* ኢህአዴግ የቁልቁለት ጉዞውን ተያይዞታል
* ከገዳዮች ቁጥር በላይ ለመሞት የተዘጋጀዉ ህዝብ ይበልጣል
እንደ መግቢያ
የኢትዮጵያን ነገረ-ፖለቲካ በቅርበት የሚከታተሉ የአገር ውስጥና የምዕራቡ አለም ምሁራን የድህረ-መለስ ኢህአዴግ ፖለቲካዊ ማሻሻያዎችን ያደርጋል ብለው በተስፋ ቢጠብቁም ከታሰበው በተቃራኒ መንገድ ሲጓዝ እየታየ ነው። ተራማጅ የፖለቲካ ሀሳብ ያረጠበት ድርጅት አፈናና ግድያ መገለጫው ሆኗል። የአገዛዙን ምሰሶ ለማጥበቅ ሲባል ህገ-መንግስታዊ ድጋፍ የሌላቸውን የፖለቲካ ሹመቶች በመንግስታዊ መዋቅር ከመሰግሰግ ጀምሮ በፓርቲና በመንግስት መካከል ፍጹም ልዩነት የለሽ አሰራሮችን አጠንክሮ መጓዝን መፍትሄ አድርጎ ይዞታል።
በአራት ነጥብ ግትር አቋም የታጠረው ኢህአዴግ፤ የፖለቲካ ተቋማት የፖለቲካ ብዝሃነትን እንዲያስተናግዱ ምቹ መደላድል ከመፍጠር ይልቅ የአንድ ፓርቲ ፍጹም የበላይነት የሚንጸባረቅባቸው ተቋማት እንዲሆኑ አድርጓል። የዲሞክራሲ ስርዓት የግድ የሚለውን የፖለቲካ ብዙሃነት በኢትዩጵያ የፖለቲካ ተቋማት ላይ የቀበረው ኢህአዴግ የቁልቁለት ጉዞውን ተያይዞታል። ለድርጎ ሰፋሪዎቹና አይዞህ ባዩ የምዕራቡ አለም መንግስታት አፍ ማዘጊያ አስመሳይ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት በመፍጠር በፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ስም ቀለብ በመስፈር የፖለቲካ አደባባዩን ለማፈን ቢተጋም የሀገሪቱ ፖለቲካዊ እውነት በሰፊው ህዝብ ላይ ከመንጸባረቅ ወደ ኋላ አላለም።
የዲሞክራሲ ተቋማት የገዥው ፓርቲ ምርኩዝ ከመሆን አልፈው የአድርባይነት ጉምቱ ምሳሌ ሆነዋል። በሀገሪቱ የሙስና መበራከት ዜጎች “መንግስት” በሚባለው አካል እምነት እንዲያጡ አድርጓቸዋል። የፖለቲካ ነፃነት፣ የማህበራዊ ፍትህና ሌሎች ህገ-መንግስታዊ የመብት ጥያቄዎችን ኃላፊነት በሚሰማው መልኩ ማስተናገድ የተሳነው የበርኸኞቹ ስብስብ ለህዝባዊ ጥያቄዎች እስር፣ እንግልት፣ ስቅየትና፣ ግድያን እንደ ብቸኛ መፍትሄ አድርጎ ይዞታል። የኢህአዴግ ማንአህሎኝ ባይነት እርምጃዎች አገሪቱ ልትወጣው ወደማትችለው የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ እየከተታት ይገኛል።
በበርኸኞቹ የፖለቲካ መሀንዲስነት የሚዘወረው ኢህአዴግ ለህዝባዊ ጥያቄዎች ፖለቲካዊ መፍትሄ ከመሻት ይልቅ ወታደራዊ የኃይል አማራጭን እንደ መፍትሄ ሲወስድ እየታየ ነው። ከዚህ አደገኛ ተግባር ተነስተን፤ በርኸኞቹ በሩብ ክፍለ ዘመን የአገዛዝ ጉዟችው ውስጥ የሲቪል አስተዳደር ጥበብን ከመላመድ ይልቅ ወታደራዊ ባህሪያቸው እየፋፋ እንደመጣ መረዳት ይቻላል። በድህረ-መለስ አራት የአገዛዝ አመታት ውስጥ ኢህአዴግ በአያሌው የተፈተነበት ዓመት ቢኖር እያገባደድነው ያለው 2008 ዓ.ም በቀዳሚነት ይጠቀሳል።
አስር የጭንቅ ወራት ያስቆጠረው የኦሮሞ ተቃውሞ እንደተጠበቀ ሆኖ በአገሪቱ የሰሜን ምዕራብ አካባቢ የማንነት ጥያቄን አስታኮ የተነሳው ብረት አከል ህዝባዊ እምቢተኝነት የኢትዮጵያን ነገ እንድንፈራው አድርጎናል። የችግሩን አሳሳቢነት የሚያጎላው ደግሞ ገዥው ፓርቲ ለችግሩ እውቅና በመስጠት ፖለቲካዊ መፍትሄ ከመሻት ይልቅ ወታደራዊ የኃይል እርምጃዎችን የሙጥኝ ብሎ መያዙ ነው። ለወታደራዊ የኃይል እርምጃዎች የማይንበረከክ ባለ ብረት ህዝብ፣ ቁሞ መሞትን ምርጫው አለማድረጉ ደግሞ ሀገሪቱ ወደ አዝጋሚ ጦርነት እየተጓዘች ያለች አስመስሏታል።
የሰሜን ምዕራብ ፖለቲካ
በዚህች ጽሁፍ ‹ሰሜን ምዕራብ› እያልን የምንጠራው አካባቢ በመደበኛው የመልከዓ-ምድር ስያሜ ሳይሆን ውስንነት ባለው መልኩ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃምን እንዲሁም የሰሜንና ደቡብ ጎንደር አካባቢዎችን ይሆናል። በዋናነት የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄን አስታኮ እየታየ ያለው ህዝባዊ እምቢተኝነት ማዕከል የሆነውን ጎንደር ከተማና አካባቢውን ይመለከታል።
በተለያዩ የህትመትና የኤሌክትሮኒክ ሚዲያዎች ብዙ እየተባለለት ያለውን የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ፤ የማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ያቀረቡትን አቤቱታና ሌሎች መሰረታዊ ቅሬታዎችን በተመለከተ በጣም አቃለልከው ካልተባልኩ በሚቀጥለው አንቀጽ ማጠቃለል ይቻል ይመስለኛል።
በቀደመው የኢትዮጵያ ታሪክ የትግራይ ወሰን ተከዜ መሆኑን የታሪክ መዛግብት ያትታሉ። ከመካከለኛው ዘመን እስከ 21ኛውክፍል ዘመን ድረስ ኢትዮጵያን በተለይም ሰሜኑን አካባቢ ባጠኑ የታሪክ ተመራማሪዎችና የታሪክ ፀሐፍት የትግራይ ወሰን ተከዜን ተሻግሮ እንደማያውቅ ይገልፃሉ። የወልቃይት መልከዓ-ምድር በሰሜን ተከዜ (ኤርትራ)፣ በደቡብ ጠገዴ (ጠገዴ በአማራ ክልል ስር ያለ ወረዳ ሲሆን፤ ጸገዴ ደግሞ በትግራይ ክልል ስር ያለ ወረዳ መሆኑንና በሁለቱም ወረዳዎች የሚኖረው ነባር ህዝብ ከታሪክ፣ ቋንቋ፣ ባህል፣ የኢኮኖሚ ትስስርና መልከዓ-ምድር አኳያ ምንም አይነት ልዩነት የሌለው መሆኑን ይልቁንስ ልዩነቱ ድህረ-ደርግን ተከትሎ ‹ጠ› እና ‹ጸ› በሚሉ ፊደላት ብቻ ልዩነት ለመፍጠር እንደተሞከረ ያስታውሷል)፣ በምስራቅ የተከዜ ወንዝን (ትግራይ) በምዕራብ አርማጭሆና ሱዳን ወልቃይትን ያዋስኑታል። ወልቃይት በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በሰሜን በጌምድር ጠቅላይ ግዛት ወገራ አውራጃ፣ በደርግ ግዜ ደግሞ በጎንደር ክፍለ ሀገር በወገራ አዉራጃ ይተዳደር የነበረ አካባቢ ነዉ። ይሁንና በዘመነ ኢህአዴግ ያለ ወልቃይት ነባር ህዝብ ፍላጎት የህዝቡን ማንነት በሚጨፈልቅ መልኩ በትግራይ ክልል፣ በምዕራብ ትግራይ ዞን ተከልሎ ይገኛል። የወልቃይት ነባር ህዝብ የራሱ የሆነ የአማርኛ ዘይቤ ያለው ሲሆን፣ የትግርኛ ቋንቋም ከገበያ ትስስር ጋራ በተያያዘ በተጨማሪነት ይናገራል። ከሱዳን በሚዋሰንበት የምዕራብ ወልቃይት አካባቢ የሚኖሩ ዜጎች የሱዳን አረብኛ ለመግቢያነት ይጠቀማሉ። የወልቃይት ነባር ህዝብ በቀደመው ጊዜ ባህላዊ ዘፈኑ፣ ጭፈራውና ዳንኪራው፣ የሃዘን እንጉርጉሮ፣ ቀረርቶውና ሽለላው ከትግራይ ባህላዊ ሁነት ይልቅ ለጎንደር ባህል ይበልጥ ቅርብ ነበር/ነው። ይሁንና አዲሱ የፌዴራሊዝም ሥርዓት ተግባራዊ መሆን ከጀመረ በኋላ የወልቃይት ነባር ህዝብ የሚናገረው አማርኛ ቋንቋና የአካባቢውን ባህላዊ ማንነት በሚጨፈልቅ መልኩ በሰፈራ ፕሮግራም አካባቢውን በተቆጣጠሩት የትግራይ ብሄርተኞች ሊዋጥ ችሏል።
“ለዘመናት የወልቃይት ህዝብ (ገበሬ) ሲያርሰው የነበረ መሬት ተነጥቆ ለትግራይ እርሻ ድርጅት ተሰጥቷል። ህዝቡ እኛ የት እንውደቅ ተብሎ አቤቱታ እንኳን ቢያቀርብም የትግራይ ክልል በየአመቱ ለምዕራባዊ ዞን እያለ አዳዲስ የመሬት አዋጅ በማውጣት ለትግራይ ተወላጅ በወልቃይት መሬት ባላባት ሆነው እንዲያስተዳድሩት ሲደረግ የወልቃይት ህዝብ ግን ከመሬቱ እንዲነሳና እንዲሰደድ የተለያዩ እርምጃ ተወስደዋል። የዚህ ሰለባ የሆኑት የወልቃይት ተወላጆች ለአብነት፡- በአማራ ክልል በሶረቃ፤ አብራሃጅራ፤ አብደራፊ፤ መተማ፤ ቋራ፤ ሽህዲ፤ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል እና በጋምቤላ ክልል ተሰደው ይገኛሉ። በሰፈራ የወጡት የትግራይ ተወላጆች ግን ከሁለት ሄክታር አልፈው የሃምሳና የአንድ መቶ ሄክታር ባለቤቶች ሆነው ይታያሉ። በአጠቃላይ በአካባቢያችን አልምተን እንዳንጠቀም አድልዎ ተፈጽሞብናል። … ልጆቻችን በቋንቋቸው እንዳይማሩ ተደርጓል። … የአካባቢያችን ጥንታዊ የሀገር፤ የወል እና የጋራ ስሞች ማለትም የወረዳ፤ ከተማ፤ መንደር፤ ወንዝ ጋራ ሸንተረር በትግረኛ ስም ተሰይመዋል”።
ከላይ የተመለከተው አንቀጽ የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ካቀረቡት ባለ ስምንት ገጽ አቤቱታ ተቀንጭቦ የቀረበ ነው። ይህች አንቀጽ የወልቃይትን ህዝብ የባህልና ማንነት ቅሬታዎችን እንዲሁም የኢኮኖሚ መገለልን ይበልጥ የምትገልጽ ነች። ከዚህ በላይ ለተመለከቱት የባህልና ማንነት ቅሬታዎች አሁንም የኢኮኖሚ መገለል የተጋለጡት ወልቃይቴዎች ለሁለት አስርት ዓመታት የማንነት ጥያቄውን በያዝ ለቀቅ፤ ከረር ላላ ባለ መልኩ ጥያቄውን ሲያገላብጡት ቆይተው ካለፉት ሁለት አመታት ወዲህ የማንነት ጥያቄውን የሚያስተባብሩ የኮሚቴ አባላትን በመምረጥ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት አቤቱታቸውን አሰምተዋል። የማንነት ጥያቄው ወደ አፈሙዝ ቋንቋ ከመቀየሩ በፊት ጥያቄውን በተመለከተ ወልቃይቴዎች በሰላማዊ መንገድ ህዝባዊ ስብሰባዎችን ከሽንፋ እስከ ጎንደር ድረስ ባሉ ከተሞች በተለያዩ ግዜያት አድርገዋል።
ለምን አሁን?
የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ ወደ ፊት ጎልቶ እንዲወጣ ያደረጉት ውስጣዊና ውጫዊ ገፊ ምክንያቶችን በቢሆን እድል ለይቶ ማስቀመጥ ይቻላል። ከውስጣዊ ግፊት አኳያ በቀዳሚነት ሊጠቀስ የሚችለዉ የቢሆን እድል ነባሩ የወልቃይት ህዝብ ከባህልና ማንነት ጋር በተያያዘ የሚያቀርባቸው ቅሬታዎችና የኢኮኖሚ መገለሎች እንዲሁም ያለፉት ሁለት አስርታት ተደማሪ ቅሬታዎችንና ብሶቶችን እየሰሙና እያዩ ያደጉት የአዲሱ ትውልድ አባላት የማንነት ጥያቄው ገፍቶ እንዲወጣ ተጽእኖ አሳድሯል ማለት ይቻላል።
ለወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ ጎልቶ መውጣት ውጫዊ ገፊ ምክንያቶችን ደግሞ በሦስት የቢሆን እድሎች ለይተን ማየት እንችላለን።
የቢሆን ዕድል አንድ፡- የዘውግ ፖለቲካን ዋነኛ የሀገሪቱ የፖለቲካ ተዋጽዖ እንዲሆን በትጋት እየሰራ ያለው ኢህአዴግ፤ የማንነት አረጋጋጭ ጥያቄዎችን መልስ ሰጥቼ ጨርሻለሁ ቢልም፤ በዘመነኛ አጥኝዎች አጠራር ከዘውግ ብሄርተኝነት አነስ ያሉ የትህተ-ብሄርተኝነት ጥያቄዎች ይነሱበት ጀምረዋል። እነዚህ ጥያቄዎች ከመሰረቱ የተበላሸው የፌዴራሊዝም ቅርጽ የወለዳቸው እንደሆኑ የሥርዓቱ ተቺዎች እምነት ነው። ከረፈደ የሚቀሰቀሱ የማንነት ጥያቄዎች የበዙበት ኢህአዴግ፤ ምንም እንኳ ጥያቄዎቹ የቆዩ ቢሆንም በድህረ መለስ የአገዛዝ ዘመኑ ሁለት የማንነት ጥያቄዎችን አስተናግዷል። የቅማንትና የቁጫ ማንነት አረጋጋጭ ጥያቄዎች ፌደሬሽን ምክር ቤት ደርሰዉ የቁጫ ማህበረሰብ የማንነት ጥያቄ ተቀባይነት ሳያገኝ ሲቀር፤ የቅማንት የማንነት ጥያቄ ግን በፌደሬሽን ምክር ቤት መሪነት የአማራ ክልል ምክር ቤት መጋቢት 2007 ዓ.ም የይሁንታ ውሳኔ ሰጥቶበታል።
የቅማንት የማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ባቀረቡት የድንበር ማካለል/ወሰን ልክ ባይሆንም የቅማንት ብሄረሰብ በልዩ ወረዳ ስር አርባ ሁለት የገጠር ቀበሌዎችን በማቀፍ እንዲከለል የክልሉ ምክር ቤት ውሳኔውን አሳልፏል። ይህ ውሳኔ ለወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላትና አማራነታችን ይከበር ለሚሉ ወልቃይቴዎች የማንነት ጥያቄውን እንዲያቀጣጥሉት በር ከፍቶላቸዋል። የቅማንት ብሄረሰብና የወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄ አቀራረብ ሞዴል የተለየ ቢሆንም ኢትዮጵያ ውስጥ የዘውግ ፖለቲካ እስከተራመደ ድረስ፤ የማንነት ጥያቄዎች ማቅረብ ህገ-መንግስታዊ መብት መሆኑንና ከረፈደም ቢሆን የማንነት ጥያቄዎችን ምላሽ እንደሚያገኙ የተማመኑት የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት የማንነት ጥያቄዉን በአዲስ ጉልበት እንዲጀምሩት ምክንያት እንደሆናቸው በቀዳሚ የቢሆን እድል ማስቀመጥ ይቻላል።
የቢሆን ዕድል ሁለት፡- በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን ስር እንደ አብርሃጅራ፤ አብደራፊ፤ ጠገዴ የተሰኙ ወረዳዎች ስር ካሉት የገጠር ቀበሌዎች የተወሰኑትን በተለይም ምዕራብ አርማጭሆ አካባቢ ያሉትን የገጠር ቀበሌዎች ወደ ትግራይ ክልል ለመደባለቅ የሚደረገው የክልሉ መንግስት እንቅስቃሴ በአካባቢው ህብረተሰብ እምቢተኝነት ዛሬም ድረስ ሊሳካ አልቻለም። አካባቢውም ውጥረት የነገሰበትና በየጊዜው ከንብረት መውደም አልፎ እስከ ህይወት መጥፋት የሚደርስ ግጭት በተደጋጋሚ እየተከሰተ በመንግስት ኃይሎች ጣልቃ ገብነት ግጭቶችን “የማብረድ” ስራ ሲሰራ ቆይቷል። የአማራ ክልል እና የትግራይ ክልል ርዕስ መስተዳድሮች፤ ከፀጥታና ደህንነት ጋር የተያያዘ ስራ የሚሰሩ የካቢኔ አባላትና ተስማሚነት ያላቸው የአገር ሽማግሌዎች በተገኙበት በተደጋጋሚ የተካሄዱ ውይይቶች ፍሬ አልባ ሆነዉ በመቅረታቸው አካባቢው ሁሌም ቢሆን ውጥረት የነገሰበት ሊሆን ተገዷል። በዚህ የተነሳ የትግራይና የአማራ ክልል ግልጽ የሆነ የድንበር አዋሳኝ ቦታ የላቸውም። ይህን ጉዳይ ከወልቃይት መሬት ጋር አስተሳስረው ለማየት የሚሞክሩ የአካባቢው መካከለኛ አመራሮች ለወልቃይት የአማራ ብሄርተኝነት ጥያቄ መቀጣጠል የራሳቸውን ድጋፍ ሲያደርጉ እንደነበር የመረጃ ምንጮች ይጠቁማሉ።
በሁለቱ ክልል የድንበር ወሰን ላይ በተለይም “ግጨው” (የቦታ ስም መሆኑን ያስታዉሷል) እና በአካባቢው የሚነሱ ደም አፋሳሽ ግጭቶች በአካባቢው መካከለኛ አመራሮች ጥልቅ ቅሬታን እየፈጠረ በመሄዱና ‹የትግራይ ወሰን ተከዜ ነው› የሚለው ተረክ አካባቢውን በሚያስተዳድሩ የአማራ ክልል መካከለኛ አመራሮች እያጎነቆለ በመምጣቱ የወልቃይት የአማራ ብሄርተኝነት ጥያቄ የደጀን ኃይል ድጋፍ አግኝንቶ ሊያንሰራራ እንደቻለ በሁለተኛ ደረጃ የቢሆን እድል ማስቀመጥ ይቻላል።
የቢሆን ዕድል ሦስት፡- በሦስተኛ ደረጃ የሚቀመጠው የቢሆን እድል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከሁለቱም የቢሆን ዕድሎች ጋር ይገናኛል። የቅማንት የማንነት ጥያቄ ከቋንቋው ተናጋሪዎች መመናመንና የባህል መግለጫዎቹ በአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪው እየተዋጡ (assimilate) መሄዳቸውን እንደ ምክንያት በማቅረብ የቅማንት የማንነት ጥያቄ ለማፈን የክልሉ መንግስት ብዙ ርቀት ለመጓዝ ሞክሯል። በዚህም የማንነት ጥያቄ አቅራቢዎች ከክልሉ ልዩ ኃይል ጋር ደም አፍሳሽ ግጭቶች አካሂደዋል። በፌዴራሉ መንግስት መሪነት የማንነት ጥያቄው በክልሉ ምክር ቤት ምላሽ እንዲሰጠው መደረጉ ይታወሳል። የቅማንት የማንንት ጥያቄ ከአመታት ዝምታ (ያዝ ለቀቅ) በኋላ በአዲስ ኃይል ገንኖ ሊወጣ የቻለበት ምክንያት የትግራይና የአማራ ክልል ድንበር ውዝግብ የአካባቢውን ውጥረት እያባባሰው ከመጣ ወዲህ ነው። የድንበር ውዝግቡ በዋናነት በምዕራብ አርማጭሆ በኩል የ“ግጨው” ቦታና አካባቢው ሲሆን፤ ጉዳዩ በሁለቱም ክልል ርዕስ መስተዳድሮች ተይዞ ሰፊ ድርድር (ክርክር ማለት ይቀላል) የተካሄደበት፤ ከዚህም ባሻገር በአካባቢው ገበሬዎች መካከል ደም አፋሳሽ ግጭት ተካሂዷል። የህወሓት አመራሮች ይህን ውጥረት ለማስቀየስ (tension divert ለማድረግ) የቅማንት የማንነት ጥያቄ ጎልቶ እንዲወጣና የአማራ ክልል መንግስት በቅማንት የማንነት ጥያቄ እንዲጠመድ ማድረጋቸው የብዙዎቹ የጉዳዩ ተከታታዮች ምልከታ ነው (ይህን ጉዳይ በተመለከተ “የኢህአዴግ ቁልቁለት” የሚለውን መጽኀፍ በማንበብ ተጨማሪ መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል)።
ወትሮዉንም ቢሆን የሴራ ፖለቲካ የተጣባው የኢህአዴግ ፖለቲካ አሁን ደግሞ ተራው የብአዴን ሆነና የወልቃይት የማንነት ጥያቄ ወደፊት እንዲገፋ ሁኔታዎችን የሚያመቻቹ አመራሮች ያሉ ይመስላል። ይህን የቢሆን እድል ይበልጥ የሚያጠናክረው ከሀምሌ 04/2008 ጀምሮ በሰሜን ምዕራብ እየታየ ያለውን ደም አፋሳሽ ግጭት በተመለከተ የአማራ ክልል መንግስት የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊዉ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ለክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጠዉ መግለጫ የ“መልካም አስተዳደር እና የማንነት ጥያቄዎችን መነሻ ያደረገ” መሆኑን አምኗል። በአንጻሩ የፌዴራሉ መንግስት “ጸረ-ሰላም ኃይሎች፣ የጥፋት ተልዕኮ ያላቸው፣ በአንድ ብሄር ያነጣጠረ ጥቃት …” በሚሉ ቃላት የታጀቡ ተከታታይ መግለጫዎችን በማውጣት የማንነት ጥያቄውን ታኮ የተፈጠረውን ግጭት ለማድበስበስ ሲታትር ተስተውሏል። የአማራ ክልልና የፌዴራሉ መንግስት በጉዳዩ ላይ እየሰጡት ያለውን ያልተናበበ መግለጫ በሴራ ፖለቲካ ልዩነት መስመር መሀል ስናስተውል የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ ጎልቶ ሊወጣ የቻለበት ምክንያት ግልጽ ይሆንልናል።
“ … ብናረፍድም የአማራ ክልል ህዝብ ከጎናችን ነው!”
ሐምሌ 04/2008 ዓ.ም ምሽት፤ ጎንደር ከተማ ላይ የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ ስራ አስፈጻሚ አባላትን ለማሰር የተደረገው ዘመቻ በፌዴራሉ መንግስት አገላለጽ “እክል” የገጠመው በመሆኑ ምሽቱንና በተከታታይ ሁለት ቀናት በጸጥታ ኃይሉና በከተማዉ ነዋሪ መካከል ደም አፍሳሽ ግጭቶች ተከስቷል። በወቅቱ የፌዴራሉ መንግስት ባመነው መረጃ መሰረት 9 የፌዴራል፣ አንድ የመከላከያ እና አንድ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ፖሊስ በድምሩ 11 የሰራዊቱ አባላት እንደተገደሉ፣ ከሲቪል ደግሞ 5 ሰዎች እንደሞቱ በተጨማሪም 9 የሰራዊቱ አባላት ቁስለኛ እንደሆኑ መገለጹ የሚታወስ ነው። ከሐምሌ 05-06/2008 ዓ.ም ድረስ በዘለቀው ህዝባዊ አመጽ በአስር ሚሊዮኖች የሚገመት ንብረት መውደሙም ይታወሳል።
የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ የታፈነው ህዝባዊ አመጽ መቀስቀሻ ሆኖል። ሐምሌ 24/2008 ጎንደር ከተማ ታሪኳን በሚመጥን መልኩ ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ተደርጓል። የተቃውሞ ሰልፉ በከተማ አስተዳደሩ እውቅና ያልተሰጠው ቢሆንም ብሶት የማያስጉዘው መንገድ የለምና የጎንደር ከተማና አካባቢ ነዋሪ በእለቱ ህግና ፍርድን በእጁ በመጨበጥ መብቱን አስከብሯል። ጎንደር የነፃነትና የክብር ፋና ከተማ መሆኗን ባስመሰከረችበት የተቃውሞ ሰልፍ ቀዳሚ አጀንዳ ሆኖ የቀረበዉ የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄና የታሰሩ የኮሚቴ አባላትን በተመለከተ ነበር። ከዚህ ጎን ለጎን ለብዙዎቹ የጉዳዩ ተከታታዮች ግርምት ሊፈጥር የቻለው በኦሮሚያ የሚደረገውን የብላቴናዎች ግድያና አፈና አጥብቀው የሚያወግዙ፣ የፖለቲካ ነፃነት መሻትን የሚያንጸባርቁ፣ የማህበራዊ ፍትህ ጥያቄዎችን ያዘሉ፣ አፋኝ አዋጆችን የሚቃወሙ፣ የኃይማኖት ነጻነትን የሚጠይቁ፣ … መፈክሮች በሰልፉ ላይ ተሰምተዋል። ከሁለቱ ታላላቅ ኃይማኖቶች (ኦርቶዶክስና እስልምና) የተጋበዙ የኃይማኖት አባቶች በተገኙበት የተቃውሞ ሰልፍ አራት መቶ ሃያ ሺህ የሚሆን ህዝብ ተሳታፊ እንደነበረ ይገመታል። የጎንደር እናቶች የመላኩ ተፈራ የመከራ ጊዜ ከአደባባይ እንዲያፈገፍጉ ሳያደርጋቸው የተቃውሞ ሰልፉ ተሳታፊ ሆነዋል። እናቶች በሰልፉ ተሳታፊ ለሆኑ ወጣቶች ከእንስራቸው ውሀ እየጨለፉ ሲያጠጡ የታየበት ሁኔታ ህዝባዊ ብሶቱ ምን ድረስ እንደዘለቀ ማሳያ ሊሆን ይችላል። በሰልፉ ማጠናቀቂያ ላይ የሰልፉ አስተባባሪዎች የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄን በተመለከተ ጥያቄውን በህገ-መንግስታዊ አግባብ እንዲመለስ፣ የታሰሩ የኮሚቴ አባላት እንዲፈቱ አጽኖት ሰጥተዉ ጠይቀዋል። የማንነት ጥያቄውን ወደ አደባባይ ለማውጣት ብዙ መስዋዕትነት እንደተከፈለበት የተናገሩት የሰልፉ አስተባባሪዎች “የማንነት ጥያቄውን ለማቅረብ ብናረፍድም የአማራ ክልል ህዝብ ከጎናችን ነው!” በሚል ደስተኛነታቸውን ገልጸዋል። ያለምንም የጸጥታ ግርግር የተጠናቀቀው የጎንደሩ የተቃውሞ ሰልፍ፤ በቀጣዮቹ ሳምንታት በሌሎች የክልሉ ከተሞች ላይ ለተካሄዱ የተቃዉሞ ሰልፎች መነቃቃት ፈጥሯል። ይሁንና ህዝባዊ ጥያቄዎችን ለሚያንጸባርቁ ሰልፈኞች አጸፋው ጠብ-መንጃ ሆነና ብዙዎቹ ብላቴኖች እንደወጡ ቀርተዋል። የአካል ጉዳተኛ የሆኑትን ቤት ይቁጠራቸው።
ከጎንደሩ የተቃውሞ ሰልፍ በኋላ ደባርቅ፣ ደባት፣ ሳንጃ፣ ሶረቃ፣ አብራሃጅራ፣ ማክሰኝት፣ ቆላድባ፣ አዲስ ዘመን፣ ወረታ፣ ሀሙሲት፣ ደብረታቦር፣ ንፋስ መውጫ (ጋይንት)፣ ባህርዳር፣ ጢስ አባይ፣ ፍኖተ ሰላም፤ ደብረማርቆስ ከተሞች ላይ ህዝባዊ ተቃውሞዎች ተካሄደዋል። በብዙዎቹ የተቃውሞ ሰልፍ በተካሄደባቸው ከተሞች የመንግስት ኃይሎች በወሰዱት የኃይል እርምጃ የብዙ ሰልፈኞች ህይወት ሊያልፍ ችሏል። በተለይም በደብረ ታቦርና በባህርዳር ከተማ የተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች የብዙዎቹን የሰላማዊ ትግል አቀንቃኞች እምነት በሚፈትን መልኩ የብዙ ብላቴኖች ህይወት በጎዳና ላይ ተቀጥፏል (ከእያንዳንዱ ከተማ የሚሰማው የሟቾች ቁጥር የተለያየና ተቀራራቢነት የሌለዉ በመሆኑ የሟቾችን ቁጥር እዚህ ላይ መጥቀሱ አንባቢን ማሳሳት ስለሚሆን ቁጥሩን መዝለሉ የተሻለ ነው)።
መፈክር ይዘው የወጡ ብላቴናዎች የጓደኞቻቸውን አስክሬን ተሸክመው ወደየሰፈራቸው ተመልሰዋል። በከፍተኛ የሀገር ፍቅር ስሜትና ወኔ ሰልፉን የተቀላቀሉ ጎልማሶች በቃሬዛ ወደ ቤታቸው ገብተዋል። ግፈኞች “በለው!” ማለታቸውን አላቆሙምና እናቶች ዛሬም እንደ ትላንቱ ዋይታ አልተለያቸውም፣ አባቶች ምርኩዝ አቀባይ ልጆቻቸውን ተነጥቀዋል። ጎዳናዉ የብላቴኖችን ደም መምጠጥ አልሰለቸውም። መንግስታዊ ፍጅት በሚመስል መልኩ በተወሰደው የኃይል እርምጃ አትራፊው ማን እንደሆነ ግዜና ትውልድ የሚወስነው ይሆናል።
የኢትዮጵያ ነገ …
ፖለቲካዊ ሁኔታዎች በፍጥነት በሚቀያየሩባት ኢትዮጵያ ነገን መተንበይ አስቸጋሪ ያደርገዋል። ይሁንና የኢትዮጵያን ዛሬ ስናስተዉል የትላንቷ ኢትዮጵያ ዉጤት መሆኗ ከአንባቢ የተሰወረ አይደለም። በዚህ አግባብ የኢትዮጵያ ዛሬ ስለ ነገዋ ኢትዮጵያ ምስል የሚሰጠን ጭብጥ ይኖራል።
የድህረ መለስ ኢህአዴግ የበዛ ዝግ አምባገነንነት ምርጫዉን አንድ መቶ ፐርሰንት ከመጠቅለል ጀምሮ የአፈና እጆቹ እየበረቱ መጥተዋል። የምርጫ ፖለቲካን ሁለንተናዊ ፋይዳ አርቆ የቀበረዉ ኢህአዴግ፤ የፖለቲካ አደባባዩን የመቃብር ስፍራ አስመስሎታል። ያም ሆኖ ፖለቲካዊ መብቃት ላይ ያልደረሱ ብላቴኖች የህዝባዊ አመጹ አቀጣጣይ ሆነዋል። አንዳች የቅቡልነት መነሾ የሌለዉ ኢህአዴግ ሁሉን ጠቅልሎ የመግዛት አባዜዉ የበዛ ዋጋ የሚያስከፍለዉ ጊዜ ላይ ይገኛል።
አስር ወራትን ያስቆጠረዉ የኦሮሞ ተቃዉሞ የወዲያዉኑ መንስኤ “የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን” ቢሆንም፣ ማስተር ፕላኑ ከተሰረዘ በኋላም ተቃዉሞዉ ተጠናክሮ ቀጥሏል። እጅግ በተጠናና በተደራጀ መንገድ በሚመስል መልኩ በኦሮሚያ ክልል ያሉ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን ጨምሮ እስከ ዮኒቨርስቲ ባሉ የክልሉ ተወላጅ ተማሪዎችን ባቀፈ መልኩ የተካሄዱ ተከታታይ ሰላማዊ ሰልፎች የወጣቶች ግድያና እስር ተጠናክሮ ቀጥሏል። የተቃዉሞዉ መሰረት በጊዜ ሂደት እየሰፋ መጥቶ በሁሉም የኦሮሚያ ዞኖች በተፈራራቂነት በመዝለቁ ህዝባዊ ተቃዉሞዉ መቆሚያ አጥቷል። እንደ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ተከታታይ ሪፖርቶች ሐምሌ 30/2008 ዓ.ም በሁሉም የኦሮሚያ ከተሞች በተጠራዉ የተቃዉሞ ሰልፍ የሞቱትን ጨምሮ አስር ወራትን ባስቆጠረዉ የኦሮሞ ተቃዉሞ ከ600 በላይ ሰዎች ህይወታቸዉ አልፏል። ኦሮሚያ ክልል በሲቪል አስተዳደር እየተመራች ያለ የሚመስለዉ በ“መንግስት” ሚዲያ ነዉ እንጂ በእዉነታዉ በወታደራዊ አስተዳደር ስር ወድቃለች።
ጥልቅ የማንነት ቅሬታዎችንና የኢኮኖሚ ብዝበዛ ተረክን እየሰሙ ያደጉት የኦሮሞ ልጆች የመሬት ባለቤትነትን አስታከዉ ያነሱት ተቃዉሞ ወደ ቀደመዉ መሰረታዊ ቅሬታ ተጠምዞ ‹የፖለቲካ ነጻነትና በማዕከላዊ መንግስቱ በቁመታችን ልክ የፖለቲካ ዉክልና ይስጠን! የኢኮኖሚ የራስ ገዥነት አቅማችን በህዳጣኖች አይወሰንም! ኦሮሚያን ለኦሮሚያ!› ወደሚል ፈታኝ አቋም ተሻግሯል። ይህ አቋም ብዙዎች የኦሮሞ ልጆች ሊወድቁለት የፈቀዱት እዉነት ሆኗል። እየሆነ ያለዉም ይሄዉ ነዉ።
በመስመር መሀል ለወራት ድምጹን አጥፍቶ የቆየዉ “የድምጻችን ይሰማ!” የሙስሊሙ ንቅናቄ በየአቅጣጫዉ በሚታዩ ህዝባዊ ተቃዉሞዎች አስታከዉ አጀንዳቸዉን በማንጸባረቅ ላይ ናቸዉ። ይህ መነቃቃት ምናልባትም በቀጣይ ወራት የንቅናቄዉ መገንፈል ከታየ የምዕራቡንና ምስራቁን የኢትዮጵያ አካባቢ ሊያዳርሰዉ ይችላል። የሙስሊሙ ንቅናቄ በራሱ ኃይማኖታዊ ነጻነትንና የኮሚቴዎቹን ጉዳይ በሚያጠይቅ የአጀንዳ መስመር ተነጥሎ ባይወጣ እንኳ በየአቅጣጫዉ እየታዩ ላሉ ህዝባዊ እምቢተኝነቶች መጎልበት ቀላል የማይባል ዋጋ ይኖረዋል።
የኢትዮጵያን ባህል መለዮ አርቃቂዉ አማራ በቅሬታ የተሞሉ ሃያ አምስት አመታትን ገፍቷል። የደርጉ ወታደራዊ ዘመን እንደ ሀገር የመጣ መዐት በመሆኑ አስከፊነቱ የወል ገጽታ ነበረዉ። ዛሬ ላይ የአማራ ጉዳይ የሥልጣን ጥያቄን በሁለተኛ አጀንዳ በመያዝ ማንነትን የማስከበርና ህልዉናን የማስቀጠል ጉዳይ ሆኗል። ሩብ ክፍለ ዘመን የተሻገረዉ የገዥዉ ግንባር አገዛዝ እንደ አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዉ ፈተና ያበዛበት ዘዉግ ቢኖር ኦሮሞ ብቻ በደሉን የሚስተካከለዉ ይመስለኛል።
ብሶት ህወሓትን ብቻ ወልዶ አልቆመምና ለአመታት የተከማቸዉ ግፍና ጭቆና በአማራ ክልል በተለይም በሰሜን ጎንደር አካባቢ እየተስተዋለ የመጣዉ ብረት ማንሳትን ያካተተ ህዝባዊ አመጽ ቀስቅሷል። ብረት አከሉ ህዝባዊ አመጽ የአመጹን ተራዛሚነት ከማበርታት ባሻገር ኢ-ተቀልባሽ ያደርገዋል። ዘውግ ተኮር የማንነት ትንቅንቅ የሀገሪቱ ዋነኛ ፖለቲካዊ ክስተት በሆነባት ኢትዮጵያ ለማንነታቸዉ የሚወድቁ ወጣቶች ቢፈጠሩ የሚገርም አይደለም።
ጥልቅ ድህነትና ሥራ አጥነት በስፋት በሚስተዋልባቸዉ ሁለቱም ክልሎች እየታየ ያለዉ ህዝባዊ እምቢተኝነት በማህበራዊ ድረ-ገጾች የጥላቻ ንግግሮች/ጽሁፎች መታጀብ ጀምሯል። ይህ አዝማሚያ የገዥዉ ግንባር አስኳል-ህወሓት ላይ የሚያርፍ ይሆናል። በህወሓት አመራሮች የበዛ የሥልጣን ጥመኝነት የተነሳ የህወሓት አወዳደቅ ከትግራይ ህዝብ ጋር የሚያያዝበት ሁኔታ እንዳይኖር ያሰጋል። በበሽር አላሳድ ቤተሰቦች በኩል የአላዋይቶች ጉዳይ እንደሚታየዉ ህወሓት ይህችን መሰል የፖለቲካ ቁማር መጫወት ሳይጀምር (አንዳንዶች ጨዋታዉን ከጀመረ ቆይቷል ይላሉ) የትግራይ ህዝብ ዝምታዉን በመስበር የህወሓትን አደጋ ያዘለ የጉርምስና ተግባር ‹ተዉ!› ሊለዉ ይገባል። ይህ የማይሆን ከሆነ የኢትዮጵያ ነገ ከተስፋ ይልቅ የጭንቅና መዐት ጊዜ እንደሚሆን እሙን ነዉ። የርስ በርስ ጦርነትም የቀረበ እንጅ የራቀ አይሆንም።
መዉጫ በር!
ሀገሪቱ ለገባችበት የፖለቲካ ቅርቃር ወታደራዊ እርምጃ ሳይሆን ፖለቲካዊ መፍትሄ ያሻታል። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ልሂቃኑ በብቸኝነት የያዙት መሆኑ ለክርክር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም። ‹በልሂቃን የበላይነት ተጠፍንጎ የተያዘዉን የፖለቲካ ተሳትፎ፤ የፖለቲካ ተሳታፊነት መብት የበርካታ የሀገሪቱ ዜጎች መብት ማድረግ ይገባል› የሚለዉን የተቺዎች ምልከታ እያሰመርንበት አፋጣኝ ጊዜያዊ መፍትሄ ከመሻት አኳያ የሀገሪቱ ልሂቃን በሰከነ መንገድ መወያያት ይኖርባቸዋል። ኢትዮጵያ ብለን የምንጠራት ሀገር እንድትሰነብት ከተፈለገ የምሁራን ሚና ጎልቶ ሊወጣ ይገባል። ጉዳዩ የሀገር ህልዉና መቋጠሪያ ዉል ነዉና ከጠባብ ልሂቅነት ሰፋ ያለ ሀገራዊ ምልከታ ማንሳት ተገቢ ነዉ። በርግጥ ምሁራዊ ዋጋ በሚጠይቁ ጭብጦች ላይ ለመናገርና ለመወያየት ብሎም ለመጻፍ አለመፍቀድ የገዥዉ ግንባር ምሁር-ጠል ፖሊሲ ዉጤት ነዉ። ግና፤ ይህን መሰል አፍራሽ የፖለቲካ መስመር ለመግራት ምሁራዊ አይናፋርነትን መግፈፍና እዉነት ላይ ቁሞ በእዉነት ስለ እዉነት መናገር ‹ሳይማር ያስተማራችሁ› ህዝብ ዉስጣዊ መሻት ነዉ። መቼም በዚህ ጊዜ እንደ ንጉሱ ዘመን ለሥርዓት ለዉጥም ሆነ ለሀገራዊ ፈተናዎች መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት መጠየቅ አዋጪነቱ አይታየኝም። የልሂቃኑ ሚናም ወሳኝነቱ ከዚህ አንጻር ነዉ።
የጥቅመኝነት ፖለቲካን በተሻገረ መልኩ ይህችን የበደል ቋት ሀገር እንደ ሀገር የሚያሰነብታትን ረብ ያለዉ የፖለቲካ ሃሳብ ወደ አደባባይ ማዉጣት በዘመን የተፈተነ የሀገር ጥሪ ነዉ። ዋጋ ባለዉ መንገድ አቻቻይ የፖለቲካ ሀሳብ ማፍለቅ ሀገርና ትዉልድ ለልሂቃኖቻችን የጣሉት ኃላፊነት ሆኗል። መፍትሄዉ በዘገየ ቁጥር ግን ፖለቲካዊ መብቃት ላይ ያልደረሱ ብላቴኖች ህግንና ፍርድን በእጃቸዉ ጨብጠዉ ጎዳናዉ ላይ እየተዋደቁ መቀጠላቸዉ አይቀሬ ነዉ። ከብላቴኖቹ ፍርካሽ ጭንቅላት ጀርባ የነገዋን ኢትዮጵያ መሰንበት መጠራጠር ተገቢ ነዉ።
በሌላኛዉ ጫፍ ከህዝብ ጋር ደም እየተቃባ ያለዉ ገዥዉ ግንባር ነገን አሻግሮ ማየት ግድ ሊለዉ ይገባል። በአለም ታሪክ ህዝብን ገድሎም ሆነ አስሮ የጨረሰ አገዛዝ አልታየም። ከገዳዮች ቁጥር በላይ ለመሞት የተዘጋጀዉ ህዝብ ይበልጣል። ከዉልደቱ እስከ ሞቱ ድረስ በድራማ የታጀበዉ ደርግ መቃብሩን የቆፈረዉ በገዛ እጁ ነዉ። ደርግ የሻዕብያንና የህወሓትን የገጠር ሽምቅ ዉጊያ መቋቋም ተስኖት የወደቀዉ አንዳች ህዝባዊ ቅቡልነት የሌለዉ በመሆኑ እንጅ በሸማቂዎቹ ብርታት አልነበረም። ማህበራዊ መሰረቱን አጥብቦ፣ አጥብቦ … ባዶ እጁን የቀረዉ ገዥዉ ግንባር ጠብ-መንጃን የብቻ መተማመኛ አድርጎ እስከምን ድረስ ይዘልቃል?!
ዛሬም የኢትዮጵያን ፖለቲካ በተሻለ መንገድ የማዘመን ዕድል በገዥዉ ግንባር እጅ ላይ ነዉ። ለታሪክ የሚበቃ ዕድል እጁ ላይ ያለዉ ገዥዉ ግንባር ሥልጣን እሰከ መቃብር ከሚለዉ መለሳዊ የድርጅት ቀኖና ተሻግሮ ነገን ቢመለከት ለዚህች መከረኛ ሀገር ይበጃል (ከዉስጣዊ ቀዉስ መሻገር እንደ ሀገር ብቻ ሳይሆን ቀጠናዊ ትሩፋቱን ከገዥዉ ግንባር በተሻለ ማን ይረዳዋል?) አሁን ያለዉን የኢህአዴግ ምክር ቤት የመሰለ ፓርላማ በማፍረስ የብሄራዊ ዕርቅ መድረክ እንዲመቻች፣ የፖለቲካና የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ፣ በአሸባሪነት የተፈረጁም ሆነ ያልተፈረጁ የትጥቅ ትግልን እንደ አማራጭ ለያዙ ኃይሎች የሰላም ጥሪ ማድረግ፣ … ብሎም የብሄራዊ አንድነት መንግስት ለማቋቋም የሚያስችሉ ፖለቲካዊ መደላድሎችን መፍጠር የገዥዉ ግንባር የመጀመሪያም የመጨረሻም በጎ እርምጃ ነዉ። ይህን ከማድረግ ይልቅ በማንአህሎኝ የትምክህት መንገዱ በማያዘግም ከህዝብ ጋር ደም መቃባቱን ‹ግፋ በለዉ!› የሚል ከሆነ፤ የቁርጡ ቀን ሲመጣ በማልኮም ኤክስ አንደበት “The chickens [are coming] home to roost” በሚል “You are welcome!” ለማለት ዝግጁ ነን።
ይህችን ጽሁፍ በማዘጋጅበት ወድቅት ለሊት “It is dangerous to be right when the government is wrong” የሚለዉ ፍርሃት አዘል ምክር በአዕምሮዬ ይመላለስ ነበር። ግና፤ የኢትዮጵያ ነገ የተሸከመዉ መዐት ከባድ ነዉና እየመጣ ያለዉን የበዛ መከራ መጠቆምም ሆነ ከሞት በመለስ መዉጫ ጫፎችን ማሳየት ትዉልዳዊ ጥሪ ነዉ። ይህችን ምክር ለማይቀሉ የገዥዉ መደብ ልሂቃን ግን ወዮ ለዚያች ቀን!!
በሙሉዓለም ገ.መድህን
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
Aserese weke says
Thank you for your contribution for showing the way out
Jijjaw says
The quiet EPRDF meeting and its decisions: same riders, same luggage, same destination, but change of mules.
By ቀኜ tebaberamhara@gmail.com http://www.abay-blog.com
EPRDF executive members just concluded their meeting in Addis on the 21st of August 2016. The main discussion point in the meeting, according to sources, was the current situation in Oromiya and Amhara. Before the EPRDF meeting, TPLF had its executive committee meeting in Mekele and discussed on how they can control the current problem and punish whom they think are responsible for it. None of the other affiliates (ANDM, OPDO, SPDM) had their executive committee meeting during the summer. So the meeting of EPRDF executive committee was simply to pipe TPLF’s decisions through EPRDF to implement it in all the regions: a typical tyrannical procedure in EPRDF’s decision making.
The current uprising of the people in Ethiopia is the result of accumulated injustice and mistreatment by the ruling party. Any keen interest to resolve the problem will at least require to recognize this and explore backward and forward in search of the causes and the solutions to the problem. However, that is not the issue for TPLF. For TPLF, they had a very successful decade of looting Ethiopia and building Tigray. They are celebrating their achievement in causing misery to the rest of us and joy to the people they think are special. The way they characterize the problem and the causes of the problem, and the solutions they proposed once again proved TPLF is a fascist colonizer who simply demands its subjects to be looted peacefully or get killed. I will prove my assertion by analyzing the decision points of EPRDF after its five day closed meeting. First I will summarize the main decision points of the meeting. Then I will reflect on how I understand what TPLF mean in these decision points.
One can summarize the whole thing in the four pages of EPRDF’s press release into the following four points. Here is the link to the full document for those of you who want to read the packed statement in Amharic.
1. EPRDF brought development to the country, especially after the split in TPLF (Tehadeso). The development registered in Ethiopia by EPRDF is mainly due to a government leadership that exclusively stands for the benefit of the people.
2. The current problem in Oromiya and Amhara is mainly caused by limitations in some of our leadership: some in the leadership circle are showing a tendency of using government power to enrich themselves and that is what caused the problems.
3. With great respect, we appreciate the struggle of the people to ensure the continuity of the development process in the country and urge the people to continue their struggle in this respect. We take full responsibility for all the problems created without any externalization to the problems.
4. By the way, beware of the anti-peace domestic and foreign elements who want you to fight along ethnic lines!
Now, let us look in detail what these statements mean in TPLF language.
EPRDF brought development: what they want to tell us here is that since we are bringing development to the country, you should not be questioning any of our misdeeds. In the first place, they are the one who drag the country into a spiral of endless conflict and war. Second, TPLF is a narrow nationalist party that works to benefit one area at the expense of the other Ethiopians. Why do they need to have absolute control on the army, intelligence, the economy, the media, all Federal and state government structures including the judiciary? If they are following a government – led development model like Korea as they claim, why do they have EFFORT exclusively for Tigray? Korea or China didn’t exploit their peasants to channel the resources to some specific ethnic group. Dewoo belongs to all Koreans. EFFORT? This is not a government led development, it is fascistic exploitation model to benefit your tribe. Third, if we have to choose between the two, we choose freedom over any form of development that turn humans into 21st century slaves.
No questions that some progress is made in the country in some sectors of the economy. The question is who is benefiting and who is not? In a normal democracy the level field is set for all to play fair and square. Under such scenario, some will make it to the top, some remain in the middle, and some will stay at the bottom. This is normal. However, when people are targeted to succeed or fail by design based on their ethnicity that is fascism. Who is having access to capital, land, and all the support system to succeed? Who is being eliminated from the competition field by dubious tax policy? Whose youth are being forced to go into exile? Whose youth are being supported to go and prosper all over the country? Whose companies are getting big public contracts directly and indirectly through a third party? Whose loan is being written off and whose property is being confiscated? These should be the questions to ask and discuss if the motive was for a real solution.
On the root causes of the problem: TPLF wants us to believe that the current uprising is simply people asking for more development and some corrupt Amhara and Oromo officials standing in-between them and the people. The unrest is not due to few corrupt people that TPLF want to use as scapegoats. It is more than that. TPLF, through well-articulated plan and structured leadership, created a system that benefits only themselves and their tribe. This is a well-documented fact and a reality on the ground. People who put together this country and defended it for centuries are now marginalized and reduced to the status of slavery in their own land. It is a fundamental question of being a citizen or a slave in your own country. No one is going to believe you on this. Even the world is now understanding how you cheated them all these years and revising their policy.
About the corrupt party officials to be eliminated soon: Here they are referring to the mules in ANDM, OPDM, and SOUTH. It is a long established practice by TPLF to recruit sellouts and retards as cadres and promote them to leadership position based on the dumbness they exhibit as they give service to TPLF. In Amhara and Oromiya, regional governments are always warned not to be cozy with their elites. The brave and bright of the region are always pushed out from the region, and the dumb and second rated encouraged to stay. If by chance a devoted hardworking person survived all the screening and started to show some result, then he or she will be cornered in all angles and given three choices: get-out and live quietly; go into exile and do whatever you want to do; or you will end up in prison or graveyard. This is a true TPLF policy crafted by their dead evil leader. Very few (with great survival skill) survive all these hurdle and able to contribute to the advancement of the people they come from. I have a strong admiration to those in OPEDO, ANDM, and SPDM who are going through all these hurdles and able to challenge TPLF’s fascistic policies. These are the “corrupt” party officials TPLF is referring to get rid of in the coming days.
Which bread of “revolutionary democrat” officials are welcome in TPLF’s Ethiopia? The Mules! Mules are not only the dumbest and shortsighted breads of their kingdom, they are detached from their population too. They are not aligned to their father or to their mother. Simply they live to please their belly, and they are always for the barely thrown to them after each service. The main task TPLF assigned to the mules in the three regions is simple but crucial to its existence: to pass on organized information to TPLF so that any “chauvinistic” or “narrow nationalistic” sentiment is detected at early stage and crashed by TPLF security forces. They are the early warning systems of TPLF. Therefore, what they are going to do next is to get rid of the leadership who aligned itself with the people and promote mules of the utmost dumbness.
Who is “forcing the people to fight along ethnic line” TPLF still thinks that Ethiopians have no brain at all and we don’t remember what have been preached to us for the last 40 years. Who want to capitalize differences and destroy any commonality between ethnic groups? TPLF. Who threatened the people with Interhamoye style ethnic cleansing if not elected? TPLF. Who was the informant when thousands of people imprisoned and killed after the last democratic election? Shall I say Amharas? Who is directing security forces whom to kill, whom to take to prison now in Amhara and Oromiya? May be the Oromos? Did the proud people of Amhara and Oromo raise their hands against this informants despite the repeated attack by them? I don’t think so. Who is controlling the media, religious establishments, and community organizations preaching day and night about the evilness of Amhara and Oromo? TPLF. So how is it even possible for the chauvinists and narrow nationalists to reach the people and divided them along ethnic lines to fight each other. Why the people are not listening to the gospel of TPLF even though they are being preached day and night? Answer these questions TPLF before pointing fingers to the others.
If there is anything like chauvinists and narrow nationalists at this point in time, it is in Tigray and Tegarus. But Tigray and Tegarus, no matter what, they are always the angels in TPLF’s eyes. The truth is that TPLF needs the chauvinist/narrow nationalist card in Amhara/Oromiya regions to get ground to involve itself in the affairs of the two regions. First, that gives them a kind of moral ground to “convince” the mules that TPLF (the guardian angele) must be involved in their affairs for the health of the democratic system. Second, the card will be used to “punish” defecting mules without any tangible explanation to prove their crimes. Third, it will make the mules to live under constant fear, fight each other (within the mule kingdom) for survival by winning the trust of their master. That is what is all about chauvinist and narrow nationalist labeling in Amhara and Oromiya regions.
In conclusion: in the eyes of TPLF the country (Tigray) is advancing as planned and no need to introduce change. What they are going to do is reinforce the tools the dead fascist leader left for them, gather some more best practices from Hitler and the Jewish state and unleash their dogs of war to suppress us. For us, it is a matter of living as slave or as a free man. We will continue to fight for our land and people. We are not divided, we are not weak, and we are not scared to fight the war that we are forced to fight.
Victory to the people!