• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር “እየቀለለ” ነው!

July 6, 2016 08:25 am by Editor 5 Comments

ጠቅላላ ወጪው 475 ሚሊዮን ዶላር እንደሆነ የተነገረለት የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር በብልሽት ምክንያት ግማሽ ያህል ባቡሮቹ እንደማይሰሩ ተነገረ፡፡ የባቡሩ ፕሮጀክት ከመጠናቀቁ በፊት ሥራው እንዲጀመር ህወሃት/ኢህአዴግ ግፊት አድርጎ ነበር፤ የቀላል ባቡር ፕሮጀክት የፖለቲካ ውሳኔ ነው፤ ቀላል ባቡሩ “እየቀለለ ነው” ተብሏል፡፡

ማክሰኞ ዕለት የተሰማው ሸገር ሬዲዮ ስማቸውና ድምጻቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ መረጃ አቀባዮቼ አደረሱኝ ባለው መሠረት ከተጀመረ ዓመት ያልሞላው የአዲስ አበባ የቀላል ባቡር ሥራ “እየቀለለ” መሆኑን ተናግሯል፡፡ ለአገልግሎት ከተመደቡት 41 ባቡሮች ውስጥ በሥራ ላይ የሚገኙት 28ቱ ብቻ መሆናቸውን መረጃ አቀባዮቹን ጠቅሶ ሬዲዮው አስረድቷል፡፡ ሃያ አንዱ ባቡሮች በብልሽት ምክንያት አብዛኛውን ጊዜያቸውን የሚሳልፉት በጥገና እንደሆነ፤ የመለዋወጫ ችግር ደግሞ ይበልጥ ሁኔታውን እንዳባባሰውና ለዚህም ተጠያቂው ኃላፊነቱን የፈረመው የቻይናው ኩባንያ ሲኤንአር መሆኑን አክሎ አስታውቋል፡፡train

በጉዳዩ ላይ የተምታታ ምላሽ የሰጡት የህወሃት/ኢህአዴግ ሹመኛ ደረጀ ተፈራ 21ዱ ባቡሮች አገልግሎት እንደማይሰጡ አልካዱም፡፡ ግን የቆሙት ባቡሮች ምክንያታቸው ብልሽት ብቻ ሳይሆን ለመጠባበቂ ነው በማለት ከተናገሩ በኋላ ብልሽት ያለባቸውን ደግሞ ህወሃት/ኢህአዴግ ለሰው ህይወት በጣም የሚያስብና የሚጠነቀቅ በመሆኑ ለአገልግሎት እንዳይወጡ ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡

ሹመኛው አክለውም ባቡሮቹ የማይሠሩት የተጠቃሚ ቁጥር በሚያንስበት ጊዜ እንዲሁም የኤሌክትሪክ አቅርቦት በማይኖርበት ወቅት መሆኑን አልሸሸጉም፡፡ “ለመጠባበቂያ ነው የቆሙት” በማለት አስቀድመው የሰጡትን ሃሳብ በመቃወምም የባቡሩ ተጠቃሚ ብዙ እንደሆነና አቅርቦቱና ፍላጎቱ ባለመመጣጠኑ ባቡሮቹ ከመጠን በላይ በመሥራታቸው ለጥገና መጋለጣቸውን ተናግረዋል፡፡ የተሳፋሪውን መጠንም ሲገልጹ “የሚጠቀመው ሰው በጣም ብዙ ነው” ያሉት ሹም “ባቡሩ ቶሎ ወደ አገልግሎት እንዲገባ ግፊት እንደነበር” በመናገር የግፊቱ እና የችኮላው መንስዔ የህዝቡ ፍላጎት እና “የእኛ ግፊት” ነበር በማለት ዋንኛው ተጽዕኖ “ሌጋሲ፤ ውርስ፤ ህዳሴ፤ የሙት መንፈስ፤ …” መሆኑን ከመጥቀስ በመቆጠብ በደምሳሳው አልፈውታል፡፡

ሬዲዮው ባገኘው መረጃ መሠረት የባቡሩ ውል ከቻናው ሲኤንአር ኩባንያ ጋር ሲፈረም የህወሃት ሹሞች ኩባንያው መለዋወጫም እንዲያቀርብ በስምምነቱ ላይ ኩባንያውን አለማስፈረማቸው እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ ምናልባት እንደ ውጫሌ ውል የቻይንኛውና የአማርኛው (ወይም የህወሃት ሰዎች እንዲገባቸው የተጻፈበት ቋንቋ) ቅጂ ካልተለያየ በስተቀር እንዲህ ዓይነቱ እጅግ በርካታ ገንዘብ የፈሰሰበት ፕሮጀክት ላይ የመለዋወጫ ዕቃ ውል መፈጸም ለጥያቄ የሚቀርብ አይደለም በማለት አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የባቡር ኮርፖሬሽኑ ለጥገና ብሎ ያስቀመጠው ወይም የበጀተው አለመኖሩ የቀላል ባቡሩን ቅለት የሚሳይ ብቻ ሳይሆን በግልጽ የፖለቲካ ውሳኔ የተፈጸመ ፕሮጀክት ለመሆኑ አብሮ ይነገራል፡፡l rail

ገና ከጅማሬው ታላቅ ገቢ ያስገኛል፤ የከተማዋን የትራንስፖርት ችግር ያስወግዳል፤ በአንድ ጉዞ ከ300 በላይ ተጓዦችን ያሳፍራል፤ በሰዓት 80ኪሜ መብረር ይችላል፤ ከምስራቅ አፍሪካ ብቸኛው ነው፤ በአፍሪካ ከሚጠቀሱት ሰባት የከተማ ባቡሮች የዘመነው ነው፤ … ተብሎ ከበሮ የተደለቀለትና ፈንዲሻ የተነሰነሰለት ቀላል ባቡር አንድ ዓመት ሳይሞላው እንዲህ እንደ ስሙ መቅለሉ የህወሃት/ኢህአዴግ ማንነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው በማለት አንድ የጎልጉል አስተያየት ሰጪ በላኩልን መልዕክት ላይ አስታውቀዋል፡፡

በአንድ ጀምበር ታላላቅ ፕሮጀክቶችን በመጀመር የታላቅነትን ነጋሪት እየመታ የሕዝብን ቀልብ ለመሳብ የሚፈልገው ህወሃት/ኢህአዴግ የከተማ ዜጎችን ቁም ስቅል እያሳየ ለከተማ ነዋሪዎች አስባለሁ ማለቱ አብሮ የማይሄድ እንደሆነ የሚናገሩ ወገኖች፤ በርግጥ ህወሃት/ኢህአዴግ ለከተማው ህዝብ የሚያስብ ከሆነ በክረምት እመጫቶችን ሳይቀር ከጨቅላ ህጻናቶቻቸው ጋር ከደሳሳ ጎጇቸው ማፈናቀሉን ያቁም፤ በሞትና በህይወት ላይ ባለ በሽተኛ ማላገጡን ትቶ ለህክምና ነጻነት ይስጠው፤ … እነዚህን ቀላል ነገሮችን ያድርግልን በማለት አንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ከተዘረጋላቸው የሃዲድ መስመሮች እያፈተለኩ እንደሚወጡ የሚነገርላቸው ባቡሮች እንቅፋት እንዳመታቸው ሃዲዶቹ እንደሚጠረጉና በባቡር ቫዝሊንም (ግራሶ) እንደሚለሰልሱ ሬዲዮው ጨምሮ ተናግሯል፡፡


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. gud says

    July 6, 2016 04:08 pm at 4:08 pm

    Golgul eyekelele new

    Anti Ethiopian news site .

    Reply
  2. gud says

    July 6, 2016 04:09 pm at 4:09 pm

    You fools . You criticize everything ,then the public see u as clowns .

    Reply
  3. አሳፋሪዎች says

    July 6, 2016 05:54 pm at 5:54 pm

    ምነው ኢሃድግም እንደ ባቡሮቹ ቢወላልቅልን ምን ነበረበት።

    Reply
  4. tesfai habte says

    July 13, 2016 03:25 pm at 3:25 pm

    ለኢትዮጵያ ህዝቢ ለማታለል እጂ ለስራ እውነተኛ ወይም ለሃገር ግንባታ ተብሎ የተሰራ ኣለመሆኑ የተረጋገጠ ነው።

    Reply
  5. ሸመልስይማም says

    July 14, 2016 12:58 pm at 12:58 pm

    መነዉ አንደ ሊቢያው መአመር ጋዳፊ ህወሀት ኢህአዴግ ቢፈራርስ ፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ደስታ ነበር ፡፡

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
Copyright © 2026 · Goolgule