ከብሄር ፖለቲካ እንውጣ! የተባበረችውን ኢትዮጵያን እንገንባ! በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚንስትር ኣቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሲናገሩ ኣገራችንን የሚበትኑ ኣጥፊ ዘሮች ያሏቸውን ሶስት ጉዳዮች ኣነሱ። ኣንደኛው ጠባብነት፣ ሁለተኛው ትምክህተኛነት፣ ሶስተኛው በሃይማኖት ሽፋን የሚራመድ ኣክራሪነት ናቸው ኣሉ። በመሰረቱ እነዚህን ጉዳዮች ኣቶ ሃይለማርያም ለመጀመሪያ ጊዜ ያነሷቸው ጉዳዮች ኣይደሉም። በ”ኢህዓዴግ” ውስጥ ብዙ ጊዜ የሚነሱ ሁሌም ሲባሉ የነበሩ ናቸው። ኣቶ ሃይለማርያም ኣዲስ ነገር ኣልተናገሩም። ለማናቸውም ግን እነዚህ ኣደገኛ ዘሮች ከየት መጡ? ኣገሪቱንስ ወዴት እየወሰዱ ነው? በርግጥ ከብሄር ፖለቲካው ኣዝማሪዎች ኣልፎ ወደ ታች ወርዶ የኔብጤው ተራው ህዝብ ኣካባቢ እነዚህ ዘሮች ጎልተው እየታዩ ነው ወይ? የሚለው ጉዳይና ኢትዮጵያ በምግብ … [Read more...] about Je Suis ኢትዮጵያዊ!
Archives for September 2015
ስለ “ጽናት” የቀረበ ተጨማሪ መረጃ
ማሳሰቢያ፡- ከዚህ በፊት ኢንጂነር መሃመድ አባስ በጽናት ዙሪያ ባቀረቡት ዘገባ ከብዙ አንባቢዎቻችን ብዙ ተብለናል፡፡ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ እንደመሆኑ ሕዝብ መረጃ ከማቅረብ ጀምሮ መጦመርና ዜና መሥራት ይችላል፡፡ በዘመናዊው ጋዜጠኝነት የተለመደ አሠራር ነው፡፡ በመሆኑም ባለፈው ከቀረበው መረጃ አኳያ አሁን ደግሞ ደጋፊ የሚሆን የድምጽ መረጃ ከአጭር መግቢያ ጽሁፍ ጋር ልከውልናል፤ እንዲህ ይነበባል፡- “እራሱን ጽናት እያለ በሚጠራው ጀሌ ላይ ላቀረብኩት ጽሁፍና ማስተባበያ ለቀረበበት “ዘረፋ” ግልጽ የሆነ ማስረጃ!” ድምጻችን ይሰማን ለሁለት በመስንጠቅ የህዝበ ሙስሊሙን አንድነት ለመናድ ሀወሃት/ኢህአዴግ እንቅልፍ አጥቶ ማደር የጀመረው ዛሬ እንዳልሆነ ይታወቃል። ህወሃት/ኢህአዴግ የሃይማኖት ነጻነት ትግሉ በተጀመረ ማግስት መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን ዘብጥያ በማውረድ … [Read more...] about ስለ “ጽናት” የቀረበ ተጨማሪ መረጃ
Guddaa saalpaa fariddi guniddaan dhessa
ማስታወሻ፡- ቀጥሎ የምታነቡትን ጽሑፍ በፍቃዱ ኃይሉ በአማርኛና በኦሮምኛ ቋንቋዎች ለአንባቢያን እንዲደርስለት ለነገረ ኢትዮጵያ የላከው ነው፡፡ Dhumnii jaarraa kudha saglaffaa dhuma yeeroo Awuroopaanoonnii ardii Afrikaa hirachuuf murtteeffatan ture. Mootootnii awuuroopaa kan ga’ee isaanii yoommuu fudhatan, ga’een Xaaliyaanii naannawa Itiyoophiyaa tuuree.Weerartoonnii Awuroopha sababni weerarreef ‘’ummata Afrikaa hirriba irra damaqsiinee qaroomsuufii’’ yoo jedhan illee dhugaan yeeroo sanaa garuu kanarraan adda.Sababnii weeraraa innii guddaan … [Read more...] about Guddaa saalpaa fariddi guniddaan dhessa
የመሐል ሀገር ሰው መልዕክት ለትግራይ ሰው!
ማስታወሻ፡- ቀጥሎ የምታነቡት ጽሑፍ በፍቃዱ ኃይሉ ከቂሊንጦ እስር ቤት ለነገረ ኢትዮጵያ የላከው ነው፡፡ ጽሑፉ በአማርኛና ትግርኛ እንዲነበብለት በጠየቀው መሰረት አማርኛው ቀጥሎ ቀርቧል፤ ትግርኛውን ከዚህ በታች ማግኘት ይቻላል፡፡ ትግራይ የኢትዮጵያ ገናና ታሪክ መሬቷ ላይ የተጻፈባት ክልል ናት፡፡ ብዙዎች ‹‹የኢትዮጵያ ራስ ናት›› የሚሉት ለዚህ ነው፡፡ የኢትዮጵያን ታሪክ ወደኋላ 3000 ዓመት የሚያደርሰው የአክሱም ስልጣኔ አሻራውን ትቶ የሄደው በትግራይ ክልል፣ አክሱም ከተማ ነው፡፡ ከአረቦች ተቀድቷል የሚባለውን የንግስተ ሳባ ታሪክ ‹‹ክብረ ነገስት›› በሚባለው መጽሐፍ ተርጉመው ለዚህ ትውልድ ያኖሩልን የትግራይ ሊቃውንት ናቸው፡፡ ሌላው ቀርቶ ህብረ-ብሄራዊ ቅርስ የሆነንን የሳባ ፊደል ለመላው ኢትዮጵያዊ ያወረሱት የትግራይ ሊቃውንት ናቸው፡፡ ከኢትዮጵያዊነት ቀለሞች አንዱ … [Read more...] about የመሐል ሀገር ሰው መልዕክት ለትግራይ ሰው!
ልጅ የአባቱን ልደት ሲያከብር
በአዲስ አበባ የሚገኙ ኤርትራ ተወላጆች ሻዕቢያ “ትጥቅ ትግል” የጀመረበትን 54ኛ ዓመት ማክበራቸውን የህወሃት ዜና አገልግሎት ፋና ዘግቧል፡፡ ኢትዮጵያ የምትባለው አገር ጠ/ሚ/ር እንደሆኑ የሚነገርላቸው ሃይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ የሻዕቢያን ጉዳይ አስመልክተው ሲናገሩ የትኛውን ሻዕቢያ እንደሆነ በግልጽ ሳይጠቅሱ ሻዕቢያ እየወጋን ነው፤ ሕዝብን አስፈቅደን እርምጃ እንወስዳለን ማለታቸው አይዘነጋም፡፡ ለኤርትራ ተቆርቋሪነታቸው ወደር የሌለውና ይህም “የኤርትራ ሕዝብ ትግል ከየት ወደየት” የሚል መጽሐፍ እስኪጽፉ ያደረሳቸው ሞት የቀደማቸው መለስ በኢትዮጵያ የሻዕቢያ ተላላኪና ጉዳይ አስፈጻሚ ነበሩ፡፡ በዚሁ መጽሃፋቸው ላይ የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው በማለት እምዬ ምኒልክን እንደ ቅኝ ገዢ የአውሮጳ ነገሥታት ኢትዮጵያንም እንደ ቅኝ ገዢ አውሮጳዊ አገር በማድረግ በማንም ቅኝ … [Read more...] about ልጅ የአባቱን ልደት ሲያከብር