የትግራይ ክልል ነዋሪዎችን ወደ አዲስ አበባ እና ሌሎች መሀል ከተሞች በማምጣት ሥራ የተደራጁ ሰው አዘዋዋሪዎች በአንድ ሰው ከ80 እስከ 150 ሺሕ ብር እያስከፈሉ መሆኑን አዲስ ማለዳ አዘዋዋሪዎቹን በማነጋገር አረጋግጣለች። መረጃውን ማግኘት የተቻለው በሥራው የተሰማሩ ሰዎች ጉዳዩን ለማስፈጸም ያመቻቸው ዘንድ በከፈቱት የቴሌግራም ቻናል አማካኝነት ነው። አዘዋዋሪዎቹ እንደገለጹት ከሆነ፤ የትግራይ ክልል ነዋሪዎችን ወደ መሀል ከተማ የሚያመጡት ፎርጂድ መታወቂያ በማሠራት እና የቀይ መስቀል የደንብ ልብስ (ዩኒፎርም) አልብሰው ሠራተኛ በማስመሰል መሆኑን በግልጽ አስረድተዋል። ከተደራጆቹ መካከል ሥሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የአዲስ ማለዳ ምንጭ፣ ‹‹ቀይመስቀል Transmitter ነኝ። አንድ ሎንግቤዝ እይዛለሁ። ስሄድ የቀይመስቀል ልብስ፤ ፎርጅድ መታወቂያ እና ባጅ በሚሰጠኝ ፎቶ … [Read more...] about በሐሰተኛ መታወቂያ ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ ለመውጣት እስከ 150 ሺህ ብር ይከፈላል
Archives for August 2022
በሆሩ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የጉደኔ ጫላ ሲበሬ ቀበሌ ነዋሪዎች በኦነግ ሸኔ ላይ ጀብዱ ፈፀሙ
ነገሩ እንዲህ ነው። በኦሮሚያ ክልል በሆሩ ጉድሩ ወለጋ ዞን ጮማን ጉዱሩ ወረዳ ውስጥ ካሉት ቀበሌዎች መካከል በአንዲት ቀበሌ ውስጥ ታላቅ ጀብዱ ተፈፅሟል። ቀበሌዋ ጉደኔ ጫላ ሲበሬ ትባላለች። እንደወትሮው ሁሉ ህዝቡ ውስጥ ለመደበቅ የአሸባሪው ሸኔ ታጣቂዎች ወደዚህች ቀበሌ ዘልቀው ይገባሉ። ነገር ግን የጉደኔ ጫላ ሲበሬ ቀበሌ አሁን በቃችሁን በማለት 07 ወጣቶች ከታጠቁት ሸኔ ታጣቂዎች ጋር በጦርና በገጀራ ጦርነት ገጠሙ። ከ7ቱ ሶስቱ የዩኒቨሪሲቲ ተማሪዎች ሲሆኑ አራቱ ደግሞ አርሶ ከደር ናቸው። ጩሃቱን የሰማው የቀበሌው ህዝብ በሙሉ በነቂስ ወጥቶ ከታጠቁት ሸኔዎች ጋር በባህላዊ ጦርና ገጀራ ገጠሙ። ይህንኑ ያላሰቡትን የህዝብ ማዕበልና ቁጣ አይተው የተደናበሩት አሸባሪዎች እግር አውጪኝ ብለው እግራቸው ወደመራቸው አቅጣጫ መሸሽን መረጡ። ነገር ግን የህዝብ ማዕበሉ አንዱን በጦር … [Read more...] about በሆሩ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የጉደኔ ጫላ ሲበሬ ቀበሌ ነዋሪዎች በኦነግ ሸኔ ላይ ጀብዱ ፈፀሙ
በኢትዮጵያ ግብርና ላይ ግብጽ ለዓመታት የፈጸመችው ሤራ
የዛሬ ዘጠኝ ዓመት ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ "ኢህአዴግ ጣና በለስን ለምን አፈራረሰው?" በሚል ርዕስ አንድ ዘገባ አቅርበን ነበር። ያንን ተከትሎ ከሦስት ዓመት በኋላ አምባ – የአማራ ባለሙያዎች ህብረት የጣና በለስ ታሪካዊ የልማት ፕሮጀክት፤ ከመፈራረስና ውድመት እስከ መሸጥ በሚል ርዕስ ሌላ ዘለግ ያለ ዘገባ ለንባብ አብቅቷል። በአገራችን ያለው እና በዘመነ ት ህነግ ተስፋፍቶ መንግሥታዊ ቅርጽ የያዘው የዘር ፖለቲካና ምክን ያቱ አገራችን በነጻነት ራሷል እና ሉዓላዊነቷን አስጠብቃ ለጥቁር ሕዝብ ኩራት ሆና የኖረችውን ያህል በኢኮኖሚውም መስክ ተመሳሳይ ፈር ቀዳጅ ድል እንዳትቀዳጅ ለማኮላሸት ነው። ከራሳችን በላይ ማንነታችንን እና እሴታችንን የሚያውቁት ጠላቶቻችን በቆፈሩልን ጉድጓድ ስንነጉድ ዓመታት አሳልፈናል። እስሌማን የዓባይ ልጅ በተለይ ከግብርና ጋር በተያያዘ ለዓመታት ሲፈጸምብን … [Read more...] about በኢትዮጵያ ግብርና ላይ ግብጽ ለዓመታት የፈጸመችው ሤራ
የስሪ ላንካው “FamilyCracy” – ከመዓቱ እስከ ተውኔቱ
የታሚል ታይገር ተገንጣይ አማፂያንን ከረጂም አመት ውጊያ በኋላ ድል ማድረጋቸው የብልሹ አሰራራቸውን ብሶት ማስታገስ አይችልም። የስሪ ላንካው መሪ ራጃፓክሳ ሊተገበሩ የሚችሉ የመፍትሄ ርምጃዎች ላይ የታየባቸው ዳተኝነት ይባሱኑ ህዝባዊ ቁጣውም ጨመረባቸውንጂ፤ የስሪ ላንካ ዜጎች ለከፍተኛ መከራ የዳረጋቸው ሙስና ብልሹ አስተዳደር ነበሩ። በተለይም ዋና ዋና የሀላፊነት ቦታዎች በዘመዳዝማድና ቤተሰብ የሰበሰበው FamilyCracy ነበር። በስሪ ላንካ የኢኮኖሚ ቀውሷ በረታ…የኢኮኖሚ ውድቀቷን bankruptcy ከወራት በፊት ማወጇ ይታወሳል። የሀብት የፀጋ የተስፋ ምድር እንዳልተባለች በየቀኑ ሳይበሉ የሚያድሩ ዜጎች መገለጫዎቿ እስኪመስሉ ተቸገሩ። የስሪ ላይካ ዜጎች ወደ አመፅ ተሸጋገረ። እውነተኛው የዜጎች መከራን እንደመልካም አጋጣሚ በመቁጠር የተሰራው የጂኦፓለቲካ ጨዋታ ግን አሳዛኝ … [Read more...] about የስሪ ላንካው “FamilyCracy” – ከመዓቱ እስከ ተውኔቱ