• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“እማ…እንደበቅ” የህጻን ኤማንዳ ሽብር ህይዎት!

July 1, 2016 04:23 am by Editor Leave a Comment

* እልፍ አዕላፍን ያመመው የአባዎራው ፖለቲለኛ ህመም
* የሐይማኖት አባቶች ሆይ ትለመናላችሁ!

የእልፍ አዕላፍን … ህመም!

አባወራው ወጣት ፖለቲከኛ ሃብታሙ አያሌው ታመመ አሉን  ፣ አንበሳው በበሽታ ተቀስፎና ተሸንፎ በህክምና እርዳታ  መስጫ አልጋ ተጋድሞ፣ የህክምና መሳሪያ ተገጥሞለት ተመለከትን …ሃብታሙን በአካል የሚያውቀው ብቻ ሳይሆን በስም በዝና የምናውቀው  ሁላችንም ደነገጥን፣ ህመሙ የመርዶ ያህል አስነባን ፣ ኢትዮጵያውያን ከአድማድ እስከ አድማስ የምንይዝ የምንጨብጠው አሳጣን …! የሃብታሙን በጸና መታመም እንደሰማሁ ለሚመለከታቸው የምልጃ መልዕክቴን እንደ ዜጋ፣ ብሎም የድረሱለት  መረጃችን በገጼ ላይ አስተላለፍኩ፣ አሰራጨሁ!

ይህንን መረጃ ተከትሎ በሽዎች የሚቆጠሩ ወዳጆቸ ከአረብ ሃገራትና ከመላው አለም የወንድም ሃብታሙ መታመም የተጎዳ ስሜታቸውን ገልጸውኛል … እንዲያው በአጠቃላይ የሃብታሙ ህመም ያላመመው ሃገር ወዳድ አይገኝም ብል የተሳሳትኩ አይመስለኝም …! የከሳሽ ፈራጁ የኢህአዴግ መንግስት ደጋፊዎች እንኳ ሰብዕና አጥቅቷቸው ያየሁበት አጋጣሚ የሃብታሙ መታመም ነበር፣ አዝነው የተጎዳ ስሜታቸውን የገለጹልኝ ብዙ ናቸው! …  ብቻ በትንታጉ ወጣት ፖለቲከኛ አያያዝ  ያላዘነ የለም፣ እውነቱ ይህ ሆነና እልፍ አዕላፎች “ሃብታሙ አያሌው የተሻለ ህክምና ያግኝ ፣  የኢትዮጵያ መንግሰት የጣለበትን እገዳ ያነሳ!” እያል በዘነበው የመረጃ ማስተላለፊያዎች የዜጋ ድምጻችን እያሰማን እንገኛለን!

” እማ … እንደበቅ” የህጻን ኤማንዳ ሽብር ህይዎት!

በደመቀው የሮመዳን ምሽት ከሃገር ቤት የመጣች የአንድ ብርቱ ወዳጆን ልጅ ሊኑንና ጎረምሳ ልጆቸን ከነጓደኞቻቸው ሰባሰቤ ወደ አምድ መዝናኛ እያመራን እያለ ስልኬ አቃጨለ … አዲስ ቁጥር ነው፣ መኪናየን በረድ አድርጌና ወደ አንዱ የመንገድ ጫፍ ጠጋ ብየ ስልኬን አነሳሁ፣ እንባ የሚተናነቃት አንዲት እህት ስለ ሃብታሙ ስቃይና የተሰማትን ሃዘን በእልህ ቁጭት ገለጸችልኝ … “አላህ አለ፣ አላህ ፍርዱን ይሰጣል!” ብላ እስክትሰናበተኝ በውስጤ ጥልቅ የተጎዳው ስሜቷ አልጠፋም…

ሃብታሙን በተጻፈውና ባየችው እንጅ በአካል የማያውቀው የዚህች ሰብአዊ እህት ቁጭትና አዘኔታ የወገን ኩራት ስንቅ ሲሆነኝ ሌላ ህመሜን ግን ጫረው  … የጫረብኝ ህመም አባት ሆኘ ከማውቀው የልጅ ፍቅር የተገናኘ ነውና ህመሙ ብርቱ ነው … ውስጤን ሲያንገላታው  የሰነበተው የሃብታሙ የአራት አመት ልጅ የኤማንዳ መከራ ነበር!

ኤማንዳ ህመሜን አበዛችው … ታሪኩን ከቀናት በፊት የሃብታሙ የክፉ ቀን ፣  የቅርብ ወዳጅ የሆነው ዳንኤል ሽበሽ ነው ያካፈለን … ያ የኤማንዳ የውስጥ እውነት የዳኒ ምስክርነት ቃል ቀልቤን ጨምድዶት ውሎ አድሯል። “እማ እንደበቅ!” ስላለችው የሃብታሙ ቅምጥል  የኤልዳማ ሽብር ህይዎት ህመም ዳንኤል ካስተላለፈውን መልዕክት ሳልወጣ ታሪኩን ሰብሰብ አድርጌ አስቃኛችኋለሁ! የፈቀዳችሁ ብቻ ተከተሉኝ …

ህጻን ኤማንዳ ከሀምሌ አንድ ቀን 2006ዓ.ም ጀምሮ ታስሮባት ለሁለት አመት ከእናትዋ ጋር አባቷን ለመጠየቅ ወደ ማዕከላዊና ቂሊንጦ ወህኒ ቤት ተመላልሳለች። በእኒህ ሁለት አመታት ለሁለት ዓመቷ ህፃን ህግ አስከባሪ ፖሊስ ማለት ጭራቅ ሆኖ ተቀርጾባታል፣ የደንብ ልብስ የለበሰ ህግ አስከባሪ ፖሊስ ለእርሷ ስታየው የምትበረግግ ጠላቷ ይሆን ዘንድ ተመርዛለች … የሁለተኛ አመቷን  ልደት በማዕከላዊ ሶስተኛ ዓመቷን በቂሊንጦ ወህኒ ቤት አክብራለች ፣ ልደቷን  በፖሊስ ከተከበበ አባቷ ጋር ላፍታ አክብራ ስትመለስ ከአባቷ የለያያት ፖሊስ መሆኑን ህጻኗ አውቀዋለችና ፖሊስን እንደ እንደ ሠይጣን ፣ ጭራቅ መፍራት ይዛለች …!

ህጻን ኤማንዳ በእስር ቤት ቆይታው በሽታ ላይ የወደቀው አባቷ  ሀብታሙ አያሌው ከእስር በነጻ ቢፈታም ህመሙ ጸንቶበት የአባቷን ስቃይ ተመልካች ሆነች … ምንም እንኳን ሃብታሙ በነጻ ከእስር ተፈትቶ አቃቤ ህግ ባቀረበው ይግባኝ ለመከራከር ቢፈቀድለትም ህመሙ አላላውስ ብሎ በርቶበታል … ህመሙ ከፍ ወዳለ ደረጃ ደርሶ በሃገር ውስጥ መታከም ስለማይችል ከሃገር ወጥቶ መታከም እንዳለበት ሐኪም መረጃ ሰጥቶታል፣ ዳሩ ግን ጉዳዩ በፍርድ እየታየ በመሆኑ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ካገር እንዳይወጣ እግድ ተጥሎበታል! ህክምናው እያደር ሲበረታ ለፍርድ ቤቱ  የተሻለ ህክምና ያገኝ ዘንድ የተጻፈለትን የሀኪም ማስረጃ በማቅረብ  እገዳው ተነስቶለት  ካገር ውጭ ይታከም ዘንድ በጠበቀው በኩል ያቀረበው አቤቱታ አዎንታ ተነፈገው!

ሃብታሙ  ከሀገር ወጥቶ የመታከም ተስፋው በተጣለበት እገዳ ምክንያት ሲጨልም የጨነቃቸው ቤተሰብና ወዳጆቹ በባህል ህክምና እንዲያገኝ ሌላ መላ መቱ! … ከአዲስ አበባ 40 ኪ.ሜ ርቀን በአንድ ገጠር ቀበሌ ውስጥ ህክምና ጀመረ … በባህል ህክምናው ከባድ የስቃይ ጊዜ ካሳለፈ በኋላ የባህል ሀኪሙ ወደ መኖሪያ ቤቱ መጥቶ እንዲረዳው የተደረገው ተማጽኖ ተሳክቶ የባህል ሀኪሙ ወደ ሃብታሙ ለመምጣት ፍቃደኛ ሆኑ፣ ባለ ባህል ሐኪሙ የፓሊስ አባል የደንብ ልብሳቸውን እንደለበሱ ወደ አባወራው ወጣት ፖለቲከኛ ሃብታሙ አያሌው ቤት ደረሱ …  በር አንኳኩተው በር ሲከፈትላቸው ብላቴናዋ የሃብታሙ ልጅ ኤማንዳ  ተመለከተች … በድንጋጤ ወደ ኋላ በመሮጥ የእናቷን ቀሚስ ይዛ ‹‹እማ … እማ … እንደበቅ ፓሊስ መጣ›› እያለች ግቢውን በጩኸት አደባለቀችው። ኤማንዳ በሁለት አመት የማዕከላዊና የቂሊንጦ  ምልልስ፣ በልደቷ ቀን … ያየቻቸው፣ የምታውቃቸው ፖሊሶችና የፖሊስ የደንብ  ልብስ  የለበሰ ያሸብራታል፣ እናም በገዛ ቤቷ ለአባቷ ፈውስ በመጣው ፖሊስ ሀኪም ትሸበር ዘንድ ግድ ሆነየኤማልዳን ሽብር ህይወት ህመም ዳንኤል በምስክር እማኝነቱ ካስተላለፈው መረጃ ጥቂቱ ህመም የጫረው የኤማንዳ ህመም የእኔን ልጆች፣ የጋዜጠኛ እስክንድር ልጅ፣ የጋዜጠኛ ውብሸት ልጅ፣ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከመደረሱ የሚያሳድጋቸው ልጆች … ብቻ ሳይሆን በግፍ የሚንገላቱ የብዙ ሽህ ወገኖች ልጆች  ህመም ነው።

የሐይማኖት አባቶች ሆይ ስሙን!

አንደበተ ርቱዑ የሃብታሙ አያሌው ዛሬ ህመሙ ከፍቶበት ከላይ የፖሊስ ደንብ ልብስ አይታ ስትሸበር በምናብ ያየናት ህጻን ኤማንዳ፣ በክፉ ደጉና በእንግልቱ ከጎኑ ያልተለየችው ባለቤቱ፣ ወዳጆቹ ፣ አፍቃሪዎቹና ራዕዩን ተከትለን የምንወደው አፍቃሪዎቹ በሃብታሙ ህመም ታመን ከፍቶናል። ህመሙ የጸናበት ሀብታሙ እግዱ ተነስቶለት የተሻለ ህክምና ያገኝ ዘንድ እልፍ አዕላፍ ዜጎች መንግስትን እየተማጸንን እንገኛለን!

የሐይማኖት አባቶች ሆይ!  ወዴት ናችሁ? እያልን ትናንት አላደረጋችሁትምና አንወቅስ አናወግዛችሁም! ዛሬ ስለ ፈጣሪ ብላችሁ፣ ሰብዕና ተሰምቷችሁ የተጨነቀው  ወንድማችን ሃብታሙ ፈውስ ያገኝ ዘንድ ምህረትን ለምኑለት! እንደ ሀገር ሽማግሌ፣ እንደ ሃይማኖት አባት ደግሞ  አባወራው ፖለቲከኛ ወጣት ሃብታሙ አያሌው ከሐገር እንዳይወጣ የተጣለበት እገዳው ተነስቶለት ወደ ውጭ ሃገር ሄዶ እንዲታከም የእናንተን ድምጽና ግፊት ይሻል፣ የቤተሰቡን ከምንም በላይ ብላቴና የኤማልዳን ህመም ተረዱት፣  አባታዊ ጣልቃ ገብነታችሁ ያስፈልገናል! ከፈጣሪ በታች ድምጽ ትሆኑን ዘንድ እንማጸናችኋለን!

ከምንም በላይ ሁሉን ማድረግ የማይሳነህ አምላክ ሁሉም በእጅህ ነውና ተማለደን! ለወጣቱ ፖለቲከኛና አባወራው ሃብታሙ አያሌው ምህረት ላክለት!

ነቢዩ ሲራክ
ሰኔ 24 ቀን 2008 ዓም

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule