• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ክላሽንኮቭ ያነገበ የህወሃት ታጣቂ የወጣቷን ህይወት አጠፋ

September 16, 2015 07:38 am by Editor Leave a Comment

አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል ለቡ አካባቢ በሚገኝ መዝናኛ ቤት ውስጥ ሰኞ ምሽት አንዲት ወጣት መግደሉ ተሰማ፡፡ ግለሰቡ ራሱን ለማጥፋት ቢሞክርም ተርፎ በሕክምና ላይ ይገኛል፡፡

ሰሎሜ ጉልላት የተባለችው የ20 ዓመት ወጣት ከጓደኛዋ ጋር በመሆን በለቡ ኮንዶሚኒየም ቤቶች አካባቢ በሚገኝ የጓደኛቸው መዝናኛ ውስጥ በመዝናናት ላይ እያሉ ነው ከተጠርጣሪው ገዳይ ጋር የተገናኙት፡፡

ለጊዜው ስሟን መናገር ካልፈለገችው ጓደኛዋ መረዳት እንደተቻለው፣ የፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሰው ግለሰብ ከዚህ ቀደም ሰሎሜን አስቸግሮ ከሚያውቅ ግለሰብ ጋር በሚዝናኑበት ባር ውስጥ እንደነበር ትናገራለች፡፡ ሁለቱ ሴት ጓደኛሞች መዝናኛ ባሩ ውስጥ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ከመውጣታቸው በፊት፣ ወደ መፀዳጃ ቤት ለመግባት ተስማምተው መሄዳቸውን ታስታውሳለች፡፡ ክፍሉ ራሱን የቻለ መዝጊያ ኖሮት መፀዳጃ ክፍሎቹም ራሳቸውን የቻሉ መሆናቸውን የገለጸችው የዓይን እማኟ፣ አንዱን ክፍል በሚከፍቱበት ወቅት ዩኒፎርም የለበሰው ፖሊስ ውስጥ ሆኖ ስላዩት ይቅርታ መጠየቃቸውን ትገልጻለች፡፡

selome1ይቅርታቸውን ተቀብሎ እንደወጣ እነሱ ወደ መፀዳጃ ክፍሎቹ ገብተው ከደቂቃ በኋላ ሲወጡ የዋና ክፍሉን በር ቆልፎ ፖሊሱ መፀዳጃ ክፍል ውስጥ እንደጠበቃቸው አስረድታለች፡፡ ወደ ሰሎሜ ተጠግቶ “አንቺ ሰው የማታናግሪው ለምንድነው?” ብሎ በጥፊ እንደመታትና እንደወደቀች የገለጸችው የሟች ጓደኛ፣ እሷ በሁኔታው ተደናግጣ ወደ መፀዳጃ ክፍሉ ገብታ መቆለፏን ትናገራለች፡፡ በክፍሉ ውስጥ እንዳለች የተኩስ ድምፅ መሰማቱን፣ የማቃሰት ድምፅ ስትሰማ መውጣቷን ገልጻለች፡፡

ጓደኛዋ ሰሎሜም ሆነች ፖሊሱ ወድቀው እንዳየቻቸው ሰው እንዲደርስላት ብትጮህም፣ ለደቂቃዎች ያህል ማንም እንዳልደረሰ ትናገራለች፡፡

በኋላ ከደረሰችላት አንዲት እንስት ጋር በመሆን እስትንፋሷ የነበረውን ጓደኛዋን ለመርዳት እየሞከረች ሳለ፣ ፖሊሶች እንደደረሱና በሥፍራው ወደሚገኝ ጤና ጣቢያ በፒክ አፕ መኪና ይዘዋት መሄዳቸውን፣ ነገር ግን የጓደኛዋ ሕይወት ማለፉን ገልጻለች፡፡

ተጠርጣሪው የፖሊስ ባልደረባ ጭንቅላቱን በጥይት መትቶ ራሱን ለማጥፋት ቢሞክርም ሕይወቱ ባለማለፉ የሕክምና ዕርዳታ እየተደረገለት ነው፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ ከፖሊስ መረጃ ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡ ይሁን እንጂ ተጠርጣሪው ገና በሕክምና ላይ በመሆኑ ፖሊስ ቃሉን እንዳልተቀበለ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

የወጣት ሰሎሜ የቀብር ሥነ ሥርዓት ማክሰኞ መስከረም 4 ቀን 2008 ዓ.ም. በለቡ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡ (ምንጭ፡ ሪፖርተር፡፡ ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም በግፍ እየገዛ ያለው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የፌዴራል፣ የመንግሥት፣ ወዘተ የሚባል ነገር በኢትዮጵያ ውስጥ የለም፡፡ ፖለቲካው የህወሃት ገንዘቡ የኤፈርት ነው፡፡ ሁለቱ ደግሞ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው፡፡ ርዕሱንም ለዚህ እንዲገጥም አድርገነዋል)

*********************

ወጣት ሰሎሜ ጉልላትን በቅርብ የሚያውቃት አሌክስ አብርሃም ይህንን ይላል (ከራሱ ፌስቡክ ያገኘነው ነው)፡-

“ልጄ ... የበኩሬ … ልጄ ... ከሰፈር ልጅስ አስጣልኩሽ መሳሪያ ከታጠቀ ሰዉ በምን አቅሜ ላስጥልሽ“

የሟች እናት ለቅሶ ነበር … ይሄ ግን የአንዲት እናት ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጲያዊ ጥያቄ ነው ለእኔ … ይታያችሁ ይች ትላንት ህልፈቷን የነገርኳችሁ ወጣት ሶሎሜ ጉልላት … ስትገደል አብራት የነበረችው ጓደኛዋ እንደገለፀችው … የታመመ ሰው ለመጠቅ ጆሞ ቁጥር 1 ወደሚባለው ኮንዶሚኒየም ይሄዳሉ … የሄዱበትን ጉዳይ ጨርሰው ወደ አንድ ካፌ ይገቡና ሲወጡ ወደመፀዳጃ ቤት ይሄዳሉ … መፃዳጃ ቤቱ ውስጥ ክላሽንኮቭ የታጠቀ የፌዴራል ፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሰ ሰው ቁሟል አልፈውት ገብተው ሲመለሱ የመፀዳጃ ቤቱ የውጭ በር ተቀርሮ መታጠቢያ ክፍሉ ውስጥ ሰውየው ቁሟል …

selomeሟችን ጠርቶ “ሰላም በይኝ” ይላታል … ሰላም ለማለት ፈቃደኛ አልሆነችም … እናም ይህ ሰው በቦክስ ሟችን ይመታትና መሬት ላይ ይጥላታል … ቀጣዩ ጉዳይ ለማመን የሚቸግር ነበር … ጓደኛዋ ወደ አንዱ መፀዳጃ ክፍል ገብታ ከውስጥ ቀረቀረችው … ወዲያው ግን አካባቢው በተኩስ ድምፅ ተናወጠ … አራት ጥይቶች ተተኮሱ ሰውየው በሶስት ጥይት ሶሎሜን ነበር የደበደባት … በመጨረሻም ራሱ ላይ ተኮሰ … ሶሎሜ ህይወቷ ወዲያው ሲያልፍ ገዳይ ይሙት ይትረፍ አልተረጋገጠም!!

እንግዲህ መሳሪያ የታጠቁና የመንግስት እና ህዝብ አደራ የተሸከሙ ሰዎች የግል ስሜታቸውን መቆጣጠርና ሃላፊነትን ከግል ጉዳይ መለየት ካልቻሉ ምን እንላለን! ከዚህ በፊት ባህር ዳር ላይ በተመሳሳይ የወደድኳት ልጅ ተወችኝ በሚል ምክንያት በርካታ ሰዎችን ተኩሶ በመግደል ራሱን ስላጠፋው የፌዴራል ፖሊስ አባል ብዙ ተብሏል … ለመሆኑ ለእንደዚህ አይነት ለህዝብም ህዝብ እጠብቃለሁ ለሚለውም አካል አሳፋሪና አሰቃቂ የሆነ ድርጊት ተጠያቂው ማነው? በቃ የሆነው ሆነ ተብሎ ዝም ማለቱስ እስከመቼ?? (አሌክስ አብርሃም)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule