“ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲዖል ድረስ እሄዳለሁ” በሚለው ሕዝብን የናቀና አገርን ያዋረደ ንግግር የሚታወቁት የአሁኑ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በአስተዳዳሪነት የተሾሙባት ትግራይ እየፈረሰች መሆኑን በራሳቸው አንደበት አረጋገጡ። ቀደም ባሉት ዓመታት የትህነግ ሰዎችና አብረዋቸው የሚሠሩ ምሥጢረኞች፣ እንዲሁም የሚታወቁ ባለ ብሮች ብቻ የሚያውቋቸው የግል እስር ቤቶች በአዲስ አበባና በአንዳንድ ክልልሎች እንደነበሩ ይታወሳል። በነዚህ እስር ቤቶች የሚታሰሩ በድርድር ጠቀም ያለ ብር ከፍለው የሚለቀቁ ሲሆን እንደ አሁኑ ሚዲያ ባለመፍላቱ ይፋ አይሆንም ነበር። ይሁን እንጂ በሾርኔ በሚታወቁ ዓምዶች ፍንጭ ይሰጥ ነበር። በወቅቱ ደኅንነቱ የራሱ ልዩ እስር ቤቶች እንዳሉት ቢታወቅም የግል እስር ቤቶቹ ግን በመንግሥት መዋቅር ሥራ ባሉ ወይም በነበሩ ከፍተኛ ባለሥልጣኖች የሚተዳደር ኃላፊነቱ … [Read more...] about የትግራይ መፍረስ በርዕሰ መስተዳደሩ አንደበት
Archives for September 2023
ከያቤሎ አዲስ አበባ የተላከ ኮንትሮባንድ ጉለሌ ተያዘ
በርካታ ሞባይሎችን፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችንና ሌሎች ቁሳቁሶችን በሕገ-ወጥ መንገድ በመኪና ሻግ ሲያዘዋውሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለፀ። በርካታ ሞባይሎችን፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችንና ሌሎች ቁሳቁሶችን በመኪና ሻግ በሕገ-ወጥ መንገድ ጭነው ሲያዘዋውሩ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገለፀ። ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ለጊዜው ባለቤቱ ባልታወቀ ተሽከርካሪ 202 ፍየሎችን ከላይ፣ ከሥር ደግሞ በርካታ ሞባይሎችን፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ መድሃኒቶችን እና የብር ጌጣጌጦችን በሻግ ጭነው ከያቤሎ በመነሳት አዲስ አበባ ከተማ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ብርጭቆ ፋብሪካ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እንደደረሱ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር … [Read more...] about ከያቤሎ አዲስ አበባ የተላከ ኮንትሮባንድ ጉለሌ ተያዘ
“እንኳን ተለያይተንና እርስ በርስ ተባልተን በአንድነት ቆመንም ወጀቡን መሻገር አቅቶናል”
እሑድ ነሐሴ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ባካሄደው የውይይት መድረክ “ፖለቲካ ማለት” በሚል ርዕስ ሰፊ ጥናት ያቀረቡት የፓርቲው መሪ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)፣ “እንኳን ተለያይተንና እርስ በርስ ተባልተን፣ በአንድነት ቆመንም ወጀቡን መቋቋም አቅቶናል” አሉ። ፕሮፌሰሩ አክለውም “ያኔ በእኛ ዘመን ዕድገት በኅብረት እንደሚባለው፣ ዛሬ ላይ ደግሞ እብደት በኅብረት የታወጀ ይመስላል” በማለት አሁን ላይ እየታየ ስላለው አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ሁኔታ ተናግረዋል። አሁን የሚታየው ውዝግብ የበዛበት የዓለም ሁኔታ የሥልጣኔ ቀውስ መሆኑንና ኢትዮጵያን ጭምር ሰለባ ማድረጉን አስረድተዋል። “የዓለም ሁኔታ ምን እየሆነ ነው? የሰው ልጅስ ወዴት እየገባ ነው?” በሚሉ ጥያቄዎች ዙሪያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጥልቀት ሲያሰላስሉ መቆየታቸውን የተናገሩት ብርሃኑ … [Read more...] about “እንኳን ተለያይተንና እርስ በርስ ተባልተን በአንድነት ቆመንም ወጀቡን መሻገር አቅቶናል”