በነጻ አውጪ ስም አገር እየገዛ ያለውን የትግራይ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃትን) ለመውጋት ብረት ያነሳው ሌላ የትግራይ ነጻ አውጪ ሃይል /ትህዴን ወይም በትግሪኛ ዴምህት/ መሪ የነበረው “ተጋዳላይ” ሞላ አስገዶም ህወሃትን ከተቀላቀለ ጥቂት ቀናት በኋላ ጦርነት መጀመሩ ተሰማ። የህወሃት ወኪል ሃይለማርያም ደሳለኝ ውጊያው የሚጀመረው የህዝብ ፈቃድ ተጠይቆ እንደሚሆን ተናግረው ነበር። የጎልጉል መረጃ አቀባዮች ከአዲስ አበባ እንደገለጹት ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ቁስለኞች እየገቡ መሆኑንን እማኞች ነግረዋቸዋል። ጦርነቱ በየትኛው መንደርና ወረዳ እንደተጀመረ ለይተው ያላስረዱት የዜናው ባለቤቶች፣ ውጊያ እየተካሄደ ያለው ኤርትራ ምድር ላይ እንደሆነ ግን አልሸሸጉም። አንድ የሆስፒታል ሰራተኛ ዘመድ ደውሎላቸው “ቁሰለኞች አሉ ሥራ በዝቶብኛል” ማለታቸውን የጎልጉል መረጃ ሰጪዎች ከአዲሰ አበባ … [Read more...] about ህወሃት ጦርነት ጀመረ፣ ቁስለኞች ታይተዋል
Archives for September 2015
ሌቦ ነይ …
ማስታወሻ፤ ከጥቂት ሳምንታት በፊት አንድ የህወሃት አባል ወይም ተላላኪ እንደሆነ የታሰበ ግለሰብ 5 ሚሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ የሚገመት (በፎቶው እንደሚታየው) ጥሬ ገንዘብና ወርቅ በሻንጣው ይዞ ከኢትዮጵያ ወደ ለንደን እንግሊዝ ሲገባ ጋትዊክ አየር ማረፊያ ላይ በፖሊሶች ተይዟል። ግለሰቡ ለመጀመሪያ የፍርድ ምርመራ ፍርድ ቤት በቀረበ ጊዜ ዳኛው “ይህን ያክል ገንዘብ እንዴት በሻንጣ ልትይዝ ቻልክ?” የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡ፣ ግለሰቡ “ገንዘቡ የመንግስት መሆኑንና ለመንግስት ስራ ለማዋል መያዙን” ገልጾዋል። ይሁን እንጂ ዳኛው “ይህን ያህል ገንዘብ በሻንጣህ የያዝከው በአገራችሁ ባንክ ስለሌለ ነው እንዴ?” በማለት ጥያቄ አቅርበዋል። ግለሰቡ ለጊዜው በዋስ የተፈታ ሲሆን፣ መስከረም ላይ በድጋሚ እንደሚቀርብ ተነግሯል። የወለላዬ ግጥም በዚህ ዘረፋ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ (ቅርብ የሆናችሁ … [Read more...] about ሌቦ ነይ …
ችግሩ ወያኔን በማስወገድ ብቻ የሚፈታ አይደለም!!
መግቢያ በየጊዜው ለመጻፍ ብዕሬን በመቃጣት ላይ እያለሁ እመለሳለሁ። ይህንን የማደርግበት ምክንያት በእንግሊዘኛም ሆነ በአማርኛ በየድህረ-ገጾች ላይ ተጽፈው ለንባብ የሚቀርቡ ጽሁፎች ስለማያረኩኝ ነው። ይህንን የምልበት ምክንያት እኔ ብቻ በትክክል የምጽፍ ሆኖ ስለሚሰማኝ ሳይሆን የጽሁፎቹን ዓላማ ለማወቅም ሆነ ለመረዳት ስለሚያስቸግረኝ ነው። ሁለተኛ፣ አብዛኛዎች ጽሁፎች በተወሰነ ሃሳብ ላይ ያተኮሩና በዚያው ላይ የሚሽከረከሩ አይደሉም። በሌላ አነጋገር እንድንወያይበትና እንድንከራከርበት በር የሚከፍቱ አይደሉም። ሁሉም እንደፈለገውና እንደመሰለው የሚጽፍ እንጂ ከተጨባጭ ሁኔታዎችና ከህሊና ሁኔታ በመነሳት ችግራችንን የሚተነትን አይደለም። በሶስተኛ ደረጃ፣ በአንዳንድ ድህረ-ገጾች ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በአንድ ግለሰብ ሃሳብና ርዕይ ላይ ያተኮሩ ሳይሆኑ፣ የግለሰብን ስም የሚያጎድፉ ወይም ሞራሉ … [Read more...] about ችግሩ ወያኔን በማስወገድ ብቻ የሚፈታ አይደለም!!
ክላሽንኮቭ ያነገበ የህወሃት ታጣቂ የወጣቷን ህይወት አጠፋ
አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል ለቡ አካባቢ በሚገኝ መዝናኛ ቤት ውስጥ ሰኞ ምሽት አንዲት ወጣት መግደሉ ተሰማ፡፡ ግለሰቡ ራሱን ለማጥፋት ቢሞክርም ተርፎ በሕክምና ላይ ይገኛል፡፡ ሰሎሜ ጉልላት የተባለችው የ20 ዓመት ወጣት ከጓደኛዋ ጋር በመሆን በለቡ ኮንዶሚኒየም ቤቶች አካባቢ በሚገኝ የጓደኛቸው መዝናኛ ውስጥ በመዝናናት ላይ እያሉ ነው ከተጠርጣሪው ገዳይ ጋር የተገናኙት፡፡ ለጊዜው ስሟን መናገር ካልፈለገችው ጓደኛዋ መረዳት እንደተቻለው፣ የፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሰው ግለሰብ ከዚህ ቀደም ሰሎሜን አስቸግሮ ከሚያውቅ ግለሰብ ጋር በሚዝናኑበት ባር ውስጥ እንደነበር ትናገራለች፡፡ ሁለቱ ሴት ጓደኛሞች መዝናኛ ባሩ ውስጥ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ከመውጣታቸው በፊት፣ ወደ መፀዳጃ ቤት ለመግባት ተስማምተው መሄዳቸውን ታስታውሳለች፡፡ ክፍሉ ራሱን የቻለ መዝጊያ ኖሮት መፀዳጃ ክፍሎቹም … [Read more...] about ክላሽንኮቭ ያነገበ የህወሃት ታጣቂ የወጣቷን ህይወት አጠፋ
ጥቂት ስለ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ
ተግባቢና በሳል ነው፤ ረጋ ባለ አንደበቱ የሚሰማውን በጥሞና መናገር ልዩ ያደርገዋል ፡፡ እምነቱን አጥበቆ ይወዳል፤ የእስልምና ሃይማኖት የሚያዛቸውን ተግባራት (ሶላት መስገድ፣ መጾም…) ፈጽሞ ሌሎች መሰሎቹ እንዲፈጽሙ ማድረግን ያውቅበታል፡፡ ከሌሎች የእምነት ተከታዮች ጋር የመግባባቱና ከሁሉም ጋር በአብሮነት መኖሩ ባጠቃላይ ማህበራዊ ኑሮ የሚጠይቀውን ግዴታ የመወጣት ልዩ ችሎታ አለው፡፡ ከማንም ሰው ጋር የመግባባት፣ ተጫውቶ የማጫወት ክህሎት አለው፡፡ ከቀለሙ በተጓዳኝ ሀይማኖታዊ እውቀቱም የተመሰከረለት ነው፡፡ ሙስሊም ተማሪዎችን በመሰብሰብ በስነ ምግባር እንዲታነጹና ለሀገራቸው ተቆርቋሪ እንዲሆኑ ያስተምራል፡፡ በግቢው ውሰጥ ተሰሚነት ካላቸው የሀይማኖት ሰዎች አንዱ ነበር፡፡ ካሚል ሽምሱን መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ሳለ አውቀው ነበር፤ አንድ ባችም ነበርን፤ በህግ ፋከልቲ ተደልድለን ለአምስት … [Read more...] about ጥቂት ስለ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ
“ኢትዮጵያ ቅደሚ!”
የቀድሞው የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር “ኢትዮጵያ ቅደሚ!” በይፋ (officially) ለህዝብ የተበሰረውና በ“አብዮት አደባባይ” የተዘመረው ልክ የዛሬ 40 አመት ቅዳሜ መስከረም 2 ቀን 1968 ዓ.ም ነበር! በርካታ የቀድሞ ተማሪዎቼና ወዳጆቼ በተገናኘን ቁጥር “የምንወደው መዝሙር ግጥም እየተዘነጋን ነውና እባክህ ባመቸህ መንገድ እንደገና አውጣው” እያሉ ሲጠይቁኝና እኔም ቃል ስገባ ብዙ ጊዜ ሆነን። 40ኛ አመቱን ምክንያት በማድረግ ለታሪክ ማስታወሻ እንዲሆን እነሆ ግጥሙን በትህትና እያቀረብሁ፤ መዝሙሩ ብዙ ውጣ ውረድ ታሪክ ስላለው ወደፊት በሰፊው ይገለፃል። ፨ ፨ ፨ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ቅደሚ በኅብረሰባዊነት አብቢ ለምልሚ! ቃል ኪዳን ገብተዋል ጀግኖች ልጆችሽ ወንዞች ተራሮችሽ ድንግል መሬትሽ ለኢትዮጵያ … [Read more...] about “ኢትዮጵያ ቅደሚ!”
አዲስ ዓመት ያለ ተስፋ!?
የተወደዳችሁ የአገራችን የሃይማኖት መሪዎች እንዲሁም የየእምነቱ ምዕመናን፡- ይህንን መልዕክት የምጽፍላችሁ ወንድማችሁ ይህንን ጥሪ የማቀርብላችሁ እንደ አንድ ሰብዓዊ ፍጡር ለእናንተ ሃሳቤን ለማቅረብና እንደ እምነቴ ደግሞ በጌታችን የሱስ ክርስቶስ ባለኝ እምነትም ጭምር ነው። ይህንን ስል ሌሎች እንደ እኔ ዓይነት እምነት የሌላችሁን የሃይማኖት መሪዎችና ተከታዮች ያገለልኩ መስሎ እንዲሰማችሁ ወይም ከእኔ ጋር ተመሳሳይ እምነት በሌላችሁ ላይ ጫና ለማድረስ በጭራሽ ምኞቴ እንዳልሆነ አስቀድማችሁ እንድታውቁልኝ እፈልጋለሁ። የራሴን መግለጼ እንደ አንድ ሰብዓዊ ፍጡር እና እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ማንነቴን አሳውቄ ሃሳቤንም በዚያው መልኩ እንድትረዱልኝ ከማድረግ አኳያ ነው። ኢትዮጵያ በምንላት አገራችን ሁላችንም የተለያየ ሃይማኖት እንከተላለን፤ እንደየ እምነታችንም የአምልኮ ሥርዓታችንን … [Read more...] about አዲስ ዓመት ያለ ተስፋ!?
ባለቤት ያጣ ሕገ መንግሥት?
የፌዴራል ሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን የቀድሞው የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ መላኩ ፈንታና በሌሎች ግለሰቦች ላይ የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 60/89፣ 368/95፣ 622/2001 እና የወንጀል ሕግን በመጥቀስ፣ በሥልጣን አለአግባብ በመገልገልና በጥቅም በመተሳሰር የቀረጥ ነፃ መብትን ያላግባብ በመገልገል፡ እንዲመረመር አለማድረግ ወይም እንዳይመረመር ማድረግ፣ ገደብና ቁጥጥር የሚደረግባቸውን ዕቃዎች (መድኃኒቶች) በማስገባት ወንጀል ክስ አቅርቦባቸው፣ ጉዳያቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት እየታየ እያለ አዲሱ የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 ወጥቷል፡፡ አዲሱ አዋጅ ነባር የጉምሩክ አዋጆችን ሙሉ በሙሉ ሽሯል፡፡ ስለዚህም ከላይ የተጠቀሱት ድርጊቶች በአዲሱ ሕግ ወንጀልነታቸው ቀርቷል፡፡ የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 22 ንዑስ … [Read more...] about ባለቤት ያጣ ሕገ መንግሥት?
መልካም አዲስ ዓመት!
የታሪክ አምድ ነባራዊ፣ ምድረ-ህይወት ፍልስፍና፣ መውጣት መውረድ፣ የዓለም ህግ፣ የተፈጥሮ ገጽ ሆነና፣ ጊዜ ክፉ፣ ጊዜ ደጉ..፣ እጥፍ-ዘርጋ፣ ዘመም-ቀና..፣ አንዴ ጽልመት..፣ አንዴ ብርሃን..፣ ባለታሪክ፣ ባለዝና፤ ስትወድቂ..፣ ስትነሺ..፣ በዘመናት ጉዞሽ ሂደት፣ ለዚህ ደረስሽ፤ እልልልል! ሁለት ሺ ሰባት ዓመት! (ሙሉውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about መልካም አዲስ ዓመት!
የግጭት ምንቸት ውጣ የእርቅና የሰላም ምንቸት ግባ!!
ከልብ በመነጨ፣ ፍጹም በሆነ የወገን ፍቅር በሶማሊያ በውትድርና ላሉ ወገኖች ፈጣሪ መፍትሄ እንዲሰጣቸው እንመኛለን። በማያውቁት ጉዳይ የበረሃ ጥሩር ለሚገርፋቸውና የነፍሳቸው ዋጋ በውል ለማይታወቀው ወገኖቻቸን እንኳን አደረሳችሁ ከማለት በላይ ሁሉም ወገኖች ድምጽ እንዲሆኗቸው እንጠይቃለን። በወር 30 ዶላር አበል ህይወታቸው ላለፈና አሁንም እያለፈ ለሚገኙት ሃዘናችን ትልቅ ነው። ትርጉም በሌለው ጦርነትና ለወደፊት ንጹሃን ዋጋ የሚከፈሉበት የፖለቲካዊ ቁማር ስትራቴጂ የደም ግብር ለመክፈል ሰልፍ ለያዛችሁ ፈጣሪ አሁንም ይድረስላችሁ!! ለራባችሁም ለጠገባችሁም፡- እንደ ልማዳችን እንኳን አደረሰን፣ አደረሳችሁ፣ እንቁጣጣሽ!! ስንል ለማለት ብቻ ባንለው ምንኛ ደስ ባለን ነበር። አዲሱን ዓመት ተቀብለን እልፍ ሳንል ባለንበት ቆመን ያረጅብናል። እኛም ያለ አንዳች ለውጥ ጎመን/አረም አሮብን … [Read more...] about የግጭት ምንቸት ውጣ የእርቅና የሰላም ምንቸት ግባ!!