የኢትዮጵያ መንግሥት ሰኔ 21 ቀን ያወጀውን የትግራይ ክልል የተኩስ አቁም አዋጅ በተመለከተ የተለያዩ ሀሳቦች እየተሠነዘሩ ይገኛሉ። እንደ እውነቱ ከሆነ መንግስት መተቸት ያለበት በመዘግየቱ ነው። የሕግ ማስከበር ዘመቻው በተጠቃለለ በሳምንታት ጊዜ ውስጥ የተኩስ አቁም አዋጁን አውጆ ወደ ፖለቲካዊ መፍትሄ ቢያመራ መልካም ነበር። ምናልባት ግን ከፊት ለፊቱ የነበረው ሐገራዊ ምርጫ ውሳኔውን እንዲያዘገይ እንዳደረገው ይታመናል። የኢትዮጵያ መንግስት ከዚህ በላይ የትግራይን ጉዳይ መሸከም አልነበረበትም። ቀድሞም የተለያዩ የውስጥና የውጭ አካላት ይሄንን ጉዳይ አንስተው ሞግተዋል። አውሮፓና አሜሪካ ጠንካራ ማእቀብ ለመጣል እየተዘጋጁ ነው። ይህ ማእቀብ የኢትዮጵያን ምርቶች እስካለመግዛት የሚደርስ ነው። ይህ ሁኔታ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከባድ ሸክም ነው። አሜሪካና የአውሮፓ ህብረት የትግራይ ችግር … [Read more...] about የትግራይ ጉዳይ፤ በረከተ መርገም!
Archives for July 2021
የህወሓት ቀጣይ ዕቅድ
(የሚከተለው ፅሁፍ ከትግረኛ ወደ አማርኛ የተተረጎመ የዲጂታል_ወያኔ ምሥጢራዊ እቅድ ነው!) በተለያዩ ሚዲያዎች እየወጣችሁ አሸነፍን እያላችሁ ደስታ ማሳየት በፍጥነት አቁሙ። ገዳዮቻችን ጠላቶቻችን ለሌላ እንደተጠቁ አድርገው ሊጠቀሙበት ይችላሉ። በቀጣዩ ቅዳሜ ወደ ትግራይ የሚወስዱ መንገዶችን በመዝጋት ድልድዮችን በማፍረስ የትግራይን ህዝብ በረሀብና ጥማት አፍኖ ለመጨረስ እየተረባረቡ ይገኛሉ በሚል በመላው አለም የሚገኝ ትግራዋይ_ሰልፍ እንዲወጣ በቀጣይ ሳምንታት ደግሞ የተደረጉ ጭፍጨፋዎችን በመዘከር የሻማ ማብራት ስነሥርዓት በማካሔድ የተለያዩ ቦታ ሰምዕታትን መዘከሪያ ፕሮግራም እንዲዘጋጅ በዚህ መሠረት፣ የመጀመሪያው ሳምንት የማይካድራን ዳንሻንና ሁመራን ሰማዕታት በመዘከር ሁለተኛ ሳምንት የአክሱምን እና የደብረ አባይ ሰማእታትን በመዘከር ሶስተኛው ሳምንት … [Read more...] about የህወሓት ቀጣይ ዕቅድ
ጩኸት ያፈናት ከተማ
የድምጽ ብክለት መጨመር የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ለምሬት እየዳረገ ይገኛል፡፡ ከመጠን ያለፉት ረባሽ ድምጾች፡- ከንግድ ትርኢቶች፣ ከሐይማኖት ተቋማት፣ ከምጽዋት ጠያቂዎች፣ ከጎዳና ላይ ንግድ፣ ከምግብና መጠጥ ቤቶች፣ ጋራዥ፣ እንጨት ቤት እና ብረት ቤትን ከመሰሉ አገልግሎት ሰጪዎች፣ ከፊልምና ሙዚቃ መሸጫዎች፣ ከተሽከርካሪዎች እና ከመሳሰሉት ይመነጫሉ፡፡ ለመሆኑ የድምጽ ብክለት ማለት ምን ማለት ነው? ምን ጉዳት ያስከትላል? እንዴት መቆጣጠር ይቻላል? የሚለውን ጥያቄ አንስተናል፡፡ በዚህ ጽሑፍ የባለሙያዎች አስተያየት እና የተጎጂዎች ሐሳብ ተካቷል፡፡ "የድምፅ ብክለት መደበኛውን የሕይወታችንን እንቅስቃሴ ይጎዳል፣ ያስተጓጉላል፣ እንቅልፍ ይነሳል፤ ውይይቶቻችንንና መደማመጣችንን ይቀንሣል፣ በአጠቃላይ የአኗኗራችን ሁኔታ የተረበሸ እንዲሆን ያደርጋል።” የሚሉት የቀድሞ የኢትዮጵያ … [Read more...] about ጩኸት ያፈናት ከተማ
ብቃት ዓልባው ቴድሮስ ዳግም መመረጥ የለበትም-ለተባበሩት መንግሥታት ጥሪ ቀረበ
በአለም ጤና ድርጅት ውስጥ እየጨመረ በመጣው የሥነ ምግባር ጉድለት፤ ማጭበርበርና ጾታዊ ጥቃት የድርጅቱ ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ተጠይቋል። አለም አቀፉ ኢንዲፔንደንት ፋይናንሽያል ኦዲት ባቀረበው የኦዲት ሪፖርት በአለም ጤና ድርጅት ውስጥ የሥነ ምግባር ጉድለት፣ ማጭበርበር፣ ጾታዊ ጥቃትና የሙያ ደረጃዎችን ያልጠበቁ አሰራሮች በከፍተኛ ሁኔታ ጨምረዋል። የአለም ጤና ድርጅት እ.ኤ.አ የ2020 አመታዊ አፈጻጸምን በተመለከተ የኦዲት ሪፖርት ቀርቧል። በዚህም በተቋሙ እየጨመረ የመጣውን የሥነ ምግባር ጉድለት ማጭበርበርና ጾታዊ ጥቃት ተከትሎ የድርጅቱ ዳይሬክተር ለሁለተኛ ጊዜ እንዳይመረጡ የአለም ኤች አይቪ ኤድስ ሄልዚኬር ፋውንዴሽን ጠይቋል። ሪፖርቱ በ2020 የበጀት አመት የአለም ጤና ድርጅት ከ332 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከአሰራር ውጪ ከአማካሪ … [Read more...] about ብቃት ዓልባው ቴድሮስ ዳግም መመረጥ የለበትም-ለተባበሩት መንግሥታት ጥሪ ቀረበ
የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!?
ከመግቢያው በፊት ይህንን ዘገባ በቴድሮስ አድሃኖም ላይ የሠራነው ከዓመት በፊት April 12, 2020 ነው። ትህነጉ ቴድሮስ አገራችንን ወክሎ የዓለም ጤና ጥበቃ ሃላፊ መሆን እንደሌለበት ገና ለምርጫ ሲወዳደር ጀምሮ አጥብቀን ተቃውመናል። አሁን ወቅቱ የደረሰ ይመስላል። ጥያቄው እየቀረበ ነው። ቴድሮስ አሸባሪውን ህወሃት እስካሁን እየደገፈ ያለ በመሆኑ ብቻ ከሥልጣኑ መወገድ ብቻ ሳይሆን ለፍርድም መቅረብ ያለበት ነው። ዘገባውን በድጋሚ አትመነዋል። እንደ መግቢያ ሰሞኑንን ከኮቪድ - 19 ጋር ተያይዞ የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሓኖም አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱ ይታወሳል። ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ካወደመው፣ የዘር ፖለቲካን ከሚያራምደው ፍጹም ጽንፈኛና ዘረኛ፣ እንዲሁም በከፍተኛ ደረጃ ኢትዮጵያውያንን በዘራቸው፣ በፖለቲካ እምነታቸው ካኮላሸ፣ ከጨፈጨፈ፣ ቶርቸር … [Read more...] about የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!?





