የኢትዮጵያ ሕዝብ በአሸባሪውና በፋሽስቱ ወያኔ ቁጥጥር ሥር ወድቆ 25 የመከራና የፍዳ ዓመታትን አሳልፎ 26ኛውን ጀምሮዋል:: በዚህ ረጅም የመከራ ዓመታት አንድም ቀን ወያኔን ከመታገል የተቆጠበበት ጊዜ ግን አልነበረም:: ወያኔም ባደራጀው የመጨቆኛ መሳሪያው: በወታደሩ: በስለላ መረቡ እና በመሳሰሉት የዘረኝነት አገዛዙን ለማራዘምና ኢትዮጵያን የማጥፋት ተልኮውን ከፍጻሜ ለማድረስ ከዚያም የኔ የሚለው አዲስ አገር ለመመስረት ባለው እቅድ ሕዝባችን በዘርና በሃይማኖት ከፋፍሎ እርስ በርሳችን ለማባላት ያደረገው ሙከራ በሕዝባችን እምቢተኝነትና አገር ፍቅር ከመከፋፈል ይልቅ አንድነትን በመምርጡ ያቀደውን ከግብ ለማድረስ ቀላል አልሆነለትም:: ይህን ተልኮውን ከግብ ለማድርስ መጀመሪያ ዓማራውን ለይቶ በሌሎች ጎሳወች ለማጥቃት ሞከረ: አልሆን ሲለው ደረጃ በደረጃ ወደሌሎች ጎሳወችም ፊቱን አዞረ:: በመሆኑም ኦሮሞውን: አፋሩን: ሱማሌውን: ጋምቤላውን ወዘተ ማጥቃቱን ቀጠለ:: በእያንዳንዱ ጎሳ ላይ ያደረሰውን ግፍና በደል ከዚህ ላይ መዘርዘሩ ለቀባሪ ማርዳት ስለሚሆን እናልፈዋለን:: አንድ ነገር ሳንጠቅሰው ማለፍ የማንፈልገው ነገር: ባለፉት ሳምንታት በአዲስ አበባ መኖሪያ ቤታቸውን በላያቸው ላይ ያፈረሰባቸውን ወገኖቻችንን ነው:: መንግሥት በሕዝብ ተጠያቂ በሆነበት አገር: ክረምትና ብርድ ሲመጣ መንግሥት ቤት ለሌላቸውና በጎዳና ለሚያድሩ ጊዜአዊም ቢሆን መጠለያ አዘጋጅቶ ያስጠልላል:: ወያኔ ግን በክረምት ቤት ያላቸውን ሰዎች ቤታቸውን በላያቸው ላይ አፍርሶ ባልቴቶችን: አዛውንቶችን: ህፃናትንና ገና ሳምንት ያልሞላቸውን ጨቅሎችን ለዝናብና ለብርድ አጋልጦአቸዋል:: ይህን አይነት ጭካኔ ለመግለጥ ቃል ወይም ቃላት ፈልገን ለማግኝት አልቻልነም::
በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ስም አርሶ አደር ወገኖቻችን አፈናቅሎ መሬታቸውን ለመዝረፍ ሲዘጋጅ የወላጆቻቸውን መሬት መነጠቅ በሰላማዊ መንገድ የተቃወሙ ወጣቶችን በጭካኔ ገደለ አሰረ አሰደደ:: ወያኔ ገና ሲጀምር ኢትዮጵያን አጥፍቶ አዲስ አገር ለመመስርት በነደፈው እቅድ መሰረት አዲስ አበባን በተቆጣጠረ ማግስት ከጎንደርና ከወሎ ለምና ሰፊ መሬት ወደትግራይ ከለለ:: የአካባቢውን ነዋሪና ተወላጅ የሆኑትን የወልቃይት: የጠገዴና የጠለምት ዓማራወችን ብትፈልጉ ትግሬነትንና የእኛን የበላይነት ተቀብላችሁ ኑሩ ካልሆነ መሬቱን እንጅ እናንተን አንፈልጋችሁም በማለት የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ዘመቻውን ቀጠለ:: የነዚህ ወረዳወች ነዋሪ የሆኑት ዓማራወችም ማንነታቸውን ለማስከበር መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አቁዋቁመው ራሱ ወያኔ ህገመንግስቴ በሚለው መንገድና ህጉን ተከትለው ያደረጉትን ሙከራ እንደድፍረት በመቁጠር: የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን ጎንደር ከተማ በሌሊት መጥቶ በማፈን: የገደለውን እየገደለ የያዘውንም እየያዘ ባለበት ጭቆናውና ግፉ ያንገፈገፈው የጎንደር ከተማና የአካባቢው ሕዝብ ሆ ብሎ ወጥቶ ወያኔን በመፋለም ላይ ይገኛል:: ወያኔም እንደለመደው ያለርህራሄ እየገደለ ነው ለመግደልም ተዘጋጅቶአል::
እኛ የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ ስብስብ በሰሜን ካሊፎርኒያ (ESNNC) አባላት የኢትዮጵያ ሕዝብ በጠቅላላ በተለይም ባሁኑ ጊዜ የጎንደር ሕዝብ ለዲሞክራሲያዊ መብቱና እንደሕዝብ ለመኖር ዋስትናው እያደረገ ያለውን ፍትሃዊ ትግል ሙሉ በሙሉ እንደግፋለን:: በምንችለው ሁሉ እገዛ ለማድረግም ዝግጁ ነን:: ቃልም እንገባለን:: ሌላውም ወገንና አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ አሁኑኑ ድጋፍና ትብብር እንዲያደርግ ጥሪአችን እናስተላልፋለን::
የኢትዮጵያ ሕዝብ በትግሉ መብቱን ያስክብራል ነፃነቱንም ይቀዳጃል!!
ETHIOPIAN SOCIETY NETWORK IN NORTH CALIFORNIA (ESNNC)
P.O. Box 612956
San Jose, CA. 95161
ethiopiansociety1@gmail.com
gud says
Even failure has a name( check the Title $