• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በሐሰተኛ መታወቂያ ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ ለመውጣት እስከ 150 ሺህ ብር ይከፈላል

August 19, 2022 04:25 pm by Editor Leave a Comment

የትግራይ ክልል ነዋሪዎችን ወደ አዲስ አበባ እና ሌሎች መሀል ከተሞች በማምጣት ሥራ የተደራጁ ሰው አዘዋዋሪዎች በአንድ ሰው ከ80 እስከ 150 ሺሕ ብር እያስከፈሉ መሆኑን አዲስ ማለዳ አዘዋዋሪዎቹን በማነጋገር አረጋግጣለች።

መረጃውን ማግኘት የተቻለው በሥራው የተሰማሩ ሰዎች ጉዳዩን ለማስፈጸም ያመቻቸው ዘንድ በከፈቱት የቴሌግራም ቻናል አማካኝነት ነው።

አዘዋዋሪዎቹ እንደገለጹት ከሆነ፤ የትግራይ ክልል ነዋሪዎችን ወደ መሀል ከተማ የሚያመጡት ፎርጂድ መታወቂያ በማሠራት እና የቀይ መስቀል የደንብ ልብስ (ዩኒፎርም) አልብሰው ሠራተኛ በማስመሰል መሆኑን በግልጽ አስረድተዋል።

ከተደራጆቹ መካከል ሥሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የአዲስ ማለዳ ምንጭ፣ ‹‹ቀይመስቀል Transmitter ነኝ። አንድ ሎንግቤዝ እይዛለሁ። ስሄድ የቀይመስቀል ልብስ፤ ፎርጅድ መታወቂያ እና ባጅ በሚሰጠኝ ፎቶ አሠርቼ እወስዳለሁ። የወሰድኩትን ዩኒፎርም ለብሰው በሎንግቤዝ ይዣቸው ነው የምመጣው። እንዲህ ሲደረግ የቀይመስቀል ሠራተኛ ሆኑ ማለት ነው። እስካሁን እንደዛ ነው የማመጣቸው›› በማለት አብራርቷል።

ድርጊቱን የሚያከናውኑት ተደራጅተው ተራ በተራ በመመላለስ መሆኑን የገለጸ ሲሆን፤ ነዋሪዎቹን ወደ አዲስ አበባ ለማምጣት የሚያስከፍሉት ብርም ለወንድ እና ለሴት የተለያየ ነው ብለዋል። አንዲትን ሴት ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ ለማምጣት ክፍያው 80 ሺሕ ብር  ሲሆን፤ ለወንድ ደግሞ 150 ሺሕ ብር መሆኑን በሥራው የተሰማሩ አካላት ገልጸዋል።

ለማለፍ ምንም ዓይነት ምክንያት ስለማይኖር እድሜው ከ20 ዓመት በታች የሆነን ሰው ማምጣት እንደማይቻል ተመላክቷል። ከክልሉ ወደ መሀል ከተማ የሚመጡት ሰዎች ግን ምንም ነገር ይዘው መምጣት አይችሉም ነው የተባለው። በተያያዘም ‹‹ብሩን ደግሞ ሳልሄድ ነው የሚከፍለኝ ምክንያቱም ከሄድኩ ኔትወርክ እዛ የለም›› ነው ብለዋል።

ለወንድ ክፍያው ከፍ ያለበትን ምክንያትም፣ ከትግራይ ክልል ይዞ መውጣት አስቸጋሪ ስለሆነ እንዲሁም ለመታወቂያ እና ለአንዳንድ ነገር የማወጣው ብር ከፍተኛ በመሆኑ ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል፣ አዘዋዋሪዎቹ ከትግራይ ክልል ውጪ የሆኑና ወደ ክልሉ ለቤተሰቦቻቸው ብር መላክ የሚፈልጉ ሰዎችን በማነጋገር ከሚላከው 30 በመቶ የሚሆነውን ለራሳቸው በማድረግ የማስተላለፍ ሥራቸውን እንዳላቋረጡ ማወቅ ተችሏል።

ከአዘዋዋሪዎቹ መካከል አንዱ ሰሞኑን ወደ ትግራይ ክልል ተጉዞ ሰዎችን ለማምጣት ተረኛ መሆኑን ጠቁሞ፤ ወደ ክልሉ 500 ሺሕ ብር ይዞ እንደሚሄድም ለአዲስ ማለዳ ሙሉ መረጃውን ዘርዝሯል።

ጥሬ ብር የማስተላለፍ ድርጊቱ ከተጀመረ ሰንበትበት በማለቱ በተለይም በድንበር አካባቢ የሚገኙ ኬላዎች የሚገኙ ፈታሾች ጥብቅ ቁጥጥር እያደረጉ መሆኑ እየተነገረ ቢሆንም፤ አስተላላፊዎቹ ግን በተለያዩ ዘዴዎች እየሸወዷቸው ስለመሆኑ በዝውውር ሂደቱ ከተሰማሩ ሰዎች መረጃው ተገኝቷል።

ፈታሾችን የሚያልፉበት ዋነኛው ዘዴ እንዲተላለፍ የተፈለገውን ብር ለብዙ ሰዎች አከፋፍሎ በማስያዝ ነው። እንዲሁ ሲያደርጉ ተነቅቶባቸው በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች እስከመከዳዳትም መድረሳቸው ተሰምቷል።

100 ሺሕ ብር ለሦስት ተከፋፍለው ከቆቦ ወደ አላማጣ ሲጓዙ የተደረሰባቸው ሰዎች ብሩን በመከዳዳታቸው እናትና ልጅ፤ እህትማማቾች ብሎም ጓደኛሞች በመካከላቸው ትልቅ ጥላቻ መፈጠሩን ሥማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ ሰዎች ተናግረዋል።

አዲስ ማለዳ በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገረቻቸው የቀይ መስቀል ማኅበር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሰለሞን አሊ፣ የቀይ መስቀልን ዩኒፎርም በማልበስ ሰዎችን ከቦታ ቦታ የሚያዘዋውሩ ሰዎች እስካሁን እንዳላገጠማቸው ገልጸዋል። ሰለሞን ጉዳዩን ከዚህ በኋላ በጥልቀት እንደሚከታተሉ አንስተው፤ ብር በማስተላለፍ ግን ከዚህ በፊትም በአፋር ክልል በኩል በቁጥጥር ሥራ የዋሉ ሰዎች እንደነበሩ አስታውሰዋል። (አዲስ ማለዳ: ቅጽ 4 ቁጥር 197 ነሐሴ 7 2014) (ፎቶ፤ ፋይል)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Left Column, News Tagged With: ethiopian terrorists, Left Column, operation dismantle tplf, tplf terrorist

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule