• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በጎንደር ሕዝባዊ አመጽ ለመቀስቀሱ መሠረታዊው ምክንያት ወያኔ በሕዝቡ ላይ ለ25 ዓመታት የፈጸመው ግፍ ነው!

July 16, 2016 10:48 am by Editor Leave a Comment

ከሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ የትግሬ ወያኔ በጎንደር ዐማራ ሕዝብ ላይ እየፈጸመ ያለው በዘር ላይ ያነጣጠረ ጭፍጨፋ፣ ከባለፉት 40 ዓመታት ጀምሮ ሲያደርገው የነበረው ጭፍጨፋና ዐማራን ከምድረገጽ የማጥፋት ዓላማው ተከታይ እንደሆነ ወያኔ የተጓዘበት ጉዞና የቆመለት ዓላማ በግልጽ ያሳያል። የጭፍጨፋው አጀማመርና ሂደት እንዲህ ነው፥ ከሃያ የሚበልጡ የወያኔ ልዩ ኃይል ፖሊሶች፣ ሐምሌ መጀመሪያ 2008 ዓም ላይ የትግሬው ገዥና የወያኔ ሊቀመንበር በሆነው ዐባይ ወልዱ ልዩ ትዕዛዝ ጎንደር ከተማ ገብተው የተለያዩ የስለላ ሥራዎችን ሢሠሩ እንዲቆዩ ተደረገ። የአፋኝ ቡድኑ አባሎች ወደ ጎንደር ከተማ እንዲገቡ የተደገበት ስበብ፣ የዐሥራ ሁለተኛ ክፍል የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተናን ለመቆጣጠር በሚል ምክንያት እንደሆነና እነርሱም ከሕዝቡ ጋር ባደሩት ግንኙነት ይኸንኑ የ«በሬ ወለደ» ወሬ ሲያዛምቱ እንደነበር ታውቋል።

ሆኖም፣ ዋና ተልዕኮአቸው የወልቃይት ጠገዴን ሕዝብ የማንነት ጥያቄ ሕገመንግሥታዊ በሆነ አግባብ መልስ እንዲያገኝ በሕዝቡ የተመረጡትን የኮሚቴ አባላት መኖሪያ ቤቶች፣ መውጫና መግቢያ ሰዓት፣ እንዲሁም የሰዎቹን ማንነት ለይቶ በማወቅ እነርሱን ሕዝብ ሳያውቅና ሳይሰማ አፍኖ ለመውሰድ የሚችሉበትን መንገድ ማጥናት ነበር። በእነርሱ እሳቤ የፈለጉትን የአፈና ሥራ ጥናት አጠናቀው፣ የሕዝቡን ተወካዮች ሕዝቡ ሳያውቅ በሌሊት አፍኖ ለመውሰድ አመች ቀን ሆኖ የመረጡት ሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ከእኩለ ሌሊት ላይ እንዲሆን ወሰኑ። በውሣኔአቸው መሠረት እኩለ ሌሊት ላይ የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴዎችን በየቤታቸው በጥንቃቄ እየዞሩ ማፈን ጀመሩ። በዚህ አፈና:

አንደኛ፥ አቶ አታላይ ዛፌ፣

ሁለተኛ፥ አቶ ጌታቸው አደመ፣

ሦስተኛ፥ አቶ መብራቱ ጌታሁን፣

አራተኛ፥ አቶ አለነ ሻማ የተባሉትን የኮሚቴ አባላት አፍነው ያዙ። እነዚህን አራት «የወልቃይት የማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ» አባላት አፍነው ከያዙ በኋላ፣ ለታፋኞቹ የሰጡዋቸው ምክንያት የፌደራል የመንግሥቱ የደኅንነት አባሎች መሆናቸውን ነው። አራቱን ጠንካራ የአስተባባሪ ኮሚቴ አባሎች ካፈኑ በኋላ ጉዞአቸውን ያደረጉት ሌሊት 10 ሰዓት ላይ የኮሚቴው ሰብሳቢ ወደሆነው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ቤት ነው። ኮሎኔል ደመቀ ወታደር ከመሆኑም በላይ ለበርካታ ዓመታት ከወያኔ ጋር የቆየ በመሆኑ የወያኔን ባሕሪ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ፣ በደረቁ ሌሊት እንደሌባ «ቤትህን ከፍተህ እጅህን ስጥ» ለሚለው ጥያቄ የሰጣቸው መልስ፣ ‹‹ሕጋዊ ሰዎች ከሆናችሁ፣ ጠዋት ሲነጋ በብርሃን እንነጋገር›› የሚል ነበር። አፋኝ ቡድኑ ግን ሕጋዊም ሆነ የፌደራሉ ደሕንነት አባሎችም ባለመሆናቸው፣ ኮሎኑል ደመቀ ለሰጣቸው ትክክለኛና ተገቢ ጥያቄ ተገዥ አልሆኑም። አስገድደው ለመውሰድ በቤተሰቡ ላይ የጥይት ናዳ አወረዱበት። ኮሎኔል ደመቀም ራሱንና ቤተሰቡን ባለው የመከላከል ተፈጥሮአዊና ሕጋዊ መንገድ በመጠቀም በከፈተው የአጸፋ ተኩስ፣ መላው የጎንደር ከተማ ሕዝብ ሁኔታውን እንዲያውቅ የግንኙነት መስመር ከፈተ።

የትግሬ ወንበዴዎች ከጎንደር ሕዝብ መሐል ጥያቄ ከማቅረብ ውጭ ምንም ዓይነት ወንጀል የሌለባቸውን ልጆቹን በሌሊት አፍኖ ለመውሰድ የተደረገው ጥረት እጅግ በማስቆጣቱ ሕዝቡ ቀፎው እንደተነካበት ንብ በመትመም በአፋኝ ቡድኑ አባላትና በወያኔ ተባባሪዎች ላይ የቁጣ መግለጫ የሆነ ርምጃ ወሰደ። የከተማዋን እምብርት የንግድ ቦታዎች ዐማራዎችን አፈናቅለው ተቆጣጥረው የነበሩትን የትግሬ ንግድ ቤቶች፣ ሱቆች፣ አውቶቡሶች፣ መኖሪያ ቤቶች፣ ባንኮችና ወርቅ ቤቶች አጋዩ። «ምንጊዜም በመስተዋት ቤት የሚኖር ሰው ቀድሞ ደንጋይ አይወረውርም» የሚባለውን ዘመን የማይሽረው ወርቃማ አባባል ከምንም ያልቆጠሩት የወያኔ ጀሌዎች፣ በተናጠል ጎንደሬውን፣ በጥቅል ዐማራውን ከመናቅና ከማዋረድ ዘለው፣ አንጡራ ሀብቱን ዘርፈውና ቀምተው፣ ካለርሱነቱ በቀር «ይህ ሀብት አለኝ» የሚለው የሌለው ሕዝብ መሀል፣ ልጆቹን በሌሊት ሰርቀው ለመውሰድ ባደረጉት ሙከራ፣ በአልሞት ባይ ተጋዳይነት የተወረወሩ ደንጋዮች የመስታውቱን ቤቶች አውድመዋል። የጎንደር ሕዝብ በአመጹ የሚያጣው ምንም ነገር ካለመኖሩም በላይ፣ በአመጹ አትራፊ ይሆናል። የታሠረበትን ሰንሰለት ያወልቃል። ነፃነቱን መልሶ ይላበሳል። ያም ሆኖ፣ የኮሎኔል ደመቀ ቤተ በከባድ መሣሪያ እንዲፈራርስ መደረጉ ታውቋል፡፡

ዐማራውን መጨፍጨፍ የለመደው የትግሬ-ወያኔ ዘረኛ ሥርዓት፣ በንጹሐኑ የጎንደር ሕዝብ ላይ በከፈተው ተኩስ በርካታ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ከሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ለተከታታይ ሦስት ቀኖች በትግሬ አፋኝ ቡድኖችና በጎንደር ከተማ ሕዝብ መካከል በተደረገው የማጥቃትና የመከላከል ሕጋዊና ሰብአዊ ግብግብ ላለቁት የዐማራ ልጆች፣ ከሁሉም በላይ ለሕዝቡ ነፃነትና መብት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ይጩሁ የነበሩት እንደ አቶ ሲሣይ ታከለ የመሳሰሉት ጀግኖችን ማጣት፣ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የተሰማው ሐዘን መሪርና ጥልቅ ነው። ይሁን እንጂ፣ ድል ካለመስዋዕትነት የሚታሰብ ባለመሆኑ፣ መስዋዕትነቱ የነፃነታችን ተገቢ ዋጋ እንዲሆን፣ የእነርሱን ፈለግ በመከተል ትግሉን ከዳር ለማድረስ ቃል እንገባለን። መስዋዕትነት፣ የጥቂቶች፣ ድል ደግሞ የብዙኃኑ ነውና፣ የድሉ ተጠቃሚ የሚሆነው ሠፊው የዐማራ ነገድ የጀግኖቻችን አርኣያነት በመከተል፣ ዘረኛው ወያኔን ከሕዝቡ አናት ላይ አምዘግዝገን ለመጠል በጎንደር ሕዝብ፣ ከሁሉም በልይ በወልቃይት ጠገዴ ማንነት ጥያቄ አቅራቢ ሕዝብ የተቀጣጠለውን የለውጥ እሳት ግለቱ እንዳይበርድ፣ ስሜቱ እንዳይቀዘቅዝ፣ የድሉ ጊዜ እንዳይራዘም በያለንበት የጎበዝ አለቃችን በመምረጥ የወያኔን ጉርንቦ አንቆ ለመፈጥረቅ ክንዳችን ልናነሳ ግድ ይለናል።

ይህም በመሆኑ፣ በሰሜን ጎንደር ባሉ የአውራጃና የወረዳ ከተሞች የሕዝባዊ አመፁ በመቀጣጠል ላይ ነው። በዚህም መሠረት፣ ሐምሌ 7 ቀን 2008 ዓም ከጎንደር ከተማ 100 ኪሎሜትር ላይ የምተገኘው የሰሜን አውራጃ ዋና ከተማ በሆነችው በደባርቅ ከተማ የወያኔ ሰላዮችና አሽቃባጮች በሆኑ ግለሰቦች ንብረት ላይ ሕዝቡ እርምጃ መውሰዱ ታውቋል። የዐማራው ሕዝብ መብቱንና ማንነቱን ለማስከበር ባደረገው ትግል ወያኔና ወያኔን በሚደግፉ ግለሰቦች ንብረት ላይ ያነጣጠረ ርምጃ መውሰዱ የሚያሳየው ዕውነታ፣ እነዚህ ሰዎች ባልደከሙበት፣ በዘረፉት የሕዝብና የመንግስት ሀብት የናጠጡ መሆናቸው ነው። እርሱ ቁንጣን ሲያስቸግራቸው ሠፊው የዐማራው ሕዝብ በገዛ አጽመ-ርስቱ የበይ ተመልካች ከመሆን አልፎ ማንነቱን በመገፈፉ ነው። ይህ ዓይነቱ ድርጊት እንዳይደገም ከፈለጉ መፍትሔው አንድ ብቻ ነው። ወያኔን እያጋለጡ ከሕዝቡ ጎን መቆም። ይህን በማያደርጉት ላይ ግን ሕዝባዊ አመፁ በስፋት መቀጠሉ አይቀሬ ነው። ንብረቱ ከርሱ ተወስዶ ለሌሎች የተሰጠ ነውና መብቱን በትግሉ ማስከበሩ የታሪክ ሐቅ ነውና ይቀጥላል። በዚህ ረገድ የጋይንት፣ የደብረታቦር፣ የሊቦ፣ የጭልጋ አውራጃ ሕዝብ የወልቃይት ጠገዴን ሕዝብ ትግል ሳይውል ሳያድር ሊቀላቀል ይገባል። በዚያው አንፃር የጎጃም፣ የሸዋ፣ የወሎና የመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ይህን ከፋፋይና አጥፊ ቡድን ለማስወገድ የጎንደርን ሕዝብ የእንቢተኝነት ትግል አካል እንዲሆን ጥሪያችን እናቀርባለን።

በወያኔ የሚመራው የፌደራል መንግሥት የወልቃይት ዐማራ ማንነት አስተባባሪ ኮሚቴዎችንና መላውን የዐማራ ሕዝብ ራሱ በተቆጣጠራቸው መገናኛ ብዙሃን «አሸባሪዎች ናቸው» ብሎ የመፈረጁ ግብ ሕዝቡን ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳ መሆኑን አመልካች ነው። «ከፌዴራል የጸረ-ሽብር ግብረ ኃይል ተላለፈ» ተብሎ በተነበበው መግለጫ፣ የኮሚቴ አባላቱን «ከኤርትራ ትእዛዝ በመቀበል ሽብር ሊያደርሱ ሲሉ እርምጃ ተወስዷል» ያለ ሲሆን፣ ለተቃውሞ የወጣውን ሕዝብ ደግሞ «የሽብርተኞች ተባባሪዎች» በማለት በግልጽ አገዛዙ በሚቆጣጠራቸው መገናኛ ብዙሃን አሳውቋል። ይህ በማጭበርበር፣ በክህደትና በውሸት ተወልዶ በውሸት የሚኖርን ዘረኛ የሞሶሎኒ ደቀመዝሙር ቡድን አጥፍቶን ሳይጠፋ፣ ፋታ ሳንሰጥ ሳያጠፋን ቀድመን ለማጥፋት የተባበረ ክንዳችን ልናነሳበት ይገባል። ይህ ዕድል እንዳለፉት ሁሉ እንዳያመልጠን በአግባቡ ልንጠቀምበት እንደሚገባ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ያሳስባል።

በጎንደር ከተማ በተካሔደው የዐማራ ሕዝብ ተጋድሎ ከአንድ መቶ ሺህ በላይ ሕዝብ ሥርዓቱን ተቃውሞ የወጣ መሆኑ ታውቋል። ይኸን ሕዝብ አሸባሪ ብሎ ወያኔ የመፈረጁ ሚስጢር፣ የዐማራውን ሕዝብ በጅምላ ለመጨረስ፣ ብሎም የወልቃይት ጠገዴን የዐማራ ማንነት ጥያቄ ለማዳፈን ካላው ጽኑ ፍላጎት የመነጨ መሆኑን ላፍታ ልንጠራጠር አይገባም። አገዛዙ በዚሁ በ2008 ዓ.ም. በኢትዮ-ሱዳን ድንበር በቋራና መተማ አካባቢ የአገራቸውን ድንበር የሚያስጠብቁ ዐማሮችን በፓርላማ (ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት) ‹‹ሽፍቶች ናቸው›› ማለቱ የታወቀ ነገር ነው። ቀደም ባሉት ዘመናትም ቢሆን በ1985/86 ዓ.ም. የዘመን መለወጫ ዋዜማ በጎንደር በአደባባይ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን በመቶዎች የሚቆጠሩ ዐማሮችን ሲገድል እና ሲያቆስል በተመሳሳይ መልኩ ‹‹ሽፍቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ›› ብሎ እንደነበር የምናስታውሰው በቁጭት ነው።

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በተደጋጋሚ ይፋ እንዳደረገው፣ የትግሬ-ወያኔ ሥርዓት የዐማራውን ሕዝብ በተለያየ መልኩ ለመጨረስ የተለያዩ የጅምላ ወንጀሎችን እየለጠፈ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን መግደሉን፤ ማፈናቀሉን፣ ማሰደዱንና ማሰሩን እናውቃለን። ዛሬም በጎንደር ዐማሮች ላይ እየወሰደ ላየው የጥፋት እርምጃ የዚሁ ተከታይ መሆኑን ላፍታ ሳንጠራጠር፣ የአጥፊውን አካል የስለላ፣ የመገናኛ፣ የኢኮኖሚ፣ የኃይል ማመንጫ፣ የወታደራዊና መሰል ተቋሞች ላይ የማያዳግም ርምጃ መወሰድ አለበት። «ጅብ ከሚበላን፣ ጅብ በልቶ መቀደስ» የሚለው የአባቶቻችን አባባል ትክክለኛ ቦታው ይህ ነው እንላለን!

የጎንደር ዐማሮች ከአገዛዙ ጋር የሚያደርጉት ተጋድሎ፣ በየትኛውም መልኩ ከውጭ ኃይሎች ጋር ግንኙነትም ሆነ ንኪኪ የለውም። ሻዕቢያ ከዐማራው ይልቅ ለወያኔ አሳዳጊ አባቱ ከመሆን አልፎ፣ መሪዎቻቸው በሥጋ ልደት የተቆራኙ መሆናቸው ይታወቃል። በዚህም ምክንያት የዐማራ ሕዝብ ንቅናቄ በራሱ ልጆች፣ ወያኔ በፈጠረው ብሶት የተቀጣጠለ እንጂ፣ እንደወያኔ በውጭ ውሻል የሚዘወር አለመሆኑ ወዳጅም ጠላትም እንዲያውቀው እንሻለን።

ከመላው የዐማራ ሕዝብ ጠንካራ ተቃውሞ የደረሰበት ወያኔ፣ አሁን «ነገሮችን በሽምግልና ለመፍታት» በሚል ማኅበረሰቡን ለማዘናጋት እየሞከረ እንዳለ እየተሰማ ነው። የሥርዓቱ አገልጋይ በሆኑ የሃይማኖት አባቶችና በብአዴን ካድሬዎች የሚደረገው ውይይትና ሽምግልና ፍጹም ተቀባይነት የሌለውና የወልቃይት ጠገዴን የዐማራ ማንነት ጥያቄ አዳፍኖ የሚያስቀር፣ ብሎም የታሠሩ ወገኖቻችንም ሕይዎት አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ መላው የዐማራ ሕዝብ ድርጊቱን በጽኑ በመቃወም፣ በተጀመረው ሕዝባዊ አመጽ ሙሉ መብትና ነፃነቱን እንዲያረጋግጥ ጥሪያችን እናቀርባለን፡፡

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብና የመገናኛ ብዙኃን ለእንቅስቃሴው አስፈላጊውን ትኩረትና በመስጠት ወያኔ በዐማራው ነገድ ላይ የሚያደርሰውን የዘር ጥፋት እንዲያወግዙና ከተጠቂው ወገን እንዲቆሙ ጥሪአችን እናቀርባለን። ለዚህ ዕውነተኛ ጥያቄ ተገቢ መልሱን እንዲያገኝ፣ ከጎኑ አለመቆም ፈጠነም ዘገየም የታሪክ ተወቃሽ ሊያደርግ እንደሚችል መናገር ነቢይ መሆንን አይጠይቅም።

በመጨረሻም በወያኔ ፖሊሶችና ደኅንነቶች በተሰው የዐማራ ታጋዮች ሞረሽ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለዘመዶቻቸው መጽናናትን በመመኘት፣ «ይዋል ይደር እንጂ፣ አህያ የጅብ ናት» እንደሚባለው፣ የወንድሞቻችን ደም ደመ-ከልብ ሆኖ የማይቀር መሆኑን ሞረሽ ወገኔ ያምናል።

ፈለገ-አሥራት የትውልዳችን ቃልኪዳን ነው!
ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!
ሞት ለወያኔና ለአጫፋሪዎቹ!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት – ቅዳሜ ሐምሌ ፱ቀን ፪ሺህ፰  ዓ.ም. – ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር ፲፮

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የሲኖዶሱ ውዝግብ አካሄድና መጪው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ February 6, 2023 02:03 am
  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule