ባለፉት 25 አምታት የአማራው ሕዝብ ላይ በትግሬ ወያኔዎች የተፈጸመበት ግፍና መከራ ፤ በአይነት ፤ በመጠንና በይዘት ተሰፍሮና ተነግሮ የማያልቅ ነው። አማራው ኢትዮጵያዊነቱን ማተቡ አድርጎ በመኖሩ ፤ በዘር ማንነቱ ላይ የተከፈተበትን የማያባራ ጦርነት ለመመከት በማንነቱ ዙሪያ ተደራጅቶ ከመታገል ይልቅ ፤ የዘር ፖለቲካ ሃገር ያፈርሳል በሚል ሰፊ አተያይ ፥ ካራ ስለው ጉድጓድ ምሰው ደሙን ሲጠጡና ስጋውን ሲበሉት የቆዩትን ሕገ አራዊት የትግሬ ነጻ አውጪ ወንበዴዎችን ከፍ ሲል በንቀት ፤ ዝቅ ሲል በአላዋቂነትና በችጋራምነት እየታዘበ በጊዜ ሂደት ሲጠግቡ ይሰክናሉ በሚል ክፉኛ ተዘናግቶ በመቆየቱ ራሱንና ሃገሩን መከላከል በማይችልበት ደርጃ ተበታትኖ የተናጥል ጥቃቱን ሲያስተናግድ ቆይቷል። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about በጎንደር የተጀመረው አመጽ የአማራው ሕዝብ የሕልውና ትግል ነው !!
Archives for July 2016
“ወልቃይትና ጠግዴ በኢትዮጵያ ታሪክ በትግራይ ስር ሆነው አያውቁም” ታሪክ
የወልቃይት ጉዳይ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ ደም እያፋሰሰ ባለበት በሁኑ ወቅት ቴድሮስ አድሃኖም ወልቃይትን የትግራይ ግዛት አድርገው በመቁጠር "የአማራ ብሔር ተወላጆች ወልቃይት መጥተው መኖር ከፈለጉ የትግራይ ሕዝብ በደስታ ይቀበላቸዋል" በማልተ የትግራይ ሕዝብ ወክለው ስለ ወልቃይት የትግራይ ክልልነት በድፍረት በፌስቡክ ላይ ይህንን ብለዋል - ሙሉው ቃል ከዚህ በታች ይገኛል:- በጎንደር የተከሰተውን የማንነት ጥያቄ ሰበብ በማድረግ አንዳንድ ግለሰቦች ብጥብጥ ለማስነሣት ቢሞክሩም መንግሥታችን በሰከነ ዘዴ በአጭር ጊዜ ውስጥ በቁጥጥር ሥር አውሎታል:: የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከአማራ ተወላጆች ጋር በመወያየትና በማሳመን የወልቃይትን መሬት የትግራይም ሆኑ የአማራ ተወላጆች በጋራ እንዲኖሩበት በማግባባት ላይ ይገኛል፡፡ ወልቃይት የአማራ ነው በማለት የሚነዛው ፕሮፓጋንዳም የሐሰት መሆኑና … [Read more...] about “ወልቃይትና ጠግዴ በኢትዮጵያ ታሪክ በትግራይ ስር ሆነው አያውቁም” ታሪክ
የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ ስብስብ በሰሜን ካሊፎርኒያ
የኢትዮጵያ ሕዝብ በአሸባሪውና በፋሽስቱ ወያኔ ቁጥጥር ሥር ወድቆ 25 የመከራና የፍዳ ዓመታትን አሳልፎ 26ኛውን ጀምሮዋል:: በዚህ ረጅም የመከራ ዓመታት አንድም ቀን ወያኔን ከመታገል የተቆጠበበት ጊዜ ግን አልነበረም:: ወያኔም ባደራጀው የመጨቆኛ መሳሪያው: በወታደሩ: በስለላ መረቡ እና በመሳሰሉት የዘረኝነት አገዛዙን ለማራዘምና ኢትዮጵያን የማጥፋት ተልኮውን ከፍጻሜ ለማድረስ ከዚያም የኔ የሚለው አዲስ አገር ለመመስረት ባለው እቅድ ሕዝባችን በዘርና በሃይማኖት ከፋፍሎ እርስ በርሳችን ለማባላት ያደረገው ሙከራ በሕዝባችን እምቢተኝነትና አገር ፍቅር ከመከፋፈል ይልቅ አንድነትን በመምርጡ ያቀደውን ከግብ ለማድረስ ቀላል አልሆነለትም:: ይህን ተልኮውን ከግብ ለማድርስ መጀመሪያ ዓማራውን ለይቶ በሌሎች ጎሳወች ለማጥቃት ሞከረ: አልሆን ሲለው ደረጃ በደረጃ ወደሌሎች ጎሳወችም ፊቱን አዞረ:: … [Read more...] about የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ ስብስብ በሰሜን ካሊፎርኒያ
በጎንደር ሕዝባዊ አመጽ ለመቀስቀሱ መሠረታዊው ምክንያት ወያኔ በሕዝቡ ላይ ለ25 ዓመታት የፈጸመው ግፍ ነው!
ከሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ የትግሬ ወያኔ በጎንደር ዐማራ ሕዝብ ላይ እየፈጸመ ያለው በዘር ላይ ያነጣጠረ ጭፍጨፋ፣ ከባለፉት 40 ዓመታት ጀምሮ ሲያደርገው የነበረው ጭፍጨፋና ዐማራን ከምድረገጽ የማጥፋት ዓላማው ተከታይ እንደሆነ ወያኔ የተጓዘበት ጉዞና የቆመለት ዓላማ በግልጽ ያሳያል። የጭፍጨፋው አጀማመርና ሂደት እንዲህ ነው፥ ከሃያ የሚበልጡ የወያኔ ልዩ ኃይል ፖሊሶች፣ ሐምሌ መጀመሪያ 2008 ዓም ላይ የትግሬው ገዥና የወያኔ ሊቀመንበር በሆነው ዐባይ ወልዱ ልዩ ትዕዛዝ ጎንደር ከተማ ገብተው የተለያዩ የስለላ ሥራዎችን ሢሠሩ እንዲቆዩ ተደረገ። የአፋኝ ቡድኑ አባሎች ወደ ጎንደር ከተማ እንዲገቡ የተደገበት ስበብ፣ የዐሥራ ሁለተኛ ክፍል የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተናን ለመቆጣጠር በሚል ምክንያት እንደሆነና እነርሱም ከሕዝቡ ጋር ባደሩት ግንኙነት ይኸንኑ የ«በሬ ወለደ» ወሬ ሲያዛምቱ … [Read more...] about በጎንደር ሕዝባዊ አመጽ ለመቀስቀሱ መሠረታዊው ምክንያት ወያኔ በሕዝቡ ላይ ለ25 ዓመታት የፈጸመው ግፍ ነው!
ያዲሳባው ሽምቅ ውጊያ!
እንዴት ናችሁ!? ‹‹በዛሬዋ መሐል አዲስ አበባ መኪና ማቆምያ ማግኘት መኪና ከመግዛት ያልተናነሰ መታደልን ይጠይቃል›› በሚል ጦማሬን ልጀምር አስቤ ተውኩት፡፡ ለምን ተውኩት? ጠዋትና ማታ እንደ ፓስታ በተዝለገለገ የታክሲ ሰልፍ እግሩ ሸምበቆ እያከለ ለመጣ አዲስ አበቤ ዐረፍተ ነገሬ ቁጣን ይቀሰቅሳል ብዬ፡፡ የዛሬ አነሳሴ በአዲስ አበባ እየከፋ ስለመጣው የመኪና ማቆምያ ችግር ለመጻፍ ነበር፡፡ ሁለተኛ አንቀጽ ላይ ስደርስ የግዜርን ቁጣና የአንባቢን ተግሳጽ ፈርቼ ተውኩት፡፡ ነገሩ ለተራበ ሕዝብ ‹‹ኬክ የመጋገሪያ ስልቶች›› የሚል አጭር ስልጠና እንደመስጠት ሆኖብኝ ተውኩት፡፡ .እንዳዲሳባ ሕዝብ አንጀት የሚበላ አለ እንዴ? ከተማ ለመኖር በመፈለጉ ብቻ ፀሐይና ብርድ የሚፈራረቅበት አዲሳቤን የመሰለ ምስኪን ሕዝብ አለ? ካለ ንገሩኝ፡፡ ኡዝቤኪስታንም- ታጃኪስታንም ቢኬድ እንዳዲሳባ … [Read more...] about ያዲሳባው ሽምቅ ውጊያ!
የኢትዮጵያ ጉዳይ መጽሔት
መጽሔቱን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። … [Read more...] about የኢትዮጵያ ጉዳይ መጽሔት
የአሁኑ የተለየ ነው
በጎንደር እየተካሄደ ያለውን ሀቅ፤ ሁላችንም በተለያየ መልክ እየተከታተልን ነው። በኢትዮጵያ ያለው መንግሥት የማንና ምን አንደሆነ በግልጽ ታይቷል። ሕዝቡም የደረሰበትን የ”በቃኝ!” ደረጃ እያየን ነው። አሁን በፓልቶክና በደረገጽ፤ በሬዲዮና በቲቪ መወሰናችን ያበቃበት ሰዓት ነው። ይህ ትግል እስከዛሬ ከተደረጉት ማናቸውም ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች የተለየ ነው። በአኝዋክ ዘመዶቻችን አልቀዋል። በኦጋዴን ዘመዶቻችን ረግፈዋል። በኦሮሚያ ዘመዶቻችን ተገድለዋል። በተለያየ መልክ ሕዝቡ ምሬቱን ገልጿል። ከፍተኛ መስዋዕትነት ክፍሏል። ይህ ሁሉ ተደማምሮ አሁን የተነሳውን ሕዝባዊ አመጽ ወልዶታል። አሁን፤ የእስከዛሬው ጥርቅም ብሶት ውጤት ነው ከኢትዮጵያ ሕዝብ ፊት የተደቀነው። የአሁኑ የተለየ ነው። በጎንደር የወልቃይትን ማንነት ይዞ የተነሳው ወገናችን ጥያቄ፤ የማንነት ብቻ ሳይሆን፤ የወራሪውን … [Read more...] about የአሁኑ የተለየ ነው
የክብር ዶክትሬት ክብሩን እያጣ ነው ተባለ
በሀገሪቱ ያሉ ዩኒቨርስቲዎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በየዓመቱ ለሁለትና ሶስት ሰዎች የክብር ዶክትሬት መስጠትን እንደ ልማድ መያዛቸው ከክብር ዶክትሬት መሰረታዊ አላማዎች ጋር የሚፃረርና ክብሩን የሚያራክስ ነው ሲሉ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለፁ፡፡ የክብር ዶክትሬት የሚሰጥባቸው መስፈርቶች በመርፌ ቀዳዳ ግመል እንደ ማሽሎክ ያህል ናቸው ያሉት ምሁራኑ፤ በአሁን ወቅት አዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች ጭምር ፉክክር በሚመስል መልኩ ዶክትሬቱን የሚሰጡበት አካሄድ በአስቸኳይ ሊታረም እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡ የክብር ዶክትሬቱ የተሰጠባቸው ግለሰቦችም ለስም መጠሪያነት መጠቀማቸው ተገቢ አይደለም ያሉት ምሁራኑ፤ መገናኛ ብዙኃን የክብር ዶክትሬት የተሰጠውን ግለሰብ፤ “የክብር ዶክተር” እያሉ መጥራታቸውም አግባብ ባለመሆኑ ማረም ይኖርባቸል ብለዋል፡፡ የቋንቋና ስነ ፅሁፍ ምሁሩ ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ፤ ከሀገሪቱ … [Read more...] about የክብር ዶክትሬት ክብሩን እያጣ ነው ተባለ
የሕዝብ መብት የማያከብር መንግሥት በሕዝብ አመፅ ይወገዳል
ላለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ሥልጣኑን በጉልበት ወስዶ፣ የሕዝቡን መብት ገፎ፣ ያገሪቱን ሃብትና ንብረት የሚዘርፈው ቡድን ሥልጣኑና አድራጎቱ ዝንተ-ዓለማዊ እንደማይሆን ከወደቁትና ከተወገዱት ተመሳሳይ መንግሥታት ታሪክ ገና አልተማረም። ከፋፍዬ እኖራለሁ የሚለው ስልቱ እየተጋለጠ በየአቅጣጫው በሕዝብ ተቃውሞ እየተዋከበ ይገኛል። ወደ ታሪክ መቃብር የሚገባበት ቀን እያጠረ መጥቷል። አሁን በጎንደር ቀደም ሲል በሸዋ በተለያዩ ያኦሮሚያ ክልል አካባቢወች በጋምቤላና በሌሎቹም ያገሪቱ ክፍሎች የተነሳው ሕዝባዊ አመፅ ይህን የሚያመላክቱና ውድቀቱን የሚያፋጥኑ ተቃውሞዎች ናቸው።... ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ … [Read more...] about የሕዝብ መብት የማያከብር መንግሥት በሕዝብ አመፅ ይወገዳል
Perspectives on the Trilateral Agreement on the Grand Ethiopian Renaissance Dam:
This commentary is our fourth installment on the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD). It is sparked by the news item which was posted on the pro Tigrean People’s Liberation Front (TPLF) website, on July 9, 2016. Citing Sudan Tribune as its source, Aigaforum indicated what the Egyptian Minister of Water Resources and Irrigation, Mohamed Abdel Ati, is reportedly had said. The statement is related to the arrangement about the legal affairs of GERD. The news item states that “…a U.K. based law … [Read more...] about Perspectives on the Trilateral Agreement on the Grand Ethiopian Renaissance Dam: