በጎንደር የሰዎች ህይወት ከማለፉ በተጨማሪ ሕዝብ የማያምንባቸውንና ከትግራይ ተገንጣይ ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው ባላቸው ንብረቶች ላይ ርምጃ መውሰዱ ታውቁዋል። ማክሰኞ ሊነጋጋ አካባቢ ተነሳ የተባለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለመቀላቀል ወደ ጎንደር ያመሩ ወገኖችም መበራከታቸው እየተሰማ ነው። ለዓመጹ ውጤታማነት የዘር ትግል ሳይሆን ኅብረብሔራዊ እንቅስቃሴ እንደሚበጅ ተገለጸ። አመጹ የተቀሰቀሰው የማንነት ጥያቄ ባነሱና "እኛ አማራ እንጂ ትግሬ አይደለንም" በሚል የተነሳውን ጥያቄ ከውጤት ለማድረስ ከተመረጡት የኮሚቴ አባላት መካከል አራት የሚሆኑትን ከትግራይ የመጡ ነፍጥ አንጋቾች ከያዟቸው በኋላ እንደሆነ ለኢሳት በድምጽ ማብራሪያ የሰጡ አረጋገጠዋል። ከዚያም ኮሎኔል ዘውዱ ደመቀን ለመያዝ ሙከራ ተደረገ። ይህን ጊዜ ኮሎኔሉ "በሬን አልከፍትም ጥዬ እወድቃለሁ" በማለት ሊያስሯቸው ከመጡት ሃይሎች … [Read more...] about በጎንደር የተነሳው አመጽ እየሰፋ ነው!
Archives for July 2016
የበጎው ሰው፣ የጎልማሳው ህልፈት…!
በያዝነው ሳምንት ... በአብዛኛው የሀበሻ መገናኛ መንደር፣ በማህበራዊ ድህረ ገጽ ዋንኛ መድረክ በ Facebook መስኮት አንድ መሪር መርዶ ተሰምቷል! የትሁት ፣ አስተዋይና አርቆ አስተዋዩ በጎ ሰው ፣ የጎልማሳው የአቡኬ አሌክስ ህልፈት!!! የአቡኬ አሌክስ በድንገት መለየት ጥልቅ ሀዘናን ሁላችንም አንገብግቦናል! "ከሞቱ አሟሟቱ " እንዲሉ አቡኬ ባንድ ጀንበር ታይቶ በርቶ ፣ ባንዱ ጀንበር ሳይታሰብ ጠፍቶብናል! እናም በቅርብ ከሚያውቁት ፣ ቤተሰብ ዘመድ አዝማድ ጓደኞች እኩል በስራው በዝና የምናውቀው በሀዘኑ አዝነን ከፍቶናል! የጎልማሳው በጎ ሰው አቡኬ አሌክስ መረጃዎች የቅርብ ተከታታይ የሆነችው ባለቤቴ በህልፈቱ ጥልቅ ሀዘን የተሰማቸው መካከል አንዷ ናት ፣ ስለአቡኬ ስትገልጽ እንዲህ ብላኛለች " አቡኬ ብሩህ አዕምሮ የነበረው ፣ ኢትዮጵያውያንን በዘር በሐይማኖታዊ ሳይለየን … [Read more...] about የበጎው ሰው፣ የጎልማሳው ህልፈት…!
የሀገሬ ዲሞክራሲያዊ የበቀል ፖለቲካ!
* የሰሜኑ ኮከብ አብርሃ ደስታ እንኳንም ተፈታህ! የሰሜኑ ኮከብ ወንድም አብርሃም ደስታ ከእስር እንደሚፈታ ቢገመትም ዘንድሮ ሲሆን እንጅ ሲባል ለማመን ተቸግሬያለሁና ዛሬን መቆየት ነበረብኝ ። እናማ የሰሜኑ ኮከብ ደፋሩና ለእውነት ግንባሩን የማያጥፈው የመቀሌው አብርሃም ደስታ " እውነት ተፈታ " ሲባል ሰማሁ ፣ ደስ አለኝ ! አብርሽ እንኳንም ከቤተሰብ ፣ ከዘመድ አዝማድና ወዳጅ አፍቃሪ ወገንህ ጋር ተቀላቀልክ እልሃለሁ ፣ አብርሽ! ከሁሉ አስቀድሞ አብርሃም ሃብታሙ ከተኛበት ሲጎበኘው የሚያሳየውን ምስል ስመለከት በደስታ ኩራት ስሜቴን መቆጣጠር አቅቶኝ ማንባቴ አልቀረም ... ሁለቱ ወንድሞች ገርድሰው የጣሉት ልዩነትና ህብረታቸው ሳውቀው ዛሬ እንደ ብርቅ ነገር አስደሰተኝ ! በዚህ ዛቢያ ስማስን የዘር ፖለቲካው ክፋት አንደርድሮ ወደ ሌላ አቅጣጫ ወረወረኝ ... ከምንም … [Read more...] about የሀገሬ ዲሞክራሲያዊ የበቀል ፖለቲካ!
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር “እየቀለለ” ነው!
ጠቅላላ ወጪው 475 ሚሊዮን ዶላር እንደሆነ የተነገረለት የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር በብልሽት ምክንያት ግማሽ ያህል ባቡሮቹ እንደማይሰሩ ተነገረ፡፡ የባቡሩ ፕሮጀክት ከመጠናቀቁ በፊት ሥራው እንዲጀመር ህወሃት/ኢህአዴግ ግፊት አድርጎ ነበር፤ የቀላል ባቡር ፕሮጀክት የፖለቲካ ውሳኔ ነው፤ ቀላል ባቡሩ “እየቀለለ ነው” ተብሏል፡፡ ማክሰኞ ዕለት የተሰማው ሸገር ሬዲዮ ስማቸውና ድምጻቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ መረጃ አቀባዮቼ አደረሱኝ ባለው መሠረት ከተጀመረ ዓመት ያልሞላው የአዲስ አበባ የቀላል ባቡር ሥራ “እየቀለለ” መሆኑን ተናግሯል፡፡ ለአገልግሎት ከተመደቡት 41 ባቡሮች ውስጥ በሥራ ላይ የሚገኙት 28ቱ ብቻ መሆናቸውን መረጃ አቀባዮቹን ጠቅሶ ሬዲዮው አስረድቷል፡፡ ሃያ አንዱ ባቡሮች በብልሽት ምክንያት አብዛኛውን ጊዜያቸውን የሚሳልፉት በጥገና እንደሆነ፤ የመለዋወጫ ችግር ደግሞ ይበልጥ … [Read more...] about የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር “እየቀለለ” ነው!
THE UGLY FACE OF DOUBLE STANDARD
It is frequently heard that campaigners saying democracy has no colour. Oh yes it has! We have seen what had happened to our compatriot Andargachew Tsige, haven’t we? It is also being heard shouting slogans like, “Injustice anywhere is injustice everywhere!” Not true!!! Habtamu Ayalew is dying in hospital bed denied of going abroad to get treatment to save his life. In reality, nobody cares, until such a crime against humanity knocks at the doors of the interest of those whose voices matter. … [Read more...] about THE UGLY FACE OF DOUBLE STANDARD
የህወሃቱ ሹም ራሳቸውን በራሳቸው ካዱ
በአዲስ አበባ ከተማ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሀና ማርያም፣ ፉሪ፣ ማንጎ ጨፌ ሌሎች በክፍለ ከተማው ስር ባሉ መንደሮች ከቤት መፍረስ ጋር በተያያዘ የሰው ሕይወት መጥፋቱ ይታወሳል፡፡ ሁለት ፖሊሶችና አንድ የወረዳው ሥራ አስፈጻሚ ህይወታቸው እንደጠፋ በይፋ ቢነገርም የዚያኑ ያህል ከዚህ ጋር በተያያዘ የተለያዩ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ፡፡ የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ባቀናበረው መረጃ ላይ እንዳመለከተው “መኖሪያ ቤቶቹ ይፈርሳሉ በመባሉ ከአካባቢው ነዋሪዎች የተወሰኑት አቤቱታ እያቀረቡ ባለበት ወቅት የመንግስት አፍራሽ ግብረኃይሎች ቤቱን ለማፍረስ የመብራት ትራንስፎርመር መንቀል እንደጀመሩና በዚህ መካከል ከፍተኛ ግጭት እንደተፈጠር ነዋሪዎች ይናገራሉ”። ከላይ በተጠቀሱት አካባቢዎች የመኖሪያ ቤቶች በዶዘር በሚፈርሱበት ወቅት ወንዶች በአካባቢው እንዳይጠጉ መከልከሉን ነዋሪዎች ይናገራሉ። ከተነሳው ግጭት … [Read more...] about የህወሃቱ ሹም ራሳቸውን በራሳቸው ካዱ
“ሰው አይደለም ! …” አለኝ
ገና ቁጭ እንዳልኩኝ ቀጥሮኝ እንዳገኘኝ እከሌ ጨርሶ «ሰው አይደለም!» አለኝ ምነው? ምን አ’ረገህ ? «ሰው አይደለም!» ስልህ እኮ! ምን አ’ረገህ? «ሰው አይደለም!» አልኩህ። ቢራችንን አዘን በዝምታ ቆየን እንደገና ደግሞ ሳሉን እየሳለ አንገቱን ነቅንቆ «ሰው አይደለም!» አለ። ሰው ይመስላል አልኩኝ ስሜቱን ልረዳ ፊቱን መረመርኩኝ ባ’ይኑ እየገረፈኝ አይምሰልህ! አለኝ ግንባሩ ታጠፈ ጥርሶቹን ነከሰ ጠረጴዛ መታ፣ ቢራችን ፈሰሰ ልጠራርግ መጥታ - ልጅት እያየችኝ በፊቷ ምልክት ምን ሆኗል? አለችኝ መዳፌን አሳየሁ፣ ከንፈሬን አስረዘምኩ እኔም ልክ እንደሷው በምልክት መለስኩ እሱ ግን ቀጠለ «ሰው አይደለም» ማለት «ሰው አይደለም!» አልኩኝ እኔም ተመቸሁት በቢራ ተራጨን በውስኪ ታጠብን ስሙን እያነሳን «ሰው አይደለም!» አልን። ልጅትም … [Read more...] about “ሰው አይደለም ! …” አለኝ
የህወሃት አውሬነት፣ ከውልደት እስከ ህልፈት? ወይስ አገር “እስክትፈርስ”?
* ይብላኝ ለእናንተ ለአውሬው ቀንድና ግምባሮች! ፈቃደኛ ስለመሆኑ ባደባባይ ባልተጠየቀው የትግራይ ህዝብ ስም ራሱን ተገንጣይ ብሎ ሰይሞ አገር የሚገዛው ህወሃት፣ ከቀን ወደ ቀን ግፍ እየመከረ ነው። በአገር ስም እስከ አፍንጫው በታጠቀው ጠመንጃና በዘረፈው ሃብት በመተማመን በያቅጣጫው ንጹሃንን እየጨፈጨፈ ነው። እስር ቤት አጉሮ እያሰቃየ ነው። ያልፈጸመውና የማይፈጽመው ሰቆቃ የለም። ህጻን፣ አዋቂ፣ አዛውንት፣ እናት፣ አባት ሳይመርጥ የጥይት አረሩን እያወረደ በያይነቱ ደም እየተጋተ ነው። ቂም እየከመረ ነው። ከቀን ወደ ቀን ደምና ግፍ የሚበቃው አይመስልም። ወዳጆቹም ሆኑ በስማቸው የሚነገድባቸውም ተው ሲሉት አይሰሙም። ምን ይሁን? ይህ አውሬነት እስከመቼ ይቀጥላል? “በጉልበት ትግሬ ተደረግን እንጂ ፍጥረታችን ትግሬ አይደለም” ያሉ ይገደላሉ፣ ይታፈናሉ፣ ይገረፋሉ፣ እርሻቸው ይነጠቃል፣ … [Read more...] about የህወሃት አውሬነት፣ ከውልደት እስከ ህልፈት? ወይስ አገር “እስክትፈርስ”?
“እማ…እንደበቅ” የህጻን ኤማንዳ ሽብር ህይዎት!
* እልፍ አዕላፍን ያመመው የአባዎራው ፖለቲለኛ ህመም * የሐይማኖት አባቶች ሆይ ትለመናላችሁ! የእልፍ አዕላፍን ... ህመም! አባወራው ወጣት ፖለቲከኛ ሃብታሙ አያሌው ታመመ አሉን ፣ አንበሳው በበሽታ ተቀስፎና ተሸንፎ በህክምና እርዳታ መስጫ አልጋ ተጋድሞ፣ የህክምና መሳሪያ ተገጥሞለት ተመለከትን ...ሃብታሙን በአካል የሚያውቀው ብቻ ሳይሆን በስም በዝና የምናውቀው ሁላችንም ደነገጥን፣ ህመሙ የመርዶ ያህል አስነባን ፣ ኢትዮጵያውያን ከአድማድ እስከ አድማስ የምንይዝ የምንጨብጠው አሳጣን ...! የሃብታሙን በጸና መታመም እንደሰማሁ ለሚመለከታቸው የምልጃ መልዕክቴን እንደ ዜጋ፣ ብሎም የድረሱለት መረጃችን በገጼ ላይ አስተላለፍኩ፣ አሰራጨሁ! ይህንን መረጃ ተከትሎ በሽዎች የሚቆጠሩ ወዳጆቸ ከአረብ ሃገራትና ከመላው አለም የወንድም ሃብታሙ መታመም የተጎዳ ስሜታቸውን ገልጸውኛል … [Read more...] about “እማ…እንደበቅ” የህጻን ኤማንዳ ሽብር ህይዎት!