትሥሥር የሀገር ሠላምና ነፃነት ፈጣን ምላሽና ምጡቅ ትምህርት እዚያች ድሃ ሀገር እዚያ ቆራጥ ነፍጠኛ ሕዝብ ደም ውስጥ እንዳለ ገባችሁ? ጎንደሬውና ጎጃሜው “የኦሮሞው ወገናችን ደም ደማችን ነው!” ሲል በህወአት/ ኢህአዴግ ጦረኞች ሜዳ ላይ የፈሰሰውን ብቻ አደለም የትውልድ በቀል አንድነቱንም ለኦነግና ህወአት እንዲሁም ለሆድአደር ካድሬም የማንቂያ ደውል ነው።
*** በዚሁ ሰሞን በአሜሪካ ሲያትል ግዛት አንድ የኦሮሞ አባት “ኦነግ ፵ ዓመት ያልሠራውን አዲሱ ትውልድ ጎንደርም ወልቃይትም ኬኛ አሉ” አዎን! ኦሮሞ ኢትዮጵያ ኬኛ! ማን ይከለክለዋል? ያልተመቸው ይንካው ! ፺፭ ሚሊየን ሕዝብ በ፹፫ ቋንቋ በ፱ ክልል ታጉሮ በ፻ ባንዲራ ለጥቂት ወሮ በሎች ማንነቱን ሸጦ የቅድመ አያቶቹን የደምና አጥንት ግብር ሰንደቅ ዘቀዘቀ ተረገመ መከነ ባከነ አሁን በንሥሃ ተነሳ!
*** አማራና ኦሮሞ ( እነዚህ ዛፎች) ከግዙፍነታቸው የተነሳ በመሬት ውስጥ የተሳሰሩት ስሮችቸው ምግብ ሊሻሙ ይችላሉ። (ማንም ምንም አልተጠቀመም “ሁላችንም የአንድ ማሰሮ ንፍሮ ነን”።
*** በአየር ላይ የሚነካኩት ቅርንጫፎቻቸው በንፋስ ጊዜ እርስበእርስ ሊላተሙ ይቻላሉ።(ቦልጥቀኞች በዉሸት ታሪክ፡ለጉራ፡ለሥልጣን፡ትውልድ ያተራምሳሉ!ይርመሰመሳሉ)
*** ከሁለቱም ዛፎች ደርቀው የረገፉ ቅጥሎችን እና ጭራሮዎችን ተጠቅማችሁ እሳት መለኮስ ካሰባችሁም ጉዳቱ ለናንተው እንደሚያመዝን እውቁ።!” ይህ ለሜንጫ አብዮት ቀስቃሽ የኢሳት ላይ ፖለቲካ ትምህርት ለቀሰሙም ትልቅ መነቃቃት ነው። አሁን በተፈጠረውም መግባባት ‘ አንድነት ‘ የሚለውን አንድ ሕዝብ አደለንም በማለት የጠባብነት የጫካ ማኒፌስቶ የሙት መንፈስ (ራዕይ ) ለማስቀጠል አማራ ለኦሮሞ ‘አጋርነት’ እያላችሁ መጃጃልነትን እንደብልጠት አትቁጠሩት ኦቦ መሐመድ ያጥላላኸው የእናትህ የመንዚቷ ሠፈር ልጆች ያሉትን ሰማህ? ወልቃይትን ለመታደግ ጎንደር መሄድ አይጠበቅብንም እኛ የምንሔድበትን እናውቃለን አሉ። በብሔራዊ ቋንቋ ሲተረጎም ሸዋ ሲነሳ በአሌልቱና ሠንዳፋ የጀግና አሰላለፍ የክብር አቀባበል እንሚደረግለት ባለሙሉ ልብ ስለሆነ ነው። አዳሜ ዙሪያውን ያንዛረጥሽበትን የሀገርህን ቁልፍ ጥለህ ያለቀስከውን ያህል ከፍተው ልባም አማራ የት እንዳለ ትማራለህ። እስከዚያው በክልል ተጃጃል ብርታት ለተገፋው አማራ!!!! የጋራ ቤታችን ኢትዮጵያ ትንሳዬ በቅርብ እውን እንዲሆን የእያንዳንዱና የሁሉም ዜጋ ተሳትፎ ወሳኝ ነው።አራት ነጥብ።