በጎንደር የሰዎች ህይወት ከማለፉ በተጨማሪ ሕዝብ የማያምንባቸውንና ከትግራይ ተገንጣይ ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው ባላቸው ንብረቶች ላይ ርምጃ መውሰዱ ታውቁዋል። ማክሰኞ ሊነጋጋ አካባቢ ተነሳ የተባለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለመቀላቀል ወደ ጎንደር ያመሩ ወገኖችም መበራከታቸው እየተሰማ ነው። ለዓመጹ ውጤታማነት የዘር ትግል ሳይሆን ኅብረብሔራዊ እንቅስቃሴ እንደሚበጅ ተገለጸ።
አመጹ የተቀሰቀሰው የማንነት ጥያቄ ባነሱና “እኛ አማራ እንጂ ትግሬ አይደለንም” በሚል የተነሳውን ጥያቄ ከውጤት ለማድረስ ከተመረጡት የኮሚቴ አባላት መካከል አራት የሚሆኑትን ከትግራይ የመጡ ነፍጥ አንጋቾች ከያዟቸው በኋላ እንደሆነ ለኢሳት በድምጽ ማብራሪያ የሰጡ አረጋገጠዋል። ከዚያም ኮሎኔል ዘውዱ ደመቀን ለመያዝ ሙከራ ተደረገ። ይህን ጊዜ ኮሎኔሉ “በሬን አልከፍትም ጥዬ እወድቃለሁ” በማለት ሊያስሯቸው ከመጡት ሃይሎች መካከል ሁለቱን” ጣሉ። ይህንን የሰሙ የወልቃይት ሚሊሻዎች በስድስት አውቶቡስ ጎንደር ደረሱ። ቀደም ሲል ህዝብ የኮሎኔሉን ቤት ከቦ አላስነካም ብሎ ቆየቶ ነበርና በመደጋገፍ ኮሎኔል ዘውዴ ጥቃት ሳይደርስባቸው ከቤታቸው ማስወጣት እንደተቻለ ለኢሳት ማብራሪያ ከሰጡት ለማወቅ ተችሏል።
አክለውም የዞኑ አስተዳደርና የክልሉ ሃላፊዎች እየሆነ ስላለው ሲነገራቸው ያለማቅማማት “የምናውቀው ነገር የለም። የምትችሉትን ርምጃ ውሰዱ። ነገር ግን መሳሪያ አንሰጣችሁም” የሚል ምላሽ እንደሰጧቸው ስም ጠቅሰው ተናግረዋል።
ከትግራይ መጡ የተባሉትና የክልሉንም ሆነ የዞኑን ፈቃድ ካላገኙት ታጣቂዎች መካከል 6 የሚሆኑት የተገደሉ ሲሆን ከህዝብ ወገን ቁጥሩ በትክክል ያልተገለጸ ህይወት ማለፉን የማህበራዊ ገጾች እየዘገቡ ነው። የህወሃት ሚዲያም 4 የፖሊስ አባላት መገደላቸውን ይፋ አድርጓል። ጉዳዩንም ከዘረፋና ከሽብር ጋር አያይዞታል።
ኢሳት በተከታታይ ያነጋገራቸው ሰው እንዳሉት የወረቀት ጥያቄ ላቀረቡ የህብረተሰብ ክፍሎች ምን በደል ሰርተው ይህ ሁሉ ስቃይ እንደሚደርስባቸው ግልጽ አይደለም። በዚሁ መነሻ በህወሃት የበረሃ ትግል ወቅት ምግብ፣ መሬት፣ ከለላ በመስጠት፣ ደግሶና አካፍሎ ሲያበላ የነበረ የወልቃይት ህዝብ ውለታው ይህ መሆኑን በማስታውስ “የትግራይን ህዝብ ከወንድሙ የአማራ ህዝብ ጋር የህወሃት ባለስልጣናት ደም እያቃቡት ነው። የትግራይ ህዝብ ይህን ጉዳይ እንዴት ያየዋል?” ሲሉ ጠየቀዋል። አያይዘውም “ለወደፊትስ አስቸጋሪ አይሆንም? አማራ ምን አደረገ?” ሲሉ መልዕት አስተላልፈዋል።
ሕዝባዊ ቁጣው መጠኑን እየጨመረ ሲሆን በዳባት ተመሳሳይ ተቃውሞ መጀመሩም ተጠቁሟል። እንደ ማብራሪያ ሰጪዎቹ ከሆነ አሁን የተነሳው ህዝባዊ አመጽ “አማራውን ሊያጠፉት ነው ሳትጠፋ የቻልከውን አጥፋ” ወደሚል ምሬትና አልሞት ባይ ተጋዳይነት ተሸጋግሯል።
አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች “አማራውን ገፍተው ገፍተው እዚህ አደረሱት” ሲሉ አሁንም ህወሃት ጥንቃቄ ሊወስድ እንደሚገባው፣ በሃይል እገፋበታለሁ ካለ ነገሮች መስመራቸውን ሊስቱ እንደሚችሉ ጠቁመዋል። ስለሆነም ዓመጹ ውጤታማ እንዲሆን በዘር ወይም በወገን ወይም በብሄር ላይ ያተኮረ ከመሆኑ ይልቅ ሁሉንም ያካተተ ህብረብሄራዊ ሊሆን እንደሚገባ ለጎልጉል አስተያየታቸውን የሰጡ ወገኖች አስታውቀዋል። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ በህወሃት ጥቃት ያልደረሰበት፥ ያልተጎዳ፥ ስቃይ ያላየ አለመኖሩ ሁሉንም የጥቃት ሰለባ በአንድነት ሊያስተባብር የሚችል ችግር መኖሩ ግልጽ ነው የሚሉት ወገኖች መፍትሔውንም በጋራ መቀመም ብልሃት የሚጠይቅ ለሁሉም ወገን የሚጠቅም አማራጭ ነው በማለት ተደማጭነት ያላቸው፥ በሁሉም ሰው ዘንድ መሰማት የሚችሉ ግለሰቦች መሪውን መጨበጥ የሚገባቸው ሰዓት አሁን ነው ይላሉ። ከዚህ በታች ያለውን የፎቶ መረጃ ያገኘነው በተለያዩ ግለሰቦች ከተሰራጩ የማህበራዊ ሚዲያዎችና ገጾች መሆኑንን እንገልጻለን።
gud says
Aye Gura
Gonder has never truly ruled itself in its history
Bekafa (Oromo ) ,Michael Shehul (tigrai ) Tewodros ( Wello Oromo ) ruled it for centuries
Melaku Tefera under Mengistu ( Gimira )order ( Gondere) ruled it for years
gud says
Fukera
These people r In 18th century . Need proper education .
Hwala kernet at its best !