በአዲስ አበባ የሚገኙ ኤርትራ ተወላጆች ሻዕቢያ “ትጥቅ ትግል” የጀመረበትን 54ኛ ዓመት ማክበራቸውን የህወሃት ዜና አገልግሎት ፋና ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያ የምትባለው አገር ጠ/ሚ/ር እንደሆኑ የሚነገርላቸው ሃይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ የሻዕቢያን ጉዳይ አስመልክተው ሲናገሩ የትኛውን ሻዕቢያ እንደሆነ በግልጽ ሳይጠቅሱ ሻዕቢያ እየወጋን ነው፤ ሕዝብን አስፈቅደን እርምጃ እንወስዳለን ማለታቸው አይዘነጋም፡፡
ለኤርትራ ተቆርቋሪነታቸው ወደር የሌለውና ይህም “የኤርትራ ሕዝብ ትግል ከየት ወደየት” የሚል መጽሐፍ እስኪጽፉ ያደረሳቸው ሞት የቀደማቸው መለስ በኢትዮጵያ የሻዕቢያ ተላላኪና ጉዳይ አስፈጻሚ ነበሩ፡፡ በዚሁ መጽሃፋቸው ላይ የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው በማለት እምዬ ምኒልክን እንደ ቅኝ ገዢ የአውሮጳ ነገሥታት ኢትዮጵያንም እንደ ቅኝ ገዢ አውሮጳዊ አገር በማድረግ በማንም ቅኝ ተገዝታ የማታውቀውን ኢትዮጵያ የቅኝ ገዢነትን “ክብር አጎናጽፈዋታል”፡፡
ባለራዕዩ በዚሁ የሻዕቢያ ተላላኪነታቸው ኢሣያስን እንደ ግለሰብ “አጉራ ዘለል”፣ “ዕብድ” ፣ … እያሉ ከመዝለፍ በስተቀር ሻዕቢያን እንደ ድርጅት በከረረ ቃል ለመናገር ይከብዳቸው እንደነበር አብሮ የሚጠቀስ ቢሆንም በመለስ ፋውንዴሽን ግን የተዘነጋ “ሌጋሲያቸው” ይመስላል፡፡
የዛሬ 54ዓመት ትግል የሚባለውን የጀመረው ጀብሃ ነው፤ ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ሻዕቢያ ተከሰተ፤ እርሱም ህወሃትን ወለደ፤ ህወሃትም ኢህዴንን (የአሁኑን ብአዴን) የአማርኛ ክፍል አድርጎ ከአባትና አያቶቹ በተማረው መሠረት ፈጠረ፡፡ ህወሃት ወላድ በመሆኑ የኦሮሚኛና ሌሎች “ጠቃሚ” የሆኑ የቋንቋ ክፍሎች ወለደ፣ እንደ ጭቃ እያቦካ ጠፈጠፈ፡፡
አሁን የኤርትራ የነጻነት ትግል የሚባለውን በባለቤትነት የሚወስደው ኤርትራን ነጻ አውጥቶ የሚገዛትና አንዳንዴም ለኢትዮጵያ ነጻነት ጥሩ አሳቢ እንደሆነ የሚደሰኮርለት ሻዕቢያ ነው፡፡
ሻዕቢያ የኢትዮጵያ የቅርብ ጠላት ነው በማለት አጥብቃችሁ በመቃወማችሁ የተገመገማችሁ፣ የታሰራችሁ፣ መከራ የተቀበላችሁ፣ … ያላችሁም የለቀቃችሁም የህወሃት አባላት፤ የአይደር ህጻናት ደም ከኅሊናችሁ ሊጠፋ ያልቻለ የትግራይ ተወላጆች፤ እንዲህ ያለውን ቤት ድረስ የመጣ የሻዕቢያ ድፍረት “የኤርትራ ሕዝብ የነጻነት ትግል የጀመረበት” በማለት አለባብሳችሁ ነው የምታልፉት ወይስ …?
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
በለው ! says
“በአዲስ አበባ የሚገኙ ኤርትራ ተወላጆች ሻዕቢያ “ትጥቅ ትግል” የጀመረበትን 54ኛ ዓመት ማክበራቸውን የህወሃት ዜና አገልግሎት ፋና ዘግቧል፡፡”
“ብሔር ብሔረሰቦች ሆኑ የኢትዮጵያ ልጆች ማለት ኤርትራውያን የየትኛው ክልል ልጆች ናቸው? ሻዕቢያ፣ ህወአት፣ ኦነግና ኦብነግ ሲጠሩ አራት ሲናገሩ አንድ፣ ሲኖሩ ጎን ለጎን፣ ሲፋቀሩ በውስጥ፣ ሲጣሉ በውጭ፣ አንድ አካል አንድ አምሳል ማለት ይህ አደለምን!?
** ይህ አዲስ አባባ ከተማ ለነዋሪው(ለተፎካካሪ ፓርቲ) በመንገድ ሥራ፣ በውጭ መሪዎች ስብሰባ፣ በሰልፉ ዕውቅና ማግኘት ፖሊስ ተሰላፊውን በቆመጥ በመደብደብ ወጣት ሴትና እርጉዝ አጥንት በመስብርና በመፈንከት ሲከለልና ሲከለከል..እንዴት ነው ለኤርትራውያን ሳያሳውቁም፣ ሳያስፈቅዱም፣ በማናቸውም ግዜና ወቅት፣ጥበቃ እየተደረገላቸው አጃቸውን ከፍ! ደረታቸውን ነፍተው! አንገታቸውን ቀና አድርገው! የሚጮሁት!? ግን ያለፈው ሰልፍ ኢሳያስ አፈወርቂ ከሥልጣን ይውርድ! ዲሞክራሲ! ፍትህ! ነበር ጥያቄያቸው አሁን ደሞ ሁሉን እረስተው በህወአት ተጋድሎ ድል አድርገን ከቅኝ ገዢዋ ኢትዮጵያ ነፃ የሆንበት ቀን ብለው ኢትዮጵያ ምድር ላይ ይጨፍራሉ!?
** እነኝህ የነፃ መሬት ባላቤቶች ፈንዳቂዎች የአሁን አልቃሾች ኢትዮጵያ ውስጥ በነፃነት እየኖሩ፣ እየሰሩና እየሰረሰሩ፣ በነፃ እየተማሩ የወደፊት ሀወአት ትግራይን ለዳግማዊ ሻዕቢያ የመሸጥ አዝማሚያ ያለው ይመስላል…ከሞላው ኤርትራዊ ኢሳያስ አፈወርቂ ብቻ የኢትዮጵያ ጠላትና ገንጣይ ሆነ!? ዛሬ የሚያለቅሱት ሁሉ የትኛውን ትግል ነው የሚዘክሩት ያው መገንጠልን አደለምን!?እንግዲህ የህወአት መናጆዎች የኦህዴድ ደሕዴን ብአዴን ይህንን ቀይ ቀለም ባንዲራ ነክሮ ከውስጥ እያባሉና እያጫረሱ ለሀገር መፍረስ አብረው እየጨፈሩ በትውልድ ባይቀልዱ የተሻለ ነው።
“እኛም መብታችን በሀገራችን!” በግፍ በአድልዎ በበቀል ያጣነው አሰብ ወደባችን፣ሉዓላዊ ክብራችን እነሱም ወንድሞቻችን… ኢህአዴግ ልዩ ቸርና ለጋስ ሆኖ እንደ ጠ/ሚኒስትሩ አማካሪ ጌታቸው ረዳ አባባል” ኢትዮጵያ ታላቅ ሀገር ናት ተቃዋሚው ጎራ ምቀኛ ነው ለምን ለሱዳን መሬት ተሰጠ፣ ለጅቡቲና ኬንያ መብራትና ውሃ ተሰጠ፣ ለሌሎች ሀገሮች ለምን ዕርዳታና እገዛ ተደረገ ይላሉ ምቀኞች! ይህ የኢህአዴግ ዓላማና ፍላጎት አደለም ለጎረቤቶቻችን እንሰጣላን!” ብለዋል ስለዚህ ኢህአዴግ ሌላውን እያበላና እያስበላን እኛን እርስ በእርስ እያባላን መቀጠል የለበትም! እንቢኝ በል! ሸዋን ተበላህ በለው!