• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የስሪ ላንካው “FamilyCracy” – ከመዓቱ እስከ ተውኔቱ

August 8, 2022 09:45 am by Editor Leave a Comment

የታሚል ታይገር ተገንጣይ አማፂያንን ከረጂም አመት ውጊያ በኋላ ድል ማድረጋቸው የብልሹ አሰራራቸውን ብሶት ማስታገስ አይችልም። የስሪ ላንካው መሪ ራጃፓክሳ ሊተገበሩ የሚችሉ የመፍትሄ ርምጃዎች ላይ የታየባቸው ዳተኝነት ይባሱኑ ህዝባዊ ቁጣውም ጨመረባቸውንጂ፤

የስሪ ላንካ ዜጎች ለከፍተኛ መከራ የዳረጋቸው ሙስና ብልሹ አስተዳደር ነበሩ። በተለይም ዋና ዋና የሀላፊነት ቦታዎች በዘመዳዝማድና ቤተሰብ የሰበሰበው FamilyCracy ነበር። በስሪ ላንካ የኢኮኖሚ ቀውሷ በረታ…የኢኮኖሚ ውድቀቷን bankruptcy ከወራት በፊት ማወጇ ይታወሳል። የሀብት የፀጋ የተስፋ ምድር እንዳልተባለች በየቀኑ ሳይበሉ የሚያድሩ ዜጎች መገለጫዎቿ እስኪመስሉ ተቸገሩ።

የስሪ ላይካ ዜጎች ወደ አመፅ ተሸጋገረ። እውነተኛው የዜጎች መከራን እንደመልካም አጋጣሚ በመቁጠር የተሰራው የጂኦፓለቲካ ጨዋታ ግን አሳዛኝ ነበር፤ የመከራ ቀናትን በሰው ሰራሽ ማራዘሙ አንዱ ሲሆን የዜጎች የትግል ፍሬ ብዙም ሳይጓዝ ራሱ ጠልፎ የሚጥለው መሆኑ ዋናው ነበር። ለእውናዊ መከራው ከመጣው አጋር ይልቅ ለቢዝነስ በርካታ ኢንቨስት ተደረገባት። መጀመሪያ ከቀውስ አለመግባህ ነውንጂ …ከገባህማ እኛም በቅርቡ የገጠመንና የምናውቀውም ነው።

ቀውሱን ተከትሎ IMF ብድር ለመስጠት ተደጋጋሚ ጥረት አደረገ። ሀገሪቱ ሪፎርም ትሰራ ዘንድ ጠየቀ። መንግስቷ ደግሞ የቻይናን ብድር መረጠ። ሀገሪቱ ካለባት የእዳ ብዛት ቻይና ለማበደር ብትፈልግም ስሪ ላንካ በአይኤምኤፍ የባሰ ቀውስ መዳረግ ሀሳቡን ወደ ኋላ አስባለ፤ ሌላው የምእራባዊያን የቻይና ብድር ወጥመድ የፈጠራ ፕሮፓጋንዳ ነበር ቤይጂንግ እጇን ሰብሰብ አርጋ ለመቆየት ምክንያት የሆናት በዚህ መሃል ወራት ተቆጠሩ። ስሪ ላንካ ከአይኤምኤፍ እንድትበደርና እዳዋን አቃልላ ሌላ መበደር እንድትችል ገለፀችላት።

ሰውየው እያመነታም እየዘገየም ከአይ.ኤም.ኤፍ. ቅርርብ ጀመረ። በዚህ መሃል የዩክሬይን ጦርነት ተጀመረ። በየካቲት ቪክቶሪያ ኑላን ኮሎምቦ ተጉዛ ነበር።

ቆይት ብለው የወጡ መረጃዎች እንዳመለከቱት ስሪ ላንካ ሩሲያን እንድታወግዝና ከእዳ ስረዛ ጋር ከፍተኛ የብድር ፕሮፓዛል ቀረበላት። ገለልተኝነትን መረጠች። ሴትዮዋ በተመለሰች በሳምንቱ አመፁ መቀጣጠል ጀመረ።

ምእራባዊያን የቻይና የብድር ወጥመድ የሚሉት ፕሮፓጋንዳ ተጠናክሯል። የቻይና ብድር ስሪ ላንካ ውስጥ ምን ይመስላል በሚል ባደረገሁት ዳሰሳ የውሸት መሆኑን የሚያሳዩ እውነታዎችን ተመለከትኩ። ስሪ ላንካ ከቻይና በርግጥም እዳ አለባት። ነገር ግን አስር በመቶ ያልበለጠው ነበር ድርሻው። የሚገርመው ጃፓን ለስሪ ላንካ ያበደረችው ከቻይና በላይ የ 11 በመቶ ብልጫ ያለው ነው። ይቱንና የጃፓን የብድር ወጥመድ የሚል ማንበብ አልቻልኩም። ከአሜሪካኖች የመጣ ተንኮለኛ አጀንዳ አለ ማለት ነው።

በስሪ ላንካውያን ላይ ያን ሁሉ መከራ ያስከተለው የብድር ወጥመድ ነው ከተባለ እሱ አበዳሪ ማን እንደሆነ ፈትሹት..። ፈልጌ ያገኘሁት እሱ አይኤምኤፍ ነበር… ቁጥሮች ይህንኑ ያስረግጣሉ፤ የእዳዋ 79 በመቶ የአይኤምኤፍ ነበር።

ከመዓቱ እስከ ተውኔቱ ከተውኔቱ አጫጭር

  • አሜሪካዊት ልኡክ ቪክቶሪያ ኑላንድ ስሪ ላንካን ጎበኙ፤ አመፁ ከመነሳቱ ከሳምንት በፊት። ሌላው አሜሪካዊ ባለስልጣን ዶናልድ ሉ በወርሃ የካቲት በኮሎምቦ ተገኝተው ነበር።
  • አንድ የስሪ ላንካ ባለስልጣን ስማቸውን ሳይገልፁ እንደተናገሩት “በአይኤምኤፍ በኩል ርዳታ ሊሰጡን ከተስማማን በኋላ አሜሪካ፣ ኔቶ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሩሲያን በማውገዝ መግለጫ እንድናወጣ አበረታተውናል።”
  •  አመፁ እየተባባሰ ቀጠለ። የምእራባዊያን ስሪት የስሪ ላንካ ማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻዎች  ስለ ቻይና ወጥመድ በማውራት ተጠምደዋል። የአለም ባንክ ወጥመድ ወይስ የጃፓን ወጥመድ? ይህን የሚጠይቁት የነገሮች መጠምዘዝ ያሳሰባቸው ሀገሬዎች ነበሩ።
  • አመፁ እየተፋፋመ ሲሄድ በስሪ ላንካ የሚገኙ የምዕራቡ ዓለም ዲፕሎማቶች አመፁን መደገፋቸውን ገልፀው የሲሪላንካ መንግሥት ተቃዋሚዎችን እንዲተዋቸው ግፊትና ጥሪ ማድረግ ቀጠሉ። ግልፅ ነው…። ይህ የአሜሪካ unipolar hegemony playbook 101 መሆኑን አትዘንጋ።
  • የሲሪላንካ ተቃውሞ ሰልፎች በዩኤስኤአይዲ ገንዘብ የሚበጀትላቸው የሀገር ውስጥ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሎቢስቶች በአለም አቀፍ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች NGOs እና ቲንክ ታንክ ሰራተኞች እና ሊበራል ምእራባዊ ሲስተምን በሚደግፉ ተጽእኖ ልሂቃን ነው። የከተማ ነዋሪዎች የላይኛው መደብ የሆኑ ሊበራሎች ናቸው።
  • የሚስተጋቡ መፈክሮች በሀገሪቱና አካባቢው ባልተለመደ የቋንቋ አጠቃቀም በአብዛኛው በእንግሊዝኛ የተጻፉ ሲሆኑ በመፈክርም ሆነ በአመፁ ኢላማ የተደረጉት የቻይና መንግስት አጋር ተቋማት/ሀገራት ናቸው።
  • የተቃዋሚዎቹ አስተባባሪዎች ደጋግመው የሚያስተጋቡት የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት በሲሪላንካ ቀውስ ጣልቃ እንዲገባ ማበረታታት ነበር።
  • በተቃውሞ ሰልፎቹ ፀረ-አይኤምኤፍ አይደሉም መልእክት አይስተጋባም። ሰልፈኞቹ አይኤምኤፍ ጋር መተባበር ሲገባው ከቻይና ጋር ለምን አደረገ የሚል ወቀሳ ደጋግመው ያቀርባሉ።
  • ኢኮኖሚያችን ይበልጥ ሊበራል ይደረግ ሲሉም ጠይቀዋል።
  • ታዋቂ የሆኑት የተቃውሞው አስተባባሪዎች ቀደም ባሉ ጊዜያት ከምዕራባውያን ዲፕሎማቶች ጋር እንዲገናኙ ተጋብዘዋል።
  • የተወሰኑት ደግሞ በምዕራባውያን ሀገራት አመቻችነት ማህበራዊ ሚዲያን ተጠቅመው ተቃውሞን ሀገራቱ ወደ ፈለጉት አላማ ማስኬድ ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎች በቅርብ ጊዜያት ስልጠና የተሰጣቸው ናቸው፤ የተቃውሞ አስተባባሪነት ላይም ሲሳተፉ ተስተውለዋል።
  • የተወሰኑት የተቃውሞው ተዋንያን በውጪ ሀገራት በሚገኙ ነገር ግን በስም ባልታወቁ ድርጅቶች “የጋዜጠኝነት ስልጠና” በተባሉ መርሃ ግብሮች የተሳተፉ ናቸው።

እስሌማን ዓባይ – የዓባይልጅ

Filed Under: Left Column, Opinions, Politics Tagged With: FamilyCracy, Sri Lanka, usa

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
Copyright © 2026 · Goolgule